EBC (Ethiopian Broadcasting Corporation)
✔
132K subscribers
45.7K photos
484 videos
80 files
13.7K links
EBC (Ethiopian Broadcasting Corporation) @etvafaanoromoo1
@ETVkidschannel
@EBCWORLD1
@etventertainment1
Download Telegram
በዳካር 2026 የወጣቶች ኦሎምፒክ ውድድር ኢትዮጵያ አንደኛ ደረጃን በመያዝ ማጠናቀቋ የሚያኮራ ታሪካዊ ውጤት ነው፡- ከንቲባ አዳነች አቤቤ

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ በዳካር 2026 የወጣቶች ኦሎምፒክ ውድድር ኢትዮጵያ በአትሌቲክስ 5 የወርቅና 3 የብር በድምሩ 8 ሜዳሊያዎችን በማስመዝገብ በሜዳሊያ ሰንጠረዡ አንደኛ ደረጃን በመያዝ ማጠናቀቋ የሚያኮራ ታሪካዊ ውጤት መሆኑን ገለጹ::

ከንቲባዋ በማኅበራዊ ትሥሥር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት፣ ለዚህ ውጤት የበቃችሁ ወጣት አትሌቶቻችንን፣ አሰልጣኞቻችንንና የስፖርቱን ቤተሰብ በሙሉ እንኳን ደስ አላችሁ እላለሁ ብለዋል
❤27👏5👍1💯1
"የእኛ አባቶች ዓድዋ ላይ ገድል ሰርተዋል፤ እኔ እና እናንተ በአረንጓዴ ዐሻራ ሌላ ገድል እየሠራን ነው"

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)
❤18🙏4
የሥራ ፈጠራ አሸናፊዎች ሊሸለሙ ነው

ነጋድራስ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የሥራ ፈጠራ ውድድር የአምስተኛ ምዕራፍ የፍፃሜ ውድድሩን እሑድ ኅዳር 6 ቀን በድምቀት ያካሂዳል::

በፕሮግራሙ ላይ አቶ ፍፁም ንጉሤን ጨምሮ የውድድሩ ዳኞች እና ሌሎች ሥራ ፈጣሪዎች ልምዳቸውን እያካፈሉ ውድድሩን ይመሩታል
❤5👍2🔥2
በ"እኛ እና እነሱ" ትርክት ሳይሆን፣ በመደመር የምትቆም የጋራ ሀገር ኢትዮጵያ

እንደ ሀገር ሁለንተናዊ ብልጽግናችንን ለማረጋገጥ እና ዘላቂ ሰላምን ለመገንባት የዜጎችን የጋራ ራዕይ፣ የታሪክ አረዳድ እና የወደፊት ግብ በአንድ ዐቢይ ሀገራዊ አቅጣጫ ማስተሳሰር ወሳኝ ጉዳይ ነው::

ገዥ ትርክት ሕዝብን የሚከፋፍሉ ትርክቶችን አስወግዶ፣ በሀገር ፍቅር፣ በፍትሕ እና በጋራ ዕጣ ፈንታ ላይ የተመሠረተ የጋራ ማንነት ማዕቀፍ መፍጠር ነው
❤15👍7
የጂኦግራፊ እስረኝነትን የሚሰብረው የባሕር በር ራዕይ

ታዋቂው የጂኦፖለቲካ ተንታኝ ቲም ማርሻል "የጂኦግራፊ እስረኛ መሆን ድህነትን አሜን ብሎ መቀበል ነው" ሲል ያስቀመጠው እውነታ፣ የዛሬዋን ኢትዮጵያ ፈተናና የነገ ዕጣ ፈንታ በግልጽ ያሳያል::

ውኃ የሕይወት መገኛና የ21ኛው ክፍለ ዘመን የጂኦፖለቲካ መዘውር በሆነበት ዓለም፣ የኢትዮጵያ ሰላም፣ ልማት እና ቀጣይነት ከሁለት ታላላቅ የውኃ አካላት ማለትም ከዓባይ ወንዝ እና ከቀይ ባሕር ጋር በጥብቅ የተቆራኘ ነው
❤15🙏4
ኑ ቡና ጠጡ!

