Daily News Ethiopian 🇪🇹🔵
5.26K subscribers
7.63K photos
164 videos
3 files
130 links
Daily News Ethiopian 🇪🇹🔵
🇪🇹ኢትዮጵያ
አዳዲስ መረጃዎች እንዲደርስዎ ቤተሰብ ይሁኑ
Daily News Ethiopian 🇪🇹🔵
@Daily_News_Ethiopian
Download Telegram
እኚህ ወጣቶች በጭነት ተሽከርካሪ የኢትዮጵያን ድንበር አቋርጠው ወደ ጅቡቲ ለመግባት ሲሞክሩ በአፋር ፖሊስ የተያዙ ናቸው።ባለፈው ወር በተሳቢ መኪና ወደ ስደት ሲጓዙ የነበሩ ወጣቶች በሰመራ ከተማ በደረሰ አሰቃቂ የትራፊክ አደጋ ከመቶ ወጣቶች የ22ቱ ሕይወት ማለፉ ይታወሳል።
ከሟቾች በተጨማሪ 65 ሰዎች ላይ ቀላልና ከባድ ጉዳት እንደደረሰ አይዘነጋም።ስለምን ከዛ አሳዛኝ አጋጣሚ እንኳን መማር አልተቻለም?
​​@Daily_News_Ethiopian
❤1
በኤሌክትሪክ መሰረተ ልማት ላይ ስርቆት ሲፈጽም የተገኘ ግለሰብ በቁጥጥር ስር ዋለ

በአማራ ክልል ደቡብ ጎንደር ዞን በነፋስ መወጫ ኃይል ማከፋፈያ ጣቢያ 33 ኪ.ቮ ወጪ መስመር ተሸካሚ የብረት ምሰሶ ላይ ስርቆት ሲፈፅም የነበረ ግለሰብ የአካባቢው የፀጥታ ኃይል ከህብረተሰቡ ጋር ባደረገው ክትትል በቁጥጥር ስር ሊውል ችሏል፡፡

መካከለኛ መስመሩ ለነፋስ መውጫ ከተማ ውሃ አገልግሎት፣ ለታች ጋይንት፣ ለክምር ድንጋይ እና አካባቢው አገልግሎት የሚሰጥ መጋቢ መስመር ነው፡፡

የባህርዳር ሪጅን ከአካባቢው መስተዳድር አካላት ጋር ባደረገው ውይይት እና የአካባቢው የፀጥታ አካላቱም ባደረጉት ክትትል ከህገ ወጥ ግለሰቦች መካከል አንዱን ግለሰብ የነፋስ መውጫ ፖሊስ በቁጥጥር ስር አውሎ ምርመራ እያካሄደ መሆኑ ተገልጿል፡፡

መረጃው ከኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልገሎት የተወሰደ ነው።

​​@Daily_News_Ethiopian
❤1
የአሁን አጫጭር መረጃዎች
• ዛሬ ጠዋት እስራኤል በተለያዩ የጋዛ አካባቢዎች በፈጸመችው ጥቃት ሁለት ሕፃናትን ጨምሮ ቢያንስ 10 ፍልስጤማውያን ተገድለዋል።
• በሰሜን ጋዛ አንድ የእስራኤል ወታደር መቁሰሉን የእስራኤል ጦር አስታውቋል።
• የሂውማን ራይትስ ዎች (Human Rights Watch) የእስራኤል እና ፍልስጤም ዳይሬክተር ኦማር ሻኪር እና ረዳት ተመራማሪ ሚሌና አንሳሪ ድርጅቱ ያዘጋጁትን ሪፖርት በማገዱ ምክንያት ሥራቸውን በገዛ ፈቃዳቸው ለቀዋል። ተመራማሪዎቹ እንደገለጹት፤ ድርጅቱ ያገደው ሪፖርት እስራኤል የፍልስጤም ስደተኞችን የመመለስ መብት መከልከሏን "በሰብአዊነት ላይ የተፈጸመ ወንጀል" ሲል የሚፈርጅ ነበር።
• ማክሰኞ ምሽት እስራኤል በተያዘው የዌስት ባንክ ኢያሪኮ (Jericho) ከተማ ላይ በፈጸመችው ወረራ አንድ ፍልስጤማዊ ሲገደል፣ ሦስት ደግሞ ቆስለዋል።
​​@Daily_News_Ethiopian
❤2
በፌደራል መንግስት እና በህወሓት መካከል በፕሪቶሪያ የተፈረመውን ግጭት የማቆም ስምምነት አተገባበር የሚከታተለው የባለሙያዎች ቡድን፤ ከ“እረፍት በኋላ” ዳግም ለስራ መሰማራቱን የአፍሪካ ህብረት የፖለቲካ ጉዳዮች፣ ሰላም እና ጸጥታ ቢሮ አስታወቀ። የባለሙያዎች ቡድኑ የስምምነቱን አፈጻጸም የመከታተል “ወሳኝ ተግባራቸውን” እንደገና ጀምረዋል ብሏል።

