EBC (Ethiopian Broadcasting Corporation)
✔
132K subscribers
45.8K photos
484 videos
80 files
13.7K links
EBC (Ethiopian Broadcasting Corporation) @etvafaanoromoo1
@ETVkidschannel
@EBCWORLD1
@etventertainment1
Download Telegram
ከአዳማዋ የመጀመሪያ ችግኝ እስከ ውቅያኖስ ውስጥ ቆሞ የተሟገተው ሚኒስትር — የዓለም መሪዎችን እንቅልፍ የሚነሳው የኮፕ (COP) ጉባኤ ያልተሰሙና አስገራሚ ታሪኮች

ግንቦት 18 ቀን 2011 ዓ.ም በአዳማ ከተማ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የመጀመሪያዋን የአረንጓዴ አሻራ ችግኝ ለመትከል ወደ መሬት ከማጎንበሳቸው በፊት "ዛሬ አምስት ሺህ ችግኝ ተዘጋጅቷል፤ ይሄን አምስት ሺህ ችግኝ በመትከል በጋራ 'ሀ' ብለን ከአራት ቢሊየኑ 5 ሺህ ዛሬ እንቀንሳለን" በማለት ታሪካዊውን ጥሪ አቀረቡ::

በዚያች ዕለት ከጉልበታቸው ዝቅ ብለው፣ እፍኝ አፈር ዘግነው የተከሏት ያቺ ለጋ ቡቃያ በሚሊዮኖች የጣት አሻራ ታጅባ ኢትዮጵያን አረንጓዴ ማልበስ ብቻ ሳይሆን ቅርንጫፎቿን ወደ ዓለም የዲፕሎማሲ ሰማይ አሳድጋ 32ኛውን የዓለም የአየር ንብረት ጉባኤ (COP32) ወደ አዲስ አበባ ማምጣት ችላለች።

ሙሉውን ያንብቡ
❤33🙏4
ኢትዮጵያ ከአረንጓዴ ዐሻራ እስከ ካርበን ንግድ

ኢትዮጵያ በዝቅተኛ የካርቦን ልቀት፣ በሰፊ የደን ሃብት እና ከፍተኛ በሚባል ደረጃ ከታዳሽ ሃብት በሚመነጨው የኤሌክትሪክ አቅርቦቷ በዓለም አቀፉ የካርቦን ገበያ ተመራጭነቷን እያሳደገች ይገኛል::

ሀገራችን የአካባቢ ጥበቃን ከኢኮኖሚ ልማት ጋር በማቀናጀት እያከናወነችው ያለው ስራ ለአፍሪካ ብቻ ሳይሆን ለዓለም አቀፉ ማህበረሰብም ጭምር በትምህርትነት የሚጠቀስ አርአያ እየሆነ ይገኛል
❤16👍9
በዳካር የወጣቶች ኦሊምፒክ ኢትዮጵያ የመጀመሪያውን የወርቅ ሜዳልያ አገኘች

በዳካር እየተካሄደ በሚገኘው የዓለም የወጣቶች ኦሊምፒክ ውድድር ኢትዮጵያ የመጀመሪያዋን የወርቅ ሜዳሊያ አግኝታለች::

በወንዶች 2000 ሜትር የመሰናክል ውድድር የተሳተፈው ወጣት አትሌት ጁነዲን አብዶ ድንቅ ብቃቱን በማሳየት ውድድሩን በቀዳሚነት በማጠናቀቅ አሸንፏል
❤41
ጠያቂዋ ሀገር መልስ ሆነች

ታኅሣሥ 2002 ዓ.ም፤ በታላቁ ብሔራዊ ቤተ መንግሥት ውስጥ የተለየ ሀገራዊ ድባብ ነግሦ ነበር::

በዴንማርክ ኮፐንሃገን ለሚካሄደው 15ኛው የዓለም የአየር ንብረት ለውጥ ጉባኤ (COP15) የሚያቀናውን የኢትዮጵያ ልዑካን ቡድን ለመሸኘት ከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች፣ የሃይማኖት አባቶች፣ ታዋቂ ግለሰቦችና የሕዝብ ተወካዮች ተሰብስበዋል
❤10👍3
አትሌት ዋቢ ወጂራ ለኢትዮጵያ 2ኛውን የወርቅ ሜዳልያ አስመዘገበ

