የሕያ ኢብኑ ኑህ | Yahya Ibnu Nuhe
22.3K subscribers
1.46K photos
275 videos
84 files
1.73K links
﷽ | Muslim | Theology | Comparative Religion | Philosophy | Student |

ለንግድ፣ ለህክምና ወይም ለጉብኝት ወደ ቱርክ፣ ዱባይ እና የተለያዩ ሀገራት ለመጓዝ ካሰባችሁ ፈሲሩ ትራቭል የትኬት ጉዳያችሁን በኃላፊነት ያጠናቅቃል። እንግልት የሌለበት ጉዞ ለማድረግ ስትፈልጉ በዋትስአፕ አግኙን፦

https://wa.me/qr/5CWCIMYBZLCJB1
Download Telegram
ላይቩ ጀምሯል፣ ተቀላቀሉ

https://vt.tiktok.com/ZS9U5ygSuGcBb-RqIzt/
👍49
❤28👏17🥰5👍2
የሕያ ኢብኑ ኑህ | Yahya Ibnu Nuhe
Photo
የትላንት ምሽቱ የቲክቶክ ላይቭ ፕሮግራማችን እጅግ አስደሳች እና የተሳካ ነበር! አልሐምዱሊላህ። ወደ 3 ሰዓታት ገደማ በፈጀው በዚህ የመጀመሪያ ቆይታችን፣ "የጽልመቱ ጥላ" የተሰኘውን መጽሐፍና በስሙ የወጣውን ግለሰብ አስመልክቶ እንደ መጀመሪያ ክፍል መግቢያ ሀሳቦችን ጨምሮ ጥቅል ዳሰሳ አድርገናል። ቀጥሎም የምዕራፍ አንድን ሙሉ ክፍል ከሞላ ጎደል በጥልቀት ዳስሰነዋል።

ይህ ፕሮግራማችን በተለይ ከክርስቲያን ወገኖቻችን ጋር ሰፊ መነጋገሪያን መፍጠሩን በተለያዩ ግብረ-መልሶች ለማስተዋል ችያለሁ። በመድረኩ ላይ ያነሳናቸውን ሀሳቦች ተንተርሶ ጥቂትም ቢሆኑ በጨዋነት ሀሳባቸውን ያጋሩ እንዳሉ ሁሉ በሌላ በኩል ደግሞ ቪዲዮዎቻችንን በመቆራረጥ ቲክቶኩን በዘለፋ እና የእልህ ብሽሽቅ ያጥለቀለቁ በርካታ የኦርቶዶክስ ምዕመናንን ታዝበናል።

የኛ ዋና ዓላማ ሰውን ስሜታዊ ማድረግ ወይም ብሽሽቅ መፍጠር ሳይሆን፣ በመጽሐፉ ላይ በተነሱት ጉዳዮች ዙሪያ ምክንያታዊ የሆነ የሐሳብ ልውውጥና ውይይት እንዲፈጠር ማድረግ ነው፤ ይህ በመጠኑም ቢሆኑ መሳካቱ ደግሞ መልካም ነገር ነው።

ምዕራፍ አንድ ላይ ያነሳቸውን አርጊውመንቶች ገጽ በገጽ ምላሽ ከመስጠት በተጨማሪ ጸሐፊው AI በመጠቀም መረጃዎችን ለመጻፍና ለመተርጎም ሲሞክር የፈጸማቸውን ጉልህ የትርጉም እና የማጣቀሻ ስህተቶች በማስረጃ አጋልጠናል።

በጥቅሉ ውይይታችን ጠቃሚና በአላህ እገዛ ስኬታማ ነበር። በቀጣይ ፕሮግራሞቻችንም ቀሪ ክፍሎችን በአላህ ፍቃድ በተመሳሳይ የምንዳስስ ይሆናል።

ሁላችሁንም እንድትከታተሉን እንጋብዛለን። በተለይ ክርስቲያን ወገኖቻችን፣ በመጽሐፍ ቅዱስ ዙሪያ ያነሳናቸውን በርካታ ካውንተር መከራከሪያዎች እና የጠየቅናቸውን ጥያቄዎች ይዛችሁ ጸሐፊውን ሞግቱት፣ ቻሌንጅ አድርጉት! በመጽሐፉ የሚተማመን ከሆነ እነዚህን ጥያቄዎች ለማብራራት ሰበብ እየፈለገ አያድበሰብሳቸውም! ተሰብስቦ እኛን መስደብ ግን ውስጣችሁ ላይ የተፈጠረን ጥያቄ በጊዜያዊነት ከማብረድ በዘለለ ዘላቂ መፍትሄ አይሰጣችሁም።

https://t.me/Yahyanuhe
❤114👍62🥰7
የሕያ ኢብኑ ኑህ | Yahya Ibnu Nuhe
Photo
ትላንት በመግቢያችን ላይ ያነሳነው አንድ ጉዳይ በቲክቶክ በኩል ሰፊ መነጋገሪያ ሆኖ በመመልከቴ፣ ሐሳቤን ለፌስቡክም በሚሆን መልኩ ይበልጥ ማብራራት እንዳለብኝ ተሰምቶኛል። ያነሳሁት ሐሳብ ሲጨመቅ የሚከተለውን ይመስላል፦

