የኡስታዝ ሱልጣን ኸድር የትምህርት መድረክ (official)
13.3K subscribers
3.58K photos
731 videos
126 files
2.42K links
ይህ በኡስታዝ ሱልጣን ኸድር እውቅና የተከፈተ ብቸኛው (official) ቻነል ሲሆን የእርሱ ትምህርቶችና አጫጭር መልእክቶች በየጊዜው የሚተላለፉበት ልዩ መድረክ ነው፡፡

አላህ መልካም ምንዳውን ይክፈለው፤ ከዕውቀቱም ተጠቃሚ ያድርገን!
ትምህርታዊ ቁም ነገሮች ላይ መሳተፍ የምትፈልጉ እንዲሁም ሐሳብና አስተያየት ካልዎት በዋትስ ኣፕ ይላኩልን!
♻: https://api.whatsapp.com/send?phone=
Download Telegram
በአንዳንድ ወጣቶች አእምሮ ውስጥ፣ አንዳንድ ጊዜ ከመጠን በላይ በሆነ እራስን የመተማመን ስሜት የታጀበ፣ ለስላሳ እና ሮማንቲክ የሆነ አስተሳሰብ ይሰረጻል፤ ይህም አንዳንዶቹ፡ «ዲኗን ያልጠበቀች ወይም የላቀ በጎ ምግባር የሌላትን ሴት አግብቼ በራሴ እጅ አርማታለሁ፤ ወይም እቀይራታለሁ ፣ ወደ ቅን መንገድም እመራታለሁ» ብለው እንዲያስቡ ያደርጋቸዋል። ይህንንም የሚያስቡት በጥበባቸው፣ በጠንካራ ስብዕናቸው እና በሰዎች ላይ ባላቸው የማነፅ አቅም በመተማመን ነው።
​ይህ አስተሳሰብ፣ ውጫዊ ገጽታው በመልካም እሴት የተሸፈነ ቢመስልም፣ በውስጡ ግን ትልቅ ስህተትን እና ፍጹም ተገቢ ያልሆነ ዓይነ-ሥውር የሆነ በራስ የመተማመን ጥግ ነው።
نعوذ بالله من الحور بعد الكور!
👍14❤7
ዲንን ማቃለል እና በ«ዑለሞች መካከል ልዩነት/ኺላፍ አለ» በሚል ሽፋን ስሜትን መከተል
በዑለሞች መካከል ኺላፍ አለባቸው በሚል ምክንያት በርካታ ዲናዊ ጉዳዮችን ለማቃለል (ለማለስለስ) መሞከር፤ በልዩነቱም በመመካት ደካማ የአቋም ብያኔዎችን ለመከተል ሰበብ መፈለግ፤ እንዲሁም የተገለሉና አሻሚ አቅዋሎችን ማስተዋወቅ፣ ማሰራጨት እና በህዝቡ መካከል ማስፋፋት ሰዎች የተሳሳቱና አሻሚ አቋሞችን እንዲይዙ ማድረግ እጅግ አደገኛ መርዝ ነው።
ይህ ድርጊት ያለ ምንም ጥርጥር ዲንን ከማበላሸት የሚቆጠር ሲሆን፣ መጥፎ አላማ ላላቸውና በሽታ ያለባቸው ደካማ ነፍስ ለአስከፊ ተግባራቸው እንዲሁም ሸይጣኖቻቸው በዓለም ላይ እንዲያሰራጩ የሚጎተጉቷቸውን መጥፎ ሃሳቦች ለመተግበር በሩን ይከፍትላቸዋል።

