EBC (Ethiopian Broadcasting Corporation)
✔
132K subscribers
45.8K photos
484 videos
80 files
13.7K links
EBC (Ethiopian Broadcasting Corporation) @etvafaanoromoo1
@ETVkidschannel
@EBCWORLD1
@etventertainment1
Download Telegram
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከፕሬዝዳንት ረጅብ ጣይብ ኤርዶጋን ጋር ተወያዩ
******************

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በCOP31 የመሪዎች ጉባኤ ዋዜማ በቱርክዬ፣ አንታሊያ በመገኘት ከቱርክዬ ሪፐብሊክ ፕሬዝዳንት ረጅብ ጣይብ ኤርዶጋን ጋር ፍሬያማ ውይይት አድርገዋል።
‎
‎"በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለውን ጠንካራ አጋርነት መሠረት በማድረግ፣ የሁለትዮሽ ትብብራችንን የበለጠ ማጠናከር በሚቻልባቸው ዕድሎች ላይ ተወያይተናል" ብለዋል ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ በፌስቡክ ማኅበራዊ ትስስር ገጽ ባጋሩት መልዕክት።
‎
‎ጠቅላይ ሚኒስትሩ በውይይቱ ወቅት፣ COP31ን ለማስተናገድ ለተደረገው ዝግጅት እና ጉባኤው በድምቀትና በስኬት እንዲጠናቀቅ ቱርክዬ እያሳየችው ላለው ጥረት አድናቆታቸውን ገልጸዋል።
ሁለቱ መሪዎች በውይይታቸው፣ ኢትዮጵያ የCOP32 ፕሬዝዳንትነትን ለመረከብ በምታደርገው ዝግጅት ላይ የሚኖረውን አጋርነት እንዲሁም የጋራ ትኩረት በሚሹ ቀጣናዊ ጉዳዮች ዙሪያ ለመተባበር የሚያስችሉ ዕድሎችን ተመልክተዋል።

#Ethiopia #Turkiye #Antaliya #COP31 #PMAbiyAhmed #RecepTayyipErdoğan #EBC

https://web.facebook.com/share/p/1cZCVhTGEP/
❤33👍1🥰1
"ልማትና ውበት ለከተማ ብቻ አይደለም፤ የገጠሩ አርሶ አደርም ንጹሕ፣ ዘመናዊና ለኑሮ ምቹ በሆነ መንደር ውስጥ መኖር አለበት።" ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)
❤9🙏3
የኮፕ 32 ወደ ኢትዮጵያ መምጣት እና የአፍሪካ አየር ንብረት ድምፅ

በዓለም አቀፍ ደረጃ እየተባባሰ የመጣውን የአየር ንብረት ለውጥ ስጋት ለመመከት የሚደረገው የጋራ ምላሽ የጀመረው በ1980ዎቹ አጋማሽ ነበር::

ይህ ጥረት እ.አ.አ በ1992 በሪዮ ጉባኤ የተባበሩት መንግሥታት የአየር ንብረት ለውጥ ማዕቀፍ ስምምነት (UNFCCC) እንዲጸድቅ መንገድ የከፈተ ሲሆን፣ ስምምነቱ በ1994 በይፋ ሥራ ላይ ውሏል
❤12
ከበርሊን እስከ አዲስ አበባ የዘለቀው የዓለም የአየር ንብረት ለውጥ ጉባኤ የሦስት አሥርተ ዓመታት ታሪካዊ ጉዞ

ዓለማችን እየበረታባት በመጣው የአየር ንብረት ቀውስ ምክንያት ለከፋ ድርቅ፣ ለተደጋጋሚ ጎርፍ፣ ለከባድ አውሎ ነፋስ፣ ለሰደድ እሳት እንዲሁም ለመሬት መንሸራተት አደጋዎች ተጋልጣለች::

የሙቀት መጠኑ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ በመምጣቱ በርካታ ሀገራት በከፍተኛ የሙቀት ማዕበል እየተመቱ የሰው ልጆች ህይወት አልፏል፤ በሰሜን እና ደቡብ ዋልታዎች የሚገኘው የበረዶ ግግር መቅለጥ ደግሞ የባሕር ወለል መጠን እንዲጨምር በማድረግ የባሕር ዳርቻ ከተሞችን የመስመጥ አደጋ እንዲጋረጥባቸው ዳርጓቸዋል፤ ሌሎቹም በስጋት እንዲኖሩ ፈርዶባቸዋል
🙏5
ሀገራት የአየር ንብረት ቅድሚያ ተግባራቸውን እንዲያሳኩ የባለብዙ ወገን የአየር ንብረት ፈንዶችን ውጤታማነት ማሳደግ አስፈላጊ ነው-ፍፁም አሰፋ(ዶ/ር)

