EBC (Ethiopian Broadcasting Corporation)
✔
132K subscribers
45.8K photos
484 videos
80 files
13.7K links
EBC (Ethiopian Broadcasting Corporation) @etvafaanoromoo1
@ETVkidschannel
@EBCWORLD1
@etventertainment1
Download Telegram
ከደመና በላይ የCOP32 ጉባኤን ስኬት ለማብሰር ሁሌም ዝግጁ ሆኖ የሚጠብቀው የኢትዮጵያ አየር መንገድ

ማንኛውም ታላቅ ጉዞ የሚጀምረው በእምነትና በተቋማዊ ጥንካሬ ነው፤ እያንዳንዱ መዳረሻ ደግሞ ሕዝቦችን፣ ባህሎችንና አዳዲስ ዕድሎችን እርስ በእርስ የሚያስተሳስር ወሳኝ ድልድይ ይፈጥራል::

የአፍሪካ ግዙፉና መሪው የኢትዮጵያ አየር መንገድ (Ethiopian Airlines) የአየር ትራንስፖርት አገልግሎት ሰጪ ብቻ አይደለም፤ ይልቁንም የሀገራችንን ታሪክ፣ ቅርሶች፣ ራዕይና የከፍታ ምኞት ወደ ተለያዩ የዓለማችን ማዕዘናት የሚያደርስ የኢትዮጵያ አምባሳደርና የብሔራዊ ማንነታችን ሕያው መገለጫ ነው
❤14🥰2
መረጃ ማሻሻያውና የኢትዮጵያ አዲስ ማክሮ-ኢኮኖሚያዊ እውነት በጂዲፒ መለኪያ ለውጥ አንድምታ

ኢትዮጵያ የጠቅላላ ሀገራዊ ምርት (GDP) የዲጂታል ኢኮኖሚ መሠረቷንና የመነሻ ዓመቷን በማሻሻል የአህጉራችን 5ኛዋ ግዙፍ ኢኮኖሚ መሆኗ ተረጋግጧል::

በብሔራዊ ስትራቴጂ ሚኒስትር ፍጹም አሰፋ (ዶ/ር) ይፋ በተደረገው መረጃ መሠረት በሐምሌ ወር በተጠናቀቀው የሒሳብ ዓመት የኢትዮጵያ ጠቅላላ ሀገራዊ ምርት 210.7 ቢሊዮን የአሜሪካ ዶላር ደርሷል
❤6👍5
የመደመር መንግሥት የዜጎች የዕለት ተዕለት ሕይወት የመለወጥ ጉዞ

የፖለቲካ አስተሳሰቦች፣ ርዕዮተ ዓለሞች እና የመንግሥታት ፖሊሲዎች እውነተኛ ፋይዳ የሚለካው፤ በሚተላለፉ ውሳኔዎች፣ በሚወጡ መመሪያዎችና በሚተገበሩ ፕሮጀክቶች አማካኝነት የዜጎችን የዕለት ተዕለት ሕይወት በበጎ መልኩ መቀየር ሲችሉ ነው::

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) "የማንኛውም የፖለቲካ አስተሳሰብ እና የመንግሥት ውሳኔ ትክክለኛ መለኪያ የሕዝቡን የዕለት ተዕለት ሕይወት ማሻሻል መቻሉ ነው" በማለት በሁለተኛው የአፍሪካ ፖለቲካ ፓርቲዎች ጉባኤ ላይ ያስተላለፉት መልዕክት፣ የፖለቲካ ሥልጣንና የአመራር ሚና የመጨረሻ ግብ ምን መሆን እንዳለበት ግልጽ ያደረገ መርህ ነው
❤9👍2
የፖሊሲ ልዩነቶች ሳይገድቧቸው በጋራ ግብ ላይ መስማማትና አዲስ መሪዎችን ማፍራት ይገባል፦ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

ገዢ እና ተፎካካሪ ፓርቲዎች የፖሊሲ ልዩነቶች ሳይገድቧቸው በጋራ ግብ ላይ መስማማትና አዲስ መሪዎችን ማፍራት ይገባቸዋል ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ተናገሩ፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በ2ኛው የአፍሪካ ፖለቲካ ፓርቲዎች ዋና ጉባኤ ባደረጉት ንግግር፣ ከምርጫ በላይ የሆኑ እና የሀገርን የረጅም ጊዜ የልማት ግቦች ከትውልድ ወደ ትውልድ ሊያስቀጥሉ የሚችሉ የብሔራዊ ጉዳዮች መኖራቸውን ገልጸዋል፡፡

