የሀ-በሻ ኪነ-ህንጻ ፡ Yeha-Besha Architecture
2.78K subscribers
688 photos
11 videos
56 files
139 links
The present Ethiopia is the remain of the greater Ethiopia

Follow us on facebook
#http://facebook.com/yehabesha students of architecture
Telegram @yehas

#For Your Comment or Info Use
@arcnat
Download Telegram
Forwarded from Association of Ethiopian Architecture Students(AEAS)
እስኪ አንድ እጥር ያለች ጽሁፍ እንሆ ተጋበዙልኝ ❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️ኢትዮጵያዊ አይደለሁም(ልዑል ሀይሌ)


እኔ ኢትዮጵያዊ አይደለሁም...የትኛው ባህሪዬ ነው ኢትዮጵያዊ
የሚያስብለኝ?...የትኛው ተግባሬ ይሆን ይህ ሰው ኢትዮጵያዊ
ነው የሚያስብለኝ?...ከሰው ጋር መኖር አቅቶት እየተነካከሰ
የሚኖር ሰው እንዴት ኢትዮጵያዊ ሊባል ይችላል??..በሃሜት
በጥላቻ የጠቆረ ጥቀርሻ ልብ ይዞ ኢትዮጵያዊነት ከወዴት ሊኖር
ይችላል?..ቁራሽ እንጀራ በመነጣጠቅ የተቀደሰች ህይወቱን
የሚያረክስ እንደኔ አይነት ሰው እንዴት ኢትዮጵያዊ ሊባል
ይችላል??..ኢትዮጵያዊነት እኮ የከበረ ማንነት ነው። እሺ
እናንተስ ኢትዮጵያዊ ነህ የምትሉኝ የትኛውን ጠላትን
የሚያንበረክክ የደነደነ ልብ ይዤ ይሆን?? ..እኔ ልቤንም
ቀልቤንም በቅኝ ተገዝቼ ከምድሯ ለመውጣት የማልፈነቅለው
ድንጋይ የሌለኝ የሃሳብ ሽፍታ የቱ ልብ ተርፎኝ ነው ጠላትን
የማንበረክክ?... የትኛው ክንዴ ነው ጠላትን ለማባረር ሰይፍና
ጎራዴ የሚመዝ ?.,ታዲያ እስቲ ፍረዱኝ የትኛው ነው
ኢትዮጵያዊነቴ?...አዎ ኢትዮጵያዊ አይደለሁም!!.,2 ቋንቋዎችን
መናገር ስለቻልኩ ብቻ እንዴት ኢትዮጵያዊ
ያስብለኛል??..ኢትዮጵያዊነት'ኮ የአፍ ሽንገላ ሳይሆን በተግባር
መኖርን የሚሻ የተከበረ ማንነት ነው።

ምክንያቱም
እንዳለመታደል ሆነና አባት አያቶቻችን ለሃገር ክብር ተዋድቀው፤
በደማቸው ኢትዮጵያዊነትን አድምቀው እየፃፉ፤ አንገታቸውን
እየሰየፉ ለጠላት የሃገርን ክብር አሳልፈው ላለመስጠት በገዛ
ህይወታቸው ላይ እየፈረዱ ኢትዮጵያዊነት ከሰው በላይ ነው
የሚል ትርጉም አሳምረው እየፃፉ፤ በባዶ እግር አሻራ
የኢትዮጵያዊነትን ማህተም በዓለም አደባባይ ላይ እያተሙ፤
የኢትዮጵያዊነትን ፊደል በመቅረፅ በራሷ መቆም የምትችል ሃገር
ያደረጉ በጥበባቸው ዓለምን ጉድ ያስባሉ አባት አያቶቻችን
የኢትዮጵያዊነትን ልክ አርቀው ሰቅለውት የቱን ታሪክ መድገም
ችዬ ኢትዮጵያዊ ልባል?... ኦሮሚያ የተተከለ ቡና ትግራይ
እየተጠጣ፤ አማራ የዘራው ጤፍ ጉራጌ ተቦክቶ እየተበላ፤
ትግራይ የተገኘው ወርቅ ሀረር እየተጌጠበት፤ ወላይታ የደለበ
ሰንጋ ሶማሌ ታርዶ እየተበላ የነበረው የተገመደው ማንነታችንን
አውርጄ ዘርን ከዘር የማማረጥ አባዜ የተጠናወተኝ ዘርን ከፈጠረ
ፈጣሪ ጋር በጠበበ አስተሳሰብ ግጭት ውስጥ የምገባ...ፈጣሪ
ውሃ ላይ ባፀናው ድንቅ ጥበብ ማመስገን ሲገባኝ ድንበር
እየከለልኩ የፈጣሪ ጥበብ ያቆመውን ምድር በድፍረት 'የኔ'
ማለት የተጠናወተኝ ሰው እንዴት ኢትዮጵያዊ ልባል እችል
ይሆን??...ብዙ ታሪክ ከተሰራባት ብዙ መስዋዕትነት ከተከፈለባት
ውብ ደማቅ ሰንደቅ አጠገብ ሌላ, መጠባበቂያ ሰንደቅ ከፍ
አድርጌ የምሰቅል ለሃገሬ የሰናፍጭ ያህል እምነት ያጣሁ
እንዴት ተብሎ ኢትዮጵያዊ ልባል እችላለሁ??... ከቀስተደመና
በተቀዱ ሶስት ቀለማት ይህቻት ሰንደቅህ ብሎ ባስረከበኝ አያት
ቅድመአያቴ ባወረሰኝ ትልቅ መለያ ላይ አንዴ አንበሣ ሌላ ጊዜ
ኮከብ እየለጠፍኩኝ የሰንደቄን ድምቀትና ውበት በ'አርቴፊሻል'
'ሜካፕ' ያስዋብኩ እየመሰለኝ ተፈጥሮን የማጎድፍ አዋቂ ባይ
ትዕቢተኛ እንዴት ኢትዮጵያዊ ልባል እንደምችል ሊገባኝ
አይችልም። አዎ ኢትዮጵያዊ አይደለሁም ምክንያቱም
ኢትዮጵያዊነት በዘፈቀደ የሚሰጥ ክብር አይደለም።