የሰው ልጅ ታሪክ ሲጻፍ ማኅበራዊ ትስስር፣ መከባበር እና የጋራ ኑሮ የጀመሩባቸውን ምዕራፎች የሚጠቁሙ ልዩ ምልክቶችን ያስቀምጣል::

ኢትዮጵያ የምድረ ቀደምት እና የቡና መገኛ በመሆን ለዓለም አቀፍ ባህል ያበረከተችው አስተዋጽኦ እንዲሁ በታሪክ ምዕራፍ ሰፍሯል
❤5
የገንዘብ ሚኒስትር እና የCOP32 ዋና ተደራዳሪ ፍጹም አሰፋ (ዶ/ር ) ከዓለም ባንክ ቡድን ዋና ዳይሬክተር እና ቺፍ ኖውሌጅ ኦፊሰር ጋር ተወያዩ

በአንታሊያ፣ ቱርክዬ እየተካሄደ ካለው የCOP31 ጉባኤ ጎን ለጎን፣ የኢትዮጵያ የገንዘብ ሚኒስትር እና የCOP32 ዋና ተደራዳሪ ፍጹም አሰፋ (ዶ/ር )፣ ከዓለም ባንክ ቡድን ዋና ዳይሬክተር እና ቺፍ ኖውሌጅ ኦፊሰር (Chief Knowledge Officer) ጋር የሁለትዮሽ ውይይት አካሂደዋል::

በውይይቱም ከCOP32 ዝግጅት አንጻር በሁለቱ ወገኖች መካከል ያለውን ትብብር ስለማጠናከር ያካተተ ሲሆን፣ በተጨማሪም በኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎች (ኢ-ሞቢሊቲ)፣ በአየር ንብረት ፋይናንስ፣ በአየር ንብረት ለውጥ ምላሽ ተግባራዊ አፈጻጸም እንዲሁም ከካርቦን ክሬዲት ጋር በተያያዙ ጉዳዮች ላይ ሀሳብ ተለዋውጠዋል
❤9👍2
የውጭ ጉዳይ ሚኒስትርና የCOP32 ተመራጭ ፕሬዚዳንት ጌዲዮን ጢሞቲዎስ (ዶ/ር) ከሩዋንዳ ሪፐብሊክ የአካባቢ ጥበቃ ሚኒስትር ጋር ተወያዩ

የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትርና የCOP32 ተመራጭ ፕሬዚዳንት ጌዲዮን ጢሞቲዎስ (ዶ/ር)፣ ከሩዋንዳ ሪፐብሊክ የአካባቢ ጥበቃ ሚኒስትር ዶ/ር በርናዴት አራክዊዬ ጋር ለCOP32 ዝግጅት ትብብርን ለማጠናከር ሁለትዮሽ ውይይት አካሂደዋል::

ሁለቱ ወገኖች በጋራ ቅድሚያ በተሰጣቸው ጉዳዮች ላይ በቅርበት ለመሥራትና ለሁሉም አካላት ትርጉም ያላቸው ውጤቶችን የሚያስገኝ የተሳካ COP32 እንዲኖር ጥረቶቻቸውን ለማስተባበር ተስማምተዋል
👍6❤4
የብሔራዊ ስትራቴጂ ሚኒስትር በረከት ፍስሀጽዮን ከኤንዲሲ አጋርነት ድርጅት ዓለም አቀፍ ዳይሬክተር ፓብሎ ኤ. ቪዬራ (ዶ/ር) ጋር ተወያዩ

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ስትራቴጂ ሚኒስትር በረከት ፍስሀጽዮን በአንታሊያ ቱርክ እየተካሄደ ባለው 31ኛው የተባበሩት መንግሥታት የአየር ንብረት ጉባኤ (COP31) ከኤንዲሲ አጋርነት ድርጅት (NDC Partnership) ዓለም አቀፍ ዳይሬክተር ዶ/ር ፓብሎ ኤ. ቪዬራ ጋር በኢትዮጵያ ፓቪሊዮን የሁለትዮሽ ውይይት አካሄዱ::

ውይይቱ ኢትዮጵያ በኅዳር 2020ዓ.ም ለምታስተናግደው 32ኛው የአየር ንብረት ጉባኤ (COP32) ዝግጅት አንጻር ስትራቴጂያዊ ትብብርን ለማጠናከር ያለመ ነው
❤6🙏2
የውጭ ጉዳይ ሚኒስትርና የCOP32 ተመራጭ ፕሬዚዳንት ጌዲዮን ጢሞቲዎስ (ዶ/ር) ከካሊፎርኒያ ገዢ ጋቪን ኒውሰም ጋር ተወያዩ

በCOP31 የመሪዎች ጉባኤ ሁለተኛ ቀን፣ የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትርና የCOP32 ተመራጭ ፕሬዚዳንት ጌዲዎን ጢሞቲዎስ (ዶ/ር) ከካሊፎርኒያ ገዢ ጋቪን ኒውሰም ጋር ተገናኝተው ተወያይተዋል::