የፖሊሲ ልዩነቶች ቢኖሩም ገዢ እና ተፎካካሪ ፓርቲዎች በዋና ዋና የረጅም ጊዜ ግቦች ላይ ሊስማሙ እንደሚገባ በማሳሰብ፣ "ፖሊሲዎቻችን ይለያያሉ፣ መራጮች ይመርጣሉ፣ ነገር ግን አንዳንድ ብሔራዊ ጥረቶች ለመንግሥት ውጥን መትረፍ አለባቸው" ሲሉ አስረድተዋል::

በተጨማሪም አዲስ መሪዎችን ማፍራት እና ተተኪዎችን ማዘጋጀት እንደሚገባ ጠቅላይ ሚኒስትሩ አንስተዋል
❤6👍4
የመደመር እሳቤ ኢትዮጵያን የታላቅነት ማሳያ እያደረጋት ነው፡- የአህጉራዊ ጉባኤው ተሳታፊዎች

የመደመር እሳቤ አዲስ አበባን የአፍሪካ እውነተኛ መዲና እና ኢትዮጵያን ደግሞ የታላቅነት ማሳያ እያደረጋት መሆኑን ከተለያዩ ሀገራት የመጡ 2ኛው የአፍሪካ የፖለቲካ ፓርቲዎች ጉባኤ ተሳታፊዎች ገለጹ፡፡
ኢትዮጵያ ባለፉት ዓመታት በመደመር መንግሥት እሳቤ ከተሞቿን በቴክኖሎጂ ለማዘመን፣ ለነዋሪዎች ምቹ ለማድረግ እና የተቀላጠፈ አኗኗርን ለመፍጠር የሠራቻቸው ሰፊ ሥራዎች ፍሬ እያፈሩ ይገኛሉ::

ይህንኑ እውነታ በሁለተኛው የአፍሪካ የፖለቲካ ፓርቲዎች ጉባኤ ላይ ለመታደም ከተለያዩ ሀገራት ወደ አዲስ አበባ የመጡ ተሳታፊዎች በሰጡት ምስክርነት አረጋግጠዋል
❤16👏2🙏2
ከአፍሪካ ሕብረት እስከ ኮፕ 32፤ ኢትዮጵያ በአየር ንብረት ዲፕሎማሲ የምታስመዘግበው ታሪካዊ ምዕራፍ

መዲናችን አዲስ አበባ ለዓመታት የአፍሪካ የፖለቲካ እና የዲፕሎማሲ የልብ ትርታ ሆና የቆየች የአፍሪካ ሀገራት መሪዎች፣ ዲፕሎማቶች እና ተመራማሪዎች ተሰብስበው የአህጉሪቱን የጋራ ዕጣ ፈንታ የሚወስኑባት፣ የሚደራደሩባት እና የጋራ ራዕይ የሚቀርጹባት ናት::

ከተማዋ የአፍሪካ ኅብረት እና የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የአፍሪካ ኢኮኖሚ ኮሚሽን (UNECA) ዋና መሥሪያ ቤቶችን ጨምሮ ከ130 በላይ የውጭ ሀገራት ኤምባሲዎችና ዓለም አቀፍ ድርጅቶች መቀመጫ በመሆኗ ከኒው ዮርክ እና ጄኔቫ ቀጥሎ በዓለም ላይ ሦስተኛ የዲፕሎማሲ ማዕከል ናት
❤15👍1
ኢትዮጵያ እና አሜሪካ ታሪካዊ ግንኙነታቸውንና ስትራቴጂያዊ አጋርነታቸውን ለማጠናከር ተስማሙ

የመከላከያ ሚኒስትር አቶ መሀመድ እድሪስ ከውጭ ሀገራት አምባሳደሮች ጋር የሚያደርጉትን ተከታታይ የወታደራዊ ዲፕሎማሲ ውይይት በመቀጠል፣ በዛሬው ዕለት በኢትዮጵያ ከአሜሪካ አምባሳደር ኤርቪን ጃሲንቶ ማሲንጋ ጋር በጽሕፈት ቤታቸው ተወያይተዋል::

ሚኒስትሩ በውይይቱ ወቅት፣ ኢትዮጵያ እና አሜሪካ ከ120 ዓመታት በላይ የዘለቀ ጠንካራና በውጤት የታጀበ ግንኙነት ያላቸው ሀገራት መሆናቸውን ገልጸዋል
❤36👍13👏2
በሴራና በተንኮል የባህር በር እንድናጣ መደረጉ ሀገራችንን ለተለያዩ ተግዳሮቶች ዳርጓታል፦ ቫይስ አድሚራል ክንዱ ገዙ