አያት ቅድመ
አያቶቼ ኢትዮጵያዊነትን ለማኖር፤ ለማነፅ ብዙ ሱባኤ፣ፆም፣ፀሎት
ፈጅቶባቸው በተሰጣቸው ጥበብ ተመስርተው ነው። ታዲያ
እንዴት በአፌ በመመፃደቅና እዚህች ድንቅ ሐገር ላይ በማደግ
ብቻ ኢትዮጵያዊነት ልጎናፀፍ እችላለሁ??...አዎ ኢትዮጵያዊ
አይደለሁም!!..ዓለም የሚደነቅባቸውን ቅርሶች ዞር ብዬ ሳላይ
ስለ አሜሪካ ህንፃዎች ዝርዝር ነገር ለማወቅ የመረጃ መረብ
ሳገላብጥ ውዬ የማድር የግሎባላይዜሽን አይነ-ጥላ እናት
ሃገሬን ፊቷን እንዳላየው የጋረደኝ የራስ ጠላት እንዴት ነው
ኢትዮጵያዊ ልባል የምችለው?..,አዎ ኢትዮጵያዊ አይደለሁም!!
ነገር ግን ኢትዮጵያዊ እሆን ዘንድ እና ፈጣሪ ከእውነተኛው
ኢትዮጵያዊነት ዘንድ ያገናኘኝ ፆም ፀሎት ይዣለሁ። ፈጣሪ ፈቅዶ
ፀሎት ልመናዬን ሰምቶ ከኢትዮጵያዊነት ጋር ሲያዋህደኝ ያኔ
ኢትዮጵያዊ የሚለውን ትልቅ የክብር ማዕረግ በኩራት
እቀበለዋለሁ። እስከዛው ግን ኢትዮጵያዊ አይደለሁም!!
Look below There is a Project of a First Year Architecture student which is selected by the instructors as a best work from the batch we want to share with you to judge for yourself.

Course: Basic Design ii
Project type: Museum Design for Hominids Species
Location :Near to Addis Ababa Stadium
Credit for : Jonathan fikru

Give your thumbs up 👍 if you like the design
👏👏👏#Lets Appreciate Our Students.👏👏👏

Look below There is another Project of a First Year Architecture student which is selected by the instructors as a best work from the batch.

Course: Basic Design ii
Project type: Museum Design (Capra Jesus)
Location :Near to Addis Ababa Stadium
Credit for : Abel Tadesse

Give your thumbs up 👍 if you like the design.
............Join for more👉👉👉 @yehas......
👏👏👏#Lets Appreciate Our Students.👏👏👏

They are a First Year Arch Students...they are Starting the Big Journey Of the Architecture Field So lets take a moment and Appreciate Them.🙏

Look below There is another Project of a First Year Architecture Student 2018 G.C( 2010 E.C).

Course: Basic Design ii
Project type: Information Center
Client: Individual
Site Location : Anwar
Credit for : Selam Werede (EIABC Lideta Campus)

Give your thumbs up 👍 if you like the design.
............Join for more👉👉👉 @yehas......
❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️💛💛💛💛💛💛💛💛💛💚💚💚💚💚💚💚💚💚💚💚💚💚
these all were belongs to us🖕🖕🖕🖕
but u know what the black panters did
👆👆👆👆👆👆