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን በርካታ ኮሌጆች፣ ዩኒቨርሲቲዎች እና የትምህርት ማዕከላት ያሏት ትልቅ ተቋም እንደመሆኗ መጠን፤ እምነቷን በተገቢው መንገድ የሚሞግቱ በርካታ ሊቃውንትን አፍርታለች ብዬ እገምት ነበር (ቢያንስ የእኔ እሳቤ ይህ ነበር)። ነገር ግን፣ አሁን ላይ አንዳንድ የእምነቱ ተከታዮች "እፎይ" ለተባለው ግለሰብ የሰጡት የተጋነነ ትልቅ ቦታና አድናቆት፣ በቤተክርስቲያኒቱ እና በአማኙ ዘንድ ያለውን ሰፊ የ"ዐቃቤ-እምነት" ክፍተት በግልጽ አጋልጦ ያሳየ ሆኖ አግኝቼዋለሁ።

ለምን ቢሉ፤ በዚህ ደረጃ ስነ-ምግባሩ ክፉኛ የወደቀ፣ እጅግ ጸያፍ ቃላትን ያለ ሀፍረት የሚጠቀም፣ አልፎ ተርፎም "የበርካታ ሴቶችን እርቃን ቪዲዮዎች እጄ ላይ አሉኝ" በሚል በይፋና በአደባባይ የሚፎክር (በቴሌግራም ቻናሉም ላይ እንደለቀቀና እንዳጠፋ የተነገረለት) አሳፋሪ ግለሰብ፤ የቤተክርስቲያኗን እምነት በዕውቀት የሚሞግት "አዳኝ" ወይም "ተከላካይ" ተደርጎ የሚታመን ከሆነ፣ በእርግጥም ምዕመኑ ሃይማኖቱን በዕውቀት የሚያቅብለት ትክክለኛ መምህር ከቤተክርስቲያኗ አጥቷል ማለት ነው።

እውነታውን እንነጋገር ከተባለ፣ እንዲህ ዓይነት የስነ-ምግባር ውድቀት ያለበት ሰው በሌላ የትኛውም ቤተ-እምነት ውስጥ ቢገኝ፣ ከምግባሩ እንዲታረምና እንዲመለስ ይመከራል፣ ይገሰጻል እንጂ፣ እንደ "አንድያ ልጅ" ወይም እንደ ጀግና ተደርጎ ሊሞገስ አይችልም።

ነገር ግን... በዚያ በዐቃቤ-እምነት መስክ ፈጽሞ አማራጭ ሲጠፋ፣ ሰው እንደሌለ ሲታመን፣ የተገኘውን ከነሙሉ እንከኑ አቅፎ ጀግና ለማድረግ መገደድ ይመጣል። አሁን ላይ በአንዳንድ የኦርቶዶክስ አማኞች ዘንድ እየታየኝ ያለው እውነታ ይህ ነው። የዚህ ልጅ መምጣትና ያለ ከልካይ በአንዳንድ ወገኖች እንደ ትልቅ ምሁር መሞገሱ የሰጠኝ ትልቅ ትምህርት ቢኖር፤ በቦታው ላይ ቤተክርስቲያኗ እጅግ ሰፊ የዕውቀትና የሰው ክፍተት እንደገጠማት ነው።

https://t.me/Yahyanuhe
🔥82👍62❤27🙉1
ነፃ የዲግሪ ትምህርት ዕድል በኢማም አል-ቡኻሪ የሸሪዓ እና የዐረብኛ ቋንቋ ኮሌጅ!

ኢማም አል-ቡኻሪ የሸሪዓ እና የዐረብኛ ቋንቋ ኮሌጅ በ2019/2020 ዓ.ል. (1448 ዓ.ሂ.) የትምህርት ዘመን፣ ለ2ኛ ዙር ተማሪዎች በነፃ የዲግሪ መርሃ-ግብር ለመቀበል ምዝገባ መጀመሩን በደስታ ያሳውቃል! 🎓

ለመመዝገብ የሚያስፈልጉ መስፈርቶች፡

• የ12ኛ ክፍል የመልቀቂያ ሰርተፍኬት

• የ12ኛ ክፍል ሰርተፍኬቱ በ2014 ዓ.ል. እና ከዚያ በኋላ የተሰጠ መሆን

• የአረብኛ ቋንቋን (መናገር፣ መስማት፣ መፃፍ እና ማንበብ) መቻል

• መሰረታዊ የሸሪዓ ዕውቀት ያለው

• የመመዘኛ ፈተናዎችን ማለፍ የሚችል

• ዕድሜው ከ18 እስከ 30 ዓመት የሆነ

• ወንድ ተማሪ የሆነ

• ከተላላፊ በሽታ ነፃ የሆነ

የምዝገባ ጊዜ፡ ከ ጥቅምት 08/2019 እስከ ጥቅምት 20/2019 ዓ.ል.

የመመዝገቢያ መንገዶች፡

• በኦንላይን፡ በምስሉ ላይ ያለውን የQR ኮድ ስካን በማድረግ ወይም በቴሌግራም @Imam_albukhari_College ቻናል በመግባት ይመዝገቡ።

• በአካል፡ ኮልፌ 18 (ሹራብ ማህበር) በሚገኘው የኢማም አል-ቡኻሪ ኮሌጅ በአካል በመቅረብ መመዝገብ ይችላሉ።

እነዚህን መስፈርቶች የምታሟሉ ወንድሞች ይህን ወርቃማ የሸሪዓ ትምህርት ዕድል በፍጥነት ተጠቀሙበት!

