የሀ-በሻ ኪነ-ህንጻ ፡ Yeha-Besha Architecture
2.77K subscribers
688 photos
11 videos
56 files
139 links
The present Ethiopia is the remain of the greater Ethiopia

Follow us on facebook
#http://facebook.com/yehabesha students of architecture
Telegram @yehas

#For Your Comment or Info Use
@arcnat
Download Telegram
በአዲስ አበባ አዳዲስ መናፈሻዎች ሊገነቡ ነው
______________

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በአራት ክፍለ ከተሞች በ132 ሄክታር መሬት ላይ የመናፈሻ ፓርኮች ሊገነቡ ነው መሆኑን ኢቢሲ ዘግቧል፡፡

የሚገነቡት የመናፈሻ ፓርኮች በመንግስት እና ከግል አልሚዎች ጋር በትብብር የሚለሙ ሲሆን፣ ለበርካታ ሴቶች እና ወጣች የስራ እድል እንደሚፈጥሩ ተነግሯል፡፡

ዕቅዱ የሚያስመሰግን ሆኖ ይህንን መሰል ከፍ ያለ ሀገራዊ ሥራ ዘመኑ በደረሰበት ሥልጡን ሙያዊ መርኅ መተግበር እንዲቻል ቢያንስ የሚከተሉት ባለሙያዎችን የያዘ ሀገራዊ አማካሪ ስብስብ (Scientific Committee) ቢመሠረት እላለሁ::

የምጣኔ ሀብት ባለሙያዎች (Economists) አርኪቴክቶች (Architects) የከተማ ፕላነሮች (Urban Planners) የገጸምድር አርኪቴክቶች (landscape Architects) የእጽዋት ባለሙያዎች (Plant Science Experts) እና ሌሎች የዘርፉ ባለሙያዎች ከዲዛይን እስከትግበራው እንዲሳተፉ እና ዕቅዶቹን እንዲተቹ እድል ቢሰጣቸው ዘመን ተሻጋሪ እጹብ ሥራ መስራት ይቻላል እላለሁ::

#የኢትዮጵያ_የአርክቴክቶች_ማኅበር
#የኢትዮጵያ_ከተማ_ፕላን_ባለሙያዎች_ማኅበር
__________________

- መልእክቱ ጠቃሚ ከመሰልዎ Share ያድርጉት!
[አይቼው የማላቀው የድንጋይ መጽሐፍ]
✍በመጋቤ ሐዲስ ዶክተር ሮዳስ ታደሰ
♥ ባለፈው እንዳስነበብኳችሁ በሰሜን አሜሪካ ኮንግረስ ቤተ መጻሕፍት በቶማስ ጄፈርሰን ሕንጻ ውስጥ ወደ 250 የሚጠጉ የኢትዮጵያ ጥንታውያን የብራና መጻሕፍትን ተፈቅዶልኝ ካየሁ በኋላ የቀረጽኳቸውን መላልሼ በማየት በመደነቅ ጊዜዬን ማሳለፍ ጀመርኩ።

♥ ከልጅነት ጀምሮ በብራና መጻሕፍት ውስጥ ማደጌ ይመስለኛል ብራና መጻሕፍት ያሉበትን ክፍል በማሽተት ጭምር ሳለየው አልቀርም። እነዚህን የቀደምት ኢትዮጵያውያኑን መጻሕፍት ስለምወዳቸው ይመስለኛል መዋደድ የጋራ ነውና በምሄድበት ሀገራት ሁሉ በፍቅር ይጠብቁኛል።

♥ ኮንግረስ ላይብረሪ ባየሁት 250 መጻሕፍት ስደነቅ 800 የብራና መጻሕፍት ያሉበት ታላቅ ዪኒቨርሲቲ እንዳለ ይልቁኑ የድንጋይ የግእዝ መጽሐፍ እንዳለ መምህር ነጸረ አብ ቁጭ ብለን ስናወጋ በጆሮዬ ሹክ አለኝ። በመገረም በመደመም ውስጥ ሆኜ ለጥቂት ደቂቃዎች ጸጥ ካልኩ በኋላ ቦታውን ስጠይቀው በካቶሊክ ዪኒቨርሲቲ ኦፍ አሜሪካ እንደሆነ በቦታው 15 ዓመታት የሠራው መምህር ነጸረ ነገረኝ።

