የሕግ ቤት
8.06K subscribers
733 photos
5 videos
1.23K files
569 links
የሕግቤት Access legal information from Law center, The House of Law.
ጠበቃ እና የሕግ አማካሪ ያማክሩ
https://www.facebook.com/lawsocieties
@HigBet #ሕግ_ቤት
lawsocieties@gmail.com
Download Telegram
የታክስ አለመግባባትን በመስማማት ስለመፍታት
ነሐሴ 27/2018 ዓ.ም (የምስራቅ አ/አ/አነ/ግ/ከ/ቅ/ጽ/ቤት )
በተሻሻለው የፌዴራል ታክስ አስተዳደር አዋጅ ቁጥር 1434/2018 አንቀጽ 61 የታክሱ ባለስልጣን የታክስ አለመግባባትን በመስማማት ለመፍታት ያለውን ስልጣን በተመለከተ የሚከተለውን ይላል፡-
👉 የታክሱ ባልስልጣን የታክስ አለመግባባቶችን በመስማማት የመፍታት ስልጣን ተሰጥቶታል።
👉 ማናቸውም በስምምነት የሚፈታ የታክስ ያለመግባባት በጽሁፍ የሚደረግ እና የተስማሚ ወገኖች ፊርማ ያረፈበት ሊሆን ይገባል።
👉 የታክስ አለመግባባቶችን በመስማማት የመፍታት ስልጣን የሰጠው ድንጋጌ ቢኖርም የሚከተሉት ሁኔታዎች ሲኖሩ ጉዳዩ በማስማማት ሊታይ አይችልም፦
1. የታክስ ማጭበርበር ወይም ሆን ተብሎ የተደረገ ታክስን የመሰወር ድርጊት መኖሩ ወይም ሌላ ከታክስ ጋር የተገናኘ ወንጀል መኖሩ ሲጠረጠር፤
2. በማስማማት የሚደረግ ስምምነት ከኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ሕገ-መንግሥት እና ከሚመለከታቸው የታክስ ሕጎች ጋር የሚጋጭ ሲሆን፤
3. ከሁለቱ ወገኖች አንዱ በሽምግልና ሂደት ውስጥ ለመሳተፍ ፈቃደኛ ካልሆነ።
👉 ሚኒስቴሩ የአስማሚውን የትምህርት እና ሙያ ደረጃን ጨምሮ የመስማማት ሂደት የሚመራበትን ሥርዓት የሚወስን ዝርዝር የአፈፃፀም መመሪያ ያወጣል፡፡
ምንጭ ፣ገቢዎች ሚኒስቴር
❤9👍3
#እንድታውቁት: የቀድሞ የይዞታ ካርታ እያለ አዲስ ሕጋዊ የካዳስተር ምዝገባ ለምን ያስፈልጋል?

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመሬት ይዞታ ምዝገባና መረጃ ኤጀንሲ የቀድሞ የይዞታ ካርታ ያላቸው ባለይዞታዎች አዲሱን ሕጋዊ የካዳስተር ምዝገባ ማካሄድ ለምን እንደሚያስፈልጋቸው በሚል በገጹ ያቀረበውን መረጃ እንናጋራችሁ።

ኤጀንሲው እንዳስታወቀው አዲሱ ምዝገባ የቀድሞውን ሰነድ ለመሻር ወይም ተመሳሳይ መብትን ለሁለተኛ ጊዜ ለመስጠት ሳይሆን፣ ያለውን የይዞታ መረጃ በዘመናዊና በተደራጀ የካዳስተር ሥርዓት ማረጋገጥን ዓላማ ያደረገ ነው።

የመብት ሰጪ እና የመዝጋቢ ተቋማት ልዩነት

ነባሩ ካርታ የመሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ የመሬት ተጠቃሚነት መብት ሲፈቅድ የሚሰጠው የፈቃድ ሰነድ ሲሆን፤ በአዋጅ ቁጥር 1381/2017 መሠረት የመሬት ይዞታ ምዝገባና መረጃ ኤጀንሲ የሚሰጠው የካዳስተር ሰርተፊኬት ደግሞ የመሬቱ ወሰን በጂፒኤስ (GPS) እና በኦርቶ ፎቶ ቴክኖሎጂ ተለክቶ የመሬቱና የንብረቱ ባለቤትነት በሕግ መረጋገጡን የሚያሳይ የዋስትና ሰነድ ነው።

