ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በሀዲያ እና ስልጤ ዞኖች የተገነቡ የሞዴል የገጠር መንደሮችን ለተጠቃሚዎች አስረክበዋል፤ የርክክብ ሥነ-ሥርዓቱ (በምሥል)
ተጨማሪ ምሥሎችን እዚህ ያገኛሉ
ተጨማሪ ምሥሎችን እዚህ ያገኛሉ
❤40👏11🤣5👍3
ስሟን መኖር የጀመረችው አዲስ አበባ - አዲስ ምዕራፍ
**********************************
አዲስ አበባ እንደ ከተማ ከተመሰረተች ከ139 ዓመታት በላይ ዕድሜ ያስቆጠረች ሲሆን፤ ዛሬ ላይ ስሟን በሚመጥን የለውጥ ጎዳና ላይ ትገኛለች።
የፌዴራል መንግሥትና የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከተማዋን ለነዋሪዎች ምቹ ለማድረግ በወሰዱት ቁርጠኛ አቋም፣ በኮሪደር ልማት የመዲናዋን ገጽታ ከመሰረቱ እየቀየሩት ይገኛሉ።
የኮሪደር ልማቱ ቀደም ሲል ተሽከርካሪዎች ብቻ ይሳለጡባቸው የነበሩ መንገዶችን ወደ ሰው ተኮር መሰረተ ልማት ቀይሯቸዋል።
አሁን ላይ፦
• ሰፋፊና ምቹ የእግረኛ መንገዶች
• የሳይክል መንገዶች
• ዘመናዊ የመንገድ ዳር መብራቶችና የሕዝብ መናፈሻ ፓርኮች ተገንብተው አገልግሎት መስጠት ጀምረዋል።
በመዲናዋ የሚኖሩት አና ዋልድማን የተባሉ የውጭ ሀገር ዜጋ ለሲጂቲኤን (CGTN) በሰጡት ቃል፥ ልማቱ የነዋሪዎችን የኑሮ ደረጃ እንዴት እንደቀየረ አስተውያለሁ ብለዋል። "መሰረተ ልማቱ በመሟላቱ በየቀኑ በሳይክል ወደ ሥራዬ እጓዛለሁ" የሚሉት አና፣ ከልጆቻቸው ጋር በምሽት በነጻነት በእግር መንቀሳቀስና በመዝናኛ ስፍራዎች ጊዜ ማሳለፍ መቻላቸው ትልቅ ደስታ እንደፈጠረላቸው ይናገራሉ።
ሌላኛው በመዲናዋ የተከናወነው አስደናቂ ሥራ የወንዝ ዳርቻ ልማት ነው። የተበከሉ ወንዞች ተጸድተው፣ ዛሬ ለዓይን የሚማርኩና ንጹህ አየር የሚገኝባቸው የቱሪስት መዳረሻዎች ሆነዋል።
የቱሪስት አስጎብኚ ድርጅት ባለቤቱ አቶ ተስፋየሱስ ያቆብ እንደሚሉት፤ ይህ ልማት "የት እንደነበሩ የማይታወቁና የተደበቁ" የከተማዋን ውበቶች ገልጦ አውጥቷል። የወንዝ ዳርቻ ልማቱ አዲስ አበባን በከተማ ቱሪዝም መዳረሻነት በዓለም አቀፍ ደረጃ እንድትታወቅ እያደረጋትም ነው ብለዋል።
የአዲስ አበባ ከተማ የኮሪደርና የወንዝ ዳርቻ ልማት አሥተዳደር ባለሥልጣን ዋና ዳይሬክተር ከድር አደም እንደሚሉት፣ ይህ ሥራ የከተማዋን መጨናነቅ ከመቀነስ ባለፈ ጤናማ አኗኗርን የሚያበረታታና ለቀጣዩ ትውልድ የሚሸጋገር ታላቅ ዐሻራ ነው።
በመሀመድ ፊጣሞ
#EthiopianBroadcastingCorporation #addisababa #Ethiopia #corridordevelopment

❤14🔥2
የኡጋንዳ ፓርላማ አባላት በውቢቷ አዲስ አበባ ያደረጉት ጉብኝት
***************
የኡጋንዳ ፓርላማ አባላት በውቢቷ አዲስ አበባ የወንዝ ዳር እና የኮሪደር ልማት ፕሮጀክት ጉብኝት አደረጉ።
በከተማ ልማት ዘርፍ አዲስ አበባ እያሳየች ያለውን ተሞክሮ ለመቅሰም በመዲናዋ የተገኙት ሶስት የዩጋንዳ ፓርላማ አባላት እየተከናወኑ ያሉ የወንዝ ዳር እና የኮሪደር ልማት ፕሮጀክቶችን ተዘዋውረው ጎብኝተዋል።
የፓርላማ አባላቱ በጉብኝታቸው ባዩት ለውጥ መነሳሳታቸውን ገልጸው፣ ተመሳሳይ ፕሮጀክቶችን በሀገራቸው ለመስራት ጥሩ ተሞክሮ የወሰዱበት መሆኑን ተናግረዋል።
አዲስ አበባ በከተማ ልማት እያሳየች ያለው መሠረታዊ ለውጥ ለአፍሪካ ሀገራት ትልቅ ተሞክሮና ትምህርት እንደሚሆንም ተናግረዋል ።
Ethiopian Broadcasting Corporation #AddisAbaba #CorridorDevelopment #Riverside #Ethiopia

❤24👏9
"አዲስ አበባን ማዕከል አድርጎ የጀመረው የኮሪደር ልማት የኢትዮጵያ የብልጽግና ማሳያ ምልክት መሆን ችሏል"
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)
#EthiopianBroadcastingCorporation #Ethiopia #CorridorDevelopment #UrbanRenewal #PMAbiyAhmed

👍11❤3🔥2👏2
ዛሬ በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የተመረቀው የኮሪደር ልማት ከየት እስከ የት ነው?
• ከቦሌ መድኃኒዓለም - ጎላጎል - እንግሊዝ ኤምባሲ
• ከቦሌ መድኃኒዓለም - ሞኤንኮ
• ከኢምፔሪያል ሆቴል - ሻላ መናፈሻ
• ከቺቺኒያ - ቦሌ ሩዋንዳ
• ከአደይ አበባ ስታዲየም - ቦሌ መንገድ
• የውስጥ ለውስጥ የመንገድ ኔትወርክ
#Ethiopia #EBC #AddisAbaba #CorridorDevelopment #UrbanDevelopment

❤20👏7