♥ ካቶሊክ ዪኒቨርሲቲ ኦፍ አሜሪካ የተመሠረተው በ1887 ዓ.ም ሲሆን ታላቅ ጥናትና የምርምር ሥራ የሚደረግበት ዪኒቨርሲቲ ነው። በስሩ ባሉት 12 ትምህርት ቤቶች ውስጥ በፒ ኤች ዲ ዶክትሬት (Doctor of Philosophy) 66 በማስተርስ ዲግሪ 103፤ በቅድመ ምረቃ 72 ፕሮግራሞችን በመስጠት ተመራማሪዎችን ለፕላኔቷ ያቀርባል።
የእኛው ቋንቋ ግእዝም እስከ ፒ ኤች ዲ የዶክትሬት ዲግሪ ከሚሰጥባቸው ታላላቅ ዓለም ዐቀፍ ዪኒቨርሲቲ ውስጥ አንደኛው ይህ ነው።

♥ በቅድመ ምረቃ 3332 በድኅረ ምረቃ 2624 በአጠቃላይ ወደ 5956 የዛሬ ተማሪዎች የነገ ተመራማሪዎች አሉት። ከUS Capitol በ3 ማይል ርቀት ላይ የሚገኘው ይህ የምርምር ዪኒቨርሲቲ ሰፊና በ176 ሔክታር ላይ ያረፈ ለዐይን ማራኪ ነው። በዪኒቨርሲቲው ያለው የጆን ኬ ሙሌን መታሰቢያ ቤተ መጻሕፍት ከ1.3 ሚሊየን በላይ መጻሕፍት፤ በ10ሺዎች የሚጠጉ ኤሌክትሮኒክ ጆርናሎች ይገኙበታል።

♥ ይህን ታላቅ የምርምር ተቋምን ማየት እንድችል ይልቁኑ የምወዳቸው የኢትዮጵያን ጥንታውያት መጻሕፍት እንድመለከት ስለተፈቀደልኝ ኅዳር 28 እሑድ ወደ ዪኒቨርሲቲው ከመምህር ነጸረ ከካሜራ ማኖቼ ከኤርሚና ከደመኢየሱስ ጋር ሄድን።

♥ ወደ ውስጥ ዘልቀን ከገባን በኋላ የኢትዮጵያ ጥንታውያት የብራና ስብስብ ወዳለበት የምድር ቤቱ ክፍል ወረድን። ወደ ክፍሉ ስንቃረብ ዕውቀትን ያመቁ የብራና መጻሕፍት ሽታ ተሰማኝ፤ ገብቼ እስከምመለከታቸው ድረስ አላስቻለኝም፤ የክፍሉን መጥሪያ ስንነካው ከውስጥ የሲሪያክ፣ የአርመን፣ የጆርጂያ ቋንቋዎች ፕሮፌሰር የሆነችው የክፍሉ ሐላፊ ዶክተር ሞኒካ ብላንቻርድ በሩን ከፍታ በፈገግታ ተቀበለችን።

♥ ረጅሙን የሕይወት ዘመኗን በጥናት በምርምር እንዳሳለፈች ያስታውቃል፤ ወዲያውኑ ጊዜ አልወሰደችም በብራና መጻሕፍት ወደተሞላው በጥንቃቄ በንጽሕና በተቀመጡበት ክፍል ውስጥ አስገብታን ዕርፍ።

♥ የፈለጋችሁትን አውጥታችሁ እዩ ወደ 400 የሚጠጉ ታላላቅ የብራና መጻሕፍትና 400 ጥቅሎች አሉላችሁ አለችን እኔም እየመረጥኩ መመልከት ጀመርኩ። ብራናዎችን ሳነባቸው የኖሩኳቸው ወዳጆቼ በመሆናቸው ከእነርሱ ጋር ለተወሰነ ሰዓት የተመስጦ ቆይታ አድርጌ ወደ 400 ጥቅሎች አመራሁ ግን ስንቱ ተነቦ ያልቃል? ብቻ የምፈልጋቸውን ከተመለከትኩ በኋላ በድንጋይ ላይ የተቀረጹ የጥንታውያን ቋንቋዎች ጽሑፎችን አየሁ።

♥ የድንጋይ ላይ ጽሑፎችን ማን ይተረጉማቸዋል? እያልኩ ስቆዝም ዶክተር ሞኒካ ሳይገባት አልቀረም ፊደላት የተቀረጸበት በእጇ ቡናማ ወረቀት ይዛ ጠጋ ብላ አዲሱን ግኝት አስተዋወቀችኝ፤ ይኸውም በቀላሉ የድንጋይ ላይ ጽሑፍን ወደ ወረቀት ላይ ለውጦ በጉልሕ ያስነብባል፤ ለትርጓሜው ችግር የለም ቀንና ሌሊት ያለዕረፍት የሚመራመሩ የቋንቋዎች ሊቃውንት ይተረጉሙታል።