አዲሱ የካዳስተር ምዝገባ የሚያካትታቸው ዝርዝሮች

አዲሱ ሥርዓት የመሬት መብት፣ ክልከላ እና ኃላፊነትን በአንድ ላይ የሚያደራጅ ሲሆን የሚከተሉትን ያካትታል፦

⚫ የቁራሽ መሬቱ ትክክለኛ ወሰን፣ ስፋት፣ ርዝመት፣ ቅርጽና የኮኦርዲኔት መረጃ
⚫ የወሰን መገናኛ ነጥቦች፣ የአጎራባች ይዞታዎች፣ የመንገድና የአድራሻ መረጃ
⚫ የቁራሽ መሬቱ ልዩ መለያ ኮድ (Unique Identification Code)
⚫ በመሬቱ ላይ ያለው ሕንፃ ወይም ሌላ ቋሚ ንብረት መረጃ

የቀድሞ ካርታ ብቻውን የሚያስከትላቸው ችግሮች

የቀድሞ ካርታ ብቻ መጠቀም የመሬት ስፋት በተለያዩ ሰነዶች ላይ በተለያየ መጠን የመመዝገብ፣ የአጎራባች ወሰን የመደራረብ፣ ትክክለኛ ኮኦርዲኔት የመጣት እና በሽያጭ፣ ውርስ፣ ሞርጌጅ ወይም ካሳ ወቅት የሕግ ክርክር የመፈጠር ችግሮችን ያስከትላል። በተጨማሪም በወረቀት ላይ ያለ መረጃ ለዲጂታል አሰራር አይመችም።

የቀድሞ ሰነድ ህልውናና የካዳስተር ጥቅም

የቀድሞ ሰነድ በምዝገባ ሂደት ወቅት እንደ ዋና ማስረጃነት የሚያገለግል እንጂ በግድ የለሽነት የሚሰረዝ አይደለም። አዲሱ አሰራር አዲስ መሬት ለመስጠት ወይም ባለይዞታውን ለማስጨነቅ ሳይሆን፣ የይዞታ ዋስትናን በማጠናከር የመሬት መረጃን ከአንድ ልዩ መለያ ኮድ ጋር ለማስተሳሰር የተዘጋጀ ነው።

የከተማ አስተዳደሩ የመሬት ይዞታ ምዝገባና መረጃ ኤጀንሲ ነባሩ ካርታ የመሬት መጠቀሚያ ፈቃድ ሲሆን፣ በአዋጅ ቁጥር 1381/2017 መሠረት የሚሰጠው የካዳስተር ምዝገባ ሰርተፊኬት ግን የሀብትና የቤት የመጨረሻ ሕጋዊ ማረጋገጫ በመሆኑ ባለይዞታዎች ይዞታቸውን በወቅቱ እንዲያስመዘግቡ ጥሪ አቅርቧል።

@TikvahethMagazine
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
❤3👍1👏1
የትምህርት ሚኒስቴር የአጠቃላይ ትምህርት መምህራን የደረጃ እድገት አፈጻጸም መመሪያን ይፋ አደረገ።

የትምህርት ሚኒስቴር በመንግሥት ትምህርት ቤቶች ከቅድመ አንደኛ እስከ ሁለተኛ ደረጃ በሚያስተምሩ መምህራን ላይ ተፈጻሚ የሚሆን "የአጠቃላይ ትምህርት መምህራን የደረጃ እድገት አፈጻጸም መመሪያ ቁጥር 1148/2018" አውጥቷል።

ሚኒስቴሩ በአጠቃላይ ትምህርት አዋጅ ቁጥር 1368/2017 በተሰጠው ሥልጣን መሠረት ያዘጋጀው ይህ መመሪያ፣ በማስተማር ሥራቸው የላቀ ውጤት የሚያስመዘግቡ መምህራንን ለማበረታታት፣ የሥራ ተነሳሽነታቸውን ለማሳደግ እንዲሁም አጠቃላይ የትምህርት ጥራትን ለማረጋገጥ ያለመ መሆኑ ተገልጿል።

በመመሪያው ድንጋጌ መሠረት የአጠቃላይ ትምህርት መምህራን የእድገት መሰላል በሰባት ደረጃዎች የተከፋፈለ ሲሆን፤ እነሱም ፦
- ጀማሪ መምህር፣
- መለስተኛ መምህር፣
- መምህር፣
- ከፍተኛ መምህር፣
- ተባባሪ መሪ መምህር፣
- መሪ መምህር እና ከፍተኛ መሪ መምህር ናቸው።

