Nejashi Printing Press
4.57K subscribers
705 photos
12 videos
6 files
805 links
ይህ የነጃሺ ማተሚያ ቤት ኦፊሻል የቴሌግራም ቻናል ነው። የተለያዩ ጠቃሚ መልዕክቶችን፣ አዳዲስ የህትመት ውጤቶቻችንና አገልግሎቶቻችንን ተከታተሉን፣ ለሌላውም ሼር አድርጉ።
Download Telegram
“ውድቀት” የሚባሉት ሙከራዎቻችን የዕድገት አካላት ናቸው።
ቶማስ ኤዲሰን፣ የብርሃን አምፖል ለመፍጠር አንድ ሺ ያልተሳኩ ሙከራዎችን አድርጎ ነበር።
አልበርት አንስታይን አራት ዓመት እስኪሞላው ድረስ ዲዳ የነበረ ሲሆን፣ የርሱ መምህራን ዋጋ ይኖረዋል ብለው አያምኑበትም ነበር።
ቢልጌትስ በመጀመሪያ የንግድ ሥራው ሲከሥር፣
ዎልት ዲዝኒ ደግሞ የበቃ የፈጠራ ክህሎት የለህም በሚል ተባሯል።
ስቴፈን ስፒልበርግ፣ በአንድ የፊልም ጥበብ ት/ቤት ሁለት ጊዜ ተባሮ ነበር።
ስቴፈን ኪንግም እጅግ ዝነኛው መጽሐፉ ለሕትመት ከመብቃቱ በፊት ሠላሳ ጊዜ በአታሚዎች ውድቅ ተደርጎበታል። በዚህ ምክንያት በእጁ የጻፈውን ረቂቅ ቆሻሻ ገንዳ ውስጥ እስከመጣል ደርሶ ነበር። ዛሬ፣ ከ35 በላይ የልቦለድ መጽሐፍት ያሉት ሲሆን ከ350 ሚሊዮን በላይ ቅጂዎች ሸጧል።

በ1962 ቪክቶር ጎርትዜል የሚባሉ የሥነ-ልቦና ባለሙያና ባለቤታቸው፣ በ400 የሀያኛው መቶ ክፍለ ዘመን ዝነኛ ሰዎች የልጅነት ሕይወት ላይ ያተኮረ መጽሐፍ አሳትመው ነበር። ለዚህ ሥራቸው ለማኅበረሰብ ከፍተኛ አስተዋጽዖ ያበረከቱ ታዋቂ ግለሰቦችን መርጠው ነበር። በጥናታቸው ያገኙት ውጤት የሚደንቅ ነው። ከመካከላቸው 75 በመቶ የሚሆኑት በወላጆቻቸው መጣል፣ ድህነት፣ ጥቃት፣ ወይም ህመምን ጨምሮ መጥፎ አጋጣሚዎችን ያስተናገዱ ነበሩ። ባለሙያው “መከራ ያላገኘው ሰው ለዝና የሚበቃ ዕጩ አይደለም” ሲሉ ጽፈዋል።

ዕድሜያቸው ከ18-101 በሚደርስ፣ ሁለት ሺ በላይ ሰዎች ላይ የተሠራ ሌላ አስደናቂ ጥናት አንዳች መከራ ያጋጠማቸው ግለሰቦች፥ ውጤታማ ሠራተኞች እና በሕይወታቸውም ደስተኛ እንደሆኑ አረጋግጧል።

የበዶነት ስሜት፤ መንስኤውና መፍትሄው
በኡስታዛ ያስሚን ሙጃሂድ
ትርጉም ሱለይማን ጠይብ ሐምዛ

https://nejashibooks.com/

https://t.me/Nejashipp
አስደሳች ድክመት ያለባችሁ ሰብኣውያን ፍጡራን ሆይ፣
ከድክመታችሁ ውስጥ ብርታትን ፈልጉ። አስፈልጎትም ሆነ ድክመት፣ ለሌለበት አምላክ ካላችሁ አስፈልጎት ብርታትን ከጅሉ። ሰብኣዊ እና ውብ፣ ደካማ እና ንቁ በመሆናችሁ፣ በእርሱ ብርታት ውስጥ ብርታትን ከጅሉ። መለኮታዊ ንድፍ ሁሌም ፍፁም ነው። ምንጊዜም! ይህን ንድፍ መስበርም ሆነ ማሻሻል አትችሉም።