♥ ይህን በተመስጦ ስመለከት በኅሊናዬ የኢትዮጵያ ጥንታዊ ሳይንሳዊ ዕውቀቶችን ጠራርጎ አሽቀንጥሮ ጥሎ ዓለም አሁን የደረሰበት ዕውቀት ሳይደርስበት የመደባደቢያ አውድማ የሆኑትን የሀገራችን የትምህርት ተቋማት ሳስብ ሐዘን ተሰማኝ።

♥ ነገር ግን ነገ ኢትዮጵያን የሚረከቧት ዛሬ ትውልዱ የዘነጋቸው ሕፃናት ትውልዱ በዝንጋኤ የጣለውን የኢትዮጵያን አልማዛዊ ዕውቀት በክብር አንሥተው ዓለም ከደረሰበት የሳይንስ ምርምር ጋር አስተባብረው ኢትዮጵያን በከፍታ ሰገነቷ ላይ እንደሚያስቀምጧት ስለማምን ሐዘኑ ከልቤ ብን ብሎ ወጣ።

♥ በመጨረሻም ዶክተር ሞኒካ ላየው የምፈልገውን የድንጋይ ላይ ተከፋች የግእዝ ጽሑፍን ያለበትን ይዛ መጣች፤ በሕይወቴ እንደዚህ ዓይነት አይቼ ስለማላውቅ በአድናቆት ተመላሁ።በድንጋይ ላይ ጽሑፍንና ሥዕልን መቅረጽ የሚችሉ ጥበቦች ኢትዮጵያውያን እንደነበሩ አይቼ የበለጠ አከበርኳቸው። ጣቶቼም እነዚያን ጽሑፎች ዳሰሱ።

♥ ምስለ ፍቁር ወልዳና ሥዕለ ሥሉስ ቅዱስ ከታተመበት ከዚ የድንጋይ ጽሑፍን ስገልጥ ረዘም ያለ የዘንባባ ሥዕል ዳርና ዳር ያለው የአንዲት የንግሥት ሴት ከፊል ገጽ ና የአንድ ወንድ ተቀርጾ ይታያል።

♥ የሴቲቱ አቀራረጽና ሹሩባን ስመለከተው በጥንት የኢትዮጵያ ኑብያና ግብጽ ሥልጣኔ የምናያቸው ንግሥታትን ይመስላልና፤ የኢትዮጵያ ልዕልት አንድሮሜዳ ትሆን? ብዬ አሰብ አረኩና ረጃጅሞች የዛፍ ቅርጾች ግን ምን ሊሆኑ እንደሚችሉ በመመርመር የጥንታውያን የኢትዮጵያን ከፍተኛ ሥልጣኔ ታሪክ የሚያውቁት ሐኪም አበበች ሽፈራውን እጠይቃቸዋለሁ በማለት ገጥሜ በነበረበት የክብር ስፍራ አስቀመጥኩት።

♥ ለ15 ዓመታት በዚህ ቤተ መጻሕፍት የሠሩት መምህር ነጸረ አብ በመጨረሻ ሲነግሩኝ ያሳዘነኝ ነገር እነዚህን መጻሕፍት ለመመርመር እጅግ ብዙዎች ዓለም ዐቀፍ ተመራማሪዎች ወደ ቤተ መጻሕፍቱ ዘወትር ሲመጡ በ16 ዓመት ውስጥ መጥቶ ያየው አንድ ኢትዮጵያዊ ብቻ ነው ሲለኝ መስማቴ ነው፤ አባቶች ሁሉን ሠርተው ፍሪጅ ውስጥ አስቀምጠው ቢሄዱም ከስንፍና ብዛት አውጥቶ አሙቆ መብላት ያቃተን ያህል እየተሰማኝ በቀዝቃዛው የማታው አየር ሰፊውን የዩኒቨርስቲውን ቅጽር ለቅቄ ስወጣ ልቤ ግን በውስጥ ካሉት ከ800 መጻሕፍት ጋር ነበር።

[ኅዳር 28/ 2012 ዓ.ም በሰሜን አሜሪካ ዋሽንግተን ዲሲ የካቶሊክ ዪኒቨርሲቲ ኦፍ አሜሪካ ቆይታዬ]
✍ መጋቤ ሐዲስ ዶክተር ሮዳስ ታደሰ
Forwarded from Deleted Account
Ermias Assefa
Architect, and art director at behagerlij studio.
After a few years of freelance work, He has built his own company that has the motto of showing creativity and ambiance.

