EBC (Ethiopian Broadcasting Corporation)
✔
132K subscribers
45.6K photos
484 videos
80 files
13.7K links
EBC (Ethiopian Broadcasting Corporation) @etvafaanoromoo1
@ETVkidschannel
@EBCWORLD1
@etventertainment1
Download Telegram
አደይ አበባ ስታዲየም: የኢትዮጵያ እግር ኳስ ተስፋ እና የ2028 የአፍሪካ ዋንጫ ራዕይ

ኢትዮጵያ በስፖርቱ መስክ፣ በተለይም በእግር ኳስ የቀድሞ ገናና ስሟን ለመመለስና የአፍሪካ የስፖርት ማዕከል ለመሆን የምታደርገው ጥረት አዲስ ምዕራፍ ላይ ደርሷል::

በአዲስ አበባ ተመርቆ ለሕዝብ ክፍት የሆነው፤ ከቦሌ መድኃኔዓለም በጎላጉል እስከ እንግሊዝ ኤምባሲ፣ ከቦሌ መድኃኔዓለም እስከ ሞኤንኮ፣ ከቦሌ ትምህርት ቤት እስከ አደይ አበባ ሞዴል መንደር፣ ከኢምፔሪያል ሆቴል እስከ ሻላ ፓርክ፣ ከቺቺኒያ እስከ ቦሌ ሩዋንዳ፣ ከአደይ አበባ ስታዲየም እስከ ቦሌ መንገድ እንዲሁም የውስጥ ለውስጥ መንገዶችን የሚያጠቃልለው እና በአጠቃላይ 57 ሄክታር የሚሸፍነው ዘመናዊ የኮሪደር ልማት ከከተማ ውበት ባሻገር ለኢትዮጵያ ስፖርት መሠረተ ልማት ትልቅ አቅም መፍጠሩን አሳይቷል
❤7🔥3
በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የተመረቀው ኮሪደር ውስጥ የለሙ ተቋማት:-

👉🏽2 የትምህርት ቤት ግንባታና ማስፋፊያ
👉🏽2 የፖሊስ ጣቢያ ግንባታና ማስፋፊያ
👉🏽1 የቱሪስት መረጃ ማእከል
❤9👏6
በመዲናዋ የኮሪደር ልማት ያሳየው ዕምቅ አቅም

አዲስ አበባ ከጊዜ ወደ ጊዜ ተጨማሪ ውበትና ግርማ ሞገስ የሚያላብሷትን አዳዲስ የልማት ሥራዎች እያስመረቀች የከተማዋን ገጽታ በፍጥነት እየቀየረች ትገኛለች::

ይህ የለውጥ ጉዞ በትናንትናው ዕለት በይፋ በተመረቀው 3ኛው ዙር የኮሪደር ልማት አማካኝነት ዳግም በተጨባጭ ታይቷል
🙏4
የአረንጓዴ ዐሻራ ስኬት ኢትዮጵያን የቀጣናው የስበት ማዕከል አድርጓታል

ኢትዮጵያ ባለፉት ዓመታት በአረንጓዴ ዐሻራ መርሐ ግብር ያከናወነቻቸው አመርቂ ሥራዎች እና ያሳየቻቸው ተጨባጭ ውጤቶች የቀጣናው የስበት ማዕከል እንድትሆን አስችሏታል::

ዓለም አቀፍ ጉባኤዎችን፣ ግዙፍ ኮንፈረንሶችን እና ዲፕሎማቲክ መድረኮችን በስኬት ማስተናገድ የዝግጅት አቅም ማሳያ ብቻ አይደለም፤ የተቋማዊ ብቃት እና የዓለም አቀፍ እምነት ትልቅ መገለጫም ነው
❤7👏3
ለ4 ዓመታት በሆድ እብጠት ስትሰቃይ የነበረች ታካሚ 10.5 ኪ.ግ የሚመዝን እጢ በቀዶ ሕክምና ተወገደላት

በሰቆጣ ከተማ በሚገኘው የተፈራ ኃይሉ መታሰቢያ ጠቅላላ ሆስፒታል 10.5 ኪሎ ግራም የሚመዝን እጢ በተሳካ የቀዶ ሕክምና ማስወገድ መቻሉ ተገለፀ፡፡
በሰቆጣ ከተማ ነዋሪ የሆነችው የ30 ዓመት ታካሚ ላለፉት አራት ዓመታት በሆድ እብጠት ስትሰቃይ የቆየች ሲሆን፣ በሆስፒታሉ የማህፀንና ፅንስ ሕክምና ስፔሻሊስት ዶክተር ዋሲሁን በሚመራ የሰባት የሕክምና ባለሙያዎች ቡድን ውጤታማ የቀዶ ሕክምና ተደርጎላታል::

