የኡስታዝ ሱልጣን ኸድር የትምህርት መድረክ (official)
13.3K subscribers
3.58K photos
731 videos
126 files
2.42K links
ይህ በኡስታዝ ሱልጣን ኸድር እውቅና የተከፈተ ብቸኛው (official) ቻነል ሲሆን የእርሱ ትምህርቶችና አጫጭር መልእክቶች በየጊዜው የሚተላለፉበት ልዩ መድረክ ነው፡፡

አላህ መልካም ምንዳውን ይክፈለው፤ ከዕውቀቱም ተጠቃሚ ያድርገን!
ትምህርታዊ ቁም ነገሮች ላይ መሳተፍ የምትፈልጉ እንዲሁም ሐሳብና አስተያየት ካልዎት በዋትስ ኣፕ ይላኩልን!
♻: https://api.whatsapp.com/send?phone=
Download Telegram
ቀልብ …
ቁርኣን እንደ ዝናብ ሲወርድበት፤ ከድርቅናው ይነጻል፣ መልካም ስራዎችና ታዛዥነቶችም ያፈሩበታል፤ እንዲሁም ጥበቱና ፍርሃቱ ወደ እርጋታ ፣ ወደ እረፍትና ወደ ብርሃን ይለወጣል።
👍32
ኢላሂ! ይህንን ቀን ኃጢአቶች የሚሰረዙበት፣ የተሰበሩ ልቦች የሚጠገኑበት፣ ሃዘኖች የሚወገዱበት፣ ልቦች የሚፈወሱበት፣ ጭንቀቶች የሚቃለሉበት እና ዱዓዎች የሚሰሙበት ቀን አድርግልን።
ኢላሂ! ይህንን ቀናችንን በአንተ እዝነት፣ ይቅርታና ችሮታ የተሞላ አድርግልን፤ ዱዓችንንም አትመልስብን፣ ተስፋችንንም ከንቱ አታድርገው፤ አንተ በሁሉም ነገር ላይ ቻይ ነህና።**
❤30👍14
የኹሹዕ እና የቁርጠኝነትን ጣዕም መቅመስ ትፈልጋለህን?
ከመጀመሪያው ቀን ጀምሮ የሰላት ጣፋጭነት ይሰማኛል ብለህ አትጠብቅ፣ ወይም ቂያሙለይል (የለይል ሰላት) ቀላል ይሆንልኛል፣ ወይም ደግሞ ቀልቤ ከመጀመሪያው ጊዜ ጀምሮ ኹሹዕ በዒባዳ መርካት ያገኛል ብለህ አታስብ።
በመጀመሪያው ላይ ትደክማለህ...
ሰነፍነትን ትዋጋለህ፣ ሰላትን በመስገድ እና ቁርኣንን በማንበብ ላይ ነፍስህን ትታገላለህ፣ ሃሳብ መበታተንንም ትቋቋማለህ... ይህ ደግሞ ተፈጥሯዊ ነገር ነው፤ ምክንያቱም ማንኛውም ጅምር ሙጃሃዳ(ትግል) አለበትና። አላህ እንዲህ ብሏል፦ ﴿በትዕግስትና በስግደትም ታገዙ﴾።
ቀጥልበት... ታገስ... በአላህም ታገዝ... ፍሬውን ለመቅጠፍ አትቸኩል!
በአላህ ፈቃድ፣ ታዛዥነት (ኢባዳ) ለልብህ እረፍት የሚሆንበት፣ ቁርኣን የልብ ጓደኛህ የሚሆንበት፣ እና ሰላት ቀደም ሲል ትግል የሚያስፈልገው ከነበረበት ተለውጦ ለልብህ በጣም ተወዳጅ ነገር(ላዛ/እርካታ) የሚሆንበት ቀን ይመጣል።
ነቢዩም ﷺ እንዲህ ብለዋል፦ "አላህ ዘንድ በጣም ተወዳጅ የሆኑ ስራዎች ምንም እንኳ ጥቂት ቢሆኑም ዘውታሪ የሆኑት ናቸው።" ስለዚህ ምስጢሩ በጠንካራ አጀማመር ላይ አይደለም... ምስጢሩ በትንንሽ እርምጃዎችም ቢሆን በመዘውተር ላይ ነው።
❤13👌11👍10
አላህ ዘንድ መለኪያዎች በቁጥር (በብዛት) አይደሉም።"
"ነቢዩ  ﷺ እንዲህ ብለዋል፦ *'በቂያማ  ቀን ትልቅና ወፍራም ሰው ይመጣል'* — እዚህ ጋ ወፍራም ሲል የግድ በሰውነት መወፈር ብቻ ሳይሆን በሰዎች ዘንድ ትልቅ ቦታና ክብር ያለውንም ያጠቃልላል — ነገር ግን አላህ ዘንድ የትንኝ ክንፍ ያህል ክብደት አይኖረውም'* አሉ።"
.. ያ ሁሉ ክብር፣ ያ ሁሉ ሀብት፣ ያ ሁሉ ማዕረግና በክብር ስፍራዎች ላይ መቀመጥ እያለው!"