GET READY to be engaged, motivated and inspired.

#GUZZO #1choice #AIESEC in EIABC #eagles

📅 28 December
📍Swidish pavilion, EiABC

Register here to attend this event.
👇
https://docs.google.com/forms/d/e/1FAIpQLScmiRRdqqSKIqFr9aMNzvDh-Cxtp9G9VYaOgeBgVVUuPgBvsA/viewform?usp=sf_link
Forwarded from Deleted channel (Yohannes Mekonnen)
በመስቀል አደባባይ ስትራቴጂክ ጉዳዮች ኢንስቲትዩት ሕንፃ ላይ የሚገኘው ታሪካዊው ሰገነት የሀገራችን ፖለቲካ አካል ሆኖ ቆይቷል::

የኢትዮጵያ አርኪቴክቶች ማኅበር ከስትራቴጂክ ጉዳዮች ኢንስቲትዩት ጋር በመተባበር ቅዱስ እሲጢፋኖስ ቤተክርስቲያን ፊትለፊት በሚገኘው የከተማ ማዕከል (Urban Center) የዲዛይን ምክረሃሳብ አቅርቧል::

ይህንኑ የከተማችን የታሪክ ትእምርት (Land Mark) መልሶ ጥቅም ላይ ለማዋል ታስቦ በተዘጋጀው የዲዛይን ምክረ ሃሳብ ዝግጅት ላይ የታሪክ ባለሙያዎች, ጋዜጠኞች, ሰብአ ጥበብ (artists) አርኪቴክቶች, ታዋቂ ግለሰቦች እና ፖለቲከኞች ተሳትፈዋል::
Forwarded from Deleted channel (Yohannes Mekonnen)
Forwarded from Deleted channel (Yohannes Mekonnen)
01 (ETRSS - 01)
................................

ኢትዮጵያ በታሪኳ የመጀመሪያ የሆነችውን 01 (ETRSS - 01) ሳተላይት ዛሬ ማለዳ ከቻይና የሳተላይት ማስወንጨፊያ ጣቢያ ወደ ህዋ ልካለች፡፡

የዛሬዋ "0" ነች። 02, 03, 04...ገና በርካታ ሳተላይቶች ይወነጨፋሉ። የኢትዮጵያን ትንሳኤ በጉጉት ለሚናፍቁ የሀገሬ ልጆች እና የኢትዮጵያ ወዳጆች ይህ መልካም ዜና ነው።
መጠኑ 1.small
2.medium and
3.large size
ፖስትካርዶቹን የምትፈልጉ በ 0921878350 ወይም በ 0967023787 ላይ በመደወል ያናግሩን በነጠላም በደርዘንም ለምትፈልጉ ደውሉልን ያሉበት እናደርሳለን በቴሌግራም ቻናላችን @Luna23art ላይ አናግሩኝ።
ሠዓሊ እና አዘጋጅ አብዲ የኋላሸት
"የቀደመውን በጥንቱ በአባቶቻችን ጥበብ እንኩራ ኋላ በእጅ ያለ ወርቅ.....እንዳይሆን የእኛ የሆነ ሁሉ ይጣፍጣል" ክብር ይህንን አሳሳል ዘይቤ ላቆዩልን አባቶች🙏
ውሳኔው እንደገና ቢታይ!
______________

የተፈጥሮአዊ ዲዛይን (Organic design) ንድፈ ሃሳብ አመንጪ እውቁ አሜሪካዊ አርኪቴክት Frank Loyed Right በከተሞች ውስጥ የሚገኙ መናፈሻ ቦታዎች እና አጸዶችን ‹‹የከተማ ሳምባዎች›› (Lungs of the city) ሲል ይጠራቸዋል፡፡ ይህንን የአርኪቴክቱን ሀሳብ ወስደን አዲስ አበባችንን ብንመዝናት "የሳምባ ምች የመታት ከተማ" ወይም "ትንፋሽ ያጠራት ከተማ" ለመሆን እያዘገመች ትመስለኛለች፡፡

ለአዲስ አበባ ከተማ በግርማዊ ቀዳማዊ ንጉስ ኃይለ ሥላሴ ዘመን የተዘጋጁላት መሪ ዕቅዶች (Master Plans) ‹‹በአትክልት ሥፍራ ውስጥ ያለች ከተማ›› (The garden city) የሚል ጽንሰ ሓሳብ የነበራቸው፣ ለመጫወቻዎች፣ ለመናፈሻ ቦታዎች፣ ለአደባባዮች እና ለከተማ ውስጥ የአረንጓዴ ሽፋን ትኩረት በመስጠት የተነደፉ ነበሩ፡፡