በዚህም 10.5 ኪሎ ግራም የሚመዝነውን እጢ ሙሉ በሙሉ ማስወገድ የተቻለ ሲሆን፣ ታካሚዋ በአሁኑ ወቅት ወደ ማገገሚያ ክፍል ተዛውራ በሐኪሞች የቅርብ ክትትል ሥር ትገኛለች
❤15🙏6👏3
"የኒውክሌር ጦርነት አሸናፊ የለውም፤ ፈጽሞም መካሄድ የለበትም" - የሦስቱ መሪዎች ታሪካዊ መግለጫ

የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ፣ የሩሲያው አቻቸው ቭላድሚር ፑቲን እና የቻይናው ፕሬዚዳንት ሺ ጂንፒንግ ባካሄዱት ታሪካዊ የሦስትዮሽ ውይይት ማጠቃለያ ላይ የጋራ የሰላም መግለጫ አውጥተዋል::

የሦስቱ ልዕለ-ኃያላን ሀገራት መሪዎች በደቡብ ምሥራቅ ቻይናዋ ሼንዠን ከተማ እየተካሄደ ከሚገኘው የእስያ-ፓስፊክ የኢኮኖሚ ትብብር (APEC) ጉባኤ ጎን ለጎን ለ90 ደቂቃዎች ያህል ዝግ ውይይት አድርገዋል
❤37🔥8🙏3🕊3🤣2
የኢትዮጵያ የአረንጓዴ ኢኮኖሚ ምህዳር ለባለብዙ ዘርፍ ተጠቃሚነት

አስተማማኝ የኃይል አቅርቦት በዘመናችን የሀገራት የኢንቨስትመንት፣ ኢንዱስትሪ ዕድገት፣ አየር ንብረት ለውጥ መቋቋም ወሳኝ ሚና ይጨዋታል::

ብዙ አዳጊ ሀገራት ለነዳጅ ግዥ ከፍተኛ የውጭ ምንዛሪ በማውጣት፣ በዓለም አቀፍ የነዳጅ ዋጋ መዋዠቅ እና በአቅርቦት ሰንሰለት መስተጓጎል ተጋላጭ ሲሆኑ ይስተዋላል
🙏4❤2👍1
የብሔራዊ ጥቅም እና የሉዓላዊነት ጉዳይ የሆነው ባሕር በር

ለኢትዮጵያ የባሕር በር ጉዳይ ከዘላቂ ኢኮኖሚያዊ ዕድገት፣ ከብሔራዊ ጥቅም፣ ከሉዓላዊነት እና ከትውልድ ተሻጋሪ ብልጽግና ጋር በጥብቅ የተሳሰረ ስትራቴጂያዊ አጀንዳ ነው::

ኢትዮጵያ በአፍሪካ ከሕዝብ ብዛት ቀዳሚ ከሆኑ ሀገራት አንዷ ብትሆንም የባሕር በር አልባ መሆኗ በወጪ ንግድ፣ በትራንስፖርትና በዓለም አቀፍ የኢኮኖሚ ትሥሥሯ ላይ ከፍተኛ ጫና ፈጥሯል
❤3🔥2👍1
የኢትዮጵያን ኢኮኖሚ መልክ የሚቀይሩት አምስቱ ግዙፍ ሜጋ ፕሮጀክቶች

በኢትዮጵያ የኢኮኖሚ ማሻሻያ ጉዞ ውስጥ ወሳኝ ምዕራፍ የሚከፍቱ አምስት ታላላቅ ሜጋ ፕሮጀክቶች በከፍተኛ ፍጥነት እየተገነቡ ይገኛሉ::

ከ22 ቢሊዮን ዶላር በላይ በጀት የተያዘላቸው የቢሾፍቱ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ፣ የጎዴ ማዳበሪያ ፋብሪካ፣ የኮይሻ የኃይል ማመንጫ ግድብ፣ የአዋሽ-ወልዲያ-ሐራ ገበያ ባቡር መስመር እና የጎዴ ነዳጅ ማጣሪያ በአቪዬሽን፣ በኬሚካል፣ በንጹሕ ኃይል እና በትራንስፖርት ዘርፎች ዘላቂ የኢኮኖሚ መሠረት ለመጣል ያለሙ ናቸው
❤24👏7🔥2
ቅርስ፣ ተፈጥሮ እና ባህል የተሳሰሩባት ነቀምቴ ከተማ

ነቀምቴ ከአዲስ አበባ በስተ ምዕራብ 328 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ የምትገኝና በ1830 ዓ.ም በደጃዝማች ሞሮዳ በከሬ የተቆረቆረች ጥንታዊ ከተማ ናት::