በመመሪያው የተቀመጠው የቆይታ ጊዜም ከጀማሪ ወደ መለስተኛ መምህርነት ለመሸጋገር 2 ዓመት፣ በቀጣዮቹ ደረጃዎች ደግሞ በእያንዳንዱ እርከን የ3 ዓመታት ቆይታ የሚጠይቅ ነው።

ይሁን እንጂ አንድ መምህር በተከታታይ ወይም በተለያየ ጊዜ በውድድር ሁለት ጊዜ እድገት ማግኘት ካልቻለ ለሦስተኛ ጊዜ የመወዳደር ዕድል እንደማይኖረው በመመሪያው ተደንግጓል።

መምህራን ለደረጃ እድገት ውድድር ብቁ ለመሆን ማሟላት ከሚገባቸው የጋራ መስፈርቶች መካከል በመምህርነት ሙያ ዕውቅና ካለው ተቋም የተመረቁ መሆን፣ የሙያ ፈቃድ ምስክር ወረቀት መያዝ፣ እንዲሁም ለጀማሪ መምህራን የመውጫ ምዘና ማለፍ በዋናነት ተቀምጠዋል።

ከዚህ በተጨማሪም አንድ መምህር ለደረጃ እድገት ለመብቃት ከሚያስተምራቸው ተማሪዎች ውስጥ ቢያንስ 75 በመቶ የሚሆኑት 50 በመቶ እና ከዚያ በላይ ውጤት ማስመዝገባቸው በገለልተኛ አካል መረጋገጥ እንዳለበት ሰነዱ ያትታል።

በተጨማሪም ጀማሪ መምህራን ቢያንስ የ40 ሰዓታት፣ ከመለስተኛ መምህር ጀምሮ ያሉት ደግሞ የ60 ሰዓታት ሙያ ተኮር አጫጭር ሥልጠናዎችን መከታተልና የተከታታይ ሙያ ማሻሻያ (CPD) ዕቅዳቸውን በአግባቡ መፈጸም ይጠበቅባቸዋል።

ወደ ከፍተኛ የእድገት እርከኖች ለመሸጋገር የተቀመጡት መመዘኛዎች የማስተማር ብቃትን ብቻ ሳይሆን የምርምርና የማኅበረሰብ አገልግሎት ተሳትፎንም ያካተቱ ናቸው።

በዚህም መሠረት መምህራን ከደረጃ ወደ ደረጃ ሲሸጋገሩ ከ70 እስከ 90 በመቶ የሚደርስ የሥራ አፈጻጸም ውጤት ማስመዝገብ፣ የተደራጀ ማኅደረ-ተግባር (Portfolio) መያዝ፣ ጀማሪ መምህራንን በአማካሪነት መደገፍ እንዲሁም ልዩ ፍላጎት ያላቸውንና ተጋላጭ ተማሪዎችን መርዳት ግዴታ ተጥሎባቸዋል።

በተለይም ከመካከለኛ ደረጃ ጀምሮ ባሉት ከፍተኛ እርከኖች ለመወዳደር የመማሪያና የመምሪያ መጻሕፍትን መገምገም፣ አጋዥ የትምህርት ጽሑፎችን ማዘጋጀት እና በመማር ማስተማር ችግሮች ዙሪያ ተግባራዊ ጥናትና ምርምሮችን (Action Research) ማካሄድ የግድ እንደሚል ሰነዱ በዝርዝር አስቀምጧል።

አዲሱ መመሪያ የላቀ አፈጻጸም ላስመዘገቡ መምህራን የተፋጠነ የደረጃ እድገት የሚሰጥበትን አሠራርም አስተዋውቋል።

በዚህም መሠረት ከመምህርነት እስከ መሪ መምህርነት ባለው እርከን የሚገኝ ማንኛውም መምህር የሚያስተምራቸው ተማሪዎች በሙሉ 85 በመቶ እና ከዚያ በላይ ውጤት በተከታታይ ሁለት ዓመታት እንዲያስመዘግቡ ካደረገ እና ይህም በገለልተኛ አካል ሲረጋገጥ፣ የሦስት ዓመት የቆይታ ጊዜውን ሳይጠብቅ በሁለት ዓመት ውስጥ እንዲያድግ ይደረጋል።