ሰዎች ሆይ፣ ደካሞች የሆናችሁት እንዲያ እንድትሆኑ ስለተወጠናችሁ ነው። በዚህ መልኩ የተነደፋችሁት ደግሞ፣ ድክመት በሌለበት አምላክ ላይ ፍፁም በመመካት ጥንካሬና ውበትን ትጎናጸፉ ዘንድ ነው።

ፍፅምናን ውስጣችሁ መፈለግ ነጥቡን መሳት ነው። ውስጣችሁ ያለው ነገር ሁሉ የተነደፈው እርሱን እንድትሹ ተደርጎ ነው። እናንተን ዳግም ወደ እርሱ ለመግፋት።
በዚህ ዓለም ላይ ያለ ነገር ሁሉ የተነደፈው እርሱ ዘንድ የነበራችሁን ቤት እንድትፈልጉ ለማስገደድ ነው። “ፍፁም” ብትሆኑ ኖሮ የእርሱን ፍፅምና ባልከጀላችሁ። ይህች ዓለም ፍፁም ብትሆን ኖሮም፣ የቀጣዩን ዓለም ፍፅምና ባላነፈነፋችሁ ነበር።

የዚህ ዓለም ሕይወት እና ጉዟችን በአጠቃላይ የመጨረሻ አይደሉም። አላህ ልቦቻችንን ለመቅረጽ ሆነ ብሎ ያስቀመጠው ሒደት ነው። ነፍሶቻችንን ከእርሱ ጋር ላለን የመጨረሻ ግንኙነት ሊያሰናዳ ያደረገው ነው። ሒደቱ እንዲያጠራችሁ ፍቀዱለት። ዳግመኛ ያበጃችሁ ዘንድ በጄ በሉት። አዎን፣ ሕመም አለው። ብዙውን ጊዜም የመጨረሻው ሊመስል ይችላል። ሆኖም ፍፃሜው አይደለም። ጉዟችሁ ቀጣይ ነው። ከሕመማችሁም መዳን ብቻ ሳይሆን ጠንክራችሁ ትወጣላችሁ።

የባዶነት ስሜት፤ መንስኤው እና ፈውሱ
በያስሚን ሙጃሂድ
ሱለይማን ጠይብ እንደተረጎመው


https://nejashibooks.com/

https://t.me/Nejashipp
ምትሃታዊ ጎበዝ ሰዎች ከሌላው የሚለዩበትና እነርሱ ብቻ የሚጋሩት አስራአምስት ባህሪያት፦
1) የሚሰሩት ለገንዘብ ሳይሆን ወደውት በጉጉት ነው፡፡ገንዘብ ሁለተኛ ጉዳያቸው ነው፡፡
2) የሚሰሩትን ነገር በጥራት ጀምረው ለመጨረስ መስእዋትነት ይከፍላሉ፡፡
3) ብቻቸውን መሆን ያረካቸዋል፡፡
4) ከሌሎች ውዳሴና ማበረታቻ አይጠብቁም፡፡
5) በገለልተኝነት ይሰራሉ፡፡
6) ድርጊታቸውን በራሳቸው ይገመግማሉ፡፡
7) በቀላል ነገር አይረኩም፡፡
8) ነቅሰው የመመልከት ችሎታ አላቸው፡፡
9) የጀመሩትን ወደተሻለ ጥራት እስከሚያመጡት ድረስ አይታክቱም፡፡
10) ልዩ በመሆን ላይ ትኩረት ያደርጋሉ፡፡
11) በተሰማሩበት መስክና ለጀመሩት ነገር ሰፊ ጊዜ ይሰጣሉ፡፡
12) አዲስ ነገር ለማወቅ ከፍተኛ ጉጉት አላቸው፡፡
13) ፈጠራ የእነርሱ ዋና መለያ ነው፡፡
14) ለግቦቻቸውና ለመርሆቻቸው ታማኞች ናቸው።