በአሁኑ ወቅት እየተከናወነላት ባለው የኮሪደር ልማት ውበቷ ይበልጥ ጎልቶ፣ ለኑሮና ለኢንቨስትመንት ምቹ እየሆነች ትገኛለች
❤5👍2
የአፍሪካን የታክስ ፍትሃዊነት የሚያረጋግጥ መድረክ በአዲስ አበባ እየተካሄደ ነው

አፍሪካ የራሷን ሀብት ለራሷ ልማት የምታውልበትን አዲስና ፍትሃዊ የታክስ ሥርዓት ዕውን ለማድረግ የሚያስችል መድረክ በአዲስ አበባ እየተካሄደ ነው::

ከመቶ ዓመታት በላይ በ38 የበለጸጉ ሀገራት ብቻ ሲዘወር የቆየውን ዓለም አቀፍ የታክስ ሥርዓት በመቀየር፣ ታዳጊ ሀገራት በዓለም አቀፍ የኢኮኖሚ ውሳኔዎች ላይ ተመልካች ሳይሆኑ ወሳኝ የሚሆኑበት አዲስ የታክስ ትብብር ማዕቀፍ እየተዘጋጀ ይገኛል
❤7👍5
ታላቁ ሩጫ ከጎዳና ሩጫ የተሻገረ ትርጉም ያለው ወሳኝ ስፖርታዊ ኩነት ነው - የባህልና ቱሪዝም ሚኒስትር ሰላማዊት ካሳ

26ኛው ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ 10 ኪሎ ሜትር የሩጫ ውድድር እሁድ ህዳር 13 2019 ዓ.ም የሚካሄድ ሲሆን ውድድሩን በማስመልከት ዛሬ ጋዜጫዊ መግለጫ የሰጡት የባህልና ቱሪዝም ሚኒስትር ሰላማዊት ካሳ ታላቁ ሩጫ ከጎዳና ሩጫ ባሻገር ዘርፈ ብዙ ፋይዳ ያለው ወሳኝ ስፖርታዊ ኩነት ነው ብለዋል::

ሚኒስትሯ መዲናችን አዲስ አበባ በአዳዲስ የኮሪደር ልማቶች ደምቃና ተውባ ለምትውልበት ለዚህ ታላቅ የስፖርትና የቱሪዝም ድግስ ለመላው ተሳታፊዎች የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል
❤5👍1
ድንጋይን ያናገሩ እጆች፡ ከላሊበላ እና አክሱም እስከ ዘመናዊቷ አዲስ አበባ

የኢትዮጵያ ሥልጣኔ ከ3 ሺህ ዓመታት በላይ የሚሻገር ጥልቅ ታሪክ ያለው፣ በጥንታዊ የሥነ ሕንጻ፣ የድንጋይ ፍልፍል እና የምህንድስና ጥበብ የዓለምን ትኩረት የሳበ ነው::

ከአንድ ወጥ ድንጋይ ተፈልፍለው የተሠሩት የላሊበላ ውቅር አብያተ ክርስቲያናት፣ የአክሱም ሐውልት እንዲሁም የሶፍ ዑመር ዋሻ ኢትዮጵያውያን ከድንጋይ እና ከተፈጥሮ ጋር ያላቸውን የቆየ ብልሃት እና ጥበብ ያሳያሉ
🔥4👍1
ጅማ፡ ከጥንታዊ የከተማ ንድፍና ቅርስ እስከ ብሔራዊ የአንድነት መድረክ

ጅማ በታሪክ፣ በባህል እና በተፈጥሮ ጸጋ የበለጸገች፣ የኢትዮጵያን ብዝኃነት እና አንድነት የምታንጸባርቅ ታላቅ ከተማ ናት::

ከተማዋ በ1931 ዓ.ም በተዘጋጁ የከተማ ፕላን እና የሕንፃ ንድፍ ዕቅዶች ውስጥ ከተካተቱ ቀዳሚ ስፍራዎች አንዷ ስትሆን፣ ዛሬ ደግሞ በመንግሥት እና በሕዝብ የተቀናጀ ተሳትፎ በተከናወኑ የኮሪደር እና የመሠረተ ልማት ሥራዎች አዲስ ገጽታ ተላብሳለች
❤7👏1🙏1🤣1
የቻይና እና አፍሪካ የምርምር ማዕከል ሥራ ጀመረ

አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ከቻይና-አፍሪካ ኢንስቲትዩት ጋር በመተባበር ያቋቋመው የቻይና እና አፍሪካ የምርምር ማዕከል በይፋ ሥራ ጀመረ::