የኢትዮጵያ የገንዘብ ሚኒስትርና የCOP32 ዋና ተደራዳሪ ከCOP31 ጎን ለጎን “ባለብዙ ወገን የአየር ንብረት ፈንዶች፡ ለተሻለ ተደራሽነትና ለላቀ ተጽዕኖ በጋራ መሥራት” በሚል ርዕስ በተዘጋጀ መድረክ ላይ፣ ንግግር አድርገዋል::

በንግግራቸውም ዓለም አቀፍ ትብብርን ማጠናከር፣ የአየር ንብረት ፋይናንስ ተደራሽነትን ማስፋት፣ እንዲሁም ታዳጊ ሀገራት የአየር ንብረት ቅድሚያ ተግባራቸውን (climate priorities) እንዲያሳኩ በመደገፍ ረገድ የባለብዙ ወገን የአየር ንብረት ፈንዶችን ውጤታማነት ማሳደግ ያለውን አስፈላጊነት አጽንኦት ሰጥተዋል
❤7
የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የዴሞክራሲ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ በቀጣይ 5 ዓመታት የሥራ ዕቅድ ላይ ተወያየ

የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የዴሞክራሲ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ በሚመራበት የ5 ዓመታት ስትራቴጂያዊ ዕቅድ ላይ ከአባላቱ ጋር ውይይት አድርጓል::

ቋሚ ኮሚቴው በተሰጠው የክትትልና ቁጥጥር ኃላፊነት መሠረት የተቋማት ዕቅድ እና አፈጻጸም ከሕግ እና አሠራር እንዲሁም ከስትራቴጂው ጋር የተጣጣመ መሆኑን የማረጋገጥ ሥራ በትኩረት እንደሚሠራ የኮሚቴው ሰብሳቢ ወ/ሮ እፀገነት መንግሥቱ ገልጸዋል
❤8
ኢትዮጵያ በኮፕ-31 ጎን ለጎን በተካሄደ የውይይት መድረክ የአረንጓዴ ክህሎት እና የሥራ ዕድል ፈጠራ ቁርጠኝነቷን ገለጸች

በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የኮፕ-31 የአየር ንብረት ለውጥ ጉባኤ ጎን ለጎን በተካሄደው "ዝቅተኛ የካርቦን ኢኮኖሚን ለመገንባት ክህሎትን ማሳደግ እና የሥራ ዕድል ፈጠራን ማፋጠን" በተሰኘ መድረክ ላይ ኢትዮጵያ በአረንጓዴ ክህሎት ልማት ላይ ያላትን ቁርጠኝነት አረጋግጣለች::

በመድረኩ ላይ የተገኙት የብሔራዊ ስትራቴጂ ሚኒስትሩ አቶ በረከት ፍስሃጽዮን እንደገለጹት፣ ኢትዮጵያ በሰው ሀብት ልማት ላይ ኢንቨስት በማድረግ የወጣቶችን የሥራ ዕድል ለማስፋፋት እና ፍትሐዊ የሆነ አረንጓዴ የኢኮኖሚ ሽግግርን ለማረጋገጥ በትኩረት እየሠራች ይገኛል
❤13
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በCOP31 የመሪዎች ጉባኤ ጎን ለጎን ከባርቤዶስ ጠቅላይ ሚኒስትር ሚያ ሞትሊ ጋር ተወያዩ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በCOP31 የመሪዎች ጉባኤ ጎን ለጎን፣ ከባርቤዶስ ጠቅላይ ሚኒስትር ሚያ ሞትሊ ጋር ተወያይተዋል::

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማኅበራዊ ትሥሥር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት፣ ከባርቤዶስ ጠቅላይ ሚኒስትር ሚያ ሞትሊ ጋር በሁለቱ ሀገራት መካከል የጋራ ትኩረት በሚሹ ጉዳዮች ላይ መወያየታቸውን ገልጸዋል
❤19
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከፊንላንድ ፕሬዚዳንት አሌክሳንደር ስተብ ጋር ተወያዩ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከፊንላንድ ፕሬዚዳንት አሌክሳንደር ስተብ ጋር ከCOP31 የመሪዎች ጉባኤ ጎን ለጎን ተገናኝተው ተወያይተዋል::