ቃዲ አቡ በክር እብኑል አረቢ እንዲህ ብለዋል፡-
«የሚከሰቱትን ኺላፎች በሙሉ የምንከተልና የምንጠብቅ ቢሆን ኖሮ፣ ዲን በማንኛውም መሰረት ላይ ሊረጋገጥና ሊፀና ባልቻለ ነበር።»
❤8
ፊትን መሸፈን(ኒቃብ) ጉዳይን በተመለከተ፡ ዑለሞች ከሴት ልጅ ፊትና ሁለት መዳፎች ውጭ ያሉትን የሰውነት ክፍሎች ሙሉ በሙሉ መሸፈን ግዴታ (ዋጅብ) መሆኑ ላይ በጋራ ተስማምተዋል (ኢጅማዕ አድርገዋል)። ማለትም፡ ሁለት እግሮቿን፣ እጅን እስከ ክርን ቢሆን ማሳየት ይፈቀዳል የሚል አንድም የለም።
​ሁለተኛ፡ ዑለሞች ፊትንና ሁለት እጆችን መሸፈን ትልቅ ደረጃ ያለው፣ (በላጭ ነው) የታዘዘበት እና የተወደደ (ሙስተሃብ) ተግባር መሆኑ ላይ ተስማምተዋል። ፊትን ማሳየት ይፈቀዳል የሚሉት እንኳ መሸፈኑ የተወደደ ነው ይላሉ፤ ምክንያቱም እጅግ ዝቅተኛው ጥቅም እንኳ ከልዩነት (ኺላፍ) ለመውጣት ይረዳልና።
​ሦስተኛ፡ በውበቷ ምክንያት ፈተና ይፈጠራል ተብሎ የሚሰጋባት ቆንጆ ሴት ፊቷንና ሁለት እጆቿን መሸፈን ግዴታ (ዋጅብ) ይሆንባታል በሚለው ላይ ተስማምተዋል። እንዲሁም ማሳየት ይፈቀዳል የተባለው ፊት ምንም ዓይነት ሜካፕ (የፊት መኳኳያ) የሌለበት መሆን አለበት በሚለው ላይም ተስማምተዋል።
❤22👍17
በመጀለት አድ-ደዕዋ (ቁጥር 1591፣ በ9/1/1418 ሂ) ላይ «ፊ ዚላሊል ቁርኣን» በተሰኘው መጽሐፍ ዙሪያ ለቀረበላቸው ጥያቄ ኢማም ኢብኑ ዑሠይሚን -ረሒመሁልላህ- ሲመልሱ እንዲህ ብለዋል፦
«ለሱረቱል ኢኽላስ የሰጡትን ተፍሲር አንብቤአለሁ፤ በእሷም ውስጥ ከአህሉሱና ወልጀማዐህ እምነት ያፈነገጠ ታላቅ (አደገኛ) ንግግር ተናግረዋል። ተፍሲራቸው የሚያመላክተው "ወሕደቱል ውጁድ" (ፍጡርና ፈጣሪ አንድ ናቸው) የሚለውን እምነት እንደሚቀበሉ ነው። እንዲሁም "ኢስቲዋእ" የሚለውን የኣላህ መገለጫ "በስልጣኑ ተቆጥጥረና በስልጣን የበላይነት" (ሀይመናህ ወሰይጠራህ) ብለው ፈስረውታል።»
👌15❤6👍5
Audio
وشهد شاهد من أهلها
ይህ እንግዲህ የዚህ ዘመን የኢኽዋን ዓሊምና ኢማም የሆኑት አል-ቀርዳዊ የሰይድ ቁጥብን የ‘ተ‘ክፊዐር አካሄድ (መንሃጅ) የሚያረጋግጡበት ምስክርነት ነው።
ዩሱፍ አል-ቀርዳዊ «አውላውያት አል-ሐረካህ አል-ኢስላሚያህ» በተሰኘወወ  መጽሐፋቸው፤(ገጽ 110) ላይ፦
