የተሻለ ሙያዊ ሥነ-ምግባርን በመገንባት ሙስናን እና ብልሹ አሰራርን መከላከል እንደሚገባ ተገለጸ
ጥቅምት 09/2019 ዓ.ም (የገቢዎች ሚኒስቴር)
የገቢዎች ሚኒስትር ዓይናለም ንጉሴ ከመካከለኛ ቁጥር ሁለት ቅ/ጽ/ቤት አመራር እና ሠራተኞች ጋር ውይይት አድርገዋል፡፡
በውይይቱ የመክፈቻ ንግግራቸው ያደረጉት የገቢዎች ሚኒስትር ዓይናለም ንጉሴ እንደ ሀገር የተሰጠንን ትልቅ ኃላፊነትና ተልዕኮ ለመወጣት የተሻለ ሙያዊ ስነ ምግባርን መገንባት፣ ሙስናን መዋጋት እንዲሁም ግልፅ እና ተጠያቂነት የሰፈነበት አገልግሎት መስጠት ይገባል ብለዋል፡፡
በትብብር ሙስናን እና ብልሹ አሰራርን መዋጋት፤ ተቋማዊ የመፈፀም አቅምን ማሳደግ፤ ዘመናዊ ቴክኖሎጂን በመዘርጋት የአገልግሎት ጥራት እና ቅልጥፍናን ማሳደግ፤ ግልጽነትና ተጠያቂነት ማስፈን እንዲሁም የተሰጠንን ተቋማዊ ተልዕኮ በብቃት መወጣት የቀጣይ የትኩረት አቅጣጫዎች መሆናቸውን ሚኒስትሯ አክለው ገልጸዋል፡፡
የሚኒስትር የታክስ አማካሪ የሆኑት አቶ ስመኝ ንጉሴ የሙስናና የብልሹ አሰራር መከላከል ልዩ የንቅናቄ እቅድ የመወያያ ሰነድ አቅርበዋል።
የገቢው ዘርፍ ለሙስና እና ብልሹ አሰራር ይበልጥ ተጋላጭ በመሆኑ በሁሉም ዘርፍ የሚገኙ አመራርና ሰራተኞች ራሳቸውን ከሙስና እና ብልሹ አሰራር በማራቅ የተጣለባቸውን ሀገራዊ ኃላፊነት በብቃት መወጣት እንደሚገባ ገልጸዋል፡፡
የመካከለኛ ቁጥር ሁለት ቅ/ጽ/ቤትን የ2019 በጀት ዓመት የመጀመሪያው ሩብ ዓመት እቅድ አፈጻጸም ሪፖርት ያቀረቡት የገቢዎች ሚኒስቴር የስትራቴጂክ ፕላን እና ፕሮጀክት አስተዳደር ዳይሬክተር አቶ ተመስገን ተሰማ በበኩላቸው በሩብ ዓመቱ የቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ አፈጻጸም አበረታች መሆኑን ገልጸው በቀሪ ጊዜያት የተሰጠን ኃላፊነት በትጋት እና በቁርጠኝነት በመከወን የተያዘውን የገቢ ዕቅድ ማሳካት እንደሚገባ ገልጸዋል፡፡
በመድረኩ ከተሳታፊዎች የተለያዩ አስተያየትና ጥያቄዎች ቀርበው ውይይት የተደረገባቸው ሲሆን ለሙስናና ብልሹ አሰራር በር የሚከፍቱ አሰራሮችን ፈጥኖ በማስተካከል ለበጀት ዓመቱ እንደ ተቋም የተያዘውን የገቢ እቅድ ሙሉ በሙሉ እንዲሳካ የቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ ሚና ከፍተኛ በመሆኑ በልዩ ትኩረት ሊሰራ እንደሚገባ ስምምነት ላይ ተደርሷል።
በበላይነሽ እጅጉ
ፎቶ:- የትናየት እንዳያፍሩ

❤10👍1
በዲጂታል መንገዶች (ፕላትፎርሞች) ለሚሰጡ የትራንስፖርት አገልግሎቶች
በዲጂታል መተግበሪያዎች (እንደ ፈረስ እና ራይድ መሰል ፕላትፎርሞች) አማካኝነት የትራንስፖርት አገልግሎት ለምትሰጡ አሽከርካሪዎች እና የቴክኖሎጂ ፕላትፎርም አቅራቢዎች ማስታወሻ፡