‎ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማኅበራዊ ትሥሥር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት፣ ከፊንላንድ ፕሬዚዳንት አሌክሳንደር ስተብ ጋር ከዚህ በፊት በG20 ጉባኤ ወቅት ባካሄድነው የሁለትዮሽ ስብሰባችን ወቅት የተደረጉ ውይይቶችን ተግባራዊነት የተመለከተ ውይይት አድርገናል ብለዋል
👏7❤4
ከበርሊን እስከ አዲስ አበባ የዘለቀው የዓለም የአየር ንብረት ለውጥ ጉባኤ የሦስት አሥርተ ዓመታት ታሪካዊ ጉዞ

ዓለማችን እየበረታባት በመጣው የአየር ንብረት ቀውስ ምክንያት ለከፋ ድርቅ፣ ለተደጋጋሚ ጎርፍ፣ ለከባድ አውሎ ነፋስ፣ ለሰደድ እሳት እንዲሁም ለመሬት መንሸራተት አደጋዎች ተጋልጣለች::

የሙቀት መጠኑ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ በመምጣቱ በርካታ ሀገራት በከፍተኛ የሙቀት ማዕበል እየተመቱ የሰው ልጆች ህይወት አልፏል፤ በሰሜን እና ደቡብ ዋልታዎች የሚገኘው የበረዶ ግግር መቅለጥ ደግሞ የባሕር ወለል መጠን እንዲጨምር በማድረግ የባሕር ዳርቻ ከተሞችን የመስመጥ አደጋ እንዲጋረጥባቸው ዳርጓቸዋል፤ ሌሎቹም በስጋት እንዲኖሩ ፈርዶባቸዋል
❤7
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከኖርዌይ ጠቅላይ ሚኒስትር ጆናስ ጋህር ስተር ጋር ተወያዩ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከኖርዌይ ጠቅላይ ሚኒስትር ጆናስ ጋህር ስተር ጋር በCOP31 የመሪዎች ጉባኤ ጎን ለጎን የሁለትዮሽ ውይይት ማድረጋቸውን ገለጹ::

‌‎ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማኅበራዊ ትሥሥር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት፣ በውይይታቸው ወቅት በአረንጓዴ ዐሻራ መርሐ ግብር ያለውን ትብብር ማሳደግ፣ በኢትዮጵያ የታዳሽ ኃይል ዘርፍ ኢንቨስትመንትን ማበረታታት እና ኖርዌይ ኢትዮጵያ ለምትረከበው የCOP32 ፕሬዚዳንትነት የምታደርገውን ድጋፍ ማጠናከር በሚቻልባቸው ዕድሎች ላይ መምከራቸውን አመልክተዋል
❤10
የመቐለ ከተማ ባላደራ አስተዳደር በኮሪደር ልማት ፕሮጀክት ዙሪያ ከክፍለ ከተሞች አመራሮች ጋር ተወያየ

የመቐለ ከተማ ባላደራ አስተዳደር በኮሪደር ልማት ፕሮጀክት ዙሪያ ከከተማዋ ክፍለ ከተሞች አመራሮች ጋር ተወያይቷል::

ውይይቱን የመቐለ ከተማ ባላደራ አስተዳደር ከንቲባ ሺሻይ አማረ (ዶ/ር) እና የከተማዋ ኮሪደር ልማት ሥራ አስኪያጅ ኢንጂነር ፀጋዘአብ ኪዳኑ መርተውታል
❤9👍1
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከኢራቁ ፕሬዚዳንት ኒዛር አሚዲ ጋር ተወያዩ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከCOP31 የመሪዎች ጉባኤ ጎን ለጎን ከኢራቁ ፕሬዚዳንት ኒዛር አሚዲ ጋር መምከራቸውን አስታወቁ::

‌‎ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማኅበራዊ ትሥሥር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት፣ ከፕሬዚዳንቱ ጋር የሁለቱን ሀገራት የሁለትዮሽ ግንኙነታችንን ለማጠናከር እንዲሁም በልማት ትብብር ረገድ የጋራ አቅም ያላቸውን ዘርፎች ወደ ውጤት የመቀየር ሥራዎች ዙሪያ ፍሬያማ ውይይት አድርገናል ብለዋል
❤19🙏1
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከሶማሊያ ፕሬዚዳንት ጋር ተወያዩ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከሶማሊያ ፕሬዚዳንት ሐሰን ሼክ መሐሙድ ጋር ከCOP31 የመሪዎች ጉባኤ ቀደም ብለው ተገናኝተዋል::