"በዚህ ደረጃ ላይ የሸሂዱ የሰይድ ቁጥብ መጻሕፍት ብቅ አሉ፤ እነዚህም የመጨረሻውን የሐሳብ እድገት ደረጃውን የሚያንፀባርቁ ሲሆኑ፡ ማህበረሰቡን በ‘ካ’ፊ’ር’ነት በመፈረጅ፣ ፊቅህን የማደስና የማሻሻል እንዲሁም ኢጅቲሃድን  (የማንቃት) ሐሳብን በመጠቀም ወደ ኢስላማዊ ስርዓት የሚደረገውን ጥሪ በማዘግየት፣ ከማህበረሰቡ የስሜት መገለልን (ዑዝላህ ሹዑሪያህ) ማድረግንና ከሌሎች ጋር ያለውን ግንኙነት ማቋረጥን ጥሪ የሚያደርጉ፣ ሁሉንም ሰዎችን የማጥቃት ጂሃድ ማወጅን እንዲነሳሱ የሚያደርጉ፣ እንዲሁም የመቻቻልና የለዘብተኝነት ጥሪ አድራጊዎችን የሚያናንቁና በምዕራባውያን ሥልጣኔ ፊት በየዋህነትና በስነ-ልቦና ሽንፈት የሚከተሷቸው ናቸው።" የሚሉ ትችቶቹ የኋላ ኋላ ብቅ ብቅ ማለት ጀመሩ። ይህ አመለካከቱ «ፊ ዚላል አል-ቁርዓን» ሁለተኛው ዕትም ላይ እና «መዓሊም ፊጥ-ጠሪቅ» መጽሐፉ ላይ በጣም በግልጽ ጎልቶ ይታያል።»
❤18👍3
የዚህ ዘመን አብዛኞቹና ዋና ዋናዎቹ የኢማን መንሸራተት መንስኤዎች ወደ ሁለት ነገሮች ይመለሳሉ፦
የመብተኝነት (የይገባኛል) ስሜት የበላይነት፤ አላህ የሚሰጣቸውን ጸጋዎች እንደ መለኮታዊ ችሮታ አድርጎ ከመመልከት ይልቅ፣ በፈጸሙት ታዛዥነት ብቻ እንደተገቢነታቸውና እንደሚገባቸው አድርጎ መገመት።
የዱንያ በልብ ውስጥ ማዕከል መሆንና፤ የተቅዋና የታዛዥነት ዓላማ የዱንያን ጥቅም በመሻት ላይ ብቻ መወሰን። በዚህም ምክንያት የአኺራ ህልውና በልብ ውስጥ ይዳከማል፤ ዱንያ ግብ ይሆናል፤ ጊዜያዊውም ነገር ዘላቂ ተደርጎ ይወሰዳል።
በልብ ውስጥ ማንኛውም ጸጋ ከአላህ የሚገኝ ችሮታና ስጦታ መሆኑ፣ እንዲሁም ዋናው ግብ አኺራ እንደሆነ ቀልባችን ውስጥ ከሰረፀና ከጸና፤ መንገዱ ይቃናል፣ ከብዙዎቹም የኢማን መንሸራተት መንስኤዎች በአላህ ፈቃድ ይጠበቃል።
👍18❤11
በቤታችሁ ውስጥ ያለውን አላውቅም፤ ነገር ግን በውስጡ ያለውን ሁሉ የሚያውቀውን አላህን እንዲህ ስል እለምነዋለሁ🤍
በውስጡ ታማሚ ካለ እንዲፈውሰው፤ በውስጡ የተጨናቀ ካለ ጭንቀቱን እንዲገላግለው፤ በውስጡ ባለዕዳ ካለ ዕዳውን እንዲከፍልለት፤ በውስጡ የተፈተነ ካለ ጤና እና ሰላም እንዲሰጠው፤ በውስጡ በዓይን ናስ የተጎዳ ካለ የዓይኑን ጉዳት እንዲያጠፋለት፤ በውስጡ መካን ካለ መልካም ዘርን (ልጅን) እንዲለግሰው፤ የእኛንም ሆነ የእናንተን ሙታን በሙሉ እንዲምርልን እማፀነዋለሁ...
❤89👍24🥰5👌1💔1
አንዳንዶቹ  እጅግ ወሰን ያለፈ አድናቆት ለዘመናዊ ግለሰቦች ባላቸው ስሜታዊ ተፅዕኖ መሸነፍ የተነሳ፤ ከነቢዩ ﷺ ባልደረቦች (ሶሃቦች) ይልቅ ለኋለኞች የበለጠ እንዲያደሉ እና እንዲቆረቆሩ ያደርጋቸዋል።
👍31😱1
«ሱኒይ» (የሱና ተከታይ) ማለት ስሜታዊ ፍላጎቶች፣ ቢድዐዎችና የተለያዩ የጥመት አንጃዎች በተወሱ ጊዜ፤ ወደ አንዱም አያዘነብልም፣ ለማናቸውም ወገንተኝነትን (ተዐሱብን) አያሳይም፤ ይልቁንም በቁርኣንና በትክክለኛው የነቢዩ  ﷺ ሱና ላይ ብቻ ይጸናል።»
አቡበጀር ኢብኑ ዐያሽ
👍21❤2
قال الشيخ العلامة زيد المدخلي
رحمه الله

