በሴኔጋል ዳካር የወጣቶች ኦሊምፒክ በአትሌቲክስ ከዓለም አንደኛ ሆኖ ላጠናቀቀው የኢትዮጵያ ልዑክ አቀባበል ተደረገ
በአፍሪካ ምድር ለመጀመሪያ ጊዜ በሴኔጋል መዲና ዳካር በተካሄደው አራተኛው የወጣቶች ኦሊምፒክ ላይ ተሳትፎ የሜዳሊያ ሰንጠረዡን በቀዳሚነት ያጠናቀቀው የኢትዮጵያ ወጣቶች አትሌቲክስ ልዑክ አዲስ አበባ ገብቷል::
ልዑኩ ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርስ የወጣቶችና ስፖርት ሚኒስትር አክሊሉ ታደሰ(ዶ/ር)፣ የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ ፕሬዝዳንት ዶክተር አሸብር ወልደጊዮርጊስ፣ ፣ የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ፕሬዝዳንት ኮማንደር ስለሺ ስህን፣ የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን ፕሬዝዳንት አቶ ኢሳያስ ጅራ እንዲሁም ሌሎች ከፍተኛ የመንግስት የስራ ኃላፊዎች፣ የፌዴሬሽኖች አመራሮች በተገኙበት አቀባበል አድርገውላቸዋል

❤21👏2
ፕሬዚዳንት ታዬ አጽቀ ሥላሴ ለ32 ሰዎች የባለ ሙሉ ሥልጣን የአምባሳደርነት ሹመት ሰጡ።
ፕሬዚዳንት ታየ አጽቀ ሥላሴ በሕገ-መንግሥቱ አንቀጽ 71 ንዑስ አንቀጽ 3 መሠረት፡-
1. አቶ ታገሰ ጫፎ
2. አቶ አገኘሁ ተሻገር
3. አቶ ዛዲግ አብርሃ
4. አምባ. ሲራጅ ራሺድ ጁንዲ
5. አምባ. መለስ ዓለም ተክኤ
6. አምባ. አንተነህ ዓለሙ ሰንበቴ
7. አምባ. ዘሪሁን አበባ ይግዛው
8. አቶ መላኩ አለበል
9. ዶ/ር ኤርጎጌ ተስፋዬ
10. ዶ/ር ስንታየሁ ወ/ሚካኤል
11. ዶ/ር ሰማን ጥሩነህ
12. ፕ/ር መስፍን አርአያ
13. ዶ/ር ካሣሁን ጎፌ
14. ዶ/ር ዓለሙ ስሜ
15. አቶ አዳም ተስፋዬ አበራ
16. አቶ አምኃ ኃ/ጊዮርጊስ አየለ
17. አቶ ሳሙኤል አዲስ ዓለማየሁ
18. አቶ በላቸው አንሺሶ ኬምበጫ
19. አቶ አበበ መብራቱ ክብረት
20. አቶ መለኩ በዳዳ ሰንበታ
21. ወ/ሮ ዑባህ መሐመድ ሁሴን
22. አቶ ዳንኤል ጠንክር አረጋ
23. ዶ/ር አምባዬ ኦጋቶ
24. ወ/ሮ ወርቅነሽ ብሩ
25. ዶ/ር ዮናስ አዳዬ
26. አቶ መለኩ ፈንታ ባልቻ
27. አቶ ዣንጥራር አባይ
28. አቶ ተመስገን ጥላሁን
29. አቶ ታደለ ነጊሾ
30. አቶ ዘሪሁን መገርሳ ጅማ
31. አቶ ሽመልስ አዱኛ ባልቻ
32. አቶ አብዱራህማን ጀማል ኑርልኝ
ባለ ሙሉ ሥልጣን አምባሳደርነት የሾሙ መሆኑን የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ፕሬዚዳንት ጽ/ቤት አስታውቋል፡፡

❤21👍9👏6
የአየር ንብረት ትግበራ ድልድይ ስትራቴጂ ይፋ ተደረገ
የኢትዮጵያ የገንዘብ ሚኒስትር እና የCOP32 ዋና ተደራዳሪ ፍጹም አሰፋ (ዶ/ር )፣ ሀገራት የአየር ንብረት ጥበቃ እርምጃ ቃል ኪዳኖቻቸውን በኢንቨስትመንት ሊደገፉ ወደሚችሉ ፕሮጀክቶችና ተጨባጭ ተግባራት ለመቀየር የሚያግዝ የCOP31 ፕሬዚዳንሲ ውጤት የሆነውን የአየር ንብረት ትግበራ ድልድይ (Climate Implementation - BRIDGE) ይፋ የማድረግ ሥነ-ሥርዓት ላይ ተሳትፈዋል::
በይፋዊ ማስጀመሪያው ላይ ከBRIDGE የመጀመሪያ ቡድን አባል ሀገራት የመጡ ሚኒስትሮች፣ የተባበሩት መንግሥታት የልማት ፕሮግራም (UNDP) እና የብዙ ወገን የልማት ባንኮች (multilateral development banks) ተወካዮች በመገኘት ፕሮግራሙ ቅድሚያ ሊሰጣቸው በሚገቡ ጉዳዮችና በጋራ ቁርጠኝነቶች ላይ ስትራቴጂያዊ ውይይት አካሂደዋል