የቀድሞው የኢትዮጵያ የጦር ኃይሎችና የፖሊስ ሠራዊት ማህበራት ህብረት አራተኛ ዓመት ጠቅላላ ጉባኤውን በማካሄድ ላይ ይገኛል::

በጉባኤው ላይ በክብር እንግድነት በመገኘት ንግግር ያደረጉት የኢትዮጵያ ባህር ኃይል አዛዥ ቫይስ አድሚራል ክንዱ ገዙ የኢትዮጵያ የባህር በር ጥያቄ ሌላ ሀገርን ለመውረር ያለመ ሳይሆን በዓለም አቀፍ ሕግና በዲፕሎማሲ አማካኝነት መፍትሔ ለማግኘት የሚደረግ ጥረት መሆኑን ገልጸዋል
❤20👍1
የሦስት ወራት የቡና አስደናቂ አፈጻጸም፡-

131,069.51 ቶን ቡና ለውጭ ገበያ ቀርቧል፤
የእቅዱን 91% ማሳካት ተችሏል፤
878.52 ሚሊዮን ዶላር ገቢ ተገኝቷል ፤

ከባለፈው ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር የ15% ወይም የ115.77 ሚሊዮን ዶላር ዕድገት አሳይቷል፡፡
👏8❤2
ስለ ሀገር ዛሬ ምሽት 12፡00 ይጠብቁን!
❤9
የተቀናጀ መሠረተ ልማት በአፍሪካውያን መዲና፡- አዲስ አበባ

አዲስ አበባ በከተማ ልማት የጀመረችው ጉዞ የአንድን ከተማ ገጽታ ከመቀየር ባለፈ፣ የከተማ ልማት ምን ያህል የዜጎችን ሕይወት መለወጥ፣ የኢኮኖሚ እድገትን ማፋጠን እና ለቀጣይ ትውልድ የተሻለ ከተማ መገንባት እንደሚችል የሚያሳይ ተግባራዊ ምሳሌ ሆኗል::

በተቋማዊ አቅም ግንባታ፣ በተቀናጀ መሠረተ ልማት ዝርጋታ፣ በአገልግሎት አሰጣጥ ማዘመን፣ በቴክኖሎጂ አጠቃቀምና በከተማ አስተዳደር ብቃት ረገድ የተከናወኑ ሥራዎች ከተማዋን ወደ አዲስ የልማት ምዕራፍ አሸጋግረዋል
❤3🙏2
በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የጤና ተቋማትና አገልግሎት አሰጣጥ አበረታች ዕድገት አሳይቷል፡- ርዕሰ መስተዳድር የትምጌታ አስራት(ዶ/ር)

በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ባለፉት ሦስት ዓመታት የጤና ተቋማትና አገልግሎት አሰጣጥ አበረታች ዕድገት ማሳየቱን የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር የትምጌታ አስራት(ዶ/ር)ገለጹ::

የኢትዮጵያን ሁለንተናዊ ብልፅግና እውን ማድረግ የሚቻለው አካላዊና አዕምሯዊ ጤንነቱ የተጠበቀ ብቁና ንቁ ዜጋ ሲገነባ መሆኑንም ተናግረዋል
❤7👍4🤣1
"ዓባይ እና ቀይ ባሕር የኢትዮጵያ ህልውና መሠረቶች ናቸው፤ ከ130 ሚሊዮን በላይ ሕዝብ ይዞ በጂኦግራፊያዊ እስር ቤት ውስጥ መቀጠል ለቀጣናውም ሆነ ለሀገራችን ዘላቂ አይሆንም።" ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)
❤15🔥4👍2
"ኢትዮጵያ በራሷ ሀብትና ባለሙያዎች የሚመራ ተጠያቂነት ያለው የጤና ሥርዓት የመገንባት ራዕይ አላት"፡- ዶ/ር መቅደስ ዳባ

28ኛው የጤና ዘርፍ ዓመታዊ ጉባኤ ላይ የጤና ሚኒስትር ዶክተር መቅደስ ዳባ ባደረጉት ንግግር፣ ኢትዮጵያ በራሷ ሀብትና ባለሙያዎች የሚመራ፣ ሰው ተኮር እና ተጠያቂነት ያለው ተቋማዊ ሥርዓት የመገንባት ራዕይ እንዳላት ገልጸዋል::

