የሀ-በሻ ኪነ-ህንጻ ፡ Yeha-Besha Architecture
2.77K subscribers
688 photos
11 videos
56 files
139 links
The present Ethiopia is the remain of the greater Ethiopia

Follow us on facebook
#http://facebook.com/yehabesha students of architecture
Telegram @yehas

#For Your Comment or Info Use
@arcnat
Download Telegram
ትምህርት ለዚች ሃገር የፈየደላት አንዳች ነገር የለም።
🦗🦗🦗🦗🦗🦗🦗
በሃገራዊ ማንነት ያልተቃኘው ሁሉን ሰልቃጭ (የባዕድ) የትምህርት ስርዓታችን የነቀዘ ቲወሪና ንድፈሃሳብ እያግበሰበሰ ከመሸጥ ያለፈ ረብ ያለው ምሁርን መፍጠር አልተቻለውም። ይልቁንም ኤሌክትሪካል ምህንድስና ተምሮ ገመድ መቀጠል የማይችል መሀንዲስ፣ እጽዋት ሳይንስ ተምሮ ስንዴ ለይቶ የማያውቅ ታክሶኖሚስት፣ ጅኦግራፊ ተምሮ ስንት አህጉር እንዳለ እንኳን በቅጡ የማያውቅ ጅኦግራፈር ብቻ ምን አለፋችሁ በየዘርፉ እልፍ አዕላፍ ሸክሞችን እየፈጠረ ነው።
እስካሁን ድረስ ሃገሪቱ የምትመራው በገበሬ እውቀት ብቻ ነው። ምሁር ነን ባዩ የገበሬ እውቀትን ከዚያም ከዚያም ቀራርሞና አዳቅሎ ገበሬው እንዳያውቅበት በእንግሊዝኛ አትቶ ለራሱ የተመራማሪነትን ካባ ይደርብበታል።
ገበሬው "ሐይቄን እምቦጭ ወረረብኝ ምን ላድርግ?" ሲለው የምሁሩ መልስ "እንቦጩን በእጅህ መንቀል የተሻለ አማራጭ ነው" ከማለት የዘለለ አይደለም።ከጤፍ ማሳ እስከ ስንዴ መሬት ከበቆሎ ማሳ እስከ ገብስ መሬት ድረስ እድሜ ልኩን አረም በመንቀል ለኖረ ለፍቶ አደር ገበሬ እንቦጭን በእጅህ ንቀል የሚል ምሁር አቤት እግዚኦ።
"ብሔራዊ ፓርኩ ተቃጠለ ምን እናድርግ?" ሲላቸው ጥርሱን ነቅሎ ያደገበትን "በቅጠልና በአፈር አጥፋው" በማለት ወገቡን ይቆርጡታል።
"ሰብሌን አንበጣ በላብኝ ምን ላድርግ?" ሲላቸው "ጅራፍ አጩህበት" በማለት ፍርደ ገምድልነታቸውን ያናፉበታል።
🦗
ሰሜን ብሔራዊ ፓርክ ከነ ብርቅየ ብዝኀ ሕይወታዊ ሃብቱ በእሳት ሲቃጠል፣ ጣና ሐይቅ ከነ ሙሉ ታሪኩና ከነገዳማቱ በእንቦጭ ሲወረር፣ የላሊበላ ውቅር አብያተ ክርስቲያናት ዓይናችን እያየ ሲፈራርሱ፣ ሰሞኑንም ቃፍታ ሁመራ ብሔራዊ ፓርክ ከነ ዝሆን ሃብቱ በእሳት ሲጋይ እንዲሁም ቆላማው ሰሜን ምስራቃዊ ኢትዮጵያ በአንበጣ መንጋ ሲወረር ምሁሩ ምን ፈየደ?
ምንም።
🦗
ዛሬ ሁሉ ነገር ሲወድም ዝም ብለው የተመለከቱ ምሁራንና ተቋማት ነገ ላይ ግን ሊቅ አክለው ምሁር መስለው ማስታወሻቸውን በቆዳ ቦርሳ ወሽቀው ለኪሳራ ግመታ የተፈጠሩ ይመስል
"Assessment of 2019 Locust invasion crisis in case of North east Ethiopia" የሚል የምርምር እንቶ ፈንቶ ደርተው በታዋቂ ዓለማቀፍ ጆርናሎች ያሳትማሉ።
ለእኛ ሃገር ምሁርነት ከዚህ ያለፈ አይደለም።
በዚች ሃገር ላይ ሰርቶ የሚበላ አርሶ አደር ብቻ ነው ሌላው አውርቶ አደርና ቀምቶ አደር ብቻ ነው።በማስመሰል አድጎ በማስመሰል አርጅቶ በማስመሰል ያልፋል።
ከ80 ፐርሰንት በላይ ለሃገሪቱ የውጭ ምንዛሬ ምክንያት የሆነ ገበሬ ስኳር ምን እንደሚመስል አያውቅም በመብራት ብርሃን ታጅቦ መኖር ምን ምን እንደሚል ለማወቅ አልታደለም።
ለመሬት ጠል ለሰማይ ደመና እግዜር አይነሳም ብሎ በእምነት ዘርቶ በተስፋ እየኖረ በነፃ የሚመግብ ይህ ደግ ገበሬ ሰብሉ በአንበጣ መንጋ ተበልቶበት ተስፋው ሲሟጠጥ ማየት እንደምን ይጨንቃል።
ተፈጥሮ በድሏት ጠጠር ላይ ከበቀለች እድሜዋ ከአንድ ጎረምሳ እድሜ የምትስተካከለው እስራኤል ጭንጫ መሬት ላይ በዘመናዊ ግብርና ከመራቀቅ ተሻግራ ሰው ሰራሽ ደመና ወደ መስራት ጥበብ እያኮበኮበች ነው። እኛ ግን የዛሬ 3000 ዓመት በታረሰበት ማረሻ አሁንም እያረስን ነው።
እናም የሞተው የትምህርት ስርዓታችን ከተቀበረበት ተነስቶ ወደ ቀደመ ማንነታችን ካልተመለስን ዓይናችን እያየ አንበጣ ይበላናል።
🦗🦗🦗
ፍትሕ ደንታቢስና ስሜት የለሽ ምሁራንን አዝሎ ጀርባው ለጎበጠው የሃገሬ ገበሬ።
🦅
አፄ እንደልቡ
The sound of ecology in the ears of architecture