አላህ ዘንድ ዜሮ ነው!
በሌላ በኩል ደግሞ፦ *'ስንት ጸጉሩ የተንጨባረረ፣ ትቢያ የለበሰ ከደጃፍ የሚገፈተር (ምስኪን) ሰው አለ፤ አላህን በውስጡ ቢማጸነው ኖሮ አላህ ልመናውን በእርግጥ የሚቀበለው' ስንትና ስንት ሰው አለ!* ይላል።
መለኪያው ይህ ነው። ለምሳሌ ኢብኑ መስዑድን ብንወስድ፤ እሱ እረኛ ነበረ፣ አጭርና በጣም ቀጭን ሰውነቱ ነበረው። እንዲያውም ከሰውነቱ ማነስ የተነሳ እሱ ቆሞ ሰሃባዎች ተቀምጠው ሳለ እኩል ጭንቅላታቸው ጋ ይደርስ ነበር ይባላል።"
  ከአጭርነቱ የተነሳ። ይህ ሆኖ ሳለ ግን አንድ ቀን ዛፍ ላይ ሲወጣ ነፋስ መጣና ቀጫጭን ባቶቹ ተርገበገቡ፣ ሰሃባዎች ይህን በተመለከቱ ግዜ ሳቁ፣ እንዲህ ያለ አጋጣሚ ሲፈጠር ሳያውቁት መሳቃቸው ተፈጥሯዊ ነው። ነቢዩም ﷺ  ይህንን ባዩ ጊዜ ምን አሏቸው? "'በሁለቱ እግሮቹ ቅጥነት ትደነቃላችሁን? ነፍሴ በእጁ በሆነችው አምላክ እምላለሁ፤ አላህ ዘንድ ከኡሁድ ተራራ በላይ ይከብዳሉ'* አሏቸው።
❤16👍10
አላህ )ሱብሃነሁ ወተዓላ የሚክስህ፤ በሱ ሀቅ ላይ፣ እሱን በማመስገንህ ላይ ጉድለት እንዳለብህ እስኪሰማህ ድረስ ነው።
እስክትደነቅ ድረስ ይተካሃል።
“በፊት ባጣሁትና ባላገኘሁት ነገር ላይ እንዴት አዝኜ ነበር?” ብለህ እስክታስብ ድረስ!
በፊትህ ላይ የተዘጉት በሮች በሙሉ፤ ከነሱ የተሻሉና እጅግ በጣም በላጭ የሆኑ በሮች ላንተ እንዲከፈቱልህ ተብሎ እንደተዘጉ ትረዳለህ።
የተከለከልከው ነገር በሙሉ ከክፉው እንደተጠበቅክበት፣ ያላገኘኸው ነገር ሁሉ አላህ ከዚያ የተሻለ መልካም ነገር እንደተካህልህ ትገነዘባለህ።
የአላህ ምትክ(መካስ) ሲመጣ ያጣኸውን ነገር ሁሉ ያስረሳሃል።
👍26❤20
> በዚህ በዕለተ ጁምዓ፦ *ኢላሂ! በልባችን ውስጥ ያለን ማንኛውንም ሐዘን በደስታ የቀየርክልን ቢሆን እንጂ አትተውልን።*
>


> በዚህ እለተ ጁምዓ፦ * ኢላሂ! ሪዝቃችንን አስፋልን፤ በልባችን ውስጥ ያሉትንና ከአንተ በቀር ማንም የማያውቃቸውን ፍላጎቶቻችንን በሙሉ ስጠን።*
>
🥰18❤14👍11
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
በመዲና ሙነወራ የምድር እርጋታ ከሰማይ ሰላም ጋር ይገናኛል፤ እግሩ ምድሯን የረገጠ ሁሉ ልቡ በሰላም ይመሰጣል፤ ለመሆኑ እንዴት ይህ አይሆን?! እርሷ እኮ የተወደዱትን የነቢዩ ሙሐመድን ﷺ አካል በሆዷ(በመሬቷ) ያቀፈችው ታላቅ ሀገር ናትና።
❤34👍12👌2
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ለእኔ ከሁሉ በላይ የተወደድሽው ሆይ፤ የአንቺ ናፍቆት እያዳከመኝ (ሊገለኝ) እንደሆነ እወቂ!