የጤና ሥርዓቱ ወረርሽኞች፣ በአየር ንብረት ለውጥና እና የተለያዩ ተግዳሮቶች ቢኖሩም ሳይቆራረጥ አገልግሎት የሚሰጥና ለትውልድ የሚሸጋገር የማይበገር እንዲሆን ቃል ኪዳን የተገባበት መሆኑን ሚኒስትሯ አብራርተዋል
❤9🙏2
በምስራቅ ጎጃም ዞን ሁለት እጁ እነሴ ወረዳ ለበጋ መስኖ የግብዓት ስርጭት በምስል:-
❤8
ሁለተኛው የአፍሪካ የፖለቲካ ፓርቲዎች ጉባኤ 22 ነጥቦችን የያዘ የአዲስ አበባ ስምምነት በማጽደቅ ተጠናቀቀ

በአዲስ አበባ ሲካሄድ የቆየው ሁለተኛው የአፍሪካ የፖለቲካ ፓርቲዎች ጉባኤ 22 ነጥብ የያዘ የአዲስ አበባ ስምምነት መግለጫ በማውጣት ተጠናቋል::

ጉባኤው በአፍሪካ የአስተዳደር ማዕከል (AGC) በተቋቋመው የአፍሪካ የፖለቲካ ፓርቲዎች ተነሳሽነት (APPI) ማዕቀፍ፣ ከኢትዮጵያ ብልጽግና ፓርቲ ጋር በመተባበር የተካሄደ ነው
❤14
የገቢዎች ሚኒስቴር የታክስ ከፋዮችን ቅሬታና ጥቆማ በዘመናዊ ቴክኖሎጂ ለመቀበል የሚያስችል አዲስ አሰራር ይፋ አደረገ

የገቢዎች ሚኒስቴር የሙስና እና የብልሹ አሰራር መከላከል ልዩ የንቅናቄ እቅድ ውይይት ማጠቃለያ እና የመጀመሪያው ሩብ ዓመት እቅድ አፈፃፀም ግምገማ ባካሄደበት መድረክ የታክስ ከፋዮችን ቅሬታና ጥቆማ በዘመናዊ መንገድ ለመቀበል የሚያስችል አዲስ አሰራር ይፋ አድርጓል::

ይህን አዲስ አሰራር የገቢዎች ሚኒስትር ዓይናለም ንጉሴ እና የሚኒስቴሩ የኢ-ዳታ ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ዳዊት ውብሸት ይፋ ያደረጉት ሲሆን ተቋሙ ግልጽነትና ተጠያቂነት የሰፈነበት የአገልግሎት አሰጣጥን እውን ለማድረግ የወሰደው ወሳኝ እርምጃ መሆኑ ተመላክቷል
❤12👍1🔥1
ከሪዮ እስከ አዲስ አበባ፡- የዓለም የአየር ንብረት ዲፕሎማሲእና የኮፕ 32 ተስፋ

ዓለማችን በታሪኳ ከፍተኛውን የበካይ ጋዝ ልቀት፣ አስከፊ የሰደድ እሳት፣ ገዳይ ድርቅ እና እጅግ ሞቃታማ ዓመታትን እያስተናገደች ትገኛለች::

ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ የመጣው ይህ የሙቀት መጠን፣ የአየር ንብረት ጉዳዮች ቸል ሊባሉ እንደማይችሉና ትብብር ቁልፍ መሆኑን ያሳያል
❤9👍2
አርሰናል ሃል ሲቲን 1 ለ 0 በማሸነፍ መሪነቱን አጠናከረ

በ10ኛ ሳምንት የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ በኢሚሬትስ ሃል ሲቲን ያስተናገደው አርሰናል 1 ለ 0 በማሸነፍ የደረጃ ሰንጠረዡን መምራቱን ቀጥሏል::

አርሰናል በውድድር ዓመቱ በሜዳው 6ኛ ድሉን ባስመዘገበበት የሊግ ጨዋታ ብቸኛዋን ግብ 72ኛው ደቂቃ ላይ ማርቲን ኦዴጋርድ ከመረብ አሳርፏል
🔥14❤4👍3
ሙስሊሙ ማኅበረሰብ በሀገረ መንግሥት ግንባታ የበለጠ ተሳትፎ አንዲያደርግ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ ጥሪ አቀረቡ

የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት 2ኛ ዓመት 1ኛ መደበኛ ጉባኤ ማጠቃለያ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ በተገኙበት ተካሂዷል::

በመድረኩ ላይ ንግግር ያደረጉት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ፣ መንግሥት የሙስሊሙ ማኅበረሰብ ለረጅም ዓመታት ሲያነሳቸው የነበሩ መሠረታዊ ጥያቄዎችን መመለሱን ገልጸዋል
❤15👍5🤣3👏2