This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
﴿ ومن يتق الله يجعل له مخرجا * ويرزقه من حيث لا يحتسب ومن يتوكل على الله فهو حسبه إن الله بالغ أمره قد جعل الله لكل شيء قدرا ﴾
🎧 القارئ فارس عباد
📜 سورة الطلاق كاملة هنا👇💚
https://surahquran.com/65.html
🎧 القارئ فارس عباد
📜 سورة الطلاق كاملة هنا👇💚
https://surahquran.com/65.html
👌9❤4👍3
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ኢማም ኢብኑ አል_ቀዪም (ረሂመሁሏህ) እንዲህ ብለዋል፡-
«ባሪያው ኃጢኣትን በታዛኝነት(በምትክ) ሲቀይር፣ አላህ በእርሱ ላይ የነበረውን ቅጣት በደኅንነት፣ ውርደትንም በክብር ይቀይራል።»
📚(አድ ዳእ ወደ_ደዋእ፣ ገጽ 73)

🔔 የማንቂያ ደወል!
የረመዳን ቀናት እየተቆጠሩ ሲያልፉ ምንኛ ይፈጥናሉ!
በኢባዳ ለመትጋት ብርታት እንዲሆነን ይህ የትርፍ ወር የተቆጠሩ ጥቂት ቀናቶች ብቻ መሆኑን ማስታወስ ጠቃሚ ነው። አላህ እንዲህ ይላል።
«أياما معدودات» البقرة 184
«የተቆጠሩን ቀኖች (ጹሙ)» አልበቀራህ 184
የረመዳን ወቅት በመልካም ስራ የምንሽቀዳደምበት ወቅት ነው።
ሆኖም የረመዳን 1,2,3..10,15 ቀናት ሲያልፉ በጣም ይፈጥናሉ!!
የመጀመሪያው ግማሽ አልፏል። መዘናጋት በማንኛውም ሰው ህይወት ውስጥ የተለመደ ክስተት ቢሆንም፤ መዘናጋታችን በአጨዳ ወቅት ከሆነ ግን ኪሳራው ከባድ ነውና እንጠንቀቅ!!
የተቀሩትን ቀናት በጥሩ ሁኔታ አልፎ ከሆነ አሻሽለን መልካም ስራን እንጨምር፤ በሚገባ ካልጠቀምንበትም ጉድለታችንንም አናሟላ፤ አናካክስ። አላህ ያበርታን!

❤7👍3
Audio
🔴 የዛሬው የጁምዓ ኹጥባ
🎙 خطبة الجمعة
النفس اللوامة
✨ወቃሽ ነፍስ
🎙በኡስታዝ ሱልጧን ኸድር
🕌 ጎተራ ሼል ዲ ፖ ፈትሕ መስጂድ
🗓 ረመዷን 17/1447 አ/ሂ
🎙 خطبة الجمعة
النفس اللوامة
✨ወቃሽ ነፍስ
🎙በኡስታዝ ሱልጧን ኸድር
🕌 ጎተራ ሼል ዲ ፖ ፈትሕ መስጂድ
🗓 ረመዷን 17/1447 አ/ሂ
❤7👌1
#ዚክር
«ከጾመኞ ሁሉ በላጩ
አላህን በጾማቸው ወቅት
በብዛት የሚያወሱ(የሚዘክሩ) ናቸው።»
📚ኢብኑል ቀይም (አል ዋቢሉ አስ–ሠይብ / ገጽ 153)
ኢላሂ! ከጾመኞች እንጂ ከረሀብተኞች አትመድበን።
«ከጾመኞ ሁሉ በላጩ
አላህን በጾማቸው ወቅት
በብዛት የሚያወሱ(የሚዘክሩ) ናቸው።»
📚ኢብኑል ቀይም (አል ዋቢሉ አስ–ሠይብ / ገጽ 153)
ኢላሂ! ከጾመኞች እንጂ ከረሀብተኞች አትመድበን።
👍18
«ሌሎች ወራቶች ሁሉ ምትክ ሊኖራቸው ይችላል፤
የረመዳን ወር ግን ምትኩን ከየት ታገኛላችሁ?»
