EBC (Ethiopian Broadcasting Corporation)
✔
132K subscribers
45.6K photos
484 videos
80 files
13.7K links
EBC (Ethiopian Broadcasting Corporation) @etvafaanoromoo1
@ETVkidschannel
@EBCWORLD1
@etventertainment1
Download Telegram
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) አትሌቶቻችን በሴኔጋል ዳካር ላስመዘገቡት አስደናቂና ታሪካዊ ድል የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክት አስተላለፉ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በመልዕእካተው ለወጣት ኢትዮጵያውያን አትሌቶቻችን በሴኔጋል ዳካር በተካሄደው የ2026 የወጣቶች ኦሊምፒክ ጨዋታዎች ላይ ላስመዘገቡት አስደናቂና ታሪካዊ ድል ከልብ የመነጨ የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክቴን ላስተላልፍ እወዳለሁ ብለዋል::

5 የወርቅ እና 3 የብር ሜዳሊያዎችን ጨምሮ በአጠቃላይ 8 ሜዳሊያዎችን በማግኘት የአትሌቲክስ የሜዳሊያ ሰንጠረዡን በ1ኛነት መምራታቸው፣ የኢትዮጵያን ጥልቅ የስፖርት ተሰጥኦ እና በአትሌቲክሱ ዘርፍ ያላትን ታላቅነት በድጋሚ ያረጋገጠ ነው ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ የኢትዮጵያን ሰንደቅ ዓላማ በክብር ከፍ አድርጋችሁ ማውለብለባችሁን እንዲሁም አዲሱን ትውልድ ለላቀ ድል እንዲተጋ ማነሳሳታችሁን ቀጥሉ! ሲሉ መልዕእታቸውን አስተላልፈዋል
❤37👍7👏3
"የአየር ንብረት ጥበቃን ከብሔራዊ ልማት ጋር ማቀናጀት ወሳኝ ነው" - ፍጹም አሰፋ (ዶ/ር)

የኢትዮጵያ የገንዘብ ሚኒስትር እና የCOP32 ዋና ተደራዳሪ ፍጹም አሰፋ (ዶ/ር)፣ በአንታሊያ እየተካሄደ በሚገኘው የCOP31 ጉባኤ ጎን ለጎን በተዘጋጀ ከፍተኛ ደረጃ የውይይት መድረክ ላይ ተሳትፈው ንግግር አደረጉ::

ሚኒስትሯ በንግግራቸው የኢትዮጵያን ተሞክሮ ለተሳታፊዎች ያካፈሉ ሲሆን፣ የአየር ንብረት ጥበቃ ርምጃዎችን ከብሔራዊ የልማት አጀንዳ፣ ከኢንቨስትመንት እና ከኢኮኖሚያዊ የመቋቋም አቅም ጋር በተቀናጀ መንገድ የማስፈጸምን አስፈላጊነት በሰፊው አብራርተዋል
❤9🙏2
የኢትዮጵያ የፕሮጀክት አፈጻጸም አዲስ ምዕራፍ

የኢትዮጵያ የልማት እና የፕሮጀክት አፈጻጸም ጉዞ ከቀደምት ጥልቅ መዋቅራዊ ችግሮች ተላቅቆ ወደ አዲስ እና አስተማማኝ ምዕራፍ ተሸጋግሯል::

በቀድሞ ጊዜ በልማት ፕሮጀክቶች ላይ ከፍተኛ የመንግሥት ኢንቨስትመንት ቢደረግም፣ በቂ የአዋጭነት ጥናት እና የረጅም ጊዜ የፋይናንስ ዋስትና ሳይኖር በመጀመራቸው ከፍተኛ የሀብት ብክነት እና የጊዜ መጓተት ያጋጥም ነበር
❤10👏4
የኢሬቻ በዓል በጋምቤላ ተከበረ

በኦሮሞ ሕዝብ ዘንድ ትልቅ ስፍራ የሚሰጠው የኢሬቻ በዓል የተራራቀው የሚቀራረብበት የእርቅ፣ የምስጋና እና የአብሮነት በዓል በመሆኑ ሁሉም ብሔር፣ ብሔረሰቦች ያለ ልዮነት በጋራ ያከብሩታል::

