ኢትዮጵያ እና ኤዥያ ኢንፍራስትራክቸር ኢንቨስትመንት ባንክ አጋርነታቸውን ለማጠናከር ተወያዩ
የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር እና የCOP32 ተመራጭ ፕሬዚዳንት ጌዲዎን ጢሞቲዎስ (ዶ/ር) እንዲሁም የገንዘብ ሚኒስትር እና የCOP32 ዋና ተደራዳሪ ፍጹም አሰፋ (ዶ/ር) ከኤዥያ ኢንፍራስትራክቸር ኢንቨስትመንት ባንክ (AIIB) ፕሬዝደንት ዞ ጂያይ ጋር የአጋርነት ሥራዎችን ለማስቀጠል ያለመ ውጤታማ የሁለትዮሽ ውይይት አካሂደዋል::
በውይይቱ ወቅት ቀደም ሲል ተጀምሮ የነበረውን የቢሾፍቱ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ግንባታን ፋይናንስ የማድረግ ሂደት አጠናክሮ ለማስቀጠል፣ የረጅም ጊዜ አብሮ የመሥራት ዕድሎችን ለመፍጠር እና ሌሎች ስትራቴጂካዊ ፕሮጀክቶችን ለመቅረፅ የሚያስችሉ ሀሳቦች ላይ መክረዋል

👍6❤1
በአየር ንብረት ውሳኔዎች ላይ የተግባር ፈጣንነት እና ግልጽ የፋይናንስ ዋስትና ሊኖር ይገባል - ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ሀገራት ለአየር ንብረት ለውጥ የሚያደርጉት ድጋፍ እና የሚገቡት የፋይናንስ ቃል ኪዳን ግልጽ፣ አስቀድሞ የሚታወቅ እና ፈጣን ምላሽ የሚሰጥ መሆን እንዳለበት አሳሰቡ::
ጠቅላይ ሚኒስትሩ ባደረጉት ንግግር የፋይናንስ ድጋፎች "ምን ያህል? እስከ መቼ? በምን ዓይነት መመዘኛ?" ለሚሉት ሦስት ዋና ጥያቄዎች ግልጽ ምላሽ መስጠት አለባቸው ብለዋል

❤11👏1🙏1
ኢትዮጵያ አርሶ አደሮችን ከአየር ንብረት አደጋ ለመታደግ በሰው ሠራሽ አስተውሎት የታገዘ ሥርዓት እየተገበረች ነዉ፡- ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)
ተለዋዋጭ የአየር ጠባይ በግብርና እና በዜጎች ኑሮ ላይ የሚያደርሰውን ጉዳት አስቀድሞ ለመከላከል፣ የሳተላይት መረጃን እና ሰው ሠራሽ አስተውሎትን (AI) ያቀናጀ ዘመናዊ ሥርዓት እየተተገበረ መሆኑን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ገለጹ::
በቱርክዬ አንታሊያ ከተማ ‘ከቃላት ባለፈ ወደ ተግባርና አፈጻጸም መሸጋገር’ በሚል መሪ ሃሳብ 31ኛው የተባበሩት መንግሥታት የአየር ንብረት ለውጥ ጉባኤ (ኮፕ31) እየተካሄደ ነው

❤5👏1
አረንጓዴ ዛፍን የቆረጠ ራሱን እንዳጠፋ ይቆጠራል፡- ፕሬዚዳንት ኤርዶጋን
በቱርክዬ አንታሊያ እየተካሄደ ባለው ዓለም አቀፍ የአየር ንብረት ጉባኤ (COP31) ላይ ንግግር ያደረጉት የቱርክዬ ፕሬዚዳንት ረጅብ ጣይብ ኤርዶጋን ተፈጥሮን እና አካባቢን መጠበቅ ከሀገራቸው የሥልጣኔ እምብርት ጋር የተያያዘ ቅዱስ አደራ መሆኑን ገልጸዋል::
ፕሬዚዳንቱ አባቶቻቸው የዛፍን ሕይወት ከሰው ሕይወት ጋር በማነጻጸር "አረንጓዴ ዛፍን የቆረጠ ራሱን እንዳጠፋ ይቆጠራል" ይሉ እንደነበር በማስታወስ የተፈጥሮን ከፍተኛ ዋጋ አጉልተዋል