ኢብኑ ረጀብ
📚(ለጣኢፍ አል-መዓሪፍ / ገጽ 263)
የረመዳን ወር ግን ምትኩን ከየት ታገኛላችሁ?»
ኢብኑ ረጀብ
📚(ለጣኢፍ አል-መዓሪፍ / ገጽ 263)
❤16👌2
ለይለቱ’ል አል–ቀድር ማለት ምን ማለት ነው?
በመጀመሪያ “ለይለቱልቀድር” ተብላ የተጠራችው "ቀድር" ማለት በዐረብኛ "ሸረፍ” (ክብር) ማለት ነው። “እገሌ "ዙ ቀድር” (የክብር ባለቤት ነው።)" እንደሚሉት። ይህ የሆነው ደግሞ ለይለቱል ቀድር ታላቅ ክቡር ለሊት ስለሆነች ነው።
☝️ሁለተኛ፡- ለይለቱል ቀድር የተባለችው፤ በዚያች ለሊት ላይ፣ በዚያ ዓመት የሚከሰተው ነገር በሙሉ ተወስኖ በዚያ ዓመት የሚሆነው ይጻፋል። ይህ ደግሞ የአላህን ጥበብ፣ አፈጣጠር፣ የተቀላጠፈ አሰራር እንዳለው አጉልቶ የሚያሳይ ነው።
☝️ሦስተኛ፡- ለይለቱል ቀድር የተባለችው በዚህች ለሊት የሚሰራ ዒባዳ ትልቅ ዋጋ እንዳለው ለመጠቆም ነው ተብሏል። ነቢዩ ﷺ እንደተናገሩት ፦
(ለይቱል ቀድር ላይ አምኖ እና ምንዳን ከአላህ በመጠባበቅ የሰገደ ሰው፤ ላለፈው ሃጢአት ምህረት ያገኛል።) ቡኻሪና ሙስሊም»

❤15
"
"
✍(ኢብኑ አል– ቀዩም)
በረመዳን 10 ለሊቶችን መጠባበቅ ይቅርና ለይለቱል ቀድር በአመት ውስጥ በአንድ ለሊት ነው የምትገኘው ቢባል እንኳን አመቱን ሙሉ ለይለቱል ቀድር ለማግኘት ጥረት አደርግ ነበር"
✍(ኢብኑ አል– ቀዩም)
❤17
ከተባዳዮች ጎን አለመሰለፍ በባለቤቱ ላይ የሚወድቅ ውርደት ነው። ወደ 7122 SMS OK | ለወዳጆ ያስተዋውቁ
👍9
ጥያቄ፦ ክቡር ከሆነው ከነቢዩ (ሶለሏሁ አለይሂ ወሰለም) እጅ ሐውድን አጠጣን ብሎ ዱዓ ማድረግ እንዴት ይታያል?
መልስ- ይህንን ልዩ በሆነው መንገድ " ክቡር ከሆነው ከነቢዩ (ሶለሏሁ አለይሂ ወሰለም) እጅ እንድንጠጣ" የማለት ዱዓ በአብዛኛዎቹ ዐሊሞች ዘንድ ተቀባይነት የለውም።
ምክንያቱም በትክክለኛው የሐዲስ መረጃዎች ውስጥ ነቢዩ (ሶለሏሁ አለይሂ ወሰለም) ሰዎችን በእጃቸው ያጠጣሉ የሚል ማስረጃ ስለሌለ።
ዝርዝር ማብራሪያ
በርካታ የሙስሊም ሊቃውንት እንደሚጠቁሙት፣ ይኸውን "ﷲም ከነቢዩ(ሶለሏሁ አለይሂ ወሰለም) እጅ ሐውድን የምንጠጣ አድርገን" ብሎ ዱዓ ማድረግበ በርካታ ምክንያቶች ተገቢ አይደለም።
1. በሐዲስ አለመገኘቱ፦ ስለ (ሐውድ) በርካታ ትክክለኛ ሐዲሶች ቢኖሩም፣ ከነዚህ ሐዲሶች በአንዱም ውስጥ ነቢዩ (ሶለሏሁ አለይሂ ወሰለም) ሰዎችን በገዛ እጃቸው ያጠጣሉ የሚል ማስረጃ የለም ። በሐዲሶቹ ውስጥ የተጠቀሰው "ከሐውዱ የጠጣ ሰው ከጠጣ በኋላ አይጠማም።" የሚለው ነው እንጂ "ነቢዩ ያጠጡታል" የሚል አይደለም ።