በሴኔጋል መዲና ዳካር እየተካሄደ በሚገኘው 4ኛው የወጣቶች ኦሊምፒክ መድረክ፣ ኢትዮጵያ በውድድሩ ሁለተኛ የወርቅ ሜዳልያዋን አግኝታለች::

በወንዶች 1 ሺህ 500 ሜትር የፍፃሜ ውድድር ሀገሩን ወክሎ የተካፈለው አትሌት ዋቢ ወጂራ፣ ርቀቱን በ3 ደቂቃ ከ58 ሴኮንድ ከ73 ማይክሮ ሴኮንድ ቀዳሚ ሆኖ በማጠናቀቅ ድል ተቀዳጅቷል
❤25👍23🙏2
አትሌት ነጻነት ሰሎሞን ለኢትዮጵያ 3ኛውን የወርቅ ሜዳልያ አስመዘገበች

በሴኔጋል ዳካር አስተናጋጅነት እየተካሄደ በሚገኘው 4ኛው የወጣቶች ኦሊምፒክ መድረክ፣ ኢትዮጵያ ሦስተኛ የወርቅ ሜዳልያዋን በሴቶች 800 ሜትር ማግኘት ችላለች::

በውድድሩ ጠንካራ ፉክክር ያደረገችው አትሌት ነጻነት ሰሎሞን፣ ርቀቱን በ2 ደቂቃ ከ4 ሰከንድ ከ44 ማይክሮ ሰከንድ በማጠናቀቅ ቀዳሚ በመሆን ለሀገሯ የወርቅ ሜዳልያ አስገኝታለች
❤47👏28👍4🔥3
"ሀገርን ከከባድ የዕዳ ሸክም ማላቀቅ ለነገው ትውልድ የኢኮኖሚ ነፃነትን ማውረስ ነው።"

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)
❤16🙏1
ቀይ ባሕር፡ የኢትዮጵያ ታላቁ ርዕስት

ኢትዮጵያ በሺህ ዓመታት ታሪኳ ውስጥ የነፃነቷን እና የሉዓላዊነቷን አጥር በጀግኖች ልጆቿ ደም እና አጥንት አስከብራ ለዚህ ትውልድ አስረክባለች::

የዛሬው ትውልድ ደግሞ ሁለንተናዊ ከፍታን የማረጋገጥ፣ የኢኮኖሚ ነፃነትን የመቀዳጀት እና የጂኦፖለቲካዊ ህልውናውን የማስከበር ታሪካዊ ጥሪ ቀርቦለታል
❤22🕊2
የአዲስ አበባ ኮሪደር ልማት እና የዓለም አቀፍ ተወዳዳሪነት

አዲስ አበባ አህጉራዊ መቀመጫነቷን ተንተርሳ ለዘመናት የዲፕሎማሲ ማዕከል ሆና አገልግላለች::

ሆኖም ፈጣን የሕዝብ ዕድገት፣ ያረጁ የመሠረተ ልማት አውታሮች እና ያልተቀናጀ የከተማ ማስፋፋት ለረጅም ዓመታት የመዲናዋን ተወዳዳሪነት እና የነዋሪዎቿን የኑሮ ጥራት ሲፈታተኑ ቆይተዋል
❤11👍1
በሐረር ከተማ በግብርና ኢንቨስትመንት የተከናወኑ የልማት ሥራዎች ወደ አዲስ ምዕራፍ እየተሸጋገሩ ነው፡- ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ

በሐረር ከተማ በግብርና ኢንቨስትመንት የተከናወኑ የልማት ሥራዎች ወደ አዲስ ምዕራፍ እየተሸጋገሩ መሆናቸውን ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ ገለጹ::

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማኅበራዊ ትሥሥር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት እንደገለጹት፣ በአነስተኛ መነሻ ካፒታል የተጀመሩ ኢንቨስትመንቶችን በጥቂት ዓመታት ውስጥ የካፒታል አቅማቸውን ማሳደግ ተችሏል
❤6🙏1
የኢትዮጵያ አየር መንገድ እና የናይጄሪያው ኤር ፒስ በአፍሪካ እና በዓለም አቀፍ ደረጃ ያላቸውን የበረራ ትሥሥር የሚያጠናክር የጋራ ስምምነት ተፈራረሙ