በዲጂታል የትራንስፖርት አገልግሎቶች ላይ የሚከተሉትን ግልጽ ግዴታዎች ደንግጓል፦
📌 1. ለፕላትፎርም አቅራቢዎች የሚመለከቱ ዋና ዋና ኃላፊነቶች፡
· የታክስ ስሌት እና አሰባሰብ፡ ፕላትፎርም አቅራቢዎች ከተሳፋሪዎች ከሚከፈለው ጠቅላላ ክፍያ (ማናቸውንም ክፍያዎች እና ኮሚሽኖችን ጨምሮ) ላይ ተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) የመሰብሰብ ኃላፊነት አለበት።
· ደረሰኝ አሰጣጥ፡ ፕላትፎርም አቅራቢው በየዕለቱ መጨረሻ ለትራንስፖርት አገልግሎት ሰጪው (ለአሽከርካሪው) የቫት ደረሰኝ መስጠት አለበት።
· መረጃዎችን የመያዝ ግዴታ፡ አገልግሎቱ የተሰጠበትን ቀን፣ ሰዓት፣ ቦታ፣ የክፍያ መጠን እና ቫትን ጨምሮ ሙሉ ዝርዝር መረጃዎችን መያዝ ይጠበቅበታል።
· ታክስን ማስተላለፍ እና ማስታወቂያ፡ የተሰበሰበውን ቫት በአዋጁ መሰረት ለታክስ ባለሥልጣኑ ማስተላለፍ እና ተገቢውን ማስታወቂያ ማቅረብ አለበት።
· የአገልግሎቱ ቦታ፡ አገልግሎቱ የተከናወነበት ቦታ ተሳፋሪው አገልግሎቱ በሚሰጥበት ጊዜ የሚገኝበት ቦታ ተደርጎ ይወሰዳል።
🚙 2. ለትራንስፖርት አገልግሎት ሰጪዎች (አሽከርካሪዎች) የሚመለከቱ ነጥቦች፡
· የግብአት ታክስ ተቀናሽ፡ አሽከርካሪዎች ከመንገደኞች ትራንስፖርት አገልግሎት አቅርቦት ጋር በቀጥታ ለተያያዙ ግዥዎች የከፈሉትን የግብአት ታክስ በአጠቃላይ የቫት ተቀናሽ አሰራር ስርዓት መሰረት ተቀናሽ እንዲደረግላቸው ሊጠይቁ ይችላሉ።
· የምዝገባ ገደብ፡ ፕላትፎርም አቅራቢው ታክሱን የመሰብሰብ እና የማስተላለፍ ኃላፊነት ቢኖረውም፤ የትራንስፖርት አቅራቢዎች ዓመታዊ የሽያጭ መጠን ለቫት ምዝገባ የተቀመጠውን ገደብ የሚያሟሉ ከሆነ ለቫት መመዝገብ አለባቸው።
· ከፕላትፎርም ውጪ የሚሰጡ አገልግሎቶች፡ አሽከርካሪዎች መተግበሪያዎችን (ፕላትፎርምን) ሳይጠቀሙ በቀጥታ ለሚሰጡት ለእያንዳንዱ የትራንስፖርት አገልግሎት ራሳቸው ቫት የመሰብሰብ እና ደረሰኝ የመስጠት ግዴታ አለባቸው ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ቴሌግራም፦ https://t.me/mormto2
ፌስቡክ፡- https://web.facebook.com/info.mto2/
ቲክቶክ፡-https://www.tiktok.com/@mto2education
ኢሜል፡- mormto2taxeducation2023@gmail.com
ዩትዩብ፡- https://www.youtube.com/@ministryofRevenues-MTO2

Telegram
Ministry of Revenues -Medium Taxpayers Branch No2
This is official Telegram Channel of Ministry of Revenues Medium Taxpayers Branch No 2.
Join the channel.
Join the channel.