በተመሳሳይም የተማሪዎቹን ውጤት 90 በመቶ እና ከዚያ በላይ ለተከታታይ ሦስት ዓመታት ያደረሰ መምህር አንድ የደረጃ መሰላል ዘሎ እንዲያድግ የሚፈቀድ ሲሆን፤ በከፍተኛ መሪ መምህርነት ደረጃ ላሉት ደግሞ የሁለት እርከን ደመወዝ ጭማሪ እንደሚሰጥ ተመላክቷል።

በሌላ በኩል መመሪያው የወሊድ ፈቃድ ላይ ያሉ መምህራንን፣ በጤና እክል ምክንያት በቦርድ ውሳኔ ከክፍል የተገለሉ ባለሙያዎችን እና በመምህራን ማኅበራት በአመራርነት የሚያገለግሉ አባላትን የደረጃ እድገት አፈጻጸም በልዩ ሁኔታ አካቷል።

የደረጃ እድገቱ በየዓመቱ በሁለት ዙር ማለትም በጥር አንድ እና በሐምሌ አንድ ቀን ተግባራዊ የሚደረግ ሲሆን፣ ሂደቱም በትምህርት ቤት ቴክኒክ ኮሚቴና በደረጃ እድገት ኮሚቴ ተጣርቶ በወረዳ ትምህርት ጽሕፈት ቤት አማካይነት ይጸድቃል።

አሠራሩ ፍትሐዊና ገለልተኛ እንዲሆን የጥቅም ግጭትን የሚከላከሉ ድንጋጌዎች የተካተቱበት ሲሆን፣ በውሳኔው ላይ ቅሬታ ያላቸው መምህራንም ደብዳቤው በደረሳቸው በ10 የሥራ ቀናት ውስጥ አቤቱታ ማቅረብ እንደሚችሉ ተደንግጓል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
አዲስ አበባ
መስከረም 17 ቀን 2019 ዓ/ም
Forwarded from አለ ሕግ
ለፌዴራል ጠበቆች መልካም ዜና የ2018 ዓ.ም. የግብር አከፋፈል አሰራር ተመቻቸ🙏🙏🙏✍️✍️
የኢትዮጵያ ፌዴራል ጠበቆች ማኅበር (EFAA) ከአዲስ አበባ ገቢዎች ቢሮ ጋር ባደረገው የጠበቀ ውይይትና ጥረት፣ ለአባላቱ የተሻለና የተቀናጀ የግብር አከፋፈል አሰራር እንዲዘረጋ ማድረጉን አስታወቀ።
የ2018 ዓ.ም. የግብር ክፍያ አፈጻጸም በ2017 ዓ.ም. በነበረው የግብር አከፋፈል መመሪያና አሰራር መሠረት እንዲስተናገድ ተደርጓል።
የጠበቆችን የሥራ ባህሪ ያገናዘበ አሰራር እንዲዘረጋ የተደረገውን ጥረት አዲስ አበባ ገቢዎች ቢሮ በመረዳት አሰራሩን ያቀለለ ሲሆን፣ የማኅበሩ አመራሮችና ባለድርሻ አካላት ላደረጉት አስተዋጽኦ ምስጋና የቀረበላቸው መሆኑ ተገልጿል።
ማኅበሩ በቀጣይም ቢሆን ለህግ ባለሙያዎችና ለጠበቆች የሥራ ባህሪ ሙሉ በሙሉ የሚስማማ የዘላቂ ግብር ሥርዓት እንዲኖር ከህግ አውጪዎችና ከፈጻሚ አካላት ጋር የሚደረገውን ውይይት እንደሚያስቀጥል ገልጿል።
ለአባላት የቀረበ ጥሪ፦✍️✍️✍️🙏🙏
የማኅበሩ አባላት የሆናችሁ ጠበቆች በየአካባቢያችሁ ወደሚገኙ የግብር ማዕከላት በመሄድ የ2018 ዓ.ም. ግብራችሁን በወቅቱ እንድትከፍሉ ጥሪ ቀርቧል።
⚖️ #አለሕግ #AleHig አለ ሕግ
https://t.me/AleHig
❤3
ታካሚዎች ላይ ሞት እና የአካል ጉዳት ጭምር ያስከተሉ የህክምና ስህተት አቤቱታዎች መቅረባቸውንና የሚቀርቡ አቤቱታዎች እየጨመሩ መሆኑን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የምግብና መድኃኒት ባለስልጣን ገለጸ።