የአፍሪካ ህብረት የፕሪቶሪያውን የግጭት ማቆም ስምምነት አፈጻጸም የመከታተል እና የማረጋገጥ ኃላፊነት የተሰጠውን ተልዕኮ ይፋ ያደረገው በታህሳስ 2015 ዓ.ም ነበር።

በዚህ ተልዕኮ ስር የተካተቱ ከኢትዮጵያ፣ ኬንያ፣ ናይጄሪያ እና ደቡብ አፍሪካ የተውጣጡ 21 ወታደራዊ እና የሲቪል ባለሙያዎች ኃላፊነታቸውን ሲወጡ ቆይተዋል።

ባለሙያዎቹ ቁጥጥር ከሚያደርጉባቸው ሂደቶች መካከል በውጊያ ሲሳተፉ የነበሩ ኃይሎች ትጥቅ መፍታት፣ እንዲበተኑ ማድረግ እና ከህብረተሰቡ ጋር መልሶ ማዋሃድን የሚመለከተው አንዱ ነው።

ከቀዬአቸው የተፈናቀሉ ሰዎች መልሶ ማስፈር፣ የኢኮኖሚያዊ እና ማህበራዊ አገልግሎቶች ዳግም መጀመር፣ የሰብአዊ እርዳታ አቅርቦትን ማመቻቸት እና የሰላማዊ ሰዎችን ደህንነት ማስጠበቅን የተመለከቱ ጉዳዮችም ባለሙያዎቹ የመከታተል ኃላፊነት ተጥሎባቸዋል።

እነዚህን ጉዳዮች ለመከታተል በትግራይ ክልል ተሰማርቶ የቆየው የአፍሪካውያን የባለሙያዎች ቡድን፤ “የአስተዳደር እረፍት” ወስዶ እንደነበር የአፍሪካ ህብረት የፖለቲካ ጉዳዮች፣ ሰላም እና ጸጥታ ቢሮ ዛሬ ባሰራጨው መረጃ አመልክቷል።

የባለሙያዎቹ ቡድኑ ከእረፍት በኋላ በዛሬው ዕለት ወደ ስምሪት መመለሱን ቢሮው በፎቶዎች አስደግፎ አስታውቋል።
@Daily_News_Ethiopian
❤2
የትግራይ ክልል ድጋፍ ወደማሰባሰብ ገብቷል።እስከዛሬ ለህውሃት ሚሊየን ዶላሮችን ሲያግዝ የኖረው ዲያስፖራ ምላሽ አለመስጠቱ ተሰምቷል።

ገቢው ለትግራይ አርበኞች ህክምና፣ ለተፈናቀሉ ሰዎች ወደ አገራቸው ለመመለስ እና የትግራይን መልሶ ለማቋቋም ይውላል ብሎ የኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮው መግለጫ ቢያወጣም ዞሮ ዞሮ ለጦርነት መሆኑ ስለታወቀ ነገሩ በዝምታ እየታየ መሆኑ ተነግሯል።