👏13❤7
የአረንጓዴ ዐሻራ እና የንጹህ ኢነርጂ ሽግግር የኢትዮጵያ አየር ንብረት ፍልስፍና ዋና ማዕከል ናቸው፡- ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)
ኢትዮጵያ የአየር ንብረት እርምጃን የኢኮኖሚ ፖሊሲዋ ዋና አካል በማድረግ የተፈጥሮ ሀብት እንክብካቤን፣ ዲጂታል ቴክኖሎጂን እና የታዳሽ ኃይል አጠቃቀምን አጣጥማ እየሠራች መሆኑን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) አስታወቁ::
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በ31ኛው የተባበሩት መንግሥታት የአየር ንብረት ለውጥ ጉባኤ (COP31) ላይ ባደረጉት ንግግር እንደገለጹት፤ በኢትዮጵያ የመደመር ፍልስፍና ሰዎችን፣ ተቋማትን እና ሀብትን ለአንድ የጋራ ዓላማ በማስተባበር ረገድ ከፍተኛ አስተዋጽኦ አበርክቷል

❤8🙏3
"የቅሪተ አካል ነዳጆች እንደ ዳይኖሰሮች መጥፋት አለባቸው" - አንቶኒዮ ጉቴሬዝ
በቱርክዬ አንታሊያ እየተካሄደ በሚገኘው 31ኛው የዓለም የአየር ንብረት ለውጥ ጉባኤ (COP31) ላይ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና ፀሐፊ አንቶኒዮ ጉቴሬዝ ጠንካራ መልዕክት አስተላልፈዋል::
ዋና ፀሐፊው በጉባኤው ላይ ባደረጉት ንግግር፤ የአየር ንብረት ለውጥን ለመከላከል በቁርጠኝነት የተወሰዱ እርምጃዎች እና የበለጸጉ ሀገራት በማደግ ላይ ላሉ ሀገራት የሚያደርጉት ድጋፍ በፈጠራና በቴክኖሎጂ የታገዘ መሆን እንዳለበት አሳስበዋል

🔥6❤1
ኢትዮጵያ የበኩሏን እየተወጣች ነው፤ ዓለምስ መቼ ወደ ተግባር ይገባል?
የዓለም የአየር ንብረት ለውጥ ቀውስ ከወደፊት ስጋትነት አልፎ የዛሬው ትውልድ የህልውና ፈተና በሆነበት በዚህ ወቅት ሀገራት ከቃላት ባለፈ ተጨባጭ የተግባር እርምጃ እንዲወስዱ የኢትዮጵያ መልዕክት በዓለም አቀፍ መድረኮች በጎላ ሁኔታ እየተደመጠ ነው::
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) እንዳሉት "መጪው ጊዜ ከአቅም በላይ ዋጋ የሚያስከፍል እንዳይሆን ለማድረግ፣ የበካይ ጋዝ ልቀትን በፍጥነት መቀነስ ያስፈልገናል ኢትዮጵያ የበኩሏን እየተወጣች ነው" ብለዋል

❤14🕊2
ዓለም የኢትዮጵያን ሕዝብ ቢከተል ምድራችን 3.58 ትሪሊዮን ችግኞች በኖራት ነበረ
ዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ በአየር ንብረት ለውጥ ዙሪያ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጠነከረ በሚመጣ አስደንጋጭ ቀውስ ውስጥ ይገኛል::
በቱርክ አንታሊያ እየተካሄደ በሚገኘው 31ኛው የተባበሩት መንግሥታት የአየር ንብረት ለውጥ ጉባኤ (COP31) ላይ እንደተስተዋለው የዓለም መንግሥታት የልቀት መጠንን ለመግታት የገቡት ቃል እና ያቀረቧቸው የድርጊት መርሐ ግብሮች ከእውነታው የራቁ እና የ30.7 ጊጋ ቶን ካርቦን ዳይኦክሳይድ ክፍተት ያለባቸው መሆናቸው ተጋልጧል

❤17