ማዕከሉ በማኅበራዊ ሳይንስ ዘርፍ ላይ ትኩረት በማድረግ ዋና ዓላማውን የዕውቀት ልውውጥ ማሳደግና የጋራ ትብብርን የሚያጠናክሩ ጥናቶችን ማካሄድ አድርጓል
❤7🙏2
ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ የአዲስ አበባን የስፖርት ቱሪዝም እና የኢኮኖሚ እንቅስቃሴ የሚያነቃቃበት ታላቅ መድረክ

በየዓመቱ የአፍሪካ መዲና የሆነችውን አዲስ አበባን በአረንጓዴ፣ ቢጫ እና ቀይ ቀለማት የሚያደምቀው ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ፣ ዘንድሮም 60 ሺህ ተሳታፊዎችን በማሰባሰብ የጎዳና ላይ ትዕይንቱን ዳግም ለማድመቅ ዝግጅቱን አጠናቅቋል::

ይህ ግዙፍ ሁነት የኢትዮጵያን የስፖርት ቱሪዝም አቅም ለዓለም የሚያስተዋውቅ እና የመዲናዋን ኢኮኖሚ የሚያነቃቃ ቁልፍ መሳሪያ ሆኖ ቀጥሏል
❤7
በመቐለ ከተማ ባለፉት 30 ቀናት ሰላምን በማስፈን እና ተቋማትን ወደ መደበኛ ሥራ በመመለስ ረገድ ውጤታማ ተግባራት ተከናውነዋል - ሺሻይ አማረ (ዶ/ር)

በመቐለ ከተማ ባለፉት 30 ቀናት ሰላምን በማስፈን፣ መንግሥታዊ ተቋማትን እና የንግድ እንቅስቃሴዎችን ወደ መደበኛ ሥራ በመመለስ ረገድ ውጤታማ ተግባራት መከናወናቸውን በትግራይ ክልል ባለአደራ አስተዳደር የከተማዋ ከንቲባ ሽሻይ አማረ (ዶ/ር) ገለጹ::

የከተማ አስተዳደሩ ያለፉት 30 ቀናት የሥራ አፈጻጸምን ከተለያዩ ቢሮዎች ጋር በገመገመበት ወቅት እንደተመላከተው፣ መንግሥታዊ አገልግሎት ሰጪ ተቋማት ሥራ በመጀመራቸው ሠራተኞች ወደ ሥራ ገበታቸው ተመልሰው የደመወዝ ክፍያ እንዲፈጸምላቸው ተደርጓል
❤6🥰1
በመቐለ ከተማ ባለፉት 30 ቀናት ሰላምን በማስፈን እና ተቋማትን ወደ መደበኛ ሥራ በመመለስ ረገድ ውጤታማ ተግባራት ተከናውነዋል - ሺሻይ አማረ (ዶ/ር)

በመቐለ ከተማ ባለፉት 30 ቀናት ሰላምን በማስፈን፣ መንግሥታዊ ተቋማትን እና የንግድ እንቅስቃሴዎችን ወደ መደበኛ ሥራ በመመለስ ረገድ ውጤታማ ተግባራት መከናወናቸውን በትግራይ ክልል ባለአደራ አስተዳደር የከተማዋ ከንቲባ ሽሻይ አማረ (ዶ/ር) ገለጹ::

የከተማ አስተዳደሩ ያለፉት 30 ቀናት የሥራ አፈጻጸምን ከተለያዩ ቢሮዎች ጋር በገመገመበት ወቅት እንደተመላከተው፣ መንግሥታዊ አገልግሎት ሰጪ ተቋማት ሥራ በመጀመራቸው ሠራተኞች ወደ ሥራ ገበታቸው ተመልሰው የደመወዝ ክፍያ እንዲፈጸምላቸው ተደርጓል
❤3
“ተልዕኳችን ለሥልጣን ሳይሆን ለምርጫ ማዘጋጀት ነው''፡- የመቐለ ከንቲባ ሺሻይ አማረ (ዶ/ር)

በትግራይ ክልል አሁን ላይ እየተሠራ ያለው ሥራ ለሥልጣን ሳይሆን፣ ክልሉን በቀጣዮቹ አምስት ወራት ለምርጫ ለማዘጋጀት መሆኑን በክልሉ ባለአደራ አስተዳደር የመቐለ ከተማ ከንቲባ ሺሻይ አማረ (ዶ/ር) አስገነዘቡ::

ከንቲባው ባለፉት 30 ቀናት ያከናወናቸውን ዋና ዋና ተግባራት አስመልክቶ ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ፣ በመከላከያ፣ በፌዴራል ፖሊስ፣ በትግራይ ሰላም ኃይል እና በሕዝቡ ትብብር በከተማዋ የወንጀል ድርጊቶች እየቀነሱ መምጣታቸውን አስታውቀዋል
❤24👍1🔥1
ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ የአብሮነታችን አሻራ፣ የኩራታችን መገለጫ
👍7🔥2