“وقهـــوةُ البُنِّ للأبــــدانِ مُنْعِشـــةٌ …
مذاقُهَـــا مُمتــعٌ كالبُرِ والعسلِ

رفيقــةُ العُمْرِ في الأسفـارِ مُؤنسةٌ …
كنفحةِ المِسْكِ إن فاحتْ بلَا جدلِ

وبُغْيةُ النَّفـسِ في الإصْبَاح مُبهجةٌ …
تَسُرُّ إلْفًا مَتَى جــاءَتْ على مَهَلِ

ِيـا حبَّذا الشِرْبَ إنْ صاغتهُ ماهِرةٌ …
لِتُكْرِمَ الضَّيْفَ مِـنْ آتٍ ومُرْتحِــل

في كُــلِّ بيتٍ لَهَــا ذِكْرٌ ومَنْقَبَــــةٌ …
تُضَاحِكُ الخِلَّ إينَاســاً بِـــلا خَطَـلِ

تقولُ مرحى وطول الوقتِ بَاسِمَةٌ …
تُعِيدُ مَرْحَى رَفيــعَ القَـــدْرِ والمُثُلِ

لا عيب فيهــا ومِنْ غَوْلٍ مُبَرَّأَةٌ …
فاشْربها صِرْفًا ولا تخشى من العِلَلِ”
___
■الشيخ العلامة زيد بن هادي المدخلي رحمه الله

■المنظومات الحسان(الديوان المليح) لزيد بن هادي المدخلي – ص 343 ط الأولى، دار الميراث النبوي.€___
የጤና ባለሙያዎች በአጠቃላይ በቀን እስከ 400 ሚሊግራም ካፌይን ወይም አራት ባለ 8 አውንስ ስኒ ቡና መጠጣት ምንም ጉዳት እንደሌለው ይናገራሉ።

ከዚህ በላይ መጠጣት ግን የጤና ችግሮችን ሊያስከትል ይችላል።

✅ የቡና ጥቅሞች:

የአልዛይመር እና የፓርኪንሰን በሽታን ይከላከላል።

ለልብ እና ለጉበት ጤና ጠቃሚ ነው።

አንዳንድ የካንሰር አይነቶችን ተጋላጭነት ይቀንሳል።
👍18❤12
🔸ሸይኽ ዑሰይሚን(ረሂመሁላህ) እንዲህ ብለዋል፦
"እኛ የምንለው ፦
ሰለፍ ማለት አህሉ ሱና ማለት ነው፣ የአህሉ ሱና መገለጫ ከነሱ ውጭ ለማንም አይሆንም።በጭራሽ!
"አህሉ ሱና ወልጀማኣ ሲባል (ሰለፍዬች፣አሽኣሪዬች እና ማቱሪዲዮች ናቸው።" የሚል ተሳስቷል።
ይህ ስሕተት ነው!!
ሁሉም አህሉ ሱናህ ሊባሉ ይችላልን?
ከሐቅ በኋላ ጥመት እንጂ ሌላ የለም።
አንዱ ሌላኛው ላይ ምላሽ እየሰጠ እንዴት ሆኖ ሁሉም አሕሉ ሱና ሊሆኑ ይችላሉ?
ይህ ሊሆን ፈፅሞ አይቻልም፣ምናልባት ሁለት ተቃራኒ ነገሮችን በአንድ ላይ ማሰባሰብ ከተቻለ እንጂ!!
ከነዚህ አንጃዎች አንዱ ብቻ ነው አህሉ ሱና ሊሆን የሚችለው።
እሱ ማነው?
አሽኣሪያ?
ወይስ ማቱሪዲያ?
ወይስ ሰለፊያ?
ሱናን የገጠመ እርሱ አሕሉ ሱና ነው፣ሱናን የተፃረረ እርሱ አሕሉል ቢድዓ ነው።
እኛ የምንለው ፦
ሰለፍ ማለት አህሉ ሱና ማለት ነው ከሰለፊዮች ውጭ የአህሉ ሱና መገለጫ ከነሱ ውጭ ለማንም አይሆንም።በጭራሽ!"