አላህ ወደ አንቺ መመለስን ከወሰነልኝ፣ በሕይወት እስካለሁ ድረስ መለያየትን ዳግመኛ አላነሳውም። የመለያየቱ ትኩሳት አካሌን አክስቶታል፣ ልቤንም አቃጥሎታል...
#መከተ_ሙከረማህ
❤30👍1
የውዷ (የነቢዩ) ﷺ ሀገር ልትወደድ ይገባታል፣
በደስታ ትዝታዋ ሁሌም ይናፈቃል፤
እንደ መዲና ያለ መኖሪያ የት አለ?
ሙሐመድ ﷺ በመግባትዋ ክብሯ እኮ ላቀ።
❤37👍5
ዑምራ በጊዜ ወይም በገንዘብ (ብቻ) የሚሆን አይደለም፤ ይልቁንም ጥንታዊ ቤቱን (ካዕባን) እንድትጎበኝ ከአር-ራህማን (ከአላህ) የሚቀርብ ጥሪ ነው።
አላህ ቤቱን እንድትጎበኝ ከጠራህ፣ እርሱ ራሱ ላንተ፣ ለጉዞህ ዋስትና ይሆንልሃል፤ እንዲሁም ባላሰብከው መንገድ ጉዞውን ያቃልልሃል።
ቸር የሆነውን አላህ መካንና መዲናን ከምትወዷቸው ሰዎች ጋር እንድትጎበኙ እንዲወፍቃችሁ እለምነዋለሁ።
ወሰላሙ አለይኩም።
👍39❤18
በኢስላም አስተምህሮ ውስጥ የቃላት አጠቃቀምና የንግግር ግልጽነት ከፍተኛ ትኩረት የሚሰጠው ጉዳይ ነው። መልዕክትን በግልጽ፣ ያለ ጥርጥርና ለአላስፈላጊ ትርጉም በር በማይከፍት መልኩ መግለጽ ከእምነቱ መርሆዎች አንዱ ነው።
ይህንን አስመልክቶ በሱረቱል በቀራህ ላይ የተጠቀሰው «ላ ተቁሉ ራዒና ወቁሉ አንዙርና»
(لَا تَقُولُوا رَاعِنَا وَقُولُوا انْظُرْنَا)
የሚለው መለኮታዊ ትዕዛዝ፣ በንግግር ውስጥ አሻሚነትንና የተደበቁ መጥፎ ትርጉሞችን ማስወገድ እንደሚገባ ያስተምረናል።
🥰6❤2👍1
🔴 የማንቂያ ደውል!
አንተ ውድቅ (ፋሺል) ሰው አይደለህም... አእምሮህ በማይመለከቱህ ነገሮች የተበታተነ ነው እንጂ!
አእምሮህ ሁልጊዜም በነገሮች ተወጥሯል... በችግሮች፣ በዜናዎች፣ ራስን ከሌሎች ጋር በማወዳደር፣ በስሜቶች እና ማለቂያ በሌላቸው የሶሻል ሚዲያ ይዘቶች!
