ከሌላ ቦታ መጥቶ የኛን ሀገር የሚሠራልን የለም፤ እኛው ተባብረን ነው ሀገር የምንሠራው - ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ዜጎች በሀገራቸው ውስጥ የሚገኙ ውብ ስፍራዎችን የመጎብኘት ባህልን እንዲያዳብሩ ጥሪ አቅርበዋል::
በተለይም አዲስ አበባ ክረምት እና ብርድ በሚሆንበት ወቅት እንደ ባሕር ዳር፣ አርባምንጭ እና ጅማ ያሉ ሞቅ ያሉ አካባቢዎች እንግዶችን ለመቀበል ሰፊ ዕድል እንዳላቸው ገልጸው፣ በአነስተኛ ወጪ በውጭ ሀገር የሚገኘውን እርካታ ሀገር ውስጥ ማግኘት እንደሚቻል አመልክተዋል

👏15❤10👍2
ዛሬ በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የተመረቀው የኮሪደር ልማት ከየት እስከ የት ነው?
• ከቦሌ መድኃኒዓለም - ጎላጎል - እንግሊዝ ኤምባሲ
• ከቦሌ መድኃኒዓለም - ሞኤንኮ
• ከኢምፔሪያል ሆቴል - ሻላ መናፈሻ
• ከቺቺኒያ - ቦሌ ሩዋንዳ
• ከአደይ አበባ ስታዲየም - ቦሌ መንገድ
• የውስጥ ለውስጥ የመንገድ ኔትወርክ
#Ethiopia #EBC #AddisAbaba #CorridorDevelopment #UrbanDevelopment

❤20👏7
ታሪክን እያከበርን፣ ማንነትን እያጠናከርን፣ ዐሻራን ለትውልድ እያስተላለፍን እንቀጥላልን፡- ከንቲባ አዳነች አቤቤ
ታሪክን እያከበርን፣ ማንነትን እያጠናከርን፣ ዐሻራን ለትውልድ እያስተላለፍን እንቀጥላልን ሲሉ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ ገለጹ::
ከንቲባዋ ታሪክን በልማት ማስቀጠል፤ ዐሻራን ለትውልድ ማስተላለፍ! በሚል በማኅበራዊ ትሥሥር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት፣ ከተማ የምትገነባው በመንገድና በሕንፃ ብቻ አይደለም፤ ታሪኳን የሠሩ፣ ለሀገር ውለታ የዋሉ ባለውለታዎቿን በክብር በማስቀጠልም ጭምር ነው ብለዋል

❤4👍3🙏2
አዲስ የከተማ ገጽታ እና የኢኮኖሚ መነቃቃትን የፈጠረው የአዲስ አበባ ኮሪደር ልማት
በመዲናችን አዲስ አበባ እየተከናወኑ ያሉት መጠነ ሰፊ የኮሪደር ልማት ሥራዎች የከተማዋን ነባር ገጽታ በመቀየር፣ ለበርካታ ዜጎች የሥራ ዕድል በመፍጠር እና የንግድ እንቅስቃሴውን በማነቃቃት ረገድ ትልቅ ለውጥ እያመጡ ናቸው::
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በትናንትናው ዕለት 57 ሄክታር የሚሸፍነውን አዲሱን የአዲስ አበባ የኮሪደር ልማት ፕሮጀክት ባስመረቁበት ወቅት፣ በመዲናዋ የተጀመሩት የኮሪደር ልማት ሥራዎች ለከተማዋ ነዋሪዎች አዳዲስ ዕድሎችን ይዘው መምጣታቸውን አጽንኦት ሰጥተዋል

