EBC (Ethiopian Broadcasting Corporation)
✔
132K subscribers
45.8K photos
484 videos
80 files
13.7K links
EBC (Ethiopian Broadcasting Corporation) @etvafaanoromoo1
@ETVkidschannel
@EBCWORLD1
@etventertainment1
Download Telegram
የነዳጅ ጥገኝነትን የሚቀንስ የከተማ ትራንስፖርት ሽግግር

ኢትዮጵያ ያሏትን የተፈጥሮ ሀብቶች በመጠቀም የዜጎቿን የኑሮ ሁኔታ ለማሻሻልና የኢኮኖሚ ነፃነቷን ለማጠናከር የጀመረችው ጥረት ተጨባጭ ውጤት እያሳየ ይገኛል::

በአዲስ አበባ ከነዳጅ ወደ ተፈጥሮ ጋዝ የተቀየሩ አውቶቡሶች ወደ አገልግሎት መግባታቸው የዚህ ጥረት አንዱ ማሳያ ነው
❤9👍1👏1
የኢትዮጵያ ተቋማዊ የዴሞክራሲ ጉዞ እና የአፍሪካ ፖለቲካ ፓርቲዎች ጉባኤ

የፖለቲካ ተሳትፎን ማስፋት፣ የተለያዩ የፖለቲካ አማራጮችን ማበረታታት እና ተቋማዊ ዴሞክራሲን ማጠናከር የአንድ ሀገር የፖለቲካ ሥርዓት ብስለት ከሚለካባቸው ዋና ዋና መስፈርቶች መካከል ተጠቃሽ ናቸው::

ኢትዮጵያ በ2010 ዓ.ም ከተካሄደው ሀገራዊ የፖለቲካ ለውጥ በኋላ በመደመር እሳቤ በፖለቲካ ምኅዳሯ፣ በምርጫ ተቋሟ ተዓማኒነት እና በፓርላማዊ ውክልናዋ ስብጥር ላይ ጉልህ ለውጦችን አስተናግዳለች
❤10🤣1
በመደመር መንግሥት የተጀመረውን የልማት፣ የብልጽግና እና የሰላም እንቅስቃሴ እንደግፋለን፡- ሀጂ ኢብራሂም ቱፋ

የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት የሁለተኛ ዓመት 1ኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤውን በአዲስ አበባ ማካሄድ ጀምሯል፡፡
የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ፕሬዚዳንት ሀጂ ኢብራሂም ቱፋ ጉባኤውን በይፋ በከፈቱት ወቅት፣ ኢትዮጵያውያን የመደመር መንግሥት የጀመራቸውን ሀገራዊ የልማት፣ የብልጽግና፣ የሰላም እና የአንድነት እንቅስቃሴዎች ከመንግሥት ጎን በመቆም ጫፍ እስኪደርሱ ማስቀጠል እንደሚገባቸው ተናግረዋል፡፡
ኢትዮጵያ የተለያዩ ፈተናዎችን አልፋ ዛሬ የተጎናጸፈችውን ነጻነት፣ ዴሞክራሲ፣ ፍቅር እና አንድነት ማጠናከር እንደሚገባም አስገንዝበዋል::

ነብዩ መሐመድ (ሰ.ዐ.ወ) ሰሃቦች በቸገራቸው ጊዜ “አንድም ሰው የማይበደልበት፣ የእኩልነት፣ የፍቅርና የፍትህ መንግሥት አለና ወደ ኢትዮጵያ (ወደ ሀበሻ) ሂዱ” በማለት ወደ ንጉሠ ነገሥት ነጃሺ መላካቸውን አስታውሰው፣ ከዛሬ 1448 ዓመታት በፊት የጀመረው ይኸው ሰላማዊ ታሪክ የኢትዮጵያን እና የእስልምናን ጥልቅ የሰላም ትሥሥር የሚያሳይ መሆኑን ገልጸዋል
❤10👍3⚡1
የቀድሞ ታጣቂዎች የትግራይን አዲስ የሰላም ምዕራፍ ለመገንባት ቁርጠኝነታቸውን ገለጹ

በሰሜኑ የሀገራችን ክፍል ታሪካዊና አዲስ የሰላም ምዕራፍ መከፈቱን የሚያበስሩ አበይት ተግባራት ተጠናክረው የቀጠሉ ሲሆን፣ የቀድሞ ታጣቂዎች ለትግራይ ክልል ሰላም ግንባታና ሁለንተናዊ እድገት የድርሻቸውን ለመወጣት ዝግጁ መሆናቸውን አስታውቀዋል::