【"ሸርሑ ዐቂደቱ አልዋሲጢያ"(1/33_34)】

(የመክተበቱ ጠበሪያ ህትመት አንደኛ ዕትም)

https://telegram.me/sultan_54
👌9❤4
Audio
من هو سيد قطب
للشيخ إلياس أحمد
👍12❤4
ኢላሂ! ከ አንተ ሌላ ወደ ማንኛውም ፍጡር አታስጠጋን፤ በ አንተ የጠነከርን፣ በ አንተም ከዓለማት ሁሉ የተብቃቃን አድርገን።
ኣሚን!
👍22❤6🥰6
ሰባሑል ኸይር!🌷
ተጠበሃል? ነገሮች ተወሳስበውበሃል? ተጨናነቀሃል?
እንግዲያውስ! ​አይዞህ! እሱኮ የ"ፈረጃው" (ከጭንቀት መውጫው)የመጀመሪያዋ ምልክት ነውና አብሽር! የፈረጃው ብርሃን የሚፈነጥቀው መንገዶች ሁሉ ሲዘጉ እና ሁኔታዎች የተወሳሰቡ እና ጨለማ ሲሆኑ ነው።
​ይህም ደግሞ የአላህ (አዘወጀለ) ደንብ (ሱንና) ነው!
​{ መልእክተኞቹ [የሕዝቦቻቸውን ማመን] ተስፋ በቆረጡ እና (መልእክተኞቻቸው ከሐዲዎችን በማጥፋትና ምዕመናንን በማዳን ረገድ የገቡላቸው ቃል )በእርግጥም የተዋሹ መሆናቸውን ባሰቡ (በጠረጠሩ)ጊዜ (ለመልክተኞች)እርዳታችን መጣላቸው...}
📚 [ዩሱፍ: 110]
❤15👍8🥰1
ምስጋና ለአላህ ይሁንና! የአህሉሱና ወልጀማዐህ ኩቱቦች በዐቂዳ፣ በፊቅህ እና በስነ-ምግባር (ሱሉክ) ዘርፎች በተሟላ እና በተደራጀ መልኩ ይገኛሉ፤ እነሱም ከሌሎች አህሉል አህዋእ መጻሕፍት ሁሉ የሚያብቃቁ ናቸው።
የስሜትና "የፊክር" ባለቤቶች የሚመጡ ኩቱቦችን ለመመልከት ዝም ብሎ በስሜታዊ ጉጉት ወይም በራሱ ላይ ባለው ከመጠን ያለፈ እምነት (ትዕቢት) የሚተማመን ሰው፣ በገዛ ኩራቱና ድፍረቱ ምክንያት ለፈተና ተዳርጓል።
نسأل الله السلامة والعافية!
والسلامة لا يعدلها شيء.
❤22👍6
*سؤال صريح..*
*لو عرضت حياتك ڪاملة بڪل تفاصيلها ڪ فيلم...*
*هل تستطيع مشاهدته مع أهلك..؟ وعرضه أمام الناس..؟!*
*إذا ڪان الجواب ( لا )*
*فأحسن انتاج الفيلم لأنه سيعرض يوم القيامه .*
*ولا تجعل الله اهون الناظرين لك.*
*وتخشي الناس والله أحق أن تخشاه.*
❤6
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
❤9
🪶
ኢማም አን-ነወዊይ እንዲህ ይላሉ፦
«የጠዋትና የማታ አዝካሮችን ሙሉ በሙሉ ለመተግበር እድሉን (ተውፊቅን) ያገኘ ሰው፤ ይህ ከአላህ የተሰጠው ትልቅ ፀጋና ችሮታ ነው፤ ለርሱም የምስራች እንለዋለን! ሁሉንም አዝካሮች ማለት ያልቻለ (የተሳነፈ) ሰው ደግሞ ከአጫጭር አዝካሮች መካከል የፈለገውን — አንድ አዝካር እንኳ ቢሆን — አጠር አድርጎ ያድርግ (ያብቃቃዋል)!»
‏📚المصدر : كتاب الأذكار (١٥٧).
👍27❤6👌3
ኢስላማዊ ነሺዳ በብዙ ዘመናዊ ቅርጾቹ ከመጀመሪያው ሸሪዓዊ ፅንሰ ሀሳብ እና እሴት ዓላማው የወጣ ሲሆን፤ ከተፈቀደ የመዝናኛና የሞራል ማነቃቂያ መንገድነት ተቀይሮ የንግድ ዘፈንን ወደሚመስል የመዝናኛ ኢንዱስትሪነትና ቁርዓንን ማዳመጥን ወደ መጋፋት ተሸጋግሯል።
ይህን እውነታ የሚክድ ሰው አላህ ልቦናውን ያጨለመበትና በስሜቱ የታወረ ሰው ብቻ ነው።
💔19👍13❤8👌2
ከመመሳሰል አልፎ ዘፈን የሆነው ዘመናዊው ነሺዳ!