ገዢው ኢትዮጵያ የCOP32 አዘጋጅ ሀገር ሆና በመመረጧ እንኳን ደስ አላችሁ በማለት የሀገሪቱን ቀጣይ የአየር ንብረት ተነሳሽነቶች አድንቀዋል
❤5🙏1
ማርታ ዓለማየሁ በዓለም አትሌቲክስ የዓመቱ ምርጥ ታዳጊ ኮከብ አትሌት ሽልማት በሴቶች የመጨረሻ 3 ዕጩዎች ውስጥ ተካተተች

ኢትዮጵያዊቷ ታዳጊ አትሌት ማርታ ዓለማየሁ፣ የዓለም አትሌቲክስ ባዘጋጀው የ2026 የዓመቱ ምርጥ ታዳጊ ሴት ኮከብ ወይም 'ራይዚንግ ስታር' ምርጫ የመጨረሻ 3 ዕጩዎች ዝርዝር ውስጥ ተካተተች::

​የዓለም አትሌቲክስ ዛሬ ይፋ ባደረገው ዝርዝር ዕጩዎቹ ዘንድሮ ከ20 ዓመት በታች ውድድሮች ላይ ላሳዩት ድንቅ ብቃት እውቅና ለመስጠት መመረጣቸውን አስታውቋል
❤6🔥2
ቀይ ባሕር ለኢትዮጵያ የደህንነቷ ካስማ እና የሁለንተናዊ ብልጽግናዋ ሞተር ነው

ኢትዮጵያ እና የቀይ ባሕር አካባቢ በጂኦግራፊ፣ በታሪክ እና በባህል የተጋመዱ፣ ዕጣ ፈንታቸው የተሳሰረ የአንድ ሳንቲም ሁለት ገጽታዎች ናቸው::

ትውልዱ የባሕር በር ጥያቄ ማንሳቱን አንዳንዶች እንደ ወቅታዊ የፖለቲካ አጀንዳ ሊያስመስሉት ቢሞክሩም፣ እውነታው ግን ኢትዮጵያ እና ቀይ ባሕር የሺህ ዘመናት ታሪካዊ ቁርኝት እና የማይነጣጠል የጋራ ሕልውና ያላቸው መሆኑ ነው
❤27👍13🥰1
በመቐለ ከተማ ኮሪደር ልማት ፕሮጀክት ዙሪያ ከሃይማኖት መሪዎችና ሀገር ሽማግሌዎች ጋር ውይይት ተካሄደ

በትግራይ ክልል መቐለ ከተማ የሃይማኖት መሪዎች እና የሀገር ሽማግሌዎች በተገኙበት በኮሪደር ልማት ዙሪያ ውይይት ተካሂዷል::

በውይይቱ በትግራይ ክልል ባለአደራ አስተዳደር የመቐለ ከተማ ከንቲባ ሺሻይ አማረ (ዶ/ር) እና የከተማዋ ኮሪደር ልማት ፕሮጀክት ዋና ሥራ አስኪያጅ ኢንጂነር ፀጋዘኣብ ኪዳኑ ተገኝተው ማብራሪያና ገለፃ አድርገዋል
❤14👍3
የኦቢኤን የቀድሞ ዋና ዳይሬክተር አቶ ግዛቸው ገቢሳ ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ

የኦሮሚያ ብሮድካስቲንግ ኔትወርክ (ኦቢኤን) የቀድሞ ዋና ዳይሬክተር አቶ ግዛቸው ገቢሳ በሕመም ምክንያት ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተዋል::

አቶ ግዛቸው በኦሮሚያ ራዲዮ እና ቴሌቪዥን ድርጅት ውስጥ ከሪፖርተር እስከ ዋና አዘጋጅነት፣ በኦሮሚያ ኮሙኒኬሽን ቢሮ እና በብልጽግና ፓርቲ የኦሮሚያ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት የሕዝብ ግንኙነት እና የሕዝብ አስተያየት ዘርፍ ኃላፊ በመሆን አገልግለዋል
😢10❤7👍1
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት የዜጎችን የኤሌክትሪክ ኃይል ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ የሚያደርገውን ጥረት አጠናክሮ ይቀጥላል

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት በ2019 በጀት ዓመት ጥቅምት ወር ውስጥ የኤሌክትሪክ ኃይል ተዳራሽነትን ለማስፋፋት ባከናወናቸው ተግባራት 16 ከተሞችንና መንደሮችን የኤሌክትሪክ ኃይል ተጠቃሚ ማድረግ መቻሉን ገለጸ::