ለድጋፍ ይፋ የሆኑትን አካውንቶች በልዩ ሁኔታ የሚከታተል ከመንግስት የሰው ኃይል መመደቡ ተሰምቷል።

በተቀራረበ መረጃ የሀገር መከላከያ ሰራዊቱ ወደ ኤርትራ ድንበር ጉዞ መጀመሩን ተከትሎ ተንቤ ድረስ ገብቶ እንደነበር የተነገረለት የኤርትራ ሰራዊት ወደ ኋላ ማፈግፈጉ ታውቋል።ውጥረቱ ከመቸውም ጊዜ በላይ ጨምሯል ነው የተባለው።
ሠላምን ለህዝባችን:ሠላም ለሀገራችን‼
​​
❤4
በትግራይ ድንበሮች ላይ ወታደራዊ እንቅስቃሴ አለ መባሉ

የኢትዮጵያ ፌደራል መንግሥት ወታደሮች እና የትግራይ ኃይሎች በትግራይ ክልል ድንበሮች ላይ ተከማችተዋል ሲል የፈረንሳዩ የዜና አገልግሎት ዘግቧል።

ዶቼ ቬለ ያነጋገራቸዉ የትግራይ ፖለቲካ ተንታኞች እንደሚሉት በትግራይ ወጥረቱ አይሏል። በትግራይ ድንበሮች ላይ ወታደራዊ እንቅስቃሴ አለ፤ ሕዝቡ ሰላሙ እንዲጠበቅ አስፈላጊዉን ጫና ማድረግ ይገባዋል።
የኢትዮጵያም የኤርትራም ጦር ተንቀሳቅሷል!

መነሻውን ባሕርዳር ያደረገ ከፍተኛ ቁጥር ያለው የመከላከያ ኃይል ወደ ትግራይ አዋሳኝ መንቀሳቀሱን ብሉምበርግ ዲፕሎማቶችን ዋቢ አድርጎ ዘግቧል። ከኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት ባለፈ የኤርትራ ጦርም ከፍተኛ ቁጥር ያለው ጦሩን አስጠግቷል ብሏል።

በሁለቱ አገራት መሐል ጦርነት የመቀስቀሱ እድል ከእለት ወደ እለት እየሰፋ ሲሆን፤ ዲፕሎማቶች እና አገራት ግጭት እንዳይቀሰቀስ ጥረቶችን እያደረጉ መሆኑ ታውቋል።
❤5
ሠልፍ‼

ትግራይ ክልል ከየካቲት 20 ጀምሮ ሰልፍ እንደሚካሄድ ተሰምቷል።

ሰልፉ ግዛት ይመለስልን የሚል እንደሆነም ተዘግቧል።

ከሰሞኑ የፌዴሬሽን ምክር ቤት በአማራ እና ትግራይ ክልሎች መካከል "የይገባኛል" ጥያቄ የሚየሳባቸው አምስት የምርጫ ክልሎች ላይ ውሳኔ ማሳለፉን የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ አሳውቆ ነበር።

ይህንኑ መረጃ ተከትሎ የፌደሬሽን ምክር ቤት ጻፈልኝ ባለው ደብዳቤ መሰረት አከራካሪ ሆነው የቆዩት፦
📌 የሁመራ፣
📌አዲረመፅ፣
📌 ኮረም አፍላ፣
📌ጠለምት እና
📌ራያ አላማጣ የሚገኙ የምርጫ ክልሎች
ከትግራይ ክልል ውጭ ሆነው ለብቻቸው ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ምርጫ እንዲደረግ መወሰኑን ቦርዱ ገልጿል።ይህ ውሳኔ ለህውሃት ትልቅ መነቃቃት እንደፈጠረለት ተነግሯል።በመላው ትግራይ ሰልፍ ለማካሄድ መዘጋጀቱን ዛሬ አሳውቋል።
​​
❤19🙏3
• የአርሲ ዞን ሽርካ ወረዳ ጭፍጨፋ

"…በአርሲ ዞን ሽርካ ወረዳ ቢርቦና ጮሌ ቀበሌ በሚገኙ ኦርቶዶክሳውያን áˆ‹á‹­ የኦሮሚያ እስላሚክ እስቴት ታጣቂዎች ናቸው በተባሉ በኦሮሞ አክራሪ የወሀቢያ እስላም ታጣቂዎች በዘግናኝ ሁኔታ ተጨፍጭፈዋል። የክርስቲያኖቹ ሀብት እና ንብረት በሙሉ ወድሟል።