የኢትዮጵያ አየር መንገድ እና የናይጄሪያው ኤር ፒስ (Air Peace) በአፍሪካ አህጉር እና በዓለም አቀፍ ደረጃ ያላቸውን የአየር ትራንስፖርት ትሥሥር ይበልጥ ለማጠናከር እና ለመንገደኞቻቸው ሰፊ የጉዞ ዕድሎችን ለመፍጠር የሚያስችላቸውን የሁለትዮሽ የጋራ የበረራ ስምምነት ተፈራርመዋል::

በዚህ የጋራ ስምምነት መሠረት፣ ሁለቱ አየር መንገዶች በመንገደኞች ጉዞ እና በሻንጣ አስተላልፍ አገልግሎት ላይ በጥምረት ይሠራሉ
❤18
የ'ኢሜጄ' እና የመደመር ፍልስፍናዎች፤ ለአየር ንብረት ለውጥ ፍቱን መፍትሔዎች

ዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ ለአየር ንብረት ለውጥ ዘላቂ ምላሽ ለመስጠት በቱርክዬ አንታሊያ ከተማ እያካሄደ ያለው COP31 ጉባኤ፣ ኢትዮጵያ የአየር ንብረት ዲፕሎማሲዋን ከተሳታፊነት ወደ አዘጋጅነት እና ተግባራዊ አርአያነት መሸጋገሯን ያሳየችበት መድረክ ሆኗል::

የዚህ ታሪካዊ ሽግግር እምብርት ደግሞ የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ‘የመደመር’ ፍልስፍና ነው
❤6🕊5🔥3
የኢትዮጵያ ባሕር በር ጥያቄ ምላሽ ማግኘት የሁለቱን ሀገራት ሕዝቦች የጋራ ተጠቃሚነት የሚያረጋግጥ ነው፡- ትውልደ ኤርትራዊው ንጉሰለተብረሃን ሱልጣን

የኢትዮጵያ የባሕር በር ጥያቄ ምላሽ ማግኘት የሁለቱን ሀገራት ሕዝቦች የጋራ ተጠቃሚነት የሚያረጋግጥ መሆኑን ትውልደ ኤርትራዊው ንጉሠለተብረሃን ሱልጣን ገልጿል::

ትውልደ ኤርትራዊው ንጉሠለተብረሃን ከኢቲቪ ጋር ባደረው ቆይታ፣ የኢትዮጵያ የባሕር በር ጥያቄ በባሕሩ ያላትን ታሪካዊ፣ ጂኦግራፊያዊ እና ፖለቲካዊ መብት በመሆኑ ህጋዊ ይዞታዋን “ይገባኛል” ሳይሆን “ይመለስልኝ” የሚል መሆን እንዳለበት አስረድቷል
❤4🙏4
የጋራ ድምፃችንን በማጠናከር፣ የአፍሪካ ከተሞችን የልማት ፍላጎት፣ የፋይናንስ ተደራሽነትና የቴክኖሎጂ ትብብር እናሳድጋለን፡- ከንቲባ አዳነች አቤቤ

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ በCOP31 በአንታሊያ ከአፍሪካ ልማት ባንክ የአየር ንብረት ለውጥ ዳይሬክተር ፕሮፌሰር አንቶኒ ኦኮን ንዮንግ እና የGlobal Covenant of Mayors አምባሳደር እና የፓሪስ ቀድሞ ከንቲባ አን ሂዳልጎ ጋር ተወያይተዋል::

ከንቲባዋ በማኅበራዊ ትሥሥር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት፣ ውይይታቸው በአዲስ አበባ የአየር ንብረት እና ዘላቂ የከተማ ልማት ጉዳዮች ዙሪያ ያተኮረ መሆኑን ገልጸዋል
❤10
የቢሾፍቱው ግዙፍ አውሮፕላን ማረፊያ እና የኢትዮጵያ ኢኮኖሚያዊ ሽግግር

የመደመር መንግሥት ኢትዮጵያን አጠቃላይ መዋቅራዊ ሽግግር ውስጥ ለማስገባት የያዘው ራዕይ በአሁኑ ወቅት በኮሪዶር ልማት፣ በኢንዱስትሪ፣ በግብርና እና በዲጂታል ቴክኖሎጂ ተጨባጭ ፍሬዎችን እያፈራ ይገኛል::