ለተጨማሪ መረጃ፦
📞 +251 911 09 3765
📞 +251 993 64 8920
📞 +251 112 74 0874
❤39👍21😢8
የሕያ ኢብኑ ኑህ | Yahya Ibnu Nuhe
Photo
ምስሉ ላይ እንደምትመለከቱት፣ እፎይ "ዝምታ ለበግም አልበጀች... ተንቀሳቀሱ እየጠበቅኋችሁ ነው!!!" በሚል ጽሑፍ እኛን እየፈለገ መሆኑን አሳውቋል፣ ሊያደርሱልን በሚችሉ የሱ ሰዎች በኩልም መልዕክት ልኳል። የእኛን ምላሽ አጀንዳ ላለማድረግ በውስጡ ከፍተኛ ትግል ቢያደርግም፣ አላስችል ብሎት የየዕለቱ የላይቭ ፕሮግራሙ መክፈቻና ማሟሻ ግን እኛው ሆነናል።

ለአንድ ሁለት ቀናት ከማኅበራዊ ሚዲያ ላይ በግል ጉዳይ ምክንያት ፖስት አለማድረጋችንን ተከትሎ በጥብቅ ተከታትሎ "የት ገቡ?" ብሎ መፈለጉና መጥራቱ በራሱ ጥሩ አጋጣሚ ነው። "ንቄ ትቻቸዋለሁ" ብለህ ላይቭ ላይ ስትናገር በዚህ መልኩ ይሆናል ብየ አላሰብኩም ነበር።

በመሠረቱ እፎይ በተከታዮቹ በኩል "መጅሊስ በጀት መድቦላቸው ነው የሚሰሩት" እያለ የሚያስወራው አሉባልታ ከእውነት የራቀ ነው። ይህንን ምላሽ የምናዘጋጀው የትኛውም ተቋም መድቦን ወይም በቋሚ ሥራነት ሳይሆን፣ በግል ተነሳሽነት በንጽጽር ዳዕዋ ማዕቀፍ ውስጥ ነው። ከዚህ ቀደም እንደሚደረገው ጊዜያዊ ጥያቄዎችን ባልተደራጀ መልኩ ከመመለስ ባለፈ፣ ለትውልድ የሚጠቅምና የተደራጀ (በማያዳግም መልኩ) ምላሽ ለመስጠት ስላሰብን ከዚህ በኃላ እስልምና ላይ ለሚነሱና ምላሽ ያስፈልጋቸዋል ብለን ለምናምናቸው ጉዳዮች ሁሉ የምንከተለው መርህ ይህ በመሆኑ ነው።

ቢሆንም ግን ለዚህ ሳምንትም እሱ እንዳሰበው ዝምብለንም ሳይሆን ስራችንን እየሰራን ነው። እሱም ሆነ ተከታዮቹ ስለኛ በብሽሽቅና በስድብ መልኩ በተናገሩ ቁጥር መልስ መመለስ ተገቢ ነው ብለን ስለማናምን የሚወረወረውን ሁሉ ድንጋይ አናነሳም።

እፎይ ገና ለምዕራፍ 1 ምላሻችን የሰጠው አንዲትም ጠብ የምትል መልስ ሳይኖር፣ "ቀጣዩን ፒዲኤፍ እየጠበቅኩ ነው" ማለቱ አስገራሚ ቢሆንም፤ እኛ ግን ብዙ መልስ ይሰጥ ዘንድ ወደፊት የምናዘጋጅለት ጹሁፎች ስላሉ በዚህ አናስቸግረውም። ከዚህ በኋላ ለቀሩት 12 ምዕራፎች፣ 12 ሳምንታትን በመፍጀት አናንዛዛውም። ይልቁንም ምዕራፎቹን በተገቢው መንገድ በማዋሃድ በአጭር ጊዜ ውስጥ ምላሹን አጠናቅቀን እንለቃለን፤ በ10 ደቂቃ አፈርሰዋለሁ ባለው መሠረት ከዚያ በኃላ ኃላፊነቱን ለሱ እንተወዋለን።

የእኛ ዋና ዓላማ ያንተን የብሽሽቅና የዘለፋ መንገድ መከተል ሳይሆን፤ "ለዚህ መጽሐፍ መልስ የለውም" ብለው ያምኑ የነበሩ ክርስቲያን ወገኖቻችን ምላሹን አንብበው፣ ሚዛናዊ በሆነ መንገድ የራሳቸውን ውሳኔ እንዲወስኑ የህሊና መንገድ መክፈት ነው።

አንተም ቢሆን በትኩረት ካነበብከው ብዙ ትማርበታለህ ብለን ተስፋ እናደርጋለን። አብሽር... በጉጉት ጠብቀን፣ በአላህ ፍቃድ በዚህ ሳምንት ከበቂ በላይ ክፍሎችን የዳሰስንበትን ፒዲኤፍ ይዘን በቶሎ እንመጣለን!