በሰለፎች  ዘንድ «ነሺዳ» ወይም «ሁዳእ» (የመንገድ ላይ እንጉርጉሮ) ማዳመጥ በምንም መልኩ አሁን እንደምናየው የዘፈን ልማድ አልነበረም። ይልቁንም በተወሰኑ አጋጣሚዎችና ለአጭር ጊዜ  “መዝናናት” በሚያስፈልግበት ወቅት ብቻ የሚደረግ እንጂ የዘወትር ልማዳቸው ወይም የቀልባቸው ዋና ቀለብ አልነበረም።
በሰለፎች ዘንድ ነሺዳ የሚደመጥባቸው ሁኔታዎች፦
በሥራና በአሰልቺ ጉዞ ጊዜ ብቻ መወሰኑ፦ እንጉርጉሮ የሚባለው ድካምን ለማቃለልና መንፈስን ለማነቃቃት ሲባል ብቻ ነበር፤ ለምሳሌ በኸንደቅ ቁፋሮ፣ በነቢዩ  ሰለሏሁ አለይሂ ወሰፀም መስጅድ ግንባታ ወቅት፣ ወይም በበረሃ ጉዞ ላይ የግመል ተጓዦችን ለማበራታት ይደረግ ነበር።
ቀላልና ድንገተኛ (ያልተዘጋጀበት) መሆኑ፦ ከሰለፎች (ቀደምት ደጋግ  የዲን አበዎች)አንዳቸው ያለ ምንም "ተከሉፍ"(አለመጨናነቅ)፣  የድምፅ አጣጠል እና ፈሰት ስለጠና ሳይወስዱ፣ ዜማን ሳያወሳስቡ፣ ድምፅን ለማለዘብ ሳይሞክሩና ምንም ዓይነት የድምፅ መሣሪያ ሳይጠቀሙ አንድ ወይም ሁለት ስንኝ ያንጎራጉሩ ነበር።
የዘፈን ቅርፅ የሌለው መሆኑ፦ ሰዎችን ሰብስቦ ማስዳመጥ፣ «ሙንሺድ» የሚባል የተለየ የሙያ ዘርፍ አለመኖሩና እራሳቸውን ለእንጉርጉሮ ስራ አለመመደብ፣ ወይም ለዚሁ ተብሎ ልዩ ፕሮግራም ማዘጋጀት በነሱ ዘንድ አልነበረም።
ሰለፎች ነሺዳን የዘወትር ልማድ የማድረግ አመለካከታቸው፦
የቀልብ ዋና ቀለብ ቁርኣን መሆኑ፦ የእነሱ የዘወትር ልማድና ቀልባቸው ለማለዘብ አዘውትሮ ቁርኣንን ማንበብ፣ አላህን ማውሳት (ዚክር) እና ሸሪዓዊ እውቀትን መቅሰም ብቻ ነበር።
በአንፃሩ ዛሬ ላይ ያሉ የዘመናዊው ነሺዳና የዘፈን መመሳሰል፦
➡️​ የድምፅ መሣሪያዎችና የዲጂታል «ሳውንድ» አጠቃቀም
➡️​ የዘፈኖችን ዜማና የአቀራረብ ስልት ቀጥታ መኮረጅ
➡️​ የግጥሞች ይዘት ወደ ፍቅርና ስሜታዊነት ማደል
➡️​ የቪዲዮ ክሊፖችና የሙንሺዶች የኮከብነት አባዜ
🔴 ከዚህ በመቀጠል ጥቂት ከሰለፎች አንደበት የተገኙ ጥቅሶችን (ኑቁላቶች) ላጋራችሁ፦

ወሰን ከማለፍ ማስጠንቀቃቸው፦ በእስልምና ሊቃውንት ዘመን (በፉቀሃዎች)
(እንደ «ተግቢር» ያሉ በድቤ የታጀቡ እና በዜማ የተዘጋጁ እንጉርጉሮዎች) ብቅ ሲሉ አበክረው ኮንነዋል።
ኢማም ሻፊዒይም (رحمة الله عليه) ደግሞ፦ «በበግዳድ ከቁርኣን የሚያዘናጋና ዚንዲቆች (መናፍቃን) የፈጠሩትን '“ተግቢር”' የሚባል ነገር ትቼ ወጣሁ» ብለዋል።