ብሔራዊ ተሃድሶ ኮሚሽን ዘላቂ ሰላምን ለማረጋገጥ እያከናወነ በሚገኘው የትጥቅ ማስፈታት፣ የቀድሞ ተዋጊዎችን ከጦር ሜዳ ማስወጣትና ወደ ማህበረሰብ መልሶ የማቀላቀል (DDR) ፕሮግራም እስካሁን በተለያዩ ክልሎች ከ93 ሺህ በላይ የቀድሞ ታጣቂዎችን ወደ ሰላማዊ ሲቪል ሕይወት መመለሱን ይፋ አድርጓል
❤11
የመደመር መንግሥት የጤና ሉዓላዊነንት ለማረጋገጥ የመድኃኒት እና የህክምና መሳርያ አምራች ፋብሪካዎች እንዲጎለብቱ እየሠራ ነው

የመደመር መንግሥት የጤና ሉዓላዊነት ለማረጋገጥ በራስ አቅም የሀገር ውስጥ ምርትን ለማሳደግ የመድኃኒት እና የህክምና መሳርያ አምራች ፋብሪካዎች እንዲጎለብቱ እየሠራ መሆኑን የጤና ሚኒስቴር ገለጸ::

በወራቤ ኮምፕርሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል የተገነባውን የኦክስጅን ማምረቻ የጤና ሚኒስትር ዶክተር መቅደስ ዳባ እና የክልሉ ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች በተገኙበት ተመርቋል
❤11👍2
የጂኦፖለቲካው አለመመጣጠን እና የኢትዮጵያ የባህር በር ጥያቄ ከታሪካዊ እውነት እስከ ዓለም አቀፍ ሕጋዊ መብት

በዓለም አቀፍ የጂኦፖለቲካ መልክዓ-ምድር ውስጥ የባህር በር ባለቤት መሆን የሉዓላዊነትና የኢኮኖሚ ነፃነት ማዕከል ነው::

ከ130 ሚሊዮን በላይ ሕዝብ እያስተዳደረች በዓለም ቀዳሚዋ የባህር በር የሌላት ሀገር መሆኗ የተፈጥሮና የታሪክ አለመመጣጠን መሆኑ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተጠናከረ መጥቷል
❤5🙏1
የአፍሪካ መጻኢ ዕድል የተመሰረተው ሕዝባዊ አንድነትን፣ ተጠያቂነትንና አካታች አስተዳደርን ማረጋገጥ በሚቻልበት አቅም ላይ ነው፦ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

“ለዕድገት መምራት” በሚል መሪ ቃል ዛሬ መካሔድ በጀመረው 2ኛው የአፍሪካ የፖለቲካ ፓርቲዎች ጉባኤ ላይ የተገኙት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ንግግር አድርገዋል፡፡
የአፍሪካ መዲና በሆነችው አዲስ አበባ ይህ ታላቅ አህጉራዊ መድረክ መካሄዱና መስተናገዱ ለሁሉም ታላቅ ኩራት መሆኑን ጠቅላይ ሚኒስትሩ ገልጸዋል፡፡

በመደመር እሳቤ እየተመሩ ሕዝባዊ አንድነትን፣ ተጠያቂነትንና አካታች አስተዳደርን ማረጋገጥ የፖለቲካ አመራር የዜጎችን ሕይወት እንዲያሻሽል የሚያስችሉ ወሳኝ መሠረቶች መሆናቸውን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) አስገንዝበዋል፡፡

ይህም ፓርቲዎች ከምርጫ ውድድር ባለፈ አሻግረው እንዲመለከቱ፣ በመንግሥት ለውጦች የማይቀያየሩ፣ ብሔራዊና ቅድሚያ በሚሰጣቸው የረጅም ጊዜ ጉዳዮች ላይ የጋራ መግባባት እንዲፈጥሩ እና ለሀገር ጥቅም በጋራ እንዲሠሩ የሚጠይቅ መሆኑን አብራርተዋል፡፡
በሌላ በኩል፣ ተተኪው ትውልድ ኃላፊነቶችን እየወሰደ የሚያድግበትን ዕድሎች እያገኘ እንዲሄድ ለማድረግ መዋዕለ ንዋይ ማፍሰስ እጅግ ወሳኝ ጉዳይ መሆኑን ጠቅላይ ሚኒስትሩ አንስተዋል፡፡