https://t.me/Yahyanuhe

#የጽልመቱ_ጥላ #ውይይት #ግልጽነት #እፎይ
3👏120❤36👍28🔥8
"የጽልመቱ ጥላ" ለተሰኘው መጽሐፍ እየሰጠነው ካለው ምላሽ ጋር ተያይዞ፣ ብዙ ሰዎች በተለያየ ጎራ ሆነው ጉዳዩን መነጋገሪያ ሲያደርጉትና ሐሳባቸውን ሲያንሸራሽሩ እየተመለከትን ነው። እውነት ለመናገር፣ በጨዋነት የቀረቡትም ሆነ በስድብ የታጀቡት አስተያየቶች ቢኖሩም፤ ለእኛ ዋናው ትርፍ ጉዳዩ የአንድ ወገን ትርክት ብቻ መሆኑ ቀርቶ የኛንም ምላሽ Counter-argument መሠረት አድርጎ ሰፊ ውይይት መፈጠሩ ነው።

ገና ከመነሻው ያቀድነውና የፈለግነውም ይህንኑ ነው። በሐሳብ ደረጃ የሰደቡንንም ቢሆን አንጠላውም፤ ምክንያቱም ስድቡ ትክክል ነው እያልን ሳይሆን፣ ከሚሰነዘረው ስድብ በላይ የመልእክታችን መነጋገሪያ መሆንና ለብዙኃን መድረስ የተሻለው መልካም አጋጣሚ በመሆኑ ነው።

ይህንን ምላሽ ስናዘጋጅ ዋነኛ ትኩረታችን፣ በተለይ ክርስቲያን ወገኖቻችን በመጽሐፉ የተጋነነ ማስታወቂያ የተነሳ የተሳሳተ መረጃ እንዳይደርሳቸው፣ ይልቁንም ሁለቱንም ሐሳቦች አነጻጽረው አይተው የራሳቸውን ህሊናዊ ውሳኔ እንዲሰጡ ማድረግ ነው። እርግጥ ነው፣ መጽሐፉ ድንገት እጃቸው ቢገባ በቂ ዕውቀት በሌላቸው ጥቂት ሙስሊሞች ዘንድ ጥያቄ ሊፈጥር ይችላል። ነገር ግን አሁን ላይ ዋነኞቹ የታለሙት Target audience ክርስቲያን ወገኖቻችን እንደመሆናቸው፣ ይህ መጽሐፍ ያለምንም ምላሽ ቢቀር ኖሮ የሚሰማቸው ስሜትና የሚፈጥረው ብዥታ ከፍ ያለ ይሆን ነበር።

ይህ መጽሐፍ አዲስ ግኝት ያመጣ ሳይሆን፣ በ18ኛው እና 19ኛው ክፍለ ዘመን የነበሩ እንደ ሰር ዊሊያም ሙር፣ ሳሙኤል ዝዌመር (The Apostle to Islam' በመባል የሚታወቀው)፣ ዴቪድ ማርጎሊዮዝ፣ አርተር ጄፍሪ እና ኢግናዝ ጎልድዚሄር የመሳሰሉ ጸሐፊዎች ያነሷቸው፣ በሙስሊም ዑለሞች ዘንድ በተደጋጋሚ ምላሽ የተሰጠባቸው ያረጁ ክሶች ስብስብ ነው።

በንጽጽር ትምህርት ውስጥ ያለ ማንኛውም ሰው እነዚህን ያረጁ ክሶች ጠንቅቆ ያውቃቸዋል። ነገር ግን ጸሐፊው፣ ሰውን በቀላሉ ማታለል እንደሚችል፣ ወይም ላይቭ ላይ ገብቶ ስለራሱ አጋኖ በመናገርና በመኮፈስ ብቻ ማንም የሚነዳው መንጋ እንዳለ አድርጎ አስቦ ሊሆን ይችላል። እኛ ግን፣ እውነትና ውሸትን መለየት የሚችል፣ አስተዋይና ሚዛናዊ የሆነ በርካታ ክርስቲያን ወገን በተቃራኒው እንዳለ ጽኑ እምነት አለን። ስለዚህ ምላሻችንን የጻፍነው ለዚህ አስተዋይ ወገናችን ስንጨነቅ እና አላህ የሂዳያ ወይንም የቅን መንገድ ሰበብ እንዲያደርገን በማሰብ ነው።

ከዚህ በተጨማሪ፣ የዚህ ምላሽ ሌላኛው ዓላማ "ሌጋሲ" ማኖር ነው። የአላህን መልእክተኛ (ﷺ) በተመለከተ ከዚህ በኋላም ቢሆን ለሚነሱት ለእነዚህ ያረጁ ክሶች፣ ቋሚና በማያዳግም ሁኔታ በአማርኛ ቋንቋ ምላሽ የተሰጠበት ሪፈረንስ ትውልድ እንዲያገኝ በማሰብ የተሰራ ነው።

በመጨረሻም፤ በተለያዩ ጎራዎች ሆናችሁ እኛን ለምትወቅሱም፣ ስራችንን ደግፋችሁ ሐሳቡን ለማሰራጨት ለምትሞክሩትም፣ እንዲሁም ለምትሳደቡትም ቢሆን... በአንድም ሆነ በተዘዋዋሪ መልኩ ስራችንን እያስተጋባችሁ ስለሆነ ለሁላችሁም ክብር አለን። ተሳዳቢን ባላከብርም፣ ቢያንስ በዛ ተሳዳቢ ጌለሰብ ምክንያት መጽሐፉንና ምላሹን የሚያውቅ በርካታ ሰው እንደሚኖር ምንም ጥርጥር የለውምና ውይይቱ ይቀጥል ዘንድ ምኞቴ ነው።

ዋናው ዓላማችን እውነታውን ማሳወቅ ነው፤ በርቱልን!