🙏3❤2
4ኛው የፓን-አፍሪካ የቀዶ ሕክምና ጤና አጠባበቅ ፎረም በአዲስ አበባ መካሄድ ጀመረ
በአፍሪካ ሀገራት የቀዶ ሕክምና እና የሰመመን አገልግሎትን ለማሻሻል የሚያስችሉ የጋራ መለኪያዎችን ለማጽደቅና የመረጃ ሥርዓቶችን ለማጠናከር ያለመው 4ኛው የፓን-አፍሪካ የቀዶ ሕክምና ጤና አጠባበቅ ፎረም በአዲስ አበባ መካሄድ ጀምሯል::
"የአፍሪካን የቀዶ ሕክምና መረጃ እና አመልካቾች መዋቅር መገንባት" በሚል መሪ ቃል እየተካሄደ ባለው የፎረሙ የመክፈቻ ንግግር ላይ፣ አስተማማኝ መረጃ ለበጀት ድልድል፣ ለተጠያቂነት እና ለጥራት መሻሻል ወሳኝ መሆኑ ተገልጿል

❤4🙏2
ኢትዮጵያና ስዊድን በአየር ንብረት ለውጥ መከላከልና ለCOP32 ጉባኤ ስኬታማነት በጋራ ለመሥራት ተስማሙ
ኢትዮጵያና ስዊድን በአየር ንብረት ለውጥ ዙሪያ ያላቸውን የሁለትዮሽ ትብብር ይበልጥ ለማጠናከር በቱርክ አንታሊያ እየተካሄደ ከሚገኘው የCOP31 ጉባኤ ጎን ለጎን ውይይት አካሂደዋል::
የውጭ ጉዳይ ሚኒስትርና የCOP32 ተመራጭ ፕሬዚዳንት ጌዲዎን ጢሞቲዎስ (ዶ/ር) ከስዊድን የአየር ንብረትና አካባቢ ሚኒስትር ሮሚና ፑርሞክታሪ ጋር ባደረጉት ምክክር፤ በአየር ንብረት እርምጃ፣ በፋይናንስ አቅርቦት፣ የአየር ንብረት ለውጥን በመቋቋም እንዲሁም በታዳሽ ኃይል ልማት ዘርፎች ያላቸውን አጋርነት ወደ ላቀ ደረጃ ለማሸጋገር መክረዋል

13ኛው ዙር ሀገር አቀፍ የጥራት ሽልማት ሥነ-ሥርዓት ሊካሄድ ነው
የኢትዮጵያ ጥራትና ሽልማት ድርጅት 13ኛውን ዙር ሀገር አቀፍ የጥራት ሽልማት ሥነ-ሥርዓት፣ ኅዳር 12 ቀን 2019 ዓ.ም በታላቁ ቤተ መንግሥት እንደሚያካሂድና ለዚህም ዝግጅቱን ማጠናቀቁን ዛሬ በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ አስታውቋል::
ድርጅቱ በምርትና አገልግሎት ጥራት የላቀ ውጤት ያመጡ ተቋማትን እንደሚያበረታታ በመግለጽ፣ በዚህኛው ዙር ከተመዘገቡት 71 ተቋማት ውስጥ 58ቱ የምዘና ሂደቱን ማጠናቀቃቸውን ጠቁሟል

❤2
ጌዲዮን ጢሞቲዎስ (ዶ/ር) ከCOP31 የድርድር ፕሬዚዳንት ክሪስ ቦወን ጋር ተወያዩ
የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር እና ኮፕ 32 ተመራጭ ፕሬዚዳንት ጌዲዮን ጢሞቲዎስ (ዶ/ር) በCOP31 እና COP32 ፕሬዚዳንትነት መካከል ያለውን ትብብር ይበልጥ ለማጠናከር፣ ከCOP31 የድርድር ፕሬዚዳንት ክሪስ ቦወን ጋር የሁለትዮሽ ውይይት አካሂደዋል::
ጌዲዮን ጢሞቲዎስ (ዶ/ር) የCOP31 ፕሬዚዳንትነት በድርድሩ ያሳየውን አመራር በማድነቅ ግልጽና አካታች ሂደቱን፣ የመጀመሪያውን ውሳኔ (cover decision) ረቂቅ በቅድሚያ መለቀቁን እና እስካሁን የተመዘገበውን ውጤት አድንቀዋል