አንተ ግን ጥቂት ቆም ማለት ያስፈልግሃል! ረጋ በል... ቅድሚያ የምትሰጣቸውን ነገሮች በጥንቃቄ መርምር... እናም ማንነትህን በትክክለኛ መንገድ መልሰህ ገንባ።
የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች ምንም በማይጠቅም ወሬ እዚያው ባለህበት እንድትሽከረከር በማድረግ ዓመታትን ወስደውብሃል። አሁን ግን ጊዜህን ጠብቅ፤ ራስህን ለማበልጸግና ለማሳደግ ዛሬውኑ መስራት ጀምር።
👍34❤5
የአላህ መልእክተኛ (ﷺ) እንዲህ ብለዋል፦
"ሁለት ጸጋዎች አሉ፤ ከሰዎች አብዛኛዎቹ በእነሱ (በአጠቃቀማቸው) ይሸወዳሉ ፦ እነሱም ጤና እና ትርፍ ጊዜ ናቸው።"
(ቡኻሪ ዘግበውታል)
❤22👍7
አብሽር! ... የአላህ ፍቃድ በሆነው ልክ ሐዘን በአንተ ውስጥ እንዲኖር ፍቀድለት፤ ይህ ሁሉ በከንቱ የሚጠፋ አይምሰልህ። ይልቁንም ለእያንዳንዱ ትንፋሽ እና እንጉርጉሮ ታላቅ ምንዳ አለው፤ ለእያንዳንዱ ስቅስቅታና የእንባ ጠብታም ታላቅ ዋጋ አለ። ስለዚህ አትበሳጭ፣ አላህ ካለቀስክባት ምሽት ወይም ከተሰማህ የሕመም ትንፋሽ እንደሚዘነጋህ አታስብ። በትዕግስት መራራነት ውስጥ በሐዘን እሾህ መካከል እየኖርክ መታገስህንና ለመታገስ መጣርህን እንደማያይ አትገምት። ሐዘን በአንተ ውስጥ ለዘላለም እንደሚኖር አድርገህ ፈጽሞ አታስብ...
❤22👍6💔2
"ስንት የተቸገረ እያለ፣ ሐጅና ዑምራን አታብዛ!"
ይህን ንግግር ከዚህ በፊት ሰምተሃል አይደል?
ነገር ግን በእርግጥ የአላህ መልእክተኛ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) ወደዚህ ነው ያመለከቱን?
የአላህ መልእክተኛ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) እንዲህ ብለዋል፦ «በሐጅና በዑምራ መካከል (አንዱን ከሌላው በማስከተል) አከታትሉ፤ እነሱ ድህነትንና ወንጀልን ያስወግዳሉና።»
ስለዚህ አላህ (ሱብሃነሁ ወተዓላ) በድጋሚ የመመለስን አቅም ከሰጠህ፣ የሰዎች ወሬ እንዳይከለክልህ።
❤37👍9🫡1
በአላህ ላይ ሙሉ እርግጠኝነት (የቂን)" የሚባል ተአምራዊ ኃይል አለ፤ በእሱም ቀውሶቻችንን እንሻገራለን። ሁሉም በሮች ተዘግተው፣ ሁኔታዎች ባይመቻቹና ነገሮች ሁሉ እኛ ከምንመኘው ተቃራኒ ቢሆኑም እንኳ ዱዓ ማድረጋችንን እንቀጥላለን። ምክንያቱም አላህ ሁሉንም ነገር በትክክለኛው ጊዜ እንደሚያስተካክለው ሙሉ እርግጠኞች ነን። በአላህና በእሱ እቅድ (አስተናባሪነት) ስለምናምን፤ አላህ ሆይ! በችሎታህ ከሚያምኑና በአንተ ጉርብትና ከሚረኩት አድርገን።
❤26👍9
• ኢብኑ ዑሰይሚን (አላህ ይዘንላቸውና) እንዲህ ብለዋል፦
"ሰዎች ከሸሪዓዊ አውራዶች (የጠዋትና የማታ ዚክሮች) በዘነጉ ጊዜ፤ በእነሱ ላይ ጅን በዛባቸው፣ ተጫወተባቸውም (አላገጠባቸውም)።"


• ሊቃኡል ባቢል መፍቱህ (197)
👍26❤2
የአላህ መልእክተኛ (ﷺ) እንዲህ ብለዋል፦