#የጽልመቱ_ጥላ #ውይይት #ግልጽነት #እስልምናና_ክርስትና #Orientalists
1👍118❤41👏6🔥1
የምናመልከው አላህ ማነው.pdf
2 MB
የምዕራፍ 1 ቀሪ ክፍል እና ሙሉ የምዕራፍ 2 ምላሽ ተለቋል!

"የምናመልከው አምላክ ማነው?" በሚል ርዕስ ከምዕራፍ 1 የተረፈውን ሰፊ ክፍል፣ ዝርዝር በሆነና ራሱን በቻለ መልኩ በማያዳግም ሁኔታ ምላሽ ሰጥተንበታል።

ከዚህ በመቀጠል ደግሞ ስለ 'ወሕይ' ወይንም ራዕይ እና ተያያዥ ጉዳዮች በሰፊው የሚዳስሰውን ሙሉ የምዕራፍ 2 ክፍል፣ አንድም ነጥብ ሳናስቀር እያንዳንዱን ሐሳብ እየነቀስን አጥጋቢ ምላሽ ሰጥተንበታል።

እንደተለመደው አንባቢዎች የእኛን ምላሽ እና የጸሐፊውን ሐሳብ በቀጥታ ማመሳከር እንዲችሉ፣ ምላሽ የሰጠንባቸውን የመጽሐፉን ገጾች ስካን በማድረግ ከፒዲኤፉ ጀርባ አያይዘናል።

ምላሹ በሚገባ የተብራራና ማስረጃዎችን ያካተተ በመሆኑ ሁላችሁም ታነቡት ዘንድ በአክብሮት ጋብዘናል። በፒዲኤፉ ይዘት ዙሪያ ያልተመቻችሁ ወይም መከራከሪያ ማቅረብ የምትፈልጉ ጸሀፊውን ጨምሮ ማንኛችሁም ወገኖች፣ ሐሳባችሁን በነፃነት እንድትገልጹና ምላሽ እንድትሰጡን መድረኩ ክፍት ነው።

ሙስሊም ወንድም እና እህቶቻችን ደግሞ ይህንን የተብራራ እውነታ ለክርስቲያን ወገኖቻችን ሼር በማድረግ እንድታደርሱ ሙሉ ፈቃድ አላችሁ። የመልካም ስራው ተጋሪ ትሆኑ ዘንድም ጥሪያችን ነው።

ቀጣይ ክፍሎችንም ልክ እንደዚሁ በተደራጀ መልኩ በአላህ ፍቃድ ምላሽ መስጠታችንን የምንቀጥል ይሆናል!

ሙሉ ፒዲኤፎችን ለማግኘት ከታች ያለውን የቴሌግራም ሊንክ ይጫኑ፦

https://t.me/Yahyanuhe
https://t.me/Abuyusra3

#የጽልመቱ_ጥላ #አላህ_ማነው #ወሕይ #እስልምናና_ክርስትና #ውይይት
👍55❤23👏2🔥1
የምዕራፍ 2 ሙሉ ምላሽ.pdf
6 MB
የምዕራፍ 1 ቀሪ ክፍል እና ሙሉ የምዕራፍ 2 ምላሽ ተለቋል!

"የምናመልከው አምላክ ማነው?" በሚል ርዕስ ከምዕራፍ 1 የተረፈውን ሰፊ ክፍል፣ ዝርዝር በሆነና ራሱን በቻለ መልኩ በማያዳግም ሁኔታ ምላሽ ሰጥተንበታል።

ከዚህ በመቀጠል ደግሞ ስለ 'ወሕይ' ወይንም ራዕይ እና ተያያዥ ጉዳዮች በሰፊው የሚዳስሰውን ሙሉ የምዕራፍ 2 ክፍል፣ አንድም ነጥብ ሳናስቀር እያንዳንዱን ሐሳብ እየነቀስን አጥጋቢ ምላሽ ሰጥተንበታል።

እንደተለመደው አንባቢዎች የእኛን ምላሽ እና የጸሐፊውን ሐሳብ በቀጥታ ማመሳከር እንዲችሉ፣ ምላሽ የሰጠንባቸውን የመጽሐፉን ገጾች ስካን በማድረግ ከፒዲኤፉ ጀርባ አያይዘናል።

ምላሹ በሚገባ የተብራራና ማስረጃዎችን ያካተተ በመሆኑ ሁላችሁም ታነቡት ዘንድ በአክብሮት ጋብዘናል። በፒዲኤፉ ይዘት ዙሪያ ያልተመቻችሁ ወይም መከራከሪያ ማቅረብ የምትፈልጉ ጸሀፊውን ጨምሮ ማንኛችሁም ወገኖች፣ ሐሳባችሁን በነፃነት እንድትገልጹና ምላሽ እንድትሰጡን መድረኩ ክፍት ነው።

ሙስሊም ወንድም እና እህቶቻችን ደግሞ ይህንን የተብራራ እውነታ ለክርስቲያን ወገኖቻችን ሼር በማድረግ እንድታደርሱ ሙሉ ፈቃድ አላችሁ። የመልካም ስራው ተጋሪ ትሆኑ ዘንድም ጥሪያችን ነው።

ቀጣይ ክፍሎችንም ልክ እንደዚሁ በተደራጀ መልኩ በአላህ ፍቃድ ምላሽ መስጠታችንን የምንቀጥል ይሆናል!