2. የነቢዩ ሚና፦ ከሐዲሶቹ እንደምንረዳው ነቢዩ (ሶለሏሁ አለይሂ ወሰለም) በሐውድ ላይ ቀድመው ተረኛ ሆነው ሕዝባቸውን ይጠብቃሉ። ሰዎች ግን በራሳቸው እየመጡ ከሐውጡ ይጠጣሉ። የሐውድ መጠጫ ዕቃዎች እንደ ከዋክብት የበዙ መሆናቸውም ሰዎች በራሳቸው እንደሚጠጡ ያመላክታል ።
3. በዱዓ ወሰን ማለፍ፦
ኢብኑል ቃይም (ረሂመሁሏህ) እንዳሉት "ከአላህ ሕግጋት ጋር የሚጋጭ ወይም ከትእዛዙ እና ከሕጉ ጋር የሚቃረን ወይም ከቁርኣን እና ሐዲስ ትምህርት ጋር የሚጻረር ማንኛውም ዱዓ ወሰን ማለፍ ነው" ። ስለዚህ በማናቸውም ትክክለኛ ሐዲስ ያልተጠቀሰን ነገር በዚህ መልኩ ማካተት የተከለከለ ነው።
ትክክለኛው የዱዓ አደራረግ
ትላልቅ ኡለማዎች እንደሚመክሩት፣ ሙስሊም በሐዲስ እንደተጠቀሰው ብቻ በመወሰን እንዲህ ማለት ይሻላል ፦
" አላህ ሆይ! ከነቢዩ (ሶለሏሁ አለይሂ ወሰለም) ሐውድ ውሃ እንድጠጣ፣ ከሱም ከጠጣሁ በኋላም ፈጽሞ የማልጠማ ውሃን (ለግሰኝ)"
ይህ ዓይነቱ ዱዓ በትክክለኛው የሐዲስ ትምህርት ላይ የተመሠረተ ነው። ከላይ በተጠቀሰው ልዩ በሆነው መንገድ (ከነቢዩ"(ሶለሏሁ አለይሂ ወሰለም) ከእጃቸው እንድንጠጣ") ብሎ ዱዓ ማድረግግን አላስፈላጊ አይደለም። አላህ ይበልጥ ዐዋቂ ነው።

❤8
ዱዓ በማድረግህ/ሽ ፈጽሞ የምታጣው/ጪው ነገር የለም!!
🌿 ዱዓህ ምላሹ ከዘገየ፤ ፈጽሞ ዱዓይ ተቀባይነት አላገም ብለህ አታስብ። አላህ በባሮቹ ላይ ከራሳቸው በላይ እጅግ በጣም አዛኝ ነው። ልቦቻቸውንና ሁኔታዎቻቸውን የሚያስተካክለውንም ነገር አዋቂ ነው።
📖 ነቢዩ ሙሐመድ (ሶለሏሁ አለይሂ ወሰለም) እንዲህ ብለዋል፦
«በምድር ላይ አላህን የሚለምን ሙስሊም፤ ኃጢአትን ወይም ዝምድናን ማቋረጥን እስካልጠየቀ ድረስ፣ አላህ የጠየቀውን ነገር ይሰጠዋል፣ ወይም ብጤውን መጥፎ ነገር ከእሱ ላይ ይመልስለታል እንጂ ዱዓ በከንቱ አይቀርም።»
[ሐሰን ሰሂሕ] ሱነን ቲርሚዚ (3573)
🌿 ይህ ሐዲስ በአንድ ሙስሊም ቀልብ ውስጥ በአላህ ላይ መልካም ጥርጣሬ እንዲኖረው ያንፃል። ዱዓ ፈጽሞ ከንቱ እንደማይሆን እምነትን በቀልቡ ይተክላል፦
1· ወይ የተጠየቀው መልካም ነገር ቶሎ ይሰጠዋል፣
2· ወይም ክፉ ነገር ከእሱ ይከላከልለታል፣
3·ወይም ለቀጣዩ ዓለም ምንዳ ይሆንለታል።
📖 እጆቻችሁን ወደ አላህ ከፍ አድርጉና ዱዓ አድርጉ። ይህን መልክት ያጋሩ፤ ልቡ የተጨነቀ ሰው በውስጡ መጽናኛን ያገኝ ይሆናልና።