የባለስልጣኑ የህግ፣ የጤና ባለሙያዎችና ሥነምግባር ክትትል ዳይሬክር አቶ መትከል ገብረመድህን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ እንደተናገሩት ከሆነ፣ ከህክምና ስህተት ጋር በተያያዘ 42 አቤቱታዎች ቀርበዋል።

የቀረቡት አቤቱታዎች ምን የተመለከቱ ናቸው? በእነዚህ አቤቱታዎች በህክምና ስህተት የሞቱ፣ የአካል ጉዳት የደረሰባቸውን የሚመለከቱ አሉ? በሚል ላቀረብነው ጥያቄ ዳይሬክተሩ፣ "አዎን። እሱማ አለ። የአካል ጉዳትም አለ፤ ሞትም አለ" ብለዋል።

"ግን እንደዚህ አይነት ነገሮች ላይ ጥንቃቄ ያስፈልጋል። ሚዲያ ላይ ሲወጣ ባለሙያዎች ላይ የሚያሳድረው አሉታዊ ተፅዕኖ ቀላል አይደለም" ብለው፣ የሟችና ጉዳተኞችን ቁጥር ከመግለጽ ተቆጥበዋል።

የህክምና ስህተት ተፈጸመ በሚል የሚያቀረቡ አቤቱታ እየጨመረ ወይስ እየቀነሰ ነው? መንስኤው ምንድን ነው? ስንላቸው፣ "በተለያዩ መንገዶች በደንብ እየሰራን ስለሆነ ህብረተሰቡ ከጊዜ ወደ ጊዜ ግንዛቤው እየዳበረ መጥቷል። ግንዛቤ እየዳበረ በመምጣቱ የሚቀርበው የቅሬታ መጠንም ከፍ እያለ መጥቷል" ብለዋል።

"የቅሬታ መጠኑ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ ነው" ያሉን ሲሆን፣ "ይህ ማለት የህክምና ስህተት ጨምሮ ሊሆንም ላይሆንም ይችላል፤ ያ በጥናት ነው የሚረጋገጠው" ሲሉም ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግረዋል።

የሚቀርቡ አቤቱታዎች ሲጨምሩ በጤና ባለሙያዎች ላይ የሚወሰደው እርምጃ የመጨመር እድሉ ሰፊ መሆኑንም ገልጸዋል።

አቶ መትከል 42 አቤቱታዎች መቅረባቸውን ተከትሎ፣ "31 የሚሆኑ ጤና ባለሙያዎችን ተጠያቂ አድርገናል። በማጣራት ሂደት ብዙ ባለሙያዎች ናቸው የሚሳተፉት፤ ከበርካታ ባለሙያዎች መካከል ነው 31 ባለሙያዎችን ተጠያቂ ያደረግነው" ሲሉ ነግረውናል።

ዘንድሮ 42 ሰዎች ካቀረቧቸው አቤቱታዎች መካከል ዋና ዋናዎቹ ምን እንደሆኑ ስንጠይቃቸው፥ የሞት፣ የአካል ጉዳት አቤቱታዎች መሆናቸውን ተናግረዋል።

- በጨቅላ ህፃናት፣
- በነፍሰጡሮች፣
- በጥርስ ህክምና
- በዓይን ህክምና
- በውስጥ ደዌ በሽታዎች
- በወሊድ እና ከወሊድ ጋር በተያያዙ ጉዳዮች መሆኑንም አስረድተዋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ፥ ጤና ባለሙያዎች የህክምና ስህተት ለመፈጸሙ ምክንያት የሚሉት ምንድን ነው? ሲል የጠየቃቸው አቶ መትከል፣ "የተለያዩ ምክንያቶች ሊያቀርቡ ይችላሉ። የሚያቀርቡት ምክንያት ግን ትክክለኛ ሊሆንም ላይሆንም ይችላል" የሚል ምላሽ ሰጥተዋል።

የህክምና ግብዓት እጥረት፣ የጤና ባለሙያዎች፣ "ትኩረት አለመስጠት"፣ "የሙያ ማነስ"፣ "የእውቀት እና ክህሎት ማነስ" ሊኖር እንደሚችል ዳይሬክተሩ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግረዋል።

