VERONICA ADANE ቬሮኒካ አዳነ
6.57K subscribers
174 photos
46 videos
7 links
Veronica Adane 🎤 ቬ.አ.ማ
Singer 🇪🇹

Official Telegram Channel (በ ቬ.አ.ማ ) ጥያቄ የተመሰረተ

Exclusive music, behind the scenes & real moments ❤️
Be part of my journey 🌍

የአድናቂዎች ግሩፕ @vr_fans
Download Telegram
አንድን ነገር ስንመኘው ቆይተን
ፀልየንበት እጃችን በተደጋጋሚ ሲገባ ደግሞ (አረ በዛ እንላለን) እንንቀዋለን which is wrong … ሰው ስለሆንን ነው ባህሪያችን

አዋርድ ሽልማት በሽልማት ሆንኩ ብዬ ሳልጨርስ
አሁን ደግሞ ሌላ ትልቅ አዋርድ ላይ ታጨው

This time የሚለየው ካሸነፍኩ 5000$ ሽልማት እና የኔ vote ከሁሉም ከበለጠ የ50,000$ ሽልማት አለው 😂

የታጨሁበት ዘርፍ ደግሞ Best female artist 2026 ሲሆን
ሙሉ መረጃውን በቪድዮ አሳውቃችዋለሁ
❤66
ቀጥታ እኔ ጋር ማውራት መማከር ምትፈልጉ እስታር በመክፈል በዚህ ሊንክ አውሩኝ አወራችኋለው።
t.me/veronicaadaneofficial?direct
❤23
ሀሙስ አይደርስም እንዴ 😔
❤29
እና እዚ telegram ላይ በዛሽ የለ፤ አበዛሽው የለ፤ በቃ እራሴን ነው የምሆነው
በቀን መቶ ጊዜ ልመጣ እችላለሁ
እዚ የተወራ ሚስጥር የትም አይወጣም፤ ቃል እንጠብቃለን
እዚ የለቀኩትን እንደ አዲስ ሰው Facebook, instagram, tik tok ላይ ብለቅ, እናንተም ባላየ እንደ አዲስ ሰው like comment ታደርጋላችሁ 🙌🏽የቤታችንን ገበና እቤታችን፤

ሌሎች social media ላይ አክት አደርጋለሁ

እዚ ግን ቤታችን ነው እሺ

ችግር ሼር እናደርጋለን
እንደጋገፋለን
የተቸገረ እንረዳለን፤ እናንተ ሳትሆኑ እኔ እረዳለሁ፤ የአቅሜን

ሌላ ምን ቀረ 🤔
ደስታ share እናደርጋለን
ብቻ እድሜ ጤና ይስጠን

አሜን ነው 🙌🏽
❤63
የመጨረሻ ትዝብቴን ይሄን ብቻ ላካፍላችሁ እና ይብቃኝ

እኛ ሰዎች በባህሪያችን በክፋትም በተንኮልም በተለያዩ ጉዳዮች እንኳን ለሰው ለፈጣሪም የማንመች ፍጡሮች ነን፤ ትላንት በቴዲ ጉዳይ ባጋራሁት መልካም ምኞት እና ምስክርነት ከማልጠብቃቸው ሰዎች የደረሱኝ መልዕክቶች በጣም ነው የተገረምኩት 😳 እኔ አንድ ሰው ነኝ አይደል? ግን ሚድያ ላይ ወጥቶ አይወራም እንጂ እያንዳንዱ የማሳልፈው ህይወት እግዚአብሔርን ባልይዝ ኖሮ በልተውኛል፤ ገለውኛል፤ ብዙ ብዙ።

ቴድሮስ ካሳሁን እንኳን እኔ የማትወዱትም ሰዎች ብቻችሁን ተደብቃችሁ ስራዎቹን የምታዳምጡ፤ አትችሉም እንጂ እንደሱ ብትሆኑ የምትመኙት ጥበበኛ ሰው ነው፤ እንኳን የቴዲን የሁሉንም ስራ በማስተዋወቅ ነው የምታወቀው( የዛኔ ምን አይነት ደግ ነሽ ብላችሁ ፅፋችሁልኝ ነበር ) ይሄኔ እኮ ስለሱ መጥፎ ባወራ አምናችሁኝ ነበር አይደል? ልክ ሌሎቹን እንዳመናችሁት? መጀመርያ ቤታችሁ ተደብቃችሁ የምታደርጉትን እናንተ እና ፈጣሪ ብቻ የሚያውቀውን ሀጥያታችሁን አቁሙ፤ የኛን ጉድ የሸፈነ አምላክ እንዳይታዘበን እንኳን ትንሽ እንፈር 🙆🏽‍♀️ ደግሞ ለምን መልካም ተመኘሽ፣ ለምን መሰከርሽ ብሎ ሰው ሲታመም ያድራል እንዴ?

ሌላው የኔ ቤተሰቦች የወደዱኝ በማንነቴ እንጂ በሰው አይደለም፤ ሀ ብዬ ስመጣ የተቀበለኝ የኔ ቤተሰብ ነው አሁንም ከፈጣሪ በታች ከኔ ጎን ያለው፤ እሱን ደግሞ ጠንቅቃችሁ ታቁታላችሁ 😆 ማንም ምንም እንዲጨምርልኝ ብዬ የማደርገው ምንም ጉዳይ አይኖረኝም። ለነገሩ አሁን አልበሙ ሲወጣ tik tok ላይ ቪድዮ ስትሰሩበት እንገናኛለን 😂😂😂

ለምታስፈራሩኝ እና በውስጥ መልዕክት የምትልኩ ….. ዋ ብያለው 😂😂😂😂 እሰይ እንኳን አሽቃበጥኩ 😛😛😛

ለማንኛውም የቴዶን አልበም በVPN እንድናዳምጠው በአክብሮት እጠይቃለሁ ❤️🙏🏽 (VPN ስናዳምጥ የተሻለ ገቢ ስለሚያስገባ ነው YouTube)

ሰላም ሁኑልኝ ❤️❤️❤️
❤58
ሌሎቹን እና ሁሉንም ሙዚቃዎቹን የራሱ ዩቱብ ላይ አዳምጡለት
❤41