በወታደራዊው የደርግ ሥልጣን ዘመን ደግሞ ምንም እኳን ሕዝባዊ ስብሰባ ለሚያካሂድባቸው (አብዮት አደባባዮች) እና ወታደራዊ ሰልፍ ለሚያሳይባቸው አደባባዮች የተለየ ትኩረት ቢኖረውም እንደ ንጉሡ ዘመን ሁሉ አዲስ አበባ "አረንጓዴ ከተማ" ለማድረግ ጥረት አድረጓል፡፡ (የችግኝ ተከላው እና ክብካቤው ሁሉ በ‹‹ዘመቻ›› ይሠራ የነበረ ቢሆንም)

በዘመነ ኢህአዴግ አዲስ አበባ ምን ትመስላለች? በአንድ ወቅት በተደረገ የዳሰሳ ጥናት በአዲስ አበባ በየሠፈሩ የነበሩ ከ160 በላይ የሚሆኑ መደበኛ የእግር ኳስ መጫወቻ ሜዳዎች ሙሉ በሙሉ በኮንዶሚንየም ግንባታዎች ጠፍተዋል፡፡

ሸገር ሬዲዮ እንደነገረን መርዶ ከሆነ ደግሞ ሟቹ ጠቅላይ ሚንስትር አቶ መለስ ዜናዊ የመሠረት ድንጋይ ያስቀመጡለት ከቦሌ ወደ መገናኛ በሚወስደው መንገድ ሞኤንኮ ፊት ለፊት የሚገኘው ረግረጋማውን የአድዋ ፓርክ ዕቅድ ተሠርዞ የከተማ መስተዳድሩ ኮንደሚኒየም ሊገነባበት ነው። የመረጃ ምንጮቼ እንደነገሩኝ ከሆነ 11 ሄክታር የሚሆነው የፓርኩ ቦታ ላይ 28 ባለ 12 ፎቅ ኮንዶሚኒየሞች ሊገነቡበት ነው። የተወሰነው መሬት ደግሞ ለባለሀብቶች ሊተላለፍ እንደሚችልም ሰምተናል።

በአካል ቦታው ድረስ ሄጄ እንደታዘብኩት ቦታው በቆሮቆሮ ታጥሮ የግንባታ እንቅስቃሴ ተጀምሮበታል። የዓለማችን ጥቁር ህዝቦች ድል ተደርጎ ለሚቆጠረው የአድዋ ድል መታሰቢያ እንዲሆን ቀደም ብሎ የተወሰነውን መናፈሻ ደምስሶ ኮንደሚኒየም መኮልኮል በምንም መሥፈርት ተገቢ አይመስለኝም።

ተዓምር ሊባል በሚችል ዕድል ከሊዝ ሽንሸና ያመለጡ ጥቂት የከተማዋን ክፍት ቦታዎች እያደኑ በግንባታ መሙላት ነገሩ ዘግይቶ ሲገባን እንደ እግር እሳት የሚያንገበግበንን ታሪካዊ ስህተት እየሠራን እንደሆነ ይሰማኛል። አካሄዱም እንደ አንድ ተራ ባለሙያ ዜጋ ያሳስበኛል።

በእኔ እምነት ፓርኩ ላይ ሊካሄድ የታቀደው የቤቶች ግንባታ መሠረታዊ የከተማ ፕላን እና የአከባቢ ጥበቃ ስህተት የሚያስከትል ነው። የከተማ መስተዳድሩ ውሳኔውንና በድጋሜ እንዲያጤነው እና እንዲቀለብሰው ግብር ከፋይ ዜጎች በትህትና እንጠይቃለን። እንደሚሰሙንም ተስፋ እናደርጋለን።
______________

- መልእክቱ ጠቃሚ ከመሠላችሁ Share አድርጉት
______________

#የከተማ_ፕላነሮች
#አርኪቴክቶች
#የአከባቢ_ጥበቃ_ተቆርቋሪዎች
#የዝክረ_አድዋ_ወዳጆች
#የኮንሰርቬሽን_ባለሙያዎች
I wishes a happy Ethiopian epiphany celebration for all of you who believe on salivation of soul by a single epiphany.