የኢማሙ አሽ–ሻፊዒ ደረሳ የሆኑት አቡ አብዲላህ(ኢማም አሕመድ) ተጠየቁ? አሕመድ ቢን ሐንበል ስለ «ተግቢር» (በዜማ ስለሚደረግ እንጉርጉሮ) ተጠይቀው፦ «አዲስ የመጣ ቢድዓ (ፈጠራ) ነው» አሉ። « የደረቀ ቀልብን ያረሰርሳል እኮ» ተብለው ሲጠየቁ፦—–ይህ ብዥታ አላህ እኛንም እነሱንም ይቅር ይበለንና አብዛኞቹ የሚያነሱት መከራከሪያ ነጥብ  ነው—እሳቸውም፦ «ከነሱ ጋር አትቀማመጡ» አሉ። !!!
የሸይኹል ኢስላም ኢብኑ ተይምያህ (ረሒመሁላህ) በኢማም አሽ-ሻፊዒይ ንግግር ላይ የሰጡት አስተያየት እጅጉን ያሰደንቃል!፤ እንዲህ ብለዋል፦
«ይህ የኢማም አሽ-ሻፊዒይ የላቀ እውቀትና የእስልምና  ጥልቅ ግንዛቤ የመጣ ነው፤ ምክንያቱም ቀልብ ግጥሞችንና ስንኞችን አዘውትሮ ማዳመጥ ከተለማመደና በእነሱ መዝናናትን ካበዛ፣ ቁርኣንንና አንቀጾቹን ከመስማት መሸሽና መራቅ ይፈጠርበታል።»
እንዲሁም ብለዋል፦

«ኢማም አሽ-ሻፊዒይ (ረ ዲየላሁ ዐንሁ) "ይህ በመናፍቃን የተፈጠረ ነው" ማለታቸው፣ በእስልምና መሠረቶች ላይ ጥልቅ እውቀት ያለው ኢማም ንግግር ነው፤ ምክንያቱም ይህን መሰሉን ስማዕ (ዜማ/ነሺዳ) ከመጀመሪያውኑ የመረጡትና ወደ እሱ የተጣሩት በመናፍቅነት የተጠረጠሩ ሰዎች እንጂ ሌላ አይደለም።»
ኢማም አጥ-ጠርጡሺይ (ረሒመሁላህ) «ተሕሪሙስ-ሰማዕ» በተሰኘው መጽሐፋቸው ላይ እንዲህ ብለዋል

፦
«አላህ እኛንም እነሱንም ቅኑን መንገድ ይምራንና፣ ከሙስሊም ወንድሞቻችን የሆኑ አንዱ ጭፍራ ሸይጧን ያንሸራተታቸው፣ ዘፈንን፣ መዝናኛን፣ "ጠቅጠቃን" እና "ተግቢርን" በመውደድ አእምሯቸውን ያሳታቸው መሆኑ ደርሶናል። ወደ አላህ የሚያቃርብ የዲን አካል አድርገው ያመኑበት ሲሆን፣ በሙስሊሞች ስብስብ ፊት ይፋ አድርገውታል፤ የሙእሚኖችንም መንገድ ተቃርነዋል፣ የፊቅህና የዲን ሊቃውንትንም ተፃርረዋል