ባለስልጣኑ፣ "ከ42 አቤቱታዎች ውስጥ አስፈላጊው ማጣራት ተደርጎ ጥፋተኛ የተባሉትን፦
- 3 ሚድዋይፈሪ፣
- 9 ዶክተሮች፣
- 14 ነርሶች፣
- 3 ጤና መኮንን፣
- 1 አንስቴቲስት፣
- 1 የድንገተኛ ቀዶ ጥገና ባለሙያ በድምሩ 31 ጤና ባለሙያዎች ላይ የጥፋተኝነት ውሳኔ ተወስኖባቸዋል" ሲል አስታውቋል።

30 ባለሙያዎች ከአንድ ወር እስከ አንድ ዓመት ከሁለት ወር የሚደርስ የሙያ ፈቃድ እገዳ እንደተጣለባቸው፣ አንድ ባለሙያ ላይ ደግሞ የጽሑፍ ማስጠንቀቂያ እንደተሰጠ ገልጿል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
አዲስ አበባ
መስከረም 19 ቀን 2019 ዓ/ም

@tikvahethiopia
❤6
የመደመር መንግስት አዲሱ ካቢኔ
#የመደመር_መንግሥት
👎6👍5
Forwarded from አለ ሕግ
📌 ያለ ሕግ ሰላም ይኖራል?
አንዳንዶች "ሕግ ነፃነቴን ይገድባል" ይላሉ፤ ነገር ግን ሕግ በሌለበት ቦታ እውነተኛ ሰላም ሊኖር አይችልም!
ሕግ የሌለበት ሰላም: ጊዜያዊ ወይም በኃይለኞች ፍላጎት ላይ የተመሠረተ የውሸት እፎይታ ነው።
ሕግና ፍትሕ ሲኖሩ: የሁሉም ሰው መብት ይከበራል፤ የሕግ የበላይነት ባለበት ቦታ ደግሞ ዘላቂ ሰላም ይነግሣል።
ሕግ ሰላምን የሚጠብቅ አጥር እንጂ ነፃነትን የሚያስር እሰር አይደለም። ያለ ሕግ አስከባሪና ያለ ሕግ የበላይነት ዘላቂ ሰላምን ማሰብ አይቻልም!
💬 እርስዎ ምን ያሰባሉ? ሰላም ከሕግ ይመነጫል ወይስ ሕግ ከሰላም? አስተያየትዎን በኮመንት ያጋሩን! 👇 🌍 Different voices. Different views. One shared humanity.
#ሕግ #ሰላም #የሕግበላይነት #ፍትሕ #PeaceAndLaw #RuleOfLaw #Justice
#Ileadpeace #PeaceStartsWithMe #YouthForPeace #PeacefulCommunities #AyreseTechShow #DignityForLife #GNRC #Arigatou
❤1
#ለመረጃ: ለአትክልት እና ፍራፍሬ ማቀናበር እና ማቆየት የሥራ ዘርፍ የሚያስፈልጉ የካፒታል ዕቃዎች ከቀረጥና ታክስ ነፃ ሆነው እንዲገቡ የገንዘብ ሚኒስቴር የማሻሻያ ደብዳቤ አውጥቷል!

መመሪያ ቁጥር 1064/2017 የኢንቨስትመንት ማበረታቻን ለማስፈጸም የወጣውን መመሪያ ማንበብ ለምትፈልጉ ከታች ተቀምጧል!
Forwarded from አለ ሕግ
የኢትዮጵያ ፌዴራል ጠበቆች ቀን ሊከበር ነው! ⚖️💎

በሺዎች የሚቆጠሩ የፌዴራል ጠበቆች አምረው፣ ደምቀው እና ተውበው በሚታዩበት ልዩ ቀን‼️


ሁሉንም የፌዴራል ጠበቆች በአንድ ጥላ ስር የሚያሰባስበው ታላቅ "የጠበቆች ቀን" (Lawyers' Day) በቅርብ ቀናት ውስጥ በደማቅ ሁኔታ ሊካሄድ መሆኑን በዝግጅት ኮሚቴው ይፋ ሆነ! ✔️💎

ጠበቆች በሀገር ግንባታ፣ በሕግ የበላይነት እና በፍትህ ማረጋገጥ ሂደት ውስጥ የሚጫወቱት ሚና የማይተካ በመሆኑ፤ የሙያዊ ህብረት እና አወንታዊ ተፎካካሪነትን ማሳደግ፣ የሚያጋጥሟቸውን ችግሮች በጋራ መፍትሔ መስጠት እና የሙያ ትስስራቸውን ማጠናከር አስፈላጊ በመሆኑ ይህ በአይነቱ ልዩ የሆነ የጠበቆች ቀን ተዘጋጅቷል‼️

ይህ በዓይነቱ ልዩ የሆነ ታሪካዊ መርሃ-ግብር የሙያውን ክብር ከፍ የሚያደርግ ከመሆኑም በላይ፣ በፌዴራል ጠበቆች ማህበር አዘጋጅነት ሁሉም ጠበቆች የሚታደሙበት የማይረሳ ምሽት ይሆናል!