"Ethiopia shall soon stretch out her hands unto God."
(Psalms 68:31)
የአድዋ ጦርነት በ የካቲት ፳፫ ቀን ፲፰፻፹፰ ዓ.ም.
በኢትዮጵያና ኢጣሊያ መካከል የተካሄደ ውጊያ
ሲሆን የ አንደኛው የኢትዮጵያና ጣሊያን ጦርነት
ክፍል ነው። በ ኢትዮጵያ አሸናፊነት የጣልያን የቀኝ
ግዛት ማስፋፋት ተኮላሸ።
ምኒሊክ ተወልዶ ባያነሣ ጋሻ
ግብሩ እንቀላል ነበር ይሄን ጊዜ አበሻ፤
*
ገበየሁ ቢሞት ተተካ ባልቻ
መድፍ አገላባጭ ብቻለብቻ፤
*

የአድዋ ሥላሴን ጠላት አረከሰው
ገበየሁ በሞቴ ግባና ቀድሰው፤
የአድዋ ድል የኢትዮጵያ ብሔራዊ ክብር ማኅተም፤
የጥቁር ህዝቦች የነፃነት ተጋድሎ ቀንዲል ነው፡፡
የመላው ዓለም ተፈጥሮአዊ ግብር እና ሰብአዊ
ክብር የታደሠው፤ በእውነትና በፍትህ ህልውናና
ምልዓት ላይ የተሰካ ትልቅ ጥርስ የተነቀለው …
በአድዋ የታላቅ ህዝቦች ታላቅ ድል ነው፡፡
ከአዲስ አበባ ወደ ሰሜን ኢትዮጵያ ስንሄድ 1066
ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ ታላቁ ጦርነት የተደረገበትና
ታላቁ ድል የተገኘበት ሥፍራ አድዋ ከተማና
የከተማው ግድም ገመገሞች ይገኛሉ፡፡
በኢትዮጵያውያንካቲት 23 ቀን 1888 ዓ.ም፤ ወይም
በአውሮጳውያን የዘመን አቆጣጠር (Gregorian
Calendar) February (የካቲት) መጨረሻ እና
March (መጋቢት) መጀመሪያ ላይ 1896.
ለጦርነቱ መነሻ የሆነው ውል የተፈፀመው በዚሁ
ዘመን ከአዲስ አበባ በስተሰሜን 468 ኪሎ ሜትር
ርቀት ግድም ከውጫሌ ከተማ ግርጌ ከአምባሰል
ተራራ ሥር ወሎ ውስጥ ንጉሥ ይስማ እየተባለ
በሚጠራ ሥፍራ ነው፡፡
ሸልዶ ተራራ ወይም (ሶሎዳ ተራራ)፤ ማርያም
ሸዊቶ፤ አዲ ተቡን፤ ረቢ አርእየኒ (እግዚሃር አሳየኝ)
… በመሠኘት የሚታወቁት እነዚህ ገመገሞችና
ተራራማ ሥፍራዎች ዋነኞቹ የጦር ግንባሮች ናቸው፡፡
በመቶ ሺህ የሚሠላ የኢትዮጵያ ገበሬ ሠራዊት
ከአንድ ቀን ባልበለጠ ጊዜ ውስጥ የአውሮጳ ቅኝ
ገዢ ወራሪዎችን ድባቅ ከመታና ረግጦ ካስወጣ
በኋላ ከምሽቱ አራት ሰዓት ግድም (የካቲት 23 ቀን)
እንዳማርያም ላይ ተሰባስቦ በአንድ እግሩ ቆሞ
ቀኙን (ድሉን) ለሰጠው አምላክ ምሥጋና አቅርቧል፡፡
አባት ሆይ፤ ንቀውን የመጡ የአገራችንን ድንበርና
ልዕልና የደፈሩ የአውሮጳ ኮሎኒያሊስት ወራሪዎችን
እንድናሸንፍ (ድል እንድናደርግ) ስለረዳኸን
እናመሰግንሃለን ...
ሃያ ዘጠኝ ሺህ ፈረሰኞችን ጨምሮ ከመቶ ሺህ
እስከ መቶ ሃያ ሺህ የሚገመት አንድ ሺህ ኪሎ
ሜትር በባዶ እግሩ የተጓዘ የኢትዮጵያ የገበሬ
