Abiy Ahmed Ali 🇪🇹
✔
187K subscribers
10.2K photos
550 videos
80 links
ነጻነት ለህዝባችን - ብልጽግና ለአገራችን!

Bilisummaan uummata keenyaaf - badhaadhinni biyya keenyaaf!

Freedom to our People – Prosperity to our Nation!
Download Telegram
በሞስኮ እየተካሄደ በሚገኘው 3ኛው የሩሲያ-አፍሪካ ጉባኤ ላይ በመገኘት መልዕክቴን ማስተላለፍ በመቻሌ ታላቅ ደስታ ይሰማኛል። በዚህ ታሪካዊ መድረክ የምናሳልፋቸው ውሳኔዎች ተጨባጭ ውጤት እንዲያስመዘግቡ የጋራ ቁርጠኝነት እና ትብብር እጅግ አስፈላጊ ነው።
ኢትዮጵያ ለዘላቂ ብልጽግናዋ እና ለሀገራዊ እድገቷ መሰረት በሆኑ ሶስት ቁልፍ ምሰሶዎች ላይ ትኩረት አድርጋ እየሰራች ትገኛለች። እነዚህም በምግብ ዋስትና እና ምርታማነት፣ በአስተማማኝ የኃይል አቅርቦት፣ እንዲሁም በክህሎት እና በዕውቀት ሽግግር ላይ የሚከናወኑ ተግባራት ናቸው።
የኢትዮጵያ እና የሩሲያ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ከአንድ ክፍለ ዘመን በላይ ያስቆጠረ፣ በመከባበር እና በጋራ ተጠቃሚነት ላይ የጸና ታሪካዊ ወዳጅነት ነው። ይህንን ወዳጅነት ይበልጥ ወደ ላቀ ደረጃ ለማሸጋገር ከሩሲያ ጋር በጋራ በመሆን ዓለም አቀፍ ደረጃውን የጠበቀ የኒውክሊየር ኃይል ማመንጫ ለመገንባት የሚያስችሉ ተግባራትን በቁርጠኝነት እያከናወንን እንገኛለን። ይህ ስትራቴጂካዊ ትብብር የኃይል አማራጮቻችንን ከማስፋት ባለፈ የሀገራችንን የብልጽግና ጉዞ በእጅጉ የሚያፋጥን እንዲሁም የሁለቱ ሀገራት ትስስር ከምንጊዜውም በላይ የሚያጠናክር ይሆናል።
ዛሬ የመጀመሪያዎቹ 26 የከተማ አውቶብሶች ከነዳጅ ወደ ተፈጥሮ ጋዝ ተለውጠው ሥራ ላይ በመዋላቸው የተሰማኝን ደስታ መግለጽ እፈልጋለሁ።

ባለፉት ጥቂት ወራት የተፈጥሮ ጋዝ ምርትን ከሚመረትበት ስፍራ ወደ አዲስ አበባ የማጓጓዝ፣ የጋዝ ማደያዎችን የማዘጋጀት እና የከተማ አውቶብሶችን ወደ ተፈጥሮ ጋዝ የመለወጥ ሰፊ ሥራዎች ሲከናወኑ ቆይተዋል። ይህ ታሪካዊ እርምጃ በነዳጅ ግዢ ላይ የሚወጣውን ከፍተኛ የውጭ ምንዛሬ በከፍተኛ ደረጃ ያስቀራል። በተጨማሪም የሕዝብ ትራንስፖርት የሥራ ማስኬጃ ወጪን በመቀነስ የዜጎችን የጉዞ ታሪፍ በግማሽ ያቃልላል። በነዳጅ የሚሰሩ ተሽከርካሪዎችን በራስ አቅም ወደ ተፈጥሮ ጋዝ የመለወጡ ተግባር ደግሞ የሀገር ውስጥ አቅምንና የቴክኖሎጂ ሽግግርን በተግባር ያረጋገጠ ነው።

በቀጣይም በነዳጅ ላይ ያለንን ጥገኝነት ሙሉ በሙሉ ለማስቀረት እና ሀገር ውስጥ እያመረትን ያለነውን የተፈጥሮ ጋዝ በስፋት ጥቅም ላይ ለማዋል የሚያስችሉ 400 አዳዲስ በተፈጥሮ ጋዝ የሚሰሩ አውቶብሶች በቅርቡ ወደ ሀገር ውስጥ ይገባሉ። በምግብ፣ በቤት እና በትራንስፖርት ዘርፎች ላይ ተጨባጭ ሥራዎችን በማከናወን በዜጎች ሕይወት ላይ መሠረታዊ ለውጥ ለማምጣት የተጀመሩት አበረታች ጥረቶች ተጠናክረው ይቀጥላሉ።
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
በተፈጥሮ ጋዝ የሚሰሩ አውቶብሶች፤ የኢትዮጵያ አዲሱ የትራንስፖርት ምዕራፍ!