🍷ይህ ደማቅ ፕሮግራም ምን ምን ያካተተ ነው?⁉️

🍽 የራት ግብዣ (Gala Dinner)
🎶 የተለያዩ ማራኪ የመዝናኛ ፕሮግራሞች
🤝 የኔትወርኪንግና የእርስ በእርስ ትውውቅ መድረክ
📺 የሀገር ውስጥና የውጭ ትልልቅ ሚዲያዎች ሽፋን
⚖️ የፍትሃዊነትና የጠበቆችን ማህበራዊ ሚና ማጎልበቻ ውይይቶች

ቀን እና ቦታው በጥቂት ቀናት ልዩነት ይፋ ይደረጋል!💡

#የኢትዮጵያፌዴራልጠበቆች #የጠበቆችቀን #FirstLawyersDay #EthiopianLawyers #Networking #GalaDinner #LegalExcellence
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
❤5
🚨   ውድ ግብር ከፋዮቻችን  
በአዲሱ የፌደራል የታክስ አስተዳደር ማሻሻያ አዋጅ (ቁጥር 1434/2018) መሠረት ከደረሰኝ አጠቃቀም እና ከድርጅት አመራሮች ተጠያቂነት ጋር  የንግድ ማህበረሰቡ ሊያውቋቸው የሚገቡ ዋና ዋና ነጥቦች፦

📌 የደረሰኝ ጥፋትና የቅጣት መጠኖች (አንቀጽ 125 እና 137)
·         ❌ ደረሰኝ አለመስጠት፦ በእያንዳንዱ ያልተሰጠ ደረሰኝ 100,000 ብር አስተዳደራዊ ቅጣት ይጣላል (ይህ ቅጣት በባለሥልጣኑ ሊነሳ አይችልም)።
·         ❌ የጋራ ዋጋ ማሳነስ ወይም መቀየር፦ 100,000 ብር መቀጫ + ከ5 እስከ 7 ዓመት በሚደርስ ጽኑ እስራት ያስቀጣል።
·         ⚖️ የወንጀል ክስ መመስረት፦ በአንድ የግብር ዘመን ውስጥ 2 ጊዜ አስተዳደራዊ ቅጣት ከተቀጡ በኋላ ተመሳሳይ ጥፋት ከተደገመ ቀጥታ ወደ ወንጀል ክስ ያመራል።
⚠️ የስራ አስኪያጆችና የፋይናንስ ኃላፊዎች ግልጽ ተጠያቂነት (አንቀጽ 149) በድርጅት ውስጥ ለሚፈጸም የታክስ ወንጀል፣ ወንጀሉ በተፈጸመበት ወቅት የነበረ ሥራ አስኪያጅ ወይም የፋይናንስ ኃላፊ በግል በወንጀል ተጠያቂ ይሆናል!
ከተጠያቂነት ነፃ መሆን የሚቻለው፦
1.      ድርጊቱ ከእሱ እውቅና ውጪ መፈጸሙን፣
2.      የወንጀሉን መፈጸም ያልፈቀደ ወይም ያልተባበረ መሆኑን፣ ወይም
3.      ወንጀሉ እንዳይፈጸም ውጤታማ የውስጥ ቁጥጥር ሥርዓት መዘርጋቱን ማስረዳት ሲችል ብቻ ነው።
💡 መፍትሔ፦ ድርጅትዎ ያልተጠበቀ ከባድ የገንዘብና የእስራት ቅጣት እንዳይገጥመው የውስጥ ቁጥጥር ሥርዓትዎን (Internal Control) ያጠናክሩ፤ የደረሰኝ አሰጣጥዎን በጥብቅ ይከታተሉ!
📲 መረጃው ለሌሎች የንግድ አጋሮችዎ እንዲደርስ ሼር (Share) ያድርጉ!
❤6