"…እነዚህ የኦሮሚያ እስላሚክ እስቴት ታጣቂ የኦሮሞ የወሀቢይ እስላም ታጣቂዎች እስልምና ታጣቂዎች ይሄን መጠነ ሰፊ አደገኛ ጥቃት ትናንት ለዛሬ ንጋት ከ10:00 ሰዓት ጀምረው እስከ ከቀኑ 6:00 ሰዓት ድረስ በማያባራ መልኩ ጭፍጨፋውን የፈጸሙ ሲሆን እስከአሁን ከ100 በላይ የሸዋ ኦሮሞ ኦርቶዶክሳውያን እና ዐማራ ኦርቶዶክሳውያን ተለይተው ለዘር እንዳይተርፉ ተደርገው ተጨፍጭፈዋል።

"…በጭፍጨፋው እስካሁን የተረጋገጠ ወደ 56  የሚደርሱ የኦርዶክሳውያን አስከሬን የተሰበሰበ ሲሆን በጫካ፣ በማሳ ውስጥ የታረዱት ተለቅመው እስኪታወቅ ድረስ ቁጥራቸው ይሄ ነው ተብሎ ለመግለጽ ያስቸግራል ነው የሚሉት ጉዳዩን በዚያው ሆነው በቅርብ እየተከታተሉ የሚገኙት የመረጃ ምንቼ።

"…ለጊዜው 35 ኦርቶዶክሳውያን የተዋሕዶ ልጆች በኦሮሞ የወሀቢያ እስላሞቹ የታረዱት ምስኪኖች በቅዱስ ሩፋኤል ቤተ ክርስቲያን፣ 3 ኦርቶዶክሳውያን በጠሬታ ቅዱስ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን በአንድ ጉድጓድ በነጠላ ተጠቅልለው መቀበራቸውን የደረሰኝ የቪድዮ ማስረጃ ያመለክታል። ቁጥራቸው በውል ያልታወቀ ቆስለዋል ደግሞ ቆስለው፣ በጎቤሣ ሆስፒታል መግባታቸውም ተሰምቷል። 

"…ጥቃት አድራሾቹ የኦሮሚያ እስላሚክ እስቴት ታጣቂዎቹ የኦሮሞ ወሀቢያ እስላሞቹ ጨፍጫፊዎች በሽርካ ወረዳ ብቻ የሚንቀሳቀሱ ሳይሆኑ፣ ከባሌ ዞን የዋቤን ወንዝ አቋርጠው እንዲሁም ከሆንቆሎ ዋቤ እና ከሮቤ ዲደዓ የተሰባሰቡ አክራሪ የእስልምና ታጣቂዎች መሆናቸውም ታውቋል። በወረዳው መቀመጫ በሆነችው ጎቤሣ ከተማ የሚገኙ ኦርቶዶክሳውያን በወገኖቻቸው ላይ እየተፈጸመ ያለውን ጥቃት በመጥቀስ ለወረዳው ፖሊስ እንዲደርሱላቸው ቢያሳስቡም ነገር ግን ከወረዳው የጸጥታ አካላት በኩል "ጥፉ ከዚህ ትዕዛዝ አልተሰጠንም" የሚል ምላሽ እንደተሰጣቸው ነው የተሰማው።

"…ቆይተውም ብዙ ኦርቶዶክሳውያን ማለቃቸውን ካረጋገጡ በኋላ ነው የወረዳው ታጣቂዎች ለይምሰል  ወደ አከባቢው ያቀኑ ሲሆን አከባቢው ላይ ደርሰውም አክራሪዎቹ ላይ ጥቃት መውሰድ ሳይችሉ ጥጋቸውን ይዘው እየተሳሳቁ መቆማቸው ነው የተነገረው። በጉዳዩ ግራ የተጋቡ ዜጎች የክልሉን የፀጥታ ኃይሎች ምንድነው የምትጠብቁት? ሕዝብ እኮ እያለቀ ነው? ለምንድነው በአሸባሪዎቹ ላይ እርምጃ የማትወስዱት በማለት ሲጠይቋቸውም "ከ በላይ አካላት ማንም ላይ እንዳትተኩሱ የሚል ትእዛዝ ታዘናል፣ ስለዚህ ምንም ልንረዳችሁ አንችልም" እንዳሏቸውም ተሰምቷል።