ሙሉ ፒዲኤፎችን ለማግኘት ከታች ያለውን የቴሌግራም ሊንክ ይጫኑ፦

https://t.me/Yahyanuhe
https://t.me/Abuyusra3

#የጽልመቱ_ጥላ #አላህ_ማነው #ወሕይ #እስልምናና_ክርስትና #ውይይት
5👍115❤21🔥7👏2🏆2
ሀሳብና አስተያየታችሁን በነጻነት አካፍሉን!

ከሰሞኑ "የጽልመቱ ጥላ" ለተሰኘው መጽሐፍ እየሰጠነው ባለው ተከታታይ ምላሽ ዙሪያ፣ በርካታ ሰዎች ሀሳብና አስተያየታቸውን ማካፈል እንደሚፈልጉ ከኮሜንት ጹሁፎችና በግል ከሚደርሱን አንዳንድ መልዕክቶች መረዳት ችለናል።

በመሆኑም፤ በመጽሐፉም ሆነ በሰጠናቸው ምላሾች ዙሪያ የተሰማችሁን ማንኛውንም ሀሳብ፣ ትችትም ይሁን ግንዛቤ በነጻነት መስጠት እንድትችሉ፣ ክፍት የሆነ የቴሌግራም አስተያየት መቀበያ አዘጋጅተናል።

ሙስሊም ወንድሞች እና እህቶቻችን፣ እንዲሁም ሙስሊም ያልሆናችሁ ወገኖቻችን ያለምንም ገደብ በነጻነት ሀሳባችሁን በዚህ ቦት በኩል ልታጋሩን ትችላላችሁ።

የሁሉንም ሰው አስተያየት መፖሰት ባንችልም፤ ትልቅ ቁምነገር ያዘሉና ሌሎች ሰዎችን ያስተምራሉ ብለን የምናምናቸውን ሚዛናዊ አስተያየቶች በቻናሎቻችን ላይ ሼር በማድረግ፣ ማኅበረሰቡ እንዲማርባቸውና እንዲወያይባቸው የምናመቻች ይሆናል።

ከታች በተቀመጠው የቴሌግራም ሊንክ በመጠቀም አስተያየቶቻችሁን አሁኑኑ አድርሱን፦

➭ https://t.me/Yahyaabuyusrabot

#የጽልመቱ_ጥላ #ውይይት #ሀሳብ_ለማካፈል #እስልምናና_ክርስትና
👍62🥰12❤6👏4
ለመጽሀፍ ምላሹ በተዘጋጀው ፒዲኤፍ ዙሪያ አስተያየት ከሰጡ ወንድሞች መካከል።
🥰77👍41❤19👏11😱1
ከ5 ደቂቃ "ፉከራ" ወደ 2 ሰዓት ልፋት... ዛሬ ምሽት በቲክቶክ ላይቭ እንገናኝ!

ዛሬ ምሽት በአላህ ፈቃድ በወንድማችን ኢብራሂም የቲክቶክ ገጽ ላይ በሳምንት አንድ ቀን የምናቀርበው የላይቭ ፕሮግራም ይኖረናል። በፕሮግራማችንም ቀሪዎቹን የፒዲኤፍ ክፍሎች በሰፊው የምናብራራ ሲሆን፣ ሁላችሁም ተጋብዛችኋል!

በዚህ አጋጣሚ፤ ላለፉት ሳምንታት የተለያዩ ሰበቦችን እየደረደረ ምላሽ ከመስጠት ተቆጥቦ የነበረው ግለሰብ፣ ትላንትና ብቅ ብሎ ምላሽ ሰጥቻለሁ ማለቱን ሰምተናል። የሰውየው ፉከራ መጀመሪያ "በ5 ደቂቃ አፈራርሰዋለሁ" ነበር፤ ከዚያ 10 ደቂቃ አለው፤ ትላንት በፖስት ደግሞ 20 ደቂቃ ብሎ የነበረ ቢሆንም ማታ ሙሉ 2 ሰዓት ተቀምጦ፣ በጣም ጥቂት ነጥቦችን ብቻ ለቅሞ በመምረጥ አብዛኛውን ጊዜውን እንደተለመደው በስድብ አባክኖታል።

የትላንቱን ግዙፍ ስህተቶቹን ጨምሮ በርካታ ዝንፈቶችን ዛሬ ምሽት ስናቀርብላችሁ እጅግ ትገረማላችሁ! በዛሬው የላይቭ ፕሮግራማችን፤ በዚህ ሳምንት የለቀቅነውን ሙሉ የፒዲኤፍ ምላሽ አስመልክቶ ሰፊ ትንታኔ የምንሰጥበት ይሆናል። እግረ መንገድ "ምላሽ" በሚል የተናገራቸውን ሀሳቦች እግረ መንገድ የምንቃኛቸው ይሆናል።

ጠብቁን ..