❤5👌2
ስለ ሐውድ በጥቂቱ፦
ሐውደ (ከውሠር ) (ለነቢዩሶለሏሁ አለይሂ ወሰለም) ሙሐመድ ሐውጥ) በቂያማ ቀን በሚከሰቱ ታላላቅ ክስተቶች ውስጥ አንዱ ሲሆን፣ አላህ ለነቢዩ ሙሐመድ (ሶለሏሁ አለይሂ ወሰለም) በልዩ ክብር የሰጣቸው የውሃ ገንዳ ነው። በርካታ እና ትክክለኛ ሐዲሶች ስለ ሐውዱ መኖር፣ ባህሪያቱና ውሃው ማን እንደሚጠጣ ያብራራሉ።
የሐውዱ ባህሪያት፦
ከሐዲሶች እንደተረዳነው የነቢዩ (ሶለሏሁ አለይሂ ወሰለም) ሐውድ ከሚከተሉት ልዩ ባህሪያት የተነሳ በቂያማ ቀን ምእምናን ከፍተኛ ፍላጎት እንዲኖራቸው ይገፋፋል፦
· ስፋቱ፦ ርዝመቱና ስፋቱ እንደ አይላ እና ሰዓ የየመን ከተሞች መካከል ካለው ርቀት ያህል ሰፊ ነው።
· ውሃው፦ ከወተት ይበልጥ ነጭ፣ ከማር ይበልጥ ጣፋጭ፣ ከምስክ ይበልጥ አሪፍ መዓዛ ያለው ነው።
· መጠጫ ዕቃዎቹ፦ በዙሪያው ያሉት የመጠጫ ዕቃዎች (ኩባያዎቹ) ቁጥር እንደ ሰማይ ከዋክብት ብዛት ነው።
· ውሃው የሚመጣበት ምንጭ፦ ከጀነት ወንዝ የሆነው ከውሠር (ከውሣር) ወንዝ ውሃ ወደ ሐውጡ ይፈስሳል።
· ዋስትናው፦ ከሐውጡ አንድ ጊዜ የጠጣ ሰው ወደ ፊት ፈጽሞ አይጠማም።
ከሐውዱ የሚጠጡት፦
ነቢዩ (ሶለሏሁ አለይሂ ወሰለም) በቂያማ ቀን ከሰዎች ቀድመው በሐውዱ ዳርቻ ተረኛ ሆነው ተከታዮቻቸውን (ሙስሊሞችን) ይጠባበቃሉ። ወደ ሐውጡ የሚመጡት ከነቢዩ ሕዝብ (ኡማ) የሆኑ ምእምናን ናቸው። ነቢዩ(ሶለሏሁ አለይሂ ወሰለም) አንዳንድ ሰዎች ወደ ሐውጡ ሲመጡ እንደሚያዩና እንደሚያስጠጡ በሐዲስ ተጠቅሷል።
ከሐውዱ የሚከለከሉት፦
በሐዲስ እንደመጣው፣ ነቢዩ (ሶለሏሁ አለይሂ ወሰለም) አንዳንድ ሰዎች ወደ ሐውጡ ሲቀርቡ እንደሚባረሩና እንደሚከለከሉ ያያሉ። ነቢዩም "እነዚህ ከእኔ በኋላ (ሃይማኖቴን) የለወጡ ናቸው" ይላሉ። ይህ ማለት በሃይማኖት ውስጥ አዳዲስ ነገሮችን (ቢድዓ) ያስገቡ፣ ከነቢዩ ትምህርት የወጡ ወይም በሃይማኖት ጉዳይ ከልክ ያለፉ ሰዎች ከሐውዱ እንደሚከለከሉ ያሳያል።
ማስጠንቀቂያ፧
ሐውዱ የነቢዩ ሙሐመድ (ሶለሏሁ አለይሂ ወሰለም) ልዩ ስጦታ ቢሆንም፣ ከሱ መጠጣት ዋስትና የሚሆነው ነቢዩን በሚገባ ለተከተሉ እና ከሃይማኖት ወሰን ላላለፉ ሰዎች ነው። ከላይ በተጠቀሰው ሐዲስ መሰረት፣ በሃይማኖት ውስጥ አዲስ ነገር ፈጣሪዎች (የቢድዓ ባለቤቶች) ከሐውዱ እንደሚባረሩ ተጠንቅቀን ማወቅ ይኖርብናል።