https://nejashibooks.com/

https://t.me/Nejashipp
ሥልጣኔ እና ዘመናዊነት
ከ (የልቦና ውቅር )መጽሐፍ
በኡስታዝ ሙሐመድ ዑመር
ነጃሺ መፃሕፍት መደብር
***
ዶ/ር ዩሱፍ አል-ቀረዳዊ፣
‹‹አሁን ያለንበት ዓለም ከፍተኛ የቁሳዊ ሃብት ምጥቀት ላይ የደረሰ ቢሆንም፣ ዳሩ ግን ይህ ሥልጣኔ የሰው ልጆች የሚፈልጉትን ዓይነት መረጋጋት መፍጠር አልቻለም። አሁን ያለው ሥልጣኔ የዝሆን አካል ሆኖ የአይጥ ነፍስ ያለው ነው… ከእውነተኛው ነገር ቅርጹ፣ ከልቡም ቅርፊቱ፣ ከተሰያሚው ነገር በላይ ስሙ ሊሸነግለን አይገባም።›› ሲሉ ጽፈዋል።

አሁን ያለው ሥልጣኔ የሚያቀነቅነው ከነብያት ሐሳብ ተቃራኒውን መንገድ ነው። ዓለማዊነትን የማግነን፣ የነብያትን መንገድ የመካድ ስውር ሴራን ይከተላል።
ሁለት ሚስት ማግባት በሕግ ወንጀል ነው፤ ሰባት ሴቶችን በፍቅረኛ ስም መያዝ ግን ዘመናዊነት ነው።
ወደ ቤተ መቅደስ ሄዶ ለአምላክ ማጎንበስና ማወደስ ኋላ ቀርነት ነው፤ ወደ ዳንስ ቤት ሄዶ አስካሪ መጠጥ ሲጋቱ ማደርና ሙዚቃ መጋበዝ ዘመናዊነት ነው።

ግብጻዊው ሊቅ ሙሐመድ አል-ገዛሊ፣ ‹‹አሁን ያለው ሥልጣኔ አላህን የረሳ፣ ለመጭው ዓለም ቅንጣት ታክል ዝግጅት የሌለው፣ ከቁሳዊ ዓለም ባሻገር ያለውን የሚያስተባብል፣ የዛሬዋን ብቻ የሚያመልክና ሁለመናው በቁሳዊ ነገር ላይ የተደገፈ ነው።›› ሲሉ ቁጭታቸውንና ትዝብታቸውን ጽፈዋል።

አሁን ባለው ዓለም የምክንያት ሰው ተፈጥሯል፤ የተማረ ሰው ተፈጥሯል፤ ሕይወትን የሚያገልግል ሰው ተፈጥሯል። ነገር ግን ግቡ ፍጹም ዓለማዊነት ነው። መገለጫዎቹ የግለሰብ ነጻነት፣ ብዝሃነት፣ የፖለቲካ ዓለማዊነት፣ የመንግሥትና የሃይማኖት መሪዎች መለያየት፣ የባህል ዓለማዊነት፣ የባህልና የሃይማኖት መነጣጠልና የመሳሰሉት ናቸው።

በሌላ በኩል ደግሞ ዘመናዊነት ብዙ በረከትንም አምጥቷል። ዋናው ነገር ነቅሶ የመመልከቱ ጉዳይ ነው። ዘመናዊነት የተለያየ አበባ ቀስማ ማር እንደምታመርት ንብ ነው። የሆነ የንብ መንጋ ሲነክሰን ማር ላለመጠቀም አንወስንም።
ስለዚህ ከዘመናዊነት ውስጥም መጥፎ ነገር መመልከታችን፣ መልካም መልካሙን መርጠን ከመጠቀም ሊከለክለን አይገባም።

https://nejashibooks.com/

https://t.me/Nejashipp
ዱዓና ሰበቡ
***
አላህ የአንድን ሰው ጉዳይ ሊፈጽምለት ሲሻ ዱዓን ያገራለታል። ዱዓ ያደረገም ጉዳዩ ያለጥርጥር ተፈጽሞለታል። ይህም ልክ በክረምት ወራት ጥቁርና ቀዝቃዛ ደመና ስናይ ዝናብ የመዝነቡ ምልክት አድርገን እንደምንወስደው ማለት ነው። መልካም ሥራ ከምንዳ፣ ወንጀል ከቅጣት ጋር ያላቸው ግንኙነትም እንደዚሁ ነው። ምልክቶች እንጂ ምክኒያቶች አይደሉም።