The present Ethiopia is the remain of the greater Ethiopia

Follow us on facebook @
#http://facebook.com/yehabesha students of architecture

#don't forget to share the @yehas
This contemporary architecture is one of greatest building in addis abeba ...the designer is architect Bereket Tesfaye ...he designed it and constructed it for his own architectural consulting office ....location lafto go there and enjoy it ....yehabesha architecture
Art of Ethiopia 11th Exhibition
Venue: Sheraton Addis
Date: 6 - 9 December, 2019
Hours: 10am - 10pm
Free Entrance
በአዲስ አበባ አዳዲስ መናፈሻዎች ሊገነቡ ነው
______________

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በአራት ክፍለ ከተሞች በ132 ሄክታር መሬት ላይ የመናፈሻ ፓርኮች ሊገነቡ ነው መሆኑን ኢቢሲ ዘግቧል፡፡

የሚገነቡት የመናፈሻ ፓርኮች በመንግስት እና ከግል አልሚዎች ጋር በትብብር የሚለሙ ሲሆን፣ ለበርካታ ሴቶች እና ወጣች የስራ እድል እንደሚፈጥሩ ተነግሯል፡፡

ዕቅዱ የሚያስመሰግን ሆኖ ይህንን መሰል ከፍ ያለ ሀገራዊ ሥራ ዘመኑ በደረሰበት ሥልጡን ሙያዊ መርኅ መተግበር እንዲቻል ቢያንስ የሚከተሉት ባለሙያዎችን የያዘ ሀገራዊ አማካሪ ስብስብ (Scientific Committee) ቢመሠረት እላለሁ::

የምጣኔ ሀብት ባለሙያዎች (Economists) አርኪቴክቶች (Architects) የከተማ ፕላነሮች (Urban Planners) የገጸምድር አርኪቴክቶች (landscape Architects) የእጽዋት ባለሙያዎች (Plant Science Experts) እና ሌሎች የዘርፉ ባለሙያዎች ከዲዛይን እስከትግበራው እንዲሳተፉ እና ዕቅዶቹን እንዲተቹ እድል ቢሰጣቸው ዘመን ተሻጋሪ እጹብ ሥራ መስራት ይቻላል እላለሁ::

#የኢትዮጵያ_የአርክቴክቶች_ማኅበር
#የኢትዮጵያ_ከተማ_ፕላን_ባለሙያዎች_ማኅበር
__________________

- መልእክቱ ጠቃሚ ከመሰልዎ Share ያድርጉት!