ስለዚህ ሙስሊም ሁሉ ከሐውጡ ለመጠጣት መመኘት ብቻ ሳይሆን፣ ያንን መመኘት ተግባራዊ ለማድረግ ነቢዩን በመከተል እና ከሃይማኖት ፈጠራዎች በመራቅ መዘጋጀት አለበት። ከላይ ባሳለፍኩት ጥያቄ እንደተገለፀው፣ ከሐውዱ ለመጠጣት በሚደረገው ዱዓም በሐዲስ በተጠቀሰው መጠን ብቻ መወሰን የተሻለ ነው።

🥰5❤2
🛑 አስቸኳይ ማሳሰቢያ ‼️
📣 ከዘሬ መግሪብ አዛን ሰአት ጀምሮ፦
🔻 በዓለም ላይ ካሉት ሌሊቶች ሁሉ በላጭ የሆኑት (የተባረኩት የአስርቱ የመጨረሻ የረመዷን ቀናት ሌሊቶች) ይጀምራሉ። እነዚህ ሌሊቶች ሴኮንዳቸው በዋጋ የማይተመን ነው። በውስጧ ከሺህ ወር የበለጠ የሆነች ሌሊት አለች።
የእርሷን በጎ ነገር የተከለከለ ሰው በእርግጥ ተከልክሏል! (እድለ–ቢስ ነው፣)ይህችም (ሌሊቱል ቀድር) ሌሊት ልትሆን ትችላለች...
🔻 ነቢያችንና መሪያችን ሙሐመድ (ሶለሏሁ አለይሂ ወአሊሂ ወሰለም) የአስር ቀናት ጊዜ በገባ ጊዜ በዒባዳላይ ያላቸው ትግህና ይጨምር ነበር፣ ሌሊታቸውን በሙሉ በዒባዳ ያሳልፉ እና ቤተሰቦቻቸውንም ያነቁ ነበር።
ይህ ለፈጣሪ ታላቅ መገለል “ኸልዋ” የሆኑ ሌሊቶች ናቸው።
ከፍጡራን ግንኙነትን በማቋረጥ። ልብንም በጌታ (አላህ) ደጃፍ ላይ በማኖር፣ በመሰበር፣ በመጸጸትና በምሕረት መጠየቅ...
🔻 ስለዚህ በሌሊትም በቀንም መጣርን መጣሩ በሁሉም የበጎ ሥራና በጎ አድራጎት ዓይነቶች መጣር ያስፈልጋል። ሁሉም ሰው ለእሱ በተመቸው መንገድ ይሠራል። እነዚህም ቁርአን ማጠናቀቂያዎች፣ ስግደቶች፣ ዱዓዎችና ምጽዋቶች ናቸው... 👌🏼
🔻 ማሳካትም በአላህ (አሏህ) ብቻ ነው፤
ስለዚህ በኢባዳ ላይ መርዳትን ሁልጊዜ ለምኑት።
🔻 የአስርቱ ቀናት ግዴታዎች (ፈርዶች) ሰላቶች ትልቁ አምልኮ ናቸው፤ ስለዚህ ለእነርሱ የሚሰጠው ትኩረት ከሁሉ የበለጠ መሆን አለበት። ቀድመን በመሄድ፣ በ (ኹሹዕ) እና በመጠባበቅ። ከዚያም ተጨማሪ ሥራዎችን (ነዋፊል) በማብዛት፣ በ በመታገል። «ከኢማም ጋር (ተራዊሕ ሶላት) እስኪያጠናቅቅ ድረስ የሰገደ ሰው የአንድ ሌሊት ቆም (ምንዳ) ይሰጠዋል» አስሩንም ሌሊት ሙሉ በኢባዳ ያሳለፈ ሰው የሌሊቱል ቀድርን በእርግጥ ያገኛታል።👌🏼
🔻 ዱዓ በእነዚህ ታላላቅ ሌሊቶች ውስጥ የምድራዊቱንና የመጨረሻይቱን ዓለም መልካም ነገር መጠየቅ።
አላህን ይቅርታንና ደህንነትን ለምኑት። ከነቢዩ ታላላቅ ዱዓዎች አንዱ፦ «አላህ ሆይ! አንተ ይቅር ባይ ነህ፤ ይቅርታን ትወዳለህ፤ ስለዚህ ይቅር በለን» ይህ ነው። ከይቅርታ በኋላ መዳን እንጂ ሌላ ነገር የለም!