#TikTokLive #የጽልመቱ_ጥላ #ውይይት #ንጽጽር
🥰81👍57❤15
የላይቭ ፕሮግራማችን ተጀምሯል፦

https://vt.tiktok.com/ZS9yJP9UyqENd-x6eyG/
👍47🥰6👏2
የሕያ ኢብኑ ኑህ | Yahya Ibnu Nuhe
Photo
«ይቅርታ» ወይስ የውርደት ሽሽት? - ግመሏን ሰርቆ ጅራቷን ስለተሳሳተው ሰውዬ!

አንድ ሰው የሰፈሩን ግመል ከነጭነቷ በጠራራ ፀሐይ ሰርቆ ሲሮጥ እጅ ከፍንጅ ይያዝና ሸንጎ ይቀርባል። ታዲያ ዳኛው ፊት ሲቆም ዓይኑን በጨው አጥቦ፦ «ክቡር ዳኛ! ሰፈሩ ለወር ያህል ሲፈልግ ቆይቶ ትላንት ማታ አንድ ከባድ ስህተት አግኝቶብኛል፤ የሰረቅኳት ግመል ጅራቷ ላይ ያለው ጸጉር ሦስት ሳይሆን ሁለት ነበር፣ ስለዚህ ሕዝቡን በትህትና ይቅርታ እጠይቃለሁ!» ቢል ምን ይባላል?

ዛሬ «እፎይ» በሚል ስም የተለቀቀችው የ«ይቅርታ» ጽሑፍ ልክ ይህንን አስቂኝ ድራማ ትመስላለች። ግለሰቡ «ለወር በዘለቀው እንከን ፍለጋ ትላንት ማታ አንድ ከባድ ስህተት አግኝተውብኛል» ይልና፣ የተገኘበት ብቸኛ ስህተት ነቢዩ (ﷺ) «ሸፍኑኝ» ያሉትን «ሦስት ጊዜ ሳይሆን ሁለት ጊዜ ነው» የሚለው የቁጥር እርማት ብቻ እንደሆነ አስመስሎ ለማቅረብ ሞክሯል።

ይህ በስነ-ልቦናው ዓለም «ትንሿን ጥፋት አምኖ ትልቁን ወንጀል የመሸፈን» የከሰረ የፕሮፓጋንዳ ስልት ይባላል። ለተከታዮቹ፦ «አያችሁ! ኡስታዞቹ ወር ሙሉ መጽሐፌን ፈትሸው ያገኙብኝ ስህተት ሁለትን ሦስት ማለቴን ብቻ ነው» የሚል የሐሰት መፅናኛ ለመስጠት የተሰራች የጭንቀት ድራማ ናት።

ነገር ግን እውነታው ምንድን ነው? በዚያው በጠቀሰው አንድ ገጽ (ገጽ 17) ላይ ብቻ የተጋለጡበትና በ«ይቅርታ» ጽሑፉ ላይ እንደ እሳት የሸሻቸው ግዙፍ የማጭበርበር ተግባራት የሚከተሉት ነበሩ፦

1/ የሐዲስ ምንጭን በጠራራ ፀሐይ ማጭበርበር፦ በገጽ 17 ላይ «Sahih Muslim 160a» ብሎ በደማቁ ከጻፈ በኋላ፣ በሰሒሕ ሙስሊም ውስጥ ጭራሽ የሌለውንና «ተኝቼ ሳለሁ... ከእንቅልፌ ነቃሁ» የሚለውን የኢብኑ ኢስሐቅን ሰንሰለቱ የተቋረጠ ጽሑፍ በሰሒሕ ሙስሊም ስም አጭበርብሮ ለጥፎታል። ታዲያ ይህንን ግዙፍ የምንጭ ሌብነት ትቶ ስለ «ሁለትና ሦስት» ቁጥር ማውራት ማንን ለማታለል ነው?

2/ በዚያችው የ«ይቅርታ» ጽሑፍ ውስጥ እንኳን የደገመው የፈጠራ ውሸት፦ ይህ ግለሰብ ይቅርታ እጠይቃለሁ ባለበት በዚያችው አጭር ጽሑፍ ውስጥ እንኳን «የከዲጃን ቀሚስ ይዞ... ሸፍኚኝ እንዳላት አስፍሬ ነበር» ብሎ በድጋሚ ዋሽቷል! በየትኛው የሐዲስ ወይም የታሪክ መጽሐፍ ውስጥ ነው «የኸዲጃን ቀሚስ ይዞ አስጥይኝ እያለ ጮኸ» ወይም «እብድ ውሻ እንዳየ እያለከለከ መጣ» የሚል ቃል ያለው? በየትኛውም መጽሐፍ ውስጥ የሌለን የመንደር ስድብ ከራስ ኪስ አውጥቶ በሐዲስ ስም መጻፍ «አሳማኝ ስህተት» አይደለም ወይ?