❤11
የክፍል አንድ ተከታታይ የሞጁለር ስልጠና ለ40ኛ ዙር ሰልጣኞች መሰጠት ተጀመረ
(ጥቅምት 10 ቀን 2019 ዓ.ም፤በመካከለኛ ግብር ከፋዮች ቁጥር 2 ቅርንጫፍ ጽ/ቤት)
**********************************
በታክስ ሕጎች፣ ደንቦች እና መመሪያዎች ላይ የሚያተኩረውና ለግብር ከፋዮች በመደበኛነት የሚሰጠው የሞጁለር ስልጠና ለ40ኛ ዙር ሰልጣኞች መሰጠት ተጀመረ።
የስልጠናው የግብር ከፋዮችን የታክስ ህግ ግንዛቤ በማሳደግ የሕግ ተገዢነትን ማጎልበት፤ ሰልጣኞች መብትና ግዴታዎቻቸውን እንዲያውቁ እንዲሁም በቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤቱና በግብር ከፋዮች መካከል ያለውን ቅንጅታዊ አሰራር ማጠናከር ነው።
የታክስ አጣጣል መሠረቶች እና የታክስ ሥርዓት ዓይነቶች ፤ ከመቀጠር የሚገኝ ገቢ ግብር እና የታክስ ምጣኔ፤ ከመቀጠር የሚገኙ የዓይነት ጥቅሞች ፤ከታክስ ነፃ የሆኑ እና በገደብ ነፃ የተደረጉ ገቢዎች ፤የወጪ መጋራት አከፋፈል ሥርዓት የሚሉት በስልጠናው ሰፊ ማብራሪያ ከተሰጠባቸው ዋና ዋና ርዕሰ ጉዳዮች መካከል ይገኙበታል::
በስልጠናው ወቅት ተሳታፊዎች በርካታ ጥያቄዎችን ያነሱ ሲሆን፣ ለቀረቡት ጥያቄዎችም በቂ ምላሽና ማብራሪያ ተሰጥቶባቸዋል። ስልጠናውን የሰጡት አቶ አወቀ ግዛው የታክስ ከፋዮች ትምህርት ዋና መሪ ባለሙያ ናቸው።
ግብር÷ለሀገር ክብር!
ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

❤4👍1
በሁኔታ ላይ የተመሰረተ የታክስ የምስክር ወረቀት (Conditional Tax Clearance Certificate) አሰጣጥ፣ አገልግሎት፣ ሕጋዊ ወሰን፣ እና የውጭ ባለሃብቶች የገንዘብ ዝውውር ቅድመ-ሁኔታዎችን በዝርዝር ይደነግጋል፦
1. የምስክር ወረቀቱ የሚሰጥባቸው ምክንያቶች
አንድ ታክስ ከፋይ ያልተከፈለ የታክስ ዕዳ ቢኖርበትም፣ ባለስልጣኑ የምስክር ወረቀቱን ሊሰጠው የሚችለው፦
ሀ) በተጣለበት የታክስ ውሳኔ ላይ ሕጋዊ መቃወሚያ፣ አቤቱታ ወይም ይግባኝ አቅርቦ በክርክር ሂደት ላይ ያለ ከሆነ፤ ወይም
ለ) ዕዳውን በጊዜ ገደብ ለመክፈል ከታክስ ባለስልጣኑ ጋር የጸና የክፍያ ስምምነት (ውል) የፈጸመ ከሆነ።
2. የምስክር ወረቀቱ የሚያገለግላቸው ተግባራት
ይህ የምስክር ወረቀት ጥቅም ላይ ሊውል የሚችለው ለሚከተሉት አገልግሎቶች ብቻ ነው፦
ሀ) የንግድ ወይም የሙያ ፈቃድ ለማደስ፤
ለ) በሕዝብና በመንግሥት ጨረታዎች ለመሳተፍ፤
ሐ) የተሽከርካሪዎች ወይም የኮንስትራክሽን ማሽነሪዎች ዓመታዊ ምርመራና ምዝገባ (ቦሎ/ክላውዶ) ለማድረግ፤
መ) ከባንኮች የብድር አገልግሎት ለማግኘት።
3. የምስክር ወረቀቱ ሕጋዊ ወሰንና ገደብ
ይህንን የምስክር ወረቀት መያዝ፦
ሀ) ታክስ የመክፈል ግዴታን የሚያስቀር፣ የሚያግድ ወይም እንደከፈለ የሚያስቆጥር አይደለም።
ለ) የታክስ ባለስልጣኑ ያልተከፈለውን ታክስ የማስከፈል ሕጋዊ መብቱን አያሳጣውም።