👍3❤2
የCOP32 ተመራጭ ፕሬዚዳንት ጌዲዮን ጢሞቲዎስ (ዶ/ር) ከጣልያን የአካባቢና የኢነርጂ ደኅንነት ሚኒስትር ጋር ተወያዩ
የCOP32 ተመራጭ ፕሬዚዳንት ጌዲዮን ጢሞቲዎስ (ዶ/ር) ከጣልያን የአካባቢና የኢነርጂ ደኅንነት ሚኒስትር ጊልቤርቶ ፒኬቶ ፍራቲን ጋር የሁለትዮሽ ውይይት አካሂደዋል::
በውይይታቸውም በኢትዮጵያና በጣልያን መካከል ባለው ዘላቂ ወዳጅነትና ጠንካራ የሁለትዮሽ ግንኙነት ላይ በመመስረት፣ ለአየር ንብረት ርምጃ ያላቸውን የጋራ ቁርጠኝነት አረጋግጠው፣ ለተሳካ COP32 ዝግጅት ትብብራቸውን የበለጠ ለማጠናከር ተስማምተዋል

❤7
የልማት ትልቁ ትርጉም በዜጎች ዕለታዊ ኑሮ ላይ ተጨባጭ ለውጥ ማምጣት ነው፡- ከንቲባ አዳነች አቤቤ
የልማት ትልቁ ትርጉም በዜጎች ዕለታዊ ኑሮ ላይ ተጨባጭ ለውጥ ማምጣት መሆኑን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ ገለጹ::
ከንቲባዋ ትናንት ያስመረቅነው የኮሪደር ልማት የከተማችንን መሠረተ ልማቶች በማገናኘትና የመንገድ ኔትወርካችንን በማስፋት ከተማችንን የበለጠ ምቹና ለኑሮ ተስማሚ ከማድረጉም በላይ ለዜጎች ቀጥተኛ የኢኮኖሚና የማኅበራዊ ጥቅም አስገኝቷል ብለዋል

❤3🙏3
የነዋሪዎችን ሕይወት የቀየረው የወንጪ ኢኮ ቱሪዝም መዳረሻ
በ"ገበታ ለሀገር" ፕሮጀክት ተገንብቶ ለአገልግሎት የበቃው የወንጪ ኢኮ ቱሪዝም መዳረሻ፣ የሀገር ውስጥ እና የውጭ ሀገር ጎብኚዎችን ቀልብ ከመሳብ ባለፈ የአካባቢውን ማኅበረሰብ ኢኮኖሚያዊ እና ማኅበራዊ ሕይወት ከመሰረቱ እየቀየረ መሆኑን የአካባቢው ነዋሪዎች ገልጸዋል::
የመደመር ንግሥት የቱሪዝም ልማት አቅጣጫ የተፈጥሮ ጸጋዎቻችንን በማልማት ዓለም አቀፍ ተወዳዳሪነትን ከማሳደግ ባለፈ፣ ልማቱን ከአካባቢው ማኅበረሰብ ሕይወት ጋር በቀጥታ ማስተሳሰር ላይ ያተኮረ ነው

❤10👍1
የአዲስ አበባን ዓለም አቀፍ ተወዳዳሪነት የሚያሳድገው ግዙፉ የኮሪደር ልማት
ሰብአዊ ክብርንና የነዋሪዎችን የኑሮ ጥራት ማዕከል በማድረግ የመዲናዋን ገጽታ የለወጠ እና ኢትዮጵያን ለዓለም አቀፍ ቱሪዝም ዝግጁ የሚያደርግ አዲሱ የአዲስ አበባ የኮሪደር ልማት ፕሮጀክት ተጠናቅቆ ለአገልግሎት ክፍት ሆኗል::
ቀደም ሲል የተከናወኑ የልማት ሥራዎችን ተሞክሮ በመቀመር በ57 ሄክታር መሬት ላይ የተገነባው ይህ ግዙፍ ፕሮጀክት፤ ትናንት በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) እና በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ በይፋ ተመርቋል

❤8🙏1