3/ ከካረን አርምስትሮንግ ልብ-ወለድ እስከ ቡኻሪ 5499 የእንግሊዘኛ ትርጉም ስርቆት፦ በገጽ 8 ላይ የሰሒሕ አል-ቡኻሪን (5499) የእንግሊዘኛ ትርጉም ሆን ብሎ ደብቆ የሌለ የውይይት ትርክት መፍጠሩ፣ በገጽ 26 ላይ የካረን አርምስትሮንግን የእንግሊዘኛ ድርሰት ከሰሒሕ ሙስሊም ጋር ደባልቆ «በዳዴ ተንፏቀቀ» ብሎ መቅጠፉ፣ እንዲሁም በራሱ በቀጥታ ስርጭቱ ላይ «ፈትሑል ባሪ (ኢብኑ ሐጀር) ማነው? እኔ ቡኻሪን እየጠቀስኩ ለምን ፈትሑል ባሪ ትጠቅሳላችሁ?» ብሎ የቡኻሪን ማብራሪያ ከቡኻሪ ጋር ሲያጋጭ ማምሸቱ የት ተረሱ?

ውድ ወገኖች! ሰውዬው አጣብቂኝ ውስጥ ሲገባና በየገጹ የፈጸማቸው የምንጭ ማጭበርበሮች እና የትርጉም ሸፍጦች አንድ በአንድ ሲጋለጡበት፣ ትኩረት ለማስቀየር ሲል «ሁለቴ ያለውን ሦስቴ በማለቴ ይቅርታ!» የሚል የጅል ቀልድ ይዞ ብቅ ብሏል።

በጽሑፉ መጨረሻ ላይ፦ «ውድ ሙስሊም እህት ወንድሞቼ መጽሐፉን እያነበባችሁ እንዲህ አሳማኝ ስህተት ካገኛችሁ አሳውቁኝ» ብሏል። እኛም በአክብሮት የምንለው፦ ወገናችን! በመጽሐፉ ውስጥ ያሉትን ቅጥፈቶችና የማጣቀሻ ስርቆቶች ለማረም ከፈለግክ፣ «ሁለትና ሦስት» የሚሉ ቁጥሮችን በላጲስ ማጥፋት ሳይሆን መጽሐፉን ከነሙሉ ሽፋኑ ሰብስቦ እንደ አዲስ መጻፍ ወይንም ማስጻፍ ነው የሚጠበቅብህ!

እውነት በማስረጃ ትገለጣለች፤ የጭንቀት ሳይኮሎጂ ግን የፈረሰን ሙግት አያድንም!

- የሕያ ኢብኑ ኑህ
👍169❤26👏13🤩2🏆1
በቀናነት የቀረበ የህሊና ጥሪ!

በቅርቡ በአንድ ቤተ ክርስቲያን ውስጥ የእየሱስ ክርስቶስ ምስል ወይንም ሐውልት ወድቆ የአንድ ቄስ ህይወት ማለፉን ተከትሎ፣ ከላይ በምስሉ የምታዩት አሳዛኝ እና አስተማሪ ትዕይንት ተፈጥሯል። ሰዎች "አምላክ" ነው ብለው ያቆሙትን ምስል በላያቸው ላይ እንዳይወድቅባቸው በብረት ሰንሰለት ወጥረው አስረውታል፤ የሃይማኖት አባቱም ራሱን ለማዳን የካስኮ (የአደጋ መከላከያ) ቆብ አድርጎ ይታያል።

ይህን ጉዳይ የማነሳው ለመሳለቅ ወይም ለማንኳሰስ ሳይሆን፣ ጤናማ አእምሮ ላለው ሰው ጥልቅ የህሊና ጥያቄን ስለሚጭር በጨዋነት ሀሳብ ለማንሳት ነው። የራሳችሁን "አምላክ" በእጃችሁ ቀርጻችሁ ከሰራችሁ በኋላ፣ ተመልሳችሁ "እንዳይጎዳን" ብላችሁ በሰንሰለት ካሰራችሁትና በስጋት ቆብ ካጠለቃችሁ፣ እምነቱ የት ላይ ነው? ራሱን ከውድቀት መጠበቅ ለማይችልና በሰንሰለት ለታሰረ ግዑዝ አካል እንዴት "ከአደጋ ጠብቀን" ብላችሁ ጸሎት ማድረግ ትችላላችሁ?

ይህ ድርጊት ታላቁ ነቢይ ኢብራሂም (ዐ.ሰ) ህዝቦቻቸውን የሞገቱበትን ታሪካዊ ጥያቄ ያስታውሰናል። ኢብራሒም ህዝባቸውን በተመለከተ እንዲህ ማለታቸውን ቁርኣን ይነግረናል፦ "አላቸው «የምትጠርቡትን ትግገዛላችሁን? አላህ እናንተንም የምትሠሩትንም የፈጠረ ሲኾን፡፡»" (ሱረቱ አስ-ሷፋት 37፡95-96)።

እጅግ ኃያል፣ በሰው እጅ የማይቀረጽ፣ የማይታይ፣ ነገር ግን የሁሉ ነገር ፈጣሪና ጠባቂ የሆነውን አንዱን አምላክ አላህን ብቻ ማምለክ ሲቻል፤ በገዛ እጅ ተቀርጾ ከዚያም ደግሞ ወድቆ እንዳይጎዳ ተፈርቶ በሰንሰለት የሚታሰርን ሀውልት መማጸን እንዴት የህሊና እረፍት ይሰጣል? ይህን በቅንነት፣ ከስሜት ርቃችሁ በምክንያታዊነት ብቻ እንድታስተነትኑት እጋብዛለሁ።

የሕያ ኢብኑ ኑህ
👏83👍29❤12😢3🔥2