።
»
በአጠቃላይ፣ ሰለፎች ነሺዳን እንደ ተቋቋመ የመዝናኛ ኢንዱስትሪ ወይም የዘወትር ልማድ አያውቁትም ነበር፤ ይልቁንም ቀልብ በቁርኣን ከመጠመድ እንዳይወጣ መጠኑን የጠበቀ አልፎ አልፎ የሚደረግ መዝናኛ ብቻ ነበር።
ይህም (ነሺዳ ማዳመጥ) ሱሰኝነት፣ ፍቅርና መዝናኛ "ለህው" ሊሆን ይችላል—አላህ ይጠብቀንና—ቀልቡም ቢሆን የዚያን የሚያፍቅረው ሙንሺድ (አዝማሪ) ድምፅ ካልሰማ በቀር አይረካም። በተለይ ሴቶች በተቃራኒ ፆታ ፈተና፣ ድምፅ በመማረክ ፈተና ውስጥ ይወድቃሉ። ልክ ዘፈን ላይ እንዳለው። የሙንሺዱ ድምፅ ከጆሮዋ ሲርቅ ነፍሷ ወደ እሱ ትጓጓለች፣ ትጠበባለች፤ ሁኔታውም ልክ እንደ ሰካራም ይሆናል።
የስነ-ልቦናው ሀኪም የሆኑት አሕመድ ቢን አብደልሐሊም—ኢብኑ ተይምያ—እንዲህ ብለዋ
ል፦
«በሚያስደስቱና በሚያወዛውዙ ድምፆች መስከር ልክ በሚያሰክሩ መጠጦች እንደ መስከር ሊሆን ይችላል፤ አላህን ከማስታወስና ከሶላት ያዘናጋቸዋል፤ ቀልቦቻቸውን የቁርኣንን ጣፋጭነት፣ ትርጉሙን መረዳትና መከተልን ይከለክላቸዋል፤ በዚህም አላህ ዘንድ "ከአላህ መንገድ ሊያሳስቱ አላስፈላጊ ወሬዎችን (ላህወል ሐዲስ) የሚገዙ" የተባሉትን ሰዎች የሚመሳሰሉ ይሆና

ሉ።»

ኢብኑል ጀውዚይ (ረሒመሁላህ) ደግሞ «ተልቢሱ ኢብሊስ» በተሰኘው መጽሐፋቸው ላይ እንዲህ ብለ
ዋል፦

«የስማዕ (የዜማ/ነሺዳ) ፍቅር የብዙዎችን ልብ ተቆጣጥሮታል፤ በመሆኑም ቁርኣንን ከማንበብ ይልቅ እሱን አስበለጡት፤ ቁርኣንን ሲቀራ የማይለዝበው ቀልባቸው እሱን ሲሰሙ ይረሰርሳል። ይህም በውስጣቸው በጥልቀት ከተቀመጠ ሸህዋ(ስሜትና) ከአሸናፊ ባህሪያቸው የተነሳ እንጂ ሌላ አይደለም፤ እነሱ ግን ከዚህ የተለየ ይመስላ

ቸዋል።»
ስለዚህ አላህ ይጠብቅህና አላስፈላጊና ዋጋ የሌላቸውን ነገሮች ተወና ወደ መልካም ሥራዎች ተጣደፍ፤ ጊዜህንም በሚጠቅምህ ነገር ላይ አውለው፤ አላህ በደነገገልህ ዒባዳዎችም ወደ እሱ ተቃረብ።
ንግግሬን በሸይኹል ኢስላም ኢብኑ ተይምያህ (ረሒመሁላህ) ድንቅ ንግግር ልቃጭ ወደድኩ፤
እንዲህ
ብለዋል፦
፦
«ባህታዊ (ዐቢዶች)፦ በውጫዊና በውስጣዊ በደነገገው ንግግርና ሥራ አላህን ከተገዙ፣ አላህ መልእክተኛውን የላከበትን የመልካም ንግግርና የጽድቅ ሥራ ጣዕም ከቀመሱ፤ ከእነዚያ ቢድዓ ከሆኑና ቁርዓን ከማዳመጥ ከሚያስወጡ እንደ "ተግቢር" እና መሰል ስማዖች—ሰዎች ከፈጠሯቸው የተለያዩ ዚክሮችና ዊርዶች—የሚያብቃቃ የጠራ መንፈሳዊ ሁኔታን፣ የላቀ ደረጃንና ታላቅ ውጤትን ያገኛሉ። እነዚህ የፈጠራ እንጉርጎሮዎችን  የፈጠሩ ሰዎች አላህ ከደነገገው ነገር ላይ ያላቸው ቁርጠኝነት በመቀነሱ የተነሳ  ነው አዲስ ከፈጠሯቸው ተጨማሪ የአምልኮ ዓይነቶች(ቢድዓዎች)ላይ
የተዘፈቁት።
»
ስላረዘምኩትና ምናልባትም ጠንከር ያለ አቀራረብ ከሆነ ይቅርታ እጠይቃለሁ፤ ምክንያቱም ወንድሜ ላንተ መልካምን ስለሚመኝልህ ነው።
አቡ ሑዘይፋ/ሱልጧን ከድር
❤22👍1