❤7👍4
ዓለም አቀፍ የበጎ አድራጎት ተቋማት ለCOP32 ስኬት ከኢትዮጵያ ጎን በመቆም የድርድር ውጤቶችን ወደ ተግባር እንዲቀይሩ ጥሪ ቀረበ
የገንዘብ ሚኒስትር እና የCOP32 ዋና ተደራዳሪ ፍጹም አሰፋ (ዶ/ር) ወደ COP32 በሚደረገው ጉዞ ላይ በአጋርነትና በድጋፍ ዙሪያ ከዓለም አቀፍ የበጎ አድራጎት ዘርፍ መሪዎች ጋር የውይይት መድረክ መርተዋል::
ሚኒስትሯ በመድረኩ ላይ COP32 ለባለብዙ ወገን ትብብር ወሳኝ ምዕራፍ መሆኑን ጠቅሰው፣ የአየር ንብረት ጥበቃ ርምጃዎችንና ልማትን በተቀናጀ መንገድ ማስኬድ እንደሚቻል አጽንኦት ሰጥተዋል

❤7
Forwarded from EBC SPORT
"ኢትዮጵያ አሸናፊ ሆና የዘለቀች እና ዓለምን በሚያስደምም መንገድ ያሸነፈች ሀገር ነች" - አክሊሉ ታደሰ(ዶ/ር)
****
የኢፌዴሪ ወጣቶችና ስፖርት ሚኒስትር አክሊሉ ታደሰ(ዶ/ር)፣ ዳካር ላይ በዓለም ወጣቶች ኦሊምፒክ ደማቅ ታሪክ የሰሩት ወጣት አትሌቶች ሁሌም አሸናፊ የሆነችውን ኢትዮጵያን በሚገባ መወከላቸውን ተናገሩ።
ሚኒስትሩ በስካይ ላይት ሆቴል በተዘጋጀው የዕውቅና መድረክ ላይ ባደረጉት ንግግር፤ "ኢትዮጵያ ሁሌም አሸናፊ ሆና የዘለቀች እና ዓለምን በሚያስደምም መንገድ ያሸነፈች ሀገር ነች" ብለዋል።
አያይዘውም ወጣቶቹ አትሌቶች የሚወክሏት ሀገር ከሌሎች የተለየች መሆኗን በማንሳት፣ በአትሌቲክሱ ከዓለም አንደኛ ሆነው በማጠናቀቃቸው የተሰማቸውን ከፍተኛ ኩራት ገልጸዋል።
በዳካር የወጣቶች ኦሊምፒክ የተመዘገበው አንጸባራቂ ድል ለዛሬው ወጣት ትውልድ ትልቅ ስንቅ እና መልዕክት የሚሰጥ መሆኑንም አስታውቀዋል።
ሚኒስትሩ በስነ ስርዓቱ ላይ እንዳብራሩት፤ አትሌቶቹ ያመጡት 5 የወርቅ እና 3 የብር ሜዳሊያዎች ለሌሎች ወጣቶች መነሳሳትን ይፈጥራል።
"አዲሱ ትውልድ ከእነዚህ አትሌቶች ሀገራችን በዘመኗ ሁሉ፣ በሁሉም መስክ አሸናፊነትን ስታበረክት የቆየች መሆኗን ማየቱ፣ ለዛሬው ትውልድ ትልቅ መልዕክት የሚያስተላልፍ ነው" ሲሉም የአሸናፊነት መንፈሱ ተጠናክሮ እንዲቀጥል አሳስበዋል።
በእሱባለው ተሾመ
#EBC #Ethiopia #YouthOlympicGames #Dakar #athletics #sports

❤4👏4🥰2🤣1
ፈጣሪ እጆች በፋይናንስ እጦት አይታሠሩም!
**************
ለውጥ የሚያመጣ፣ ጉድለትን የሚሞላ፣ መፍትሄ የሚያበጅ ሀሳብ ያላቸው
ሀሳባቸው ወደተግባር ገብቶ ያለሙት ተሳክቶ ሥራ ፈጥረው ራሳቸውን ጠቅመው፣ ለወገን ለሀገር ለመትረፍ አንድ ነገር ይጎድላቸው ነበር። ፋይናንስ።
“ነጋድራስ” ሀሳባቸውን ይዘው ቁጭ ያሉ የፈጣሪ አእምሮ ባለቤቶችን ወደፊት ለማምጣት እውን ሆነ።
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ እኔ እያለሁ ፈጣሪ እጆችማ በፋይናንስ እጦት አይታሠሩም አለ።
እነሆ “ነጋድራስ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የሥራ ፈጠራ ውድድር” ከኢቢሲ ጋር በመተባበር ሚሊየነሮችን እያፈራ አምስተኛው ምእራፍ ላይ ደረሰ።
ባለፉት ሶስት ዙሮች የሥራ ፈጠራቸው ላሸነፈ ተወዳዳሪዎች ያለማስያዣ 150 ሚሊዮን ብር ብድር ያመቻቸው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ፣ አሁንም ለአምስተኛው ዙር አሸናፊዎች 50 ሚሊዮን ብር ብድር ያለማስያዣ አመቻችቷል።
እሁድ ህዳር 6 ቀን 2019 ዓ.ም ሚሊየነሮቹ ይለያሉ።

❤10