"…የጸጥታ ኃይሎቹ  ከዚያው ቅርብ ቦታ ላይ ሆነው የታጠቁ መስሊም ገበሬዎች ሳይቀር መስጊድ ውስጥ ሆነው ወደ ኦርቶዶክሳውያን ሲተኩሱ የነበሩትን እያዩ እሺ እነዚህን እንኳ አስቁሟቸው ተብለው ቢጠየቁም ፈቃደኛ ሳይሆኑ ቀርተው ብዞዎች ከአንድ ቤተሰብ ስምንት እና ዘጠኝ ሰው በተኛበት በኦሮሞ አክራሪ እስላሞች እንደበግ ታርዷል። ይህ ጥቃት ከመፈጸሙ በፊት በዕለተ ረቡዕ (ጥቅምት 11/2019ዓ.ም) የሪጴ ሎላው አዛዥ ወደ ዞኑ የጸጥታ ኃይል ደውሎ"በሽርካ ወረዳ ሸኔ (ሸኔ የሚለው አክራራውን ቡድን ነው) የሚባል የለም ጠፍቷል። አሁን ያለው ሙስሊሞችን የሚገድለው የኦርቶዶክሱ አማጺ የሆነው ፋኖ ነው። እሱን መምታት ያስፈልጋል" እያለ ሪፖርት ሲያደርግም ተደርሶበታል። ሪፓርቱ በተደረገ በሁለተኛው ቀን ላይ ሁለት ቅጥቅጥና አንድ ፓትሮል ሪጴሎላ ወደ ወረዳው ገባ። ያ ሪጴ ሎላ ነው ኦርቶዶክሳውያን አድኑን ሲሏቸው "አልተዘዝንም" እያለ ቆሞ ያሳረደው።

"…ይኽ በእንዲህ እንዳለ በዚሁ ወረዳ በሶሌ ጉና ቀበሌ  ባሉት ኦርቶዶክሳውያን ላይ ጥቃት ተከፍቶ  የመድኃኔዓለም ቤተ ክርስቲያን በአክራሪዎቹ ጥቃት ደርሶበት ጥበቃውም ተገድሏል። በአከባቢው ላይ ያሉ ኦርቶዶክሳውያን እየተሰደዱ ይገኛሉ። ይኽ ሁሉ ጥቃት ሲፈጸም ሪጴ ሎላ ቻይና ካምፕ የሚባል ስፍራ ላይ  ሰፍሮ በዝምታ ይመለከት ነበር።

"…ከላይ በወረደ ትእዛዝ መሠረት ከአካባቢው አንድም የሚወጣ ሰው፣ በሕይወት የሚተርፍ እንዳይኖር። ስትገድሉ አቁስላችሁ ነካክታችሁ እንዳትተዉ። ጨርሷቸው፣ ልጅ ሕፃን፣ ሴት፣ ነፍሰጡር፣ ሽማግሌ፣ አሮጊት፣ ወጣት ሴት በ ላችሁ መርጣችሁ አትተዉ። አትራሩላቸው የሚል ትእዛዝ ገዳይ አራጆቹ እንደተቀበሉም ተሰምቷል። አሁን የወረዳው ዋና ከተማ በሆነችው በጎቤሣ የጸጥታ አካላት ኦርቶዶክሳውያንን  እያገቱ ይገኛሉ። ወደ ወረዳው የሚያስገቡ መንገዶች  ተዘጋግተዋል። አስቀድመው መኪኖች እንዳያልፉባቸው ተቆፋፍረው እንዲበላሹ ተደርገዋል።

• ቤተ ክህነት    ~ ዝም ጭጭ።
• መንግሥት     ~ ዝም ጭጭ
• ኢትዮጵያውያን ~ ዝም ጭጭ
• መከላከያው ~ ዝም ጭጭ
• ፌደራል ፖሊስ~ ዝም ጭጭ
• የክልሉ ፖሊስ ~ ዝም ጭጭ
• ሚዲያዎች ~ ዝም ጭጭ
• አክቲቪስቶች ~ ዝም ጭጭ
❤3