«የጠራችሁን ሰው ጥሪ ተቀበሉ (እሺ በሉ)፣ ስጦታን አትመልሱ፣ ሙስሊሞችንም አትምቱ።»
(አህመድ ዘግበውታል፣ አልባኒም ሰሂህ ነው ብለውታል)

የሐዲሱ ማብራሪያ (የግርጌ ማስተዋሻ)
«የጠራችሁን ሰው ጥሪ ተቀበሉ»፦ ይህ የሰርግ ድግስም ይሁን ሌላ ማንኛውም ዓይነት ምግብ ላይ እንዲገኝ የጠራውን ሰው ጥሪ ምላሽ እንዲሰጥ የታዘዘበት ነው።
«ስጦታን አትመልሱ»፦ ይህ ደግሞ ሁለተኛው ትዕዛዝ ሲሆን፣ የቀረበን ስጦታ ባለመመለስ መካከል ላይ ፍቅርና መተሳሰር እንዲኖር ያደርጋል።
«ሙስሊሞችንም አትምቱ»፦ ይህ ሦስተኛው ትዕዛዝ ሲሆን፣ ያለ ምንም (ሸሪዓዊ ቅጣት) ወይም ያለ አግባብ ሙስሊሞችን ከመምታትና ከመበደል መቆጠብን ያዛል። መሠረቱ ግን ከእነሱ ጋር በቃልም ሆነ በተግባር በደግነትና በለስላሳነት መኖር ነው።
👍11❤6
ፈትዋ
ጥያቄ፦ ነጋዴው የዚህ ዕቃ ዋጋ በጥሬ ገንዘብ (ካሽ) ከተከፈለ 100 ዲናር ነው፤ በየወሩ እየተከፋፈለ በክሬዲት (በተቅሲጥ) ከሆነ ግን 150 ዲናር ነው ይላል። ታዲያ የዚህ ብይን ምንድን ነው? አላህ ምንዳዎን ይክፈልዎና።
መልስ (በሸይኽ ኢብኑ ዑሰይሚን)፦ ይህ አሰራር ይፈቀዳል፣ ምንም ችግር የለውም። አላህ በትዕዛዙ በጥቅሉ እንዲህ ስላለ፦
"አላህ መሸጥን ፈቀደ፤ ወለድን ግን እርም አደረገ።" (አል-በቀራህ፡ 275)

እንዲሁም አላህ እንዲህ ብሏል፦

"እናንተ ያመናችሁ ሆይ! እስከ ታወቀ ጊዜ ድረስ ባለ እዳ በተዋዋላችሁ ጊዜ ጻፉት።" (አል-በቀራህ፡ 282)

ይህ ገዥ ዕቃው በሁለት የተለያየ ዋጋ ቀረበለት ማለት ነው፤ በጥሬ ገንዘብ (በካሽ) የሚከፈል ዋጋ እና በጊዜ ገደብ (በክሬዲት) የሚከፈል ዋጋ። ለምሳሌ የጥሬ ገንዘቡ ዋጋ 100 ነው እንበል፤ የጭልፊቱ ዋጋ ደግሞ 150 ነው፤ እሱም በዚያው በተቀመጡበት መጅሊስ ከቦታው ሳይበተኑ የክሬዲቱነረ (የ150ውን) መረጠ። ከዚያም ዕቃውን ይዞ ሄደ። በዚህ ጊዜ በእሱ እዳ ላይ 150 ዲናር በትክክልና በግልጽ ተቀምጦ ጸና።
ይህ ዓይነቱ ሽያጭ ምንም ችግር የሌለበት ትክክለኛ ሽያጭ ነው። ምክንያቱም ገዢው በዚህ ወይም በዚያኛው ዋጋ ለመግዛት ምርጫ ተሰጥቶታል።
ይህ ደግሞ በምንም መልኩ ከወለድ (ሪባ) ጋር አይገናኝም። ምክንያቱም ወለድ ማለት "ብርን በብር" (ገንዘብን በገንዘብ) ላይ ጨምሮ መሸጥ ማለት ነው። እዚህ ጋር ግን እየተሸጠ ያለው ዕቃ ነው፤ ዕቃን ደግሞ በጥሬ ገንዘብ ሲሆን በዚህ ዋጋ፣ በጊዜ ገደብ ሲሆን ደግሞ በዚያ ዋጋ መሸጥ ሙሉ በሙሉ የተፈቀደ ነው።
እንዲሁም ይህ ሽያጭ ነቢዩ (ሰለሏሁ አለይሂ ወሰለም) ከከለከሉት "በአንድ ሽያጭ ውስጥ ሁለት ሽያጭ ማድረግ" (بيعتين في بيعة) ከሚለው ክልከላ ውስጥ አይገባም። ምክንያቱም እዚህ ጋር የተፈጸመው አንድ ሽያጭ ብቻ ነው። ሰውየው በሁለት አማራጮች መካከል ምርጫ ተሰጥቶት አንደኛውን መርጦ በአንዱ ላይ ብቻ ተስማምቶ ወጥቷልና።
❤17👍8