ሐ) በሂደት ላይ ያለውን የታክስ አለመግባባት ወይም ክርክር ውጤት አይቀይርም/አያደናቅፍም።
4. የትግበራ ወሰንና የውጭ ባለሃብቶች ግዴታ
ባንኮች የውጭ ባለሃብቶች የሚከተሉትን ገቢዎች ወደ ውጭ ሀገር እንዲልኩ ከመፍቀዳቸው በፊት፣ ባለሃብቱ ግብር የመክፈሉን የታክስ የምስክር ወረቀት በቅድሚያ መጠየቅ አለባቸው፦
የትርፍ ድርሻ (Dividend)፣
የአክሲዮን ትርፍ፣ ወይም
ድርጅቱን/ንብረቱን በመሸጥ ያገኘውን ገቢ።

❤15👍1😱1
❤4
የታክስ ስርዓት ዘርፍ የ1ኛ ሩብ ዓመት የሥራ አፈፃፀም ግምገማ አካሄደ
(ጥቅምት 12 ቀን 2019 ዓ.ም በመካከለኛ ግብር ከፋዮች ቁጥር 2 ቅርንጫፍ ጽ/ቤት)
***************************************
የመካከለኛ ግብር ከፋዮች ቁጥር 2 ቅርንጫፍ ጽ/ቤት የታክስ ስርዓት ዘርፍ በስሩ ከሚገኙ የሥራ ክፍሎች ጋር በመሆን የ2019 በጀት ዓመት የ1ኛ ሩብ ዓመት የሥራ አፈፃፀሙን ገመገመ። በዚህም የተከናወኑ ዋና ዋና ስራዎች፣ ያጋጠሙ ተግዳሮቶች እና በቀጣይ ሊከናወኑ የሚገባቸው የትኩረት አቅጣጫዎች ላይ ሰፊ ውይይት ተደርጓል።
በውይይቱ ባለፉት ሶስት ወራት ውስጥ የተከናወኑ አበይት የሥራ አፈፃፀሞች የተነሱ ሲሆን የኦዲት ሥራ አፈፃፀም የግብር ከፋዮችን የህግ ተገዥነት ለማረጋገጥ እና ህገ-ወጥ እንቅስቃሴዎችን ለመከላከል የተከናወኑ የኦዲት ክንውኖች ፣የአገልግሎት አሰጣት ጥራትና ቅልጥፍና ለግብር ከፋዮች የሚሰጠው አገልግሎት ከጊዜ ወደ ጊዜ ይበልጥ ውጤታማ እና ተደራሽ ስለሚደርግበት ሁኔታ፣ የግንዛቤ ማስጨበጫ ሥራዎችና የህግ ተገዥነት የግብር ከፋዮችን የታክስ ህግ ግንዛቤ በማሳደግ በፈቃደኝነት ላይ የተመሰረተ የግብር አከፋፈል ስርዓት እንዲጎለብት ለግብር ከፋዩ ማህበረሰብ ዘንድ ለማስረፅ የተደረጉ ጥረቶች ፣የደረሰኝ እና የሽያጭ መመዝገቢያ መሳሪያ አጠቃቀም ዙሪያ ያለውን ነባራዊ ሁኔታና አፈፃፀም በስፋት ተነስተዋል።
በውይይቱ ወቅት በርካታ አበረታች ውጤቶች መመዝገባቸው የተመላከተ ሲሆን፣ ለተቋማዊ ውጤታማነት እና ለስራው መሳካት እንቅፋት የሆነው የሰው ሀይል ዕጥረት ችግር በግንባር ቀደምትነት ተነስቷል። ለዚህም አፋጣኝ መፍትሄ ሊሰጠው እንደሚገባ በጥብቅ ተመላክቷል።
ውይይቱን የመሩት የታክስ ስርዓት ዘርፍ ም/ሥራ አስኪያጅ ወ/ሮ ሮዛ ጀማል በሰጡት ማጠቃለያ ባለፉት ወራት የታዩ ጥንካሬዎችን በማስቀጠል በየስራ ክፍሉ ያጋጠሙ ችግሮችን በዘላቂነት በመፍታት በቀጣይ ለገቢው ስኬት በትጋት መስራት እንደሚገባ አጽንኦት ሰጥተዋል። አክለውም ህግን እና ስርዓትን መሠረት ያደረጉ ውጤታማ የሥራ አፈፃፀሞችን በማከናወን በከፍተኛ የኃላፊነት ስሜት ለግብር ከፋዩ ማህበረሰብ ምቹ፣ ፈጣን እና ቀልጣፋ አገልግሎት በመስጠት ሀገራችን ከእኛ የምትጠብቀውን ታሪካዊ አደራና የገቢ ዕቅድ ለማሳካት በትብብር እና በቁርጠኝነት መንፈስ መስራት ይኖርብናል ሲሉ ጥብቅ አቅጣጫ አስቀምጠዋል።
ግብር÷ለሀገር ክብር!
ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ቴሌግራም፦ https://t.me/mormto2
ፌስቡክ፡- https://web.facebook.com/info.mto2/
ቲክቶክ፡-https://www.tiktok.com/@mto2education
ኢሜል፡- mormto2taxeducation2023@gmail.com
ዩትዩብ፡- https://www.youtube.com/@ministryofRevenues-MTO2
(ጥቅምት 12 ቀን 2019 ዓ.ም በመካከለኛ ግብር ከፋዮች ቁጥር 2 ቅርንጫፍ ጽ/ቤት)
***************************************
የመካከለኛ ግብር ከፋዮች ቁጥር 2 ቅርንጫፍ ጽ/ቤት የታክስ ስርዓት ዘርፍ በስሩ ከሚገኙ የሥራ ክፍሎች ጋር በመሆን የ2019 በጀት ዓመት የ1ኛ ሩብ ዓመት የሥራ አፈፃፀሙን ገመገመ። በዚህም የተከናወኑ ዋና ዋና ስራዎች፣ ያጋጠሙ ተግዳሮቶች እና በቀጣይ ሊከናወኑ የሚገባቸው የትኩረት አቅጣጫዎች ላይ ሰፊ ውይይት ተደርጓል።
በውይይቱ ባለፉት ሶስት ወራት ውስጥ የተከናወኑ አበይት የሥራ አፈፃፀሞች የተነሱ ሲሆን የኦዲት ሥራ አፈፃፀም የግብር ከፋዮችን የህግ ተገዥነት ለማረጋገጥ እና ህገ-ወጥ እንቅስቃሴዎችን ለመከላከል የተከናወኑ የኦዲት ክንውኖች ፣የአገልግሎት አሰጣት ጥራትና ቅልጥፍና ለግብር ከፋዮች የሚሰጠው አገልግሎት ከጊዜ ወደ ጊዜ ይበልጥ ውጤታማ እና ተደራሽ ስለሚደርግበት ሁኔታ፣ የግንዛቤ ማስጨበጫ ሥራዎችና የህግ ተገዥነት የግብር ከፋዮችን የታክስ ህግ ግንዛቤ በማሳደግ በፈቃደኝነት ላይ የተመሰረተ የግብር አከፋፈል ስርዓት እንዲጎለብት ለግብር ከፋዩ ማህበረሰብ ዘንድ ለማስረፅ የተደረጉ ጥረቶች ፣የደረሰኝ እና የሽያጭ መመዝገቢያ መሳሪያ አጠቃቀም ዙሪያ ያለውን ነባራዊ ሁኔታና አፈፃፀም በስፋት ተነስተዋል።
በውይይቱ ወቅት በርካታ አበረታች ውጤቶች መመዝገባቸው የተመላከተ ሲሆን፣ ለተቋማዊ ውጤታማነት እና ለስራው መሳካት እንቅፋት የሆነው የሰው ሀይል ዕጥረት ችግር በግንባር ቀደምትነት ተነስቷል። ለዚህም አፋጣኝ መፍትሄ ሊሰጠው እንደሚገባ በጥብቅ ተመላክቷል።
ውይይቱን የመሩት የታክስ ስርዓት ዘርፍ ም/ሥራ አስኪያጅ ወ/ሮ ሮዛ ጀማል በሰጡት ማጠቃለያ ባለፉት ወራት የታዩ ጥንካሬዎችን በማስቀጠል በየስራ ክፍሉ ያጋጠሙ ችግሮችን በዘላቂነት በመፍታት በቀጣይ ለገቢው ስኬት በትጋት መስራት እንደሚገባ አጽንኦት ሰጥተዋል። አክለውም ህግን እና ስርዓትን መሠረት ያደረጉ ውጤታማ የሥራ አፈፃፀሞችን በማከናወን በከፍተኛ የኃላፊነት ስሜት ለግብር ከፋዩ ማህበረሰብ ምቹ፣ ፈጣን እና ቀልጣፋ አገልግሎት በመስጠት ሀገራችን ከእኛ የምትጠብቀውን ታሪካዊ አደራና የገቢ ዕቅድ ለማሳካት በትብብር እና በቁርጠኝነት መንፈስ መስራት ይኖርብናል ሲሉ ጥብቅ አቅጣጫ አስቀምጠዋል።
ግብር÷ለሀገር ክብር!
ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ቴሌግራም፦ https://t.me/mormto2
ፌስቡክ፡- https://web.facebook.com/info.mto2/
ቲክቶክ፡-https://www.tiktok.com/@mto2education
ኢሜል፡- mormto2taxeducation2023@gmail.com
ዩትዩብ፡- https://www.youtube.com/@ministryofRevenues-MTO2
Telegram
Ministry of Revenues -Medium Taxpayers Branch No2
This is official Telegram Channel of Ministry of Revenues Medium Taxpayers Branch No 2.
Join the channel.
Join the channel.
❤3