አገልግሎቱ ባከናወነው የኃይል መስመር ዝርጋታ ሥራ በዋናው መረብ 15 ከተሞች እንዲሁም በኦፍ ግሪድ አማራጭ 1 ከተማ በድምሩ 16 ከተሞችና መንደሮች የኤሌክትሪክ አገልግሎት ተጠቃሚ ማድረጉን ነው የገለጸው
❤15
የትግራይ ክልል ባለአደራ አመራር ከደቡብ ምስራቅ ዞን አመራሮች ጋር እየተወያየ ነው

የትግራይ ክልል ባለአደራ አመራር ከደቡብ ምስራቅ ዞን አመራሮች ጋር እየተወያየ ይገኛል::

በባለአደራ አስተዳደሩ የኢኮኖሚና መልሶ ግንባታ ዋና ሥራ አስፈፃሚ ቴዎድሮስ አረጋይ (ዶ/ር) በውይይቱ መክፈቻ ላይ ባደረጉት ንግግር፣ ሕዝብን ያማከለ ሥራ በመሠራቱ በክልሉ ተጨባጭ ለውጦች መምጣታቸውን ተናግረዋል
❤6👍6
በ5 ዓመታት ውስጥ ቤቶችን ገንብተን ለማስረከብ ለሕዝባችን የገባነውን ቃል በተግባር ለማረጋገጥ ቀን ከሌት ያለ እረፍት እየተጋን እንገኛለን - ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ሕዝቡ በመኖሪያ ቤት እጥረት ምክንያት የሚገጥመውን ፈተናና ስጋት በሚገባ እንደሚረዱ ገልጸዋል፡፡

"ደረጃቸውን የጠበቁ እና በተመጣጣኝ ዋጋ የሚቀርቡ መኖሪያ ቤቶችን ማመቻቸት የልማት ግብ ብቻ ሳይሆን፣ ለዜጎቻችን ያለብን አደራና ኃላፊነት መሆኑንም ጠንቅቀን እንገነዘባለን" ብለዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በመልዕክታቸው የመንግሥታቸው ዋና ትኩረት ተጨባጭ ውጤት በማስመዝገብ፣ የሕዝብን የመኖሪያ ቤት ጫና ማቃለል እና በመላው ሀገራችን ለሚገኙ ቤተሰቦች የተሻለ የኑሮ ምዕራፍ መክፈት መሆኑን ገልጸዋል፡፡


አክለውም፣ "በአምስት ዓመታት ውስጥ ቤቶችን ገንብተን ለማስረከብ ለሕዝባችን የተገባውን ቃል በተግባር ለማረጋገጥም ቀን ከሌት ያለ እረፍት እየተጋን እንገኛለን" ሲሉ አጽንኦት ሰጥተዋል፡፡
❤14👏12🆒2
"በአምስት ዓመታት ውስጥ ቤቶችን ገንብተን ለማስረከብ ለሕዝባችን ቃል ገብተናል፤ ይህንንም ቃላችንን በተግባር ለማረጋገጥ ቀን ከሌት ያለ እረፍት እየተጋን እንገኛለን"

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)
🙏6❤3
በምዕራብ ኦሮሚያ እና ቤኒሻንጉል ጉሙዝ ሕዝቦች መካከል የቆየውን የአብሮነት እሴት ለማጠናከር እየተሠራ ነው - ኮሚሽነር እድሪስ መሐመድ

የቤኒሻንጉል ጉሙዝ እና የኦሮሚያ ክልል አጎራባች ወረዳዎች የጸጥታ ምክር ቤት በወቅታዊ የሰላም እና ጸጥታ ጉዳዮች ዙሪያ በአሶሳ ከተማ የምክክር መድረክ አካሂዷል::

በመድረኩ ላይ የተገኙት የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር እድሪስ መሐመድ በሁለቱ ወንድማማች ሕዝቦች መካከል ለዘመናት የቆየውን የአብሮነት እሴት ከመቼውም ጊዜ በላይ ማጠናከር እንደሚገባ አስገንዝበዋል
❤10
በአዲስ አበባ በ21 ሳይቶች 100 ሺህ ቤቶችን እየገነባን ነው፡- ከንቲባ አዳነች አቤቤ

ከጉባ ብስራቶች አንዱ እንደ ሀገር በአምስት ዓመታት ውስጥ 1.5 ሚሊዮን ቤቶችን ለዜጎቻችን ለማስረከብ የገባነው ቃል ነው ሲሉ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ ገለጹ::

ከንቲባዋ በማኅበራዊ ትሥሥር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት፣ እንደ አዲስ አበባ በ21 ሳይቶች 100 ሺህ ቤቶችን እየገነባን ነው ብለዋል
❤7🙏7