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የቢሾፍቱ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ግንባታ ማስጀመርያ ላይ “የዛሬ 10 ዓመት የአውሮፕላን ማረፊያ ግንባታ ሁለቱም ምዕራፎች እና በርካታ የጀመርናቸው ታላላቅ ፕሮጀክቶች ሲጠናቀቁ ኢትዮጵያ በአፍሪካ ቀዳሚውን ኢኮኖሚ ትገነባለች” በማለት ያደረጉት ንግግር የኢትዮጵያን የብልጽግና ጉዞ የሚያመላክት ነው
❤9🔥2
"የዛሬ 10 ዓመት የቢሾፍቱ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ግንባታ ሁለቱም ምዕራፎች እና በርካታ የጀመርናቸው ታላላቅ ፕሮጀክቶች ሲጠናቀቁ ኢትዮጵያ በአፍሪካ ቀዳሚውን ኢኮኖሚ ትገነባለች"

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)
❤16👏4🙏4
የ52 ሚሊየን ብር የሽልማት ውድድር

ነጋድራስ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የሥራ ፈጠራ ውድድር የአምስተኛ ምዕራፍ የፍፃሜ ውድድሩን እሑድ ኅዳር 6 ቀን በድምቀት ያከናውናል::

በፕሮግራሙ ላይ ኢንጂነር ፀደቀ ይሁኔን ጨምሮ የውድድሩ ዳኞች እና ሌሎች ሥራ ፈጣሪዎች ልምዳቸውን እያካፈሉ ውድድሩን ይመሩታል
❤10👍1
ግብፅ የዓባይ ተፋሰስ ሀገራትን ፍላጎት አክብራ አታውቅም፡- ሀብታሙ ኢተፋ (ዶ/ር)

የኢትዮጵያን ዘላቂ የኢኮኖሚ ዕድገት ማፋጠን፣ የውጭ ንግድ ፍሰትን ማሳደግ እና የዜጎችን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ የባሕር በር ባለቤትነትን ማረጋገጥ ከመደመር ታላቁ ስትራቴጂ አንዱ እና ዋነኛው አካል መሆኑን የውኃና ኢነርጂ ሚኒስትር ኢንጂነር ሀብታሙ ኢተፋ (ዶ/ር) ገለጹ::

ሚኒስትሩ እንዳሉት፣ ኢትዮጵያ የዓባይን ወንዝ የማልማት የዘመናት ቁጭት በታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ግንባታ እውን በማድረግ ታሪክ ጽፋለች
❤16🔥4
ከንቲባ አዳነች አቤቤ ከዩኤን ሃቢታት ዋና ዳይሬክተር አናክላውዲያ ሮስባክ ጋር ተወያዩ

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ ከዩኤን ሃቢታት ዋና ዳይሬክተር አናክላውዲያ ሮስባክ ጋር በአዲስ አበባ የከተማ ለውጥና ዘላቂ ልማት ዙሪያ ያለውን ትብብር ለማጠናከር መወያየታቸውን ገለጹ::

ከተማችን በሻንጋይ በተካሄደው የዓለም የከተሞች ቀን ያገኘችውን የዘላቂ የከተሞች ልማት ሽልማትና በሴኡል የተሰጣትን የስማርት ከተማ ዕውቅና በማስመልከት፣ የዩኤን ሃቢታት ዋና ዳይሬክተር እንኳን ደስ አላችሁ ማለታቸውን ገልጸው፣ እኛም ምስጋናችንን ገልጸናል ብለዋል
❤12🙏3🤩1
የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር እና የCOP32 ተመራጭ ፕሬዚዳንት ጌዲዎን ጢሞቴዎስ (ዶ/ር) ከታዳጊ ሀገራት (LDCs) ኃላፊዎች ጋር ተወያዩ

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር እና የCOP32 ተመራጭ ፕሬዚዳንት ጌዲዎን ጢሞቴዎስ (ዶ/ር) ከኮፕ 31 ጎን ለጎን ከታዳጊ ሀገራት (LDCs) ቡድን ሊቀመንበር እና የቲሞር-ሌስቴ አምባሳደር አዳኦ ሶአሬስ ባርቦሳ ጋር ተወያይተዋል::

በኢትዮጵያ ፓቪሊዮን በተካሄደው በዚህ ውይይት ሁለቱ ወገኖች የታዳጊ ሀገራትን ቅድሚያ የሚሰጧቸውን የኮፕ አጀንዳዎች እና ለCOP32 በሚደረጉ ቅድመ ዝግጅቶች ዙሪያ ፍሬያማ ምክክር አድርገዋል
❤20👍2