ኢትዮጵያ በአፍሪካ አመራር የልህቀት አካዳሚ በኩል የምትሰጠውን ሥልጠና በአህጉሪቱ ለሚገኙ የፖለቲካ ፓርቲዎች ክፍት ማድረጓን እንደምትቀጥልም አረጋግጠዋል፡፡
ለሕዝባችን የተሻለ መጻኢ ዕድል የመገንባት ኃላፊነታችን ሊቀጥል ይገባል ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) መልእክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡
❤11🙏2
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የተገኙበት ሁለተኛው የአፍሪካ ፖለቲካ ፓርቲዎች ጉባኤ፦ (በምሥል)
❤4🔥4
“የምንከተለው ፖሊሲ ‘የሕዝባችንን የዕለት ተዕለት ሕይወት ቀይሯል ወይ?’ የሚለው ጥያቄ ዋነኛ የሕልውና መለኪያ ነው”፦ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

"የሕዝባችን የዕለት ተዕለት ሕይወት በምንከተለው ፖሊሲ እና እምነት ምክንያት የተሻለ ሆኗል ወይ?” የሚለው ጥያቄ እያንዳንዱ የፖለቲካ መሪ ራሱን ሊጠይቅ የሚገባው ዋነኛ የሕልውና መለኪያ መሆን እንደሚገባ የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር እና የብልጽግና ፓርቲ ፕሬዚዳንት ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) አሳሰቡ::

“ለዕድገት መምራት፦ የፖለቲካ ፓርቲዎች እንደ የአፍሪካ መፃኢ የኢኮኖሚ መሐንዲሶች” በሚል መሪ ሐሳብ በዓድዋ ድል መታሰቢያ እየተካሄደ ባለው ሁለተኛው የአፍሪካ ፖለቲካ ፓርቲዎች ጉባኤ ላይ የተገኙት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የመክፈቻ ንግግር አቅርበዋል
🙏6❤5
“ተፎካካሪ ፓርቲዎች በሀገራዊ ግቦች ላይ እየተስማሙ፣ የዕቅዶችን አፈጻጸም፣ ወጪ እና ውጤታማነት መጠየቅ እና መሞገት ይችላሉ፤ መንግሥትም ለጥያቄዎቹ ምላሽ የመስጠት ኃላፊነት አለበት።”

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)
❤6👍5
ከመደመር ማዕቀፍ እስከ አህጉራዊ ትሥሥር

መደመር ለአፍሪካ ማለት የጋራ ሉዓላዊነትን፣ የኢኮኖሚ ትሥሥርን እና የሰላም አርማን ከፍ አድርጎ ማስቀጠል ማለት ነው::

አፍሪካዊ ብልጽግና በእጃችን ተቀርጿል!
❤7🙏1
የአፍሪካ መጻኢ ዕድል የተመሠረተው ሀገራዊ አቅማችንን ወደ ውጤታማ አቅም መቀየር በምንችልበት ቁመና ላይ ነው፦ አቶ አደም ፋራህ

በአዲስ አበባ በመካሄድ ላይ ባለው ሁለተኛው የአፍሪካ ፖለቲካ ፓርቲዎች ጉባኤ ላይ ንግግር ያደረጉት የብልጽግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዚዳንት አቶ አደም ፋራህ፣ የአፍሪካ የኢኮኖሚ መጻኢ ዕድል ሙሉ በሙሉ የተመሠረተው የያዝነውን ሀገራዊ አቅም ወደ እውነተኛ እና ውጤታማ አቅም መቀየር በሚቻልበት ቁመና ላይ ነው ሲሉ ገልጸዋል::

“ለዕድገት መምራት፦ የፖለቲካ ፓርቲዎች እንደ የአፍሪካ መጻኢ የኢኮኖሚ መሐንዲሶች” በሚል መሪ ሐሳብ በተካሄደው በዚህ ጉባኤ ላይ ንግግር ያደረጉት አቶ አደም ፋራህ፣ የፖለቲካ ኃላፊነት ሁልጊዜም የልማት እና የዕድገት ማዕከል ሊሆን እንደሚገባ አሳስበዋል
👍6❤3
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከአፍሪካ ኅብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር ማህሙድ አሊ ዩሱፍ ጋር ተወያዩ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከ2ኛው የአፍሪካ የፖለቲካ ፓርቲዎች ጉባኤ ጎን ለጎን ከአፍሪካ ኅብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር ማህሙድ አሊ ዩሱፍ ጋር መወያየታቸውን ገለጹ::