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በመልዕክታቸው፣ "በሶማሊያ ወቅታዊ የደኅንነት ሁኔታና ሰፋ ባሉ ቀጣናዊ ጉዳዮች ዙሪያ ሃሳቦችን ተለዋውጠናል" ብለዋል
❤26🙏3👍1
ከንቲባ አዳነች አቤቤ ከህፃናት ኢንቨስትመንት ፈንድ ፋውንዴሽን ዋና ሥራ አስፈጻሚ ጋር ተወያዩ

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ ዛሬ ከCOP31 መድረክ ጎን ለጎን፣ ከህፃናት ኢንቨስትመንት ፈንድ ፋውንዴሽን (CIFF) ዋና ሥራ አስፈጻሚ ኬት ሃምፕተን ጋር ገንቢ ውይይት ማድረጋቸውን ገለጹ::

ከንቲባዋ ከዋና ሥራ አስፈጻሚ ሃምፕተን ጋር ኢትዮጵያ የCOP32 አዘጋጅ ሀገር እንደመሆኗ በትብብር ዕድሎች እንዲሁም በቆሻሻ አያያዝና አጠቃቀም፣ በአረንጓዴ ዐሻራ መርሐ ግብር፣ የአየር ንብረት ለውጥን መቋቋምና የከተሞች ትብብርን በማጠናከር ዙሪያ ተወያይተናል ብለዋል
❤8🙏6
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከቦትስዋናው ፕሬዚዳንት ዱማ ጌዲዮን ቦኮ ጋር ተወያዩ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በCOP31 የመሪዎች ጉባኤ ወቅት ከቦትስዋናው ፕሬዚዳንት ዱማ ጌዲዮን ቦኮ ጋር መወያየታቸውን ገለጹ::

‌‌‎ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማኅበራዊ ትሥሥር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት በውይይታቸው ወቅት ሁለቱ ሀገራት የተጋረጡባቸውን የጋራ የአየር ንብረት ለውጥ ተግዳሮቶችና እየወሰድናቸው ያሉትን ምላሾች ጨምሮ በCOP32 ላይ ትብብራችንን ለማጠናከር፣ ጠንካራ የአፍሪካ አየር ንብረት አጀንዳን ወደፊት ማስቀጠል እንዲሁም በሌሎች ሰፊ የሁለትዮሽ ትብብር መስኮች ላይ መክረናል ብለዋል
❤4
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በቱርክዬ ፕሬዝዳንት ረጅብ ጣይፕ ኤርዶጋን እና በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ዋና ጸሐፊ አንቶኒዮ ጉቴሬዝ የተደረገላቸው ሞቅ ያለ አቀባበል፤ ቀጣይነት ያለውን ግንኙነታቸውን እንዲሁም ለባለብዙ ወገን ትብብርና ለዓለም አቀፍ ዕድገት ያላቸውን የጋራ ቁርጠኝነት የሚያንጸባርቅ ነው።
👏7❤6
በCOP31 የመሪዎች ጉባኤ ላይ የአየር ንብረት ተግዳሮቶችን ለመፍታት የዓለም አቀፍ ትብብርና የጋራ ኃላፊነት አስፈላጊነትን የሚያንጸባርቅና ለዚሁ ግዙፍ ዓላማ የዓለም መሪዎች የጋራ ስብስብን የሚያሳይ ቅጽበት::
❤6👏5
"የአየር ንብረት ቃል ኪዳኖች ተደራሽ በሆነ ፋይናንስ፣ በጠንካራ የቅድመ ማስጠንቀቂያ ሥርዓትና ተጋላጭ ማኅበረሰቦችን በሚደግፍ ኢንቨስትመንት ወደ ተግባር መቀየር አለባቸው"
❤7
የኢትዮጵያ የታዳሽ ኃይል መሪነት እና የCOP32 ታሪካዊ ኃላፊነት

የኢንዱስትሪ አብዮት የፈጠረው የዘመነ ቴክኖሎጂ ለሰው ልጅ ዕድገት የላቀ አስተዋጽኦ ቢኖረውም የዕድገቱ መሠረት የሆኑት የኃይል ምንጮች ለአየር ንብረት መዛባት ዋነኛ መንስኤ ሆነዋል::

ግዙፎቹ ኢንዱስትሪዎች፣ የአምራች ዘርፎች እና የትራንስፖርት መዋቅሮች ይጠቀሙበት የነበረው የድንጋይ ከሰል፣ ነዳጅ እና የተፈጥሮ ጋዝ ከፍተኛ መጠን ያለው የካርቦን ዳይኦክሳይድ ልቀት ወደ ከባቢ አየር በመልቀቅ የዓለምን ሙቀት እጅግ ከፍ አድርጎታል
❤7