🔻 በገበያዎችና በበከንቱ ወሬ በማውራትጊዜን ከማባከን ተጠንቀቁ። ምክንያቱም ሽልማቶች እየተከፋፈሉ ነው። ስጦታዎች እየተከፋፈሉ ነው። እዝነቶች እየወረዱ ነው። ከእሳት ነጻ መውጫ ሰነዶች እየተጻፉ ነው። ስለዚህ የንጉሠ ነገሥታት ንጉሥን ስጦታ እንዳያመልጣችሁ !!
🔻 ውድ ወንድሞችና እህቶች! ዋናው ነገር መጨረሻ ላይ ነው! ባለፈው ጊዜ መልካም የሠራ ይጨምር። ያጓደለም ያስተካክል... ረመዳን ታላቅ የሆነው በእነዚህ የመጨረሻ ሌሊቶች ምክንያት ነው። ስለዚህ ለእነርሱ ምትክ የለም፤ በዋጋም አይደረደሩም!
🔻 ከዚህ ከተባረኩት ሀብቶች የሚቆጠርልህ እያንዳንዱ ሴኮንድ፣ ከ83 ዓመት አምልኮ (= 1000 ወር = 30,000 ቀን) በአላህ ዘንድ የበለጠ የሆነች ሌሊት (12 ሰአት ገደማ) ናት። ስለዚህ እንዘጋጀን፣ እንትጋ፣ መጨረሻችንንም እናሳምር...
🍃 አላህ እኛንም እናንተንም ቤተሰቦቻችንንም፣ ወዳጆቻችንንም እና ሙስሊሞችንም ሁሉ በሌሊቱል ቀድር ከሚያገኙት፣ ከሚበዛላቸው ዕድልና ምንዳ ጋር ከሚመለሱት ያድርገን። ምስጋና ሁሉ ለአላህ ይገባዋል። ሶላትና ሰላምታም በባሪያውና በወዳጁ ሙሐመድ صلى الله عليه وسلم ላይ ይሁን።

❤36👍5
የታላቁ ሙሐዲስ አልባኒ ምሁራዊ ምክር!
"በአሁኑ ዘመን፣ ሰዎችን በስህተታቸው ምክንያት ማግለል እና ማኩረፍ ፈጽሞ ብልህነት አይደለም። ስህተታቸው በአስተሳሰብ (እምነት) ወይም የሱሉክ (ስነ-ምግባር) ላይ የሆነ ቢሆንም። ከእነርሱ ጋር በመቀራረብ (በመወዳጀት)፣ታጋሽ መሆን አለብን፣አንተ ጠማማ! ፣ አንተ ካፊር ብለን እንዳንፈርጅ፣ (እንደ ከሃዲ እንዳንቆጥራቸው) ይገባናል። ምክንያቱም ይህ ሰዎችን ጠማማ፣ ካፉር ወ·ዘ·ተ… ብለን መፈረጅ ምንም አይጠቅመንም። ይልቁንም አላህ ባለው መሠረት ማስታወስ (መገሰጽ) አለብን፤ (እርሱም)፦ 'አስታውስ፤ ማስታወስ ምእምናንን ይጠቅማል' ብሏል።"
📚ምንጭ፦ ሲልሲላት አል-ሁዳ ወአ-ኑር፣ ቁጥር 80፣ ሁለተኛ ገጽ

❤11👌3😱1