‎ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማኅበራዊ ትሥሥር ገጽ ባሰፈሩት መልዕክት፣ “በአህጉራዊ አስተዳደር፣ አካታች የፖለቲካ ሂደቶች፣ ቅድሚያ በሚሰጣቸው የረጅም ጊዜ የልማት ጉዳዮች እንዲሁም የአፍሪካን አመራር በማጠናከር ዙሪያ ሰፊ የሃሳብ ልውውጥ አድርገናል” ብለዋል
🙏6❤4
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በ2ኛው የአፍሪካ ፖለቲካ ፓርቲዎች ጉባኤ ላይ ያደረጉት ንግግር ዋና ዋና ሐሳቦች

• የማንኛውም የፖለቲካ አስተሳሰብ እና የመንግሥት ውሳኔ ትክክለኛ መለኪያ የሕዝቡን የዕለት ተዕለት ሕይወት ማሻሻል መቻሉ ነው::

• ዕድገት እና ለውጥ ወደ ዜጎች ደጃፍ ካልደረሰ፣ ሕዝቡ በፓርቲዎች ላይ ብቻ ሳይሆን በአጠቃላይ የፖለቲካ ሥርዓቱ ላይ እምነት ያጣል
❤10
በአፍሪካ የፖለቲካ ፓርቲዎች በሕዝብ እና በተቋማት መካከል ድልድይ በመሆን ማገልገል አለባቸው፡- መሀሙድ አሊ ዩሱፍ

በአፍሪካ የፖለቲካ ፓርቲዎች በሕዝብ እና በተቋማት መካከል ድልድይ በመሆን ማገልገል እንዳለባቸው የአፍሪካ ሕብረት ኮሚሽን ሊቀ መንበር መሀሙድ አሊ ዩሱፍ አስገነዘቡ::

2ኛው የአፍሪካ ፖለቲካ ፓርቲዎች ጉባዔ “ለዕድገት መምራት፦ የፖለቲካ ፓርቲዎች እንደ የአፍሪካ መጻኢ የኢኮኖሚ መሐንዲሶች” በሚል መሪ ሐሳብ በዓድዋ ድል መታሰቢያ እየተካሄደ ይገኛል
❤2👍2
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ለአፍሪካ ፖለቲካ ፓርቲዎች ያቀረቧቸው ሁለቱ ዋና ዋና ምክረ ሐሳቦች

በሁለተኛው የአፍሪካ ፖለቲካ ፓርቲዎች ጉባኤ መድረክ ላይ የተገኙት የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)፣ በሚጸድቀው ‘የአዲስ አበባ የአቋም መግለጫ’ ውስጥ እንዲካተቱ አህጉራዊ ፋይዳ ያላቸውን ሁለት ታላላቅ ሐሳቦች ለአፍሪካ የፖለቲካ መሪዎች አቅርበዋል::

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ያቀረቡት የመጀመሪያው ጥሪ፤ “ከምርጫ ውድድሮች ባሻገር የሚጸኑ ሀገራዊ ቅድሚያ የሚሰጣቸው ግቦች ላይ መስማማት” የሚል ነው
❤10
መደመር መከፋፈልን አሸንፎ ሁለንተናዊ ብልጽግናን የሚገነባ የጋራ ቤታችን ነው፦ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

በአዲስ አበባ በታሪካዊው የዓድዋ ድል መታሰቢያ እየተካሄደ በሚገኘው 2ኛው የአፍሪካ የፖለቲካ ፓርቲዎች አህጉራዊ ጉባኤ ላይ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ንግግር አድርገዋል::

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በንግግራቸው፤ ብልፅግና ፓርቲ ከተፎካካሪ ፓርቲዎች መሪዎች የተውጣጣ አዲስ የመደመር መንግሥት ማቋቋሙን ተናግረዋል
❤12👍1
መደመር መከፋፈልን አሸንፎ ሁለንተናዊ ብልጽግናን የሚገነባ የጋራ ቤታችን ነው፦ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

በአዲስ አበባ በታሪካዊው የዓድዋ ድል መታሰቢያ እየተካሄደ በሚገኘው 2ኛው የአፍሪካ የፖለቲካ ፓርቲዎች አህጉራዊ ጉባኤ ላይ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ንግግር አድርገዋል::

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በንግግራቸው፤ ብልፅግና ፓርቲ ከተፎካካሪ ፓርቲዎች መሪዎች የተውጣጣ አዲስ የመደመር መንግሥት ማቋቋሙን ተናግረዋል
❤10
"መደመር ማለት ሌሎች በጀመሩት ላይ መገንባት ማለትም ነው። ቀደም ሲል የተጀመሩ ሀገራዊ ሥራዎችን አጠናክሮ መጨረስ፤ ለዚህም የሕዳሴ ግድብ ማሳያ ነው።” …

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)
❤12👍1