ውጤት ከምክኒያት ጋር የተሣሠረ ነው፡፡ ማለትም መጥገብ ከመብላት፣ የጥም መቆረጥ ከመጠጣት ፣ መውለድ ከፆታዊ ግንኙነት፣ የአዝርዕት መብቀል ከመዝራት፣ ጀነት መግባት ከመልካም ሥራ፣ እሣት መግባት ደግሞ ከመጥፎ ሥራ የተሣሠሩ ናቸው።
እንደዚሁ ደግሞ ዱዓ ከውጤቱ ጋር የተሣሠረ ነው። ምክኒያት (ሰበብ) ሲገኝ ውጤት (ሙሰበብ) ይገኛል። ምክኒያት ሲጠፋ ውጤትም ይጠፋል። ዱዓ የከጀሉትን ለማግኘት ጠንካራ ሰበብ ነው። ለመጥገብ መብላት ጥምን ለመቁረጥ መጠጣት አያስፈልግም እንደማይባለው ሁሉ የከጀሉትን ለማግኘት ዱዓ አያስፈልግም አይባልም።

የሚፈልጉትን ለማሳካት ከዱዓ የተሻለ ጠቃሚ መሣሪያ የለም። እስልምናን ከማንም በላይ የሚያውቁት ሶሐቦች ከማንም በላይ አላህን ይለምኑት ነበር። የዱዓን ሰበብ ስርዓቱን አሟልተው ያደርሱም ነበር።

ታላቁ ኸሊፋ ዑመር ኢብኑል ኸጧብ (ረ.ዐ) ጠላቶቻቸውን በዱዓ ድል ይነሳሉ። እንዲህ ይሉ እንደነበርም ተወስቷል፡-
“እኔ የዱዓን እንጂ የተቀባይነትን ሃሳብ አልሸከምም። ዱዓ እንዳደርግ እድል ካገኘሁ ተቀባይነት አብሮት እንዳለ አውቃለሁ።”


“ፈፊሩ ኢለላህ/ ወደ አላህ ሽሹ” ከተሠኘው መጽሐፍ የተወሰደ
ትርጉም ፡ አሕመድ ሑሴን (አቡ ቢላል)

https://nejashibooks.com/


https://t.me/Nejashipp
መታወቅ የፈለገ …
***
“ዑመር ነህ ወይ?” አሏቸው፡፡ ሰዎች ለምእመናን መሪ ዑመር ኢብኑል ኸጧብ፡፡
“አዎን ዑመር ነኝ፡፡” አሏቸው፡፡
“ ኦ ያ ጀግናው! ያ ፋርሦችን ድል ያደረገው! ያ ሩሞችን ያፈራረሰው ዑመር?!” አሏቸው፡፡
“ ላ ላ አይደለም፡፡ እኔ ዑመር ነኝ፡፡ ያ የአላህ መልዕክተኛ ባልደረባ የነበረው ዑመር ነኝ፡፡ ከዚህ የበለጠ ክብርም ማዕረግም የለኝ፡፡” አሏቸው አሉ፡፡
ያንቱ ኡመት ከመሆን በላይ ምን ክብር አለ ያ ነቢየሏህ!!፡፡