ሠራዊት በወታደራዊ አካዳሚ የሠለጠነውን
የአውሮጳ ወራሪ ጦር የካቲት 23 ማለዳ አሥራ አንድ
ሰዓት ግድም ገጥሞ ከረፋዱ አራት ሰዓት ላይ
ማሸነፉን አረጋግጧል ይለናል የታሪክ ተመራማሪው
ጆርጅ በርክሌይ የአድዋ ጦርነትና ዳግማዊ አፄ
ምኒሊክ በተሰኘና ዳኘው ኃይለሥላሴ ወደ አማርኛ
በተረጐሙት መጽሐፉ ላይ፡፡ የኢትዮጵያ ገበሬ
ሠራዊት ፈረሱ ላይ ሆኖ የጋሻውን እምብርት መሬት
ላይ እያጠቀሰ ጐራዴውን አየር ውስጥ እየቀዘፈ
ባበደ መንፈስ (በተቆጣና በቆረጠ መንፈሥ)
በጀግንነት ተዋግቷል፡፡
ጦርነቱ በተጀመረ ከአምስት ሰዓት ባልበለጠ ጊዜ
ውስጥ ሃምሣ ስድስቱም የኢጣሊያ መድፎች ሙሉ
ለሙሉ ተማርከዋል፤ የቅኝ ገዢውን ወራሪ ሠራዊት
ከመሩት ጀኔራሎች ጄኔራል አልቤርቶኒ ሲማረክ
የሠራዊቱ ዋና አዛዥ ጄኔራል ባራቴሪ ከጥቂት
አጃቢዎቹና በሽንፈት ከተበታተኑ የኢጣሊያ
ወታደሮች ጋር ሸሽቷል፡፡
በዚህ ድብልቅልቅ ያለ ውጊያ ከሃምሣ ስድስቱ
የኢጣሊያ መድፎች በተጨማሪ ብዙ ሺህ ቀላልና
ከባድ መትረየሶች እንዲሁም የነፍስ ወከፍ
ጠመንጃዎች በአሥር ሺሆችና በመቶ ሺዎች
ከሚቆጠሩ መሰል ጥይቶቻቸው ጋር ተማርከዋል፡፡
በአጠቃላይ ምርኮው ወደ አዲስ አበባ የተጓጓዘው
በአምስት መቶ አጋሰሶች ተጭኖ ነው፡፡
በማግስቱ የካቲት 24 ቀን 1888 ዓ.ም ከጠዋቱ
አራት ሰዓት ላይ የኢጣሊያ ምርኮኞች በምኒሊክ
ድንኳን ፊት ሲያልፉ የኢትዮጵያ ጀግና የገበሬ
ሠራዊት እየፎከረ እየሸለለ አሳልፉዋቸዋል፡፡ ጄኔራል
አልቤርቶኒ በምርኮኛነት ኢትዮጵያ ውስጥ ቆይቶ
አገሩ ከተመለሰ በኋላ በፃፈው መጽሐፍ ላይ
ከሚፎክሩት ጥቁር የነፃነት ተዋጊዎች መሃከል
አንዱ እንደ እኛው ነጭ አውሮጳዊ ነው ብሎአል፡፡
ይህ ሰው ከፈረንሣይ አገር ወደ ኢትዮጵያ ለጦር
መሣሪያ ጥገና የመጣ ካፒቴን ኦርዲናንስ ሲሆን፤
አሁን ጊዜው የጦርነት ስለሆነ ወደ አገርህ ተመለስ
ቢባል አሻፈረኝ ብሎ ከእኛ ጋር አድዋ ድረስየዘመተ ነው፡፡
ኢትዮጵያ በአድዋ ጦርነት ላይ ከተዋጋችባቸው
የጦር መሣሪያዎች ሠማንያ ሺህ የሚሆኑት አሮጌ
ጠመንጃዎች የተገዙት ከፈረንሳይ አገር በምሥጢር ነው፡፡ ጠመንጃዎቹን ገዝተው ወደ ኢትዮጵያ
ያስገቡት ለመጀመሪያ ጊዜ መኪና ወደ ኢትዮጵያ
ያስገቡት በሥጋ በደምና በትውልድ አርመናዊ
በነፍስና በመንፈስ በዜግነትና በልብ ፍቅር
ኢትዮጵያዊ የሆኑት የኢትዮጵያ የልብ ወዳጅ ሰርኪስ
ቴሪዝያን ናቸው፡፡ሺህ ጠመንጃዎቹን
አገዛዝ ሁናቴ የሚያውቁት ደግሞ ከአርሾ ቀደም
የሚሉትና ከአሥራ ስድስት ዓመታት በፊት
ለሪፖርተር ጋዜጣ ይሄንኑ በአንደበታቸው የገለፁት