https://nejashibooks.com/

https://t.me/Nejashipp
የልብ ጤንነት ምልክቶች ፦
1. አኺራ ላይ እስኪያርፍ ድረስ ዱንያን መናቁ ነው፦ በአኺራ ውስጥ ልክ ከነዋሪዎቿና ከልጆቿ እንደ አንዱ እስኪሆን ድረስ ይሰፍራል፣ ወደዚህች አገር (ዱንያ) የመጣው ደግሞ ጉዳዩን ወስዶ ወደ አገሩ እንደሚመለስ ባይተዋር እንግዳ ሆኖ ነው፤ ነቢዩ (صلى الله عليه وسلم) ለዐብዱላህ ኢብኑ ዑመር (رضي الله عنهما) እንዳሉት፦
«كُنْ فِي الدُّنْيَا كَأَنَّكَ غَرِيبٌ أَوْ عَابِرُ سَبِيلٍ»
«በዱንያ ውስጥ እንደ እንግዳ ወይም እንደ መንገደኛ ሁን።» (ቡኻሪ ዘግበውታል)።
ልብ በታመመ ቁጥር ግን ዱንያን ይመርጣል፣ ከዘላቂ ነዋሪዎቿ እስኪሆን ድረስም አገሩ አድርጎ ይይዛታል።
2. ባለቤቱን ወደ አላህ እስኪመለስና እስኪተናነስ ድረስ መጎትጎቱን አለማቋረጡ፦ ፍቅር ያገረሸበት አፍቃሪ ከተወዳጁ ጋር እንደሚቆራኘው በአላህ ላይ ይንጠለጠላል፤ በእርሱ ፍቅር ከሌላው ፍቅር፣ እርሱን በማውሳት ሌላውን ከማውሳት፣ በእርሱም አገልግሎት ከሌላው አገልግሎት ይብቃቃል።
3. የዕለት ተዕለት የቁርኣን ወይም የዚክር ድርሻው (ዊርዱ) ወይም አንዲት መታዘዝ (ጧዓ) ካመለጠው፣ ስግብግብ ሰው ገንዘቡ ሲያመልጠውና ሲጠፋበት ከሚሰማው ሕመም የበለጠ ሕመም መሰማቱ።
4. የተራበ ሰው ምግብና መጠጥን እንደሚናፍቀው ሁሉ አላህን ወደ ማገልገል መናፈቁ፦ የሕያ ኢብኑ ሙዓዝ (رحمه الله) እንዳሉት፦ «አላህን በማገልገል የተደሰተ ሰው ነገሮች ሁሉ እርሱን በማገልገል ይደሰታሉ፤ ዓይኑ በአላህ የረካችም ሰው የሁሉም ሰው ዓይን ወደ እርሱ በመመልከት ትረካለች።»
5. ሐሳቡ (ጭንቀቱ) አንድ ብቻ መሆኑና እርሱም በአላህ (በአላህ ውዴታና መታዘዝ) ውስጥ መሆኑ።
6. ከሰዎች ሁሉ ለገንዘቡ እጅግ ንፉግ ከሆነው ሰው ይበልጥ፣ ጊዜው በከንቱ እንዳይባክን ለጊዜው በጥብቅ ተጠባባቂና ንፉግ መሆኑ።
7. ወደ ሰላት ሲገባ የዱንያ ጭንቀቱና ሐዘኑ ሁሉ ከእርሱ ላይ መሄዱ፦ በሰላት ውስጥ እረፍቱን፣ ድሎቱን፣ የዓይኑን ማረፊያና የልቡን ደስታ የሚያገኝ መሆኑ።
8. ጌታውን ከማውሳት አለመቦዘኑ፣ እርሱን ከማገልገል አለመሰልቸቱና ወደ አላህ ከሚያመላክተውና እርሱን ከሚያስታውሰው ሰው በስተቀር ከሌላ ሰው ጋር አለመወዳጀቱ።
9. ከሥራው ራሱ ይልቅ ሥራውን በማስተካከል ላይ ያለው ትኩረት የበለጠ መሆኑ፦ በሥራው ውስጥ ለኢኽላስ፣ ለቅንነት፣ ለሱንና ተከታይነትና ለመልካምነት ይጓጓል፣ ከዚህም ሁሉ ጋር በእርሱ ላይ ያለውን የአላህን ውለታና በአላህ መብት ላይ ያለውን የራሱን ጉድለት ይመሰክራል።