አቬዲስ ቴሪዝያን ናቸው፡፡ ሠርኪስ ቴሪዝያን
ጠመንጃዎቹን ከገዙ በኋላ ወደ ኢትዮጵያ ያስገቡት
በጅቡቲ በኩል ነፋስ ባህሩን ሲያነሳና እንደ ግድግዳ
ሲያቆም በዚያ ተፈጥሮአዊ ክንውን በመጠቀም
ደብቀውና ሸሽገው ነው፡፡
የአድዋ ድል ለመጀመሪያ ጊዜ የተከበረው በሠባተኛ
ዓመቱ በ1895 ዓ.ም (እ.ኤ.አ በ1903) አሁን ጊዮርጊስ
ቤተክርስቲያን ያለበት ሥፍራ ምኒሊክ አደባባይ
ነው፡፡ በክብረ በዓሉ (በድል በዓሉ) ላይ
ዲፕሎማቶችና የውጪ አገር መንግሥታት
ተወካዮች አርበኞች የመንግስት ባለሥልጣኖች ብዙ
ሺህ ፈረሰኞችና ሥፍር ቁጥር የሌላቸው
ኢትዮጵያውያን ከሊቅ እስከ ደቂቅ መገኘታቸውን፤
ከፈረሰኞቹ ብዛት የተነሳ ፀሐይ በአቧራ እስከመጋረድ
መድረሷን ጳውሎስ ኞኞ የኢጣሊያና የኢትዮጵያ
ጦርነት በተሰኘ መጽሐፉ ላይ ጽፎአል፡፡ እንዲሁም
ተክለፃዲቅ መኩሪያን የመሳሰሉ ኢትዮጵያውያን
የታሪክ ተመራማሪዎችና የውጪ አገር ዜግነት
ያላቸው ፀሐፍትና ተመራማሪዎች በተለያዩ
መፃሕፍቶቻቸው ይሄንን አሣምረው ጽፈውታል፡፡
ታላቁ የጥቁር ህዝቦች ድል (የአድዋ ድል) በመላው
ዓለም ፖለቲካ ላይ ከፍተኛና ዋነኛ ለውጦች
አምጥቶአል፡፡ የእንግሊዝ ጋዜጦች በአድዋ ድል
ማግስት የዓለም ታሪክ ተገለበጠ ታላቅ የትውልድ
ኃይል በአፍሪቃ ተቀሰቀሰ … ብለው ፃፉ፡፡
በኢንሳይክሎፒዲያ ብሪታኒካ፡- ዘመናዊት ኢትዮጵያን
የፈጠረ የተባሉት ዳግማዊ ዓፄ ምኒሊክ በሌሉበት
(እርሳቸው በአካል ባልተገኙበት የነፃነት ተጋድሎ
መሪዎች ጉባኤ) የአፍሪቃና የመላው ዓለም ጥቁር
ህዝቦች የነፃነት ተጋድሎ መሪ ተደርገው ተመረጡ፡፡
ጦርነቱ ከመደረጉ በፊት እ.ኤ.አ በ1880ዎቹ
መጀመሪያ ጀርመን አገር በርሊን ከተማ ላይ
በተደረገው የአውሮጳ ቅኝ ገዢ (ኮሎኒያሊስት)
መንግስታት ሥልጣናትና ልሂቃን የጦር ጄኔራሎችና
ሊቃውንት ስብሰባ ላይ ጥቁር ትልቅ ትል ነው
ቅንቡርስ ነው እንጂ ነፍስ ያለው ሰው አይደለም
ብለው የነበሩ አፈሩ፤ እውነትና ፍትህ ኢትዮጵያና
አፍሪቃ ከበሩ፡፡ ከሲግመንድ ፍሮይድ የሳይኮ
አናላይሲስ ጥናትና ምርምር በፊት፡- ጥቁር ህዝብ
ትልቅ ትል ላይሆን ነፍስ ያለው ሰው ከሰውም ሰው
ጀግና መሆኑን በተጨባጭ ያስመሰከረ የኢትዮጵያ
ገበሬ ሠራዊት ነው፡፡
ከፈረንጅ የአውሮጳ መንግሥታት ሩሲያና ፈረንሳይ
የአድዋን ድል ከልብ ደገፉ፡፡ ጀኔራል ባራቴሪ በአገሩ
በኢጣሊያ ጦር ፍርድ ቤት ቀርቦ ማዕረጉ ተገፈፈ፡፡
የአገሪቱ ጠቅላይ ሚኒስትር ሲኞር ክሪስፒ
በፈቃዳቸው ሥልጣናቸውን ለቀቁ፡፡
የኢጣሊያዊው ንጉሥ አማኑኤል ኡምቤርቶ የልደት
ቀን የሀዘን ቀን እንዲሆን ተወሰነ፡፡ ሮማ (ሮም)