በየዓመቱ የክረምቱን መውጣት ተከትሎ በተለያዩ አካባቢዎች በድምቀት የሚከበረው የኢሬቻ በዓል፣ በጋምቤላ ከተማ "ኢሬቻ ለሀገራዊ መግባባት" በሚል መሪ ቃል በፓናል ውይይት ተከብሯል
❤7🔥2
የኢትዮጵያ የገንዘብ ሚኒስትርና የCOP32 ዋና ተደራዳሪ ፍጹም አሰፋ (ዶ/ር) ከካናዳ የአካባቢ፣ የአየር ንብረት ለውጥና ተፈጥሮ ጥበቃ ሚኒስትር ጁሊ ዳብሩዚን ጋር ተወያዩ

የኢትዮጵያ የገንዘብ ሚኒስትርና የCOP32 ዋና ተደራዳሪ ፍጹም አሰፋ (ዶ/ር)፣ ከካናዳ የአካባቢ፣ የአየር ንብረት ለውጥና ተፈጥሮ ጥበቃ ሚኒስትር ጁሊ ዳብሩዚን ጋር በአየር ንብረት ለውጥ ላይ ያተኮረ የሁለትዮሽ ትብብርና አጋርነትን ስለማጠናከር ተወያይተዋል::

ውይይቱ የአየር ንብረት ለውጥ ተግዳሮቶችን በጋራ ለመቋቋም፣ የአየር ንብረት መቋቋም አቅምን ለማጠናከርና ዘላቂ ልማትን ለማረጋገጥ በጋራ የተለዩ ቅድሚያ ጉዳዮችን ለማራመድ ትብብርን በማጠናከር ላይ ያተኮረ ሲሆን፣ የኢትዮጵያን የCOP32 ራዕይ ለማሳካት በጋራ ለመሥራት ያለውን ቁርጠኝነትም አረጋግጧል
❤14
"መደመር ያለፈውን በጎ ነገር ጠብቆ፣ የጎደለውን ሞልቶ፣ ስህተቱን አርሞ ለነገው ትውልድ የበለጸገች ሀገር ማስረከብ ማለት ነው።" ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)
🙏10❤5
5ኛው ዙር የ"ነጋድራስ" የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሥራ ፈጠራ ውድድር ዛሬ ፍጻሜውን ያገኛል

የኢትዮጵያ ብርቱ አዕምሮዎችንና ሥራ ፈጣሪዎችን አቅም በመገንባት ሀገራዊ ተጽዕኖ እያመጣ የሚገኘው የ"ነጋድራስ" የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የሥራ ፈጠራ ውድድር አምስተኛ ምዕራፍ በዛሬው ዕለት ፍጻሜውን ያገኛል::

ውድድሩ በኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን እና በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ትብብር የሚካሄድ ሲሆን፣ ወጣቶች ከሥራ ጠባቂነት ወጥተው የየሥራ ባለቤቶች እንዲሆኑ ትልቅ በር የከፈተ ነው
❤10🔥1🥰1
የአዲስ አበባ የወንዞች ዳርቻዎችና የኮሪደር ልማት ከተማዋን ከዘመናዊ ልማት ጋር በማዋሃድ አዲስ የከተማ ህይወትን እየፈጠሩ ነው

የአዲስ አበባ ከተማ የወንዞች ዳርቻዎችና የኮሪደር ልማት ለቱሪስቶች የመስህብ ማዕከል፣ ለስፖርተኞችና ለነዋሪዎች የጤናና የእንቅስቃሴ ስፍራ፣ ለማኅበራዊ ትሥሥር መድረክ፣ ለኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴም አዲስ ዕድል ሆነዋል::

ይህ የአካታችነት፣ የውበትና የልማት ትሥሥር የአዲስ አበባን የስበት ማዕከልነት ከሀገር አልፎ ለዓለም አቀፍ ማኅበረሰብ እያስተዋወቀ መሆኑን የከተማ አስተዳደሩ ከንቲባ ጽሕፈት ቤት መረጃ ያመላክታል
❤15🙏4🤣1
በዓመት 3 ሚሊዮን ሜትሪክ ቶን የዩሪያ ማዳበሪያ የሚያመርተው ግዙፍ ፕሮጀክት

ግብርና የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ የጀርባ አጥንት በመሆኑ የምግብ ዋስትናን ከማረጋገጥ ባለፈ ለኢንዱስትሪው ግብዓት በማቅረብ እና የውጭ ምንዛሪ በማስገኘት ረገድ ያለው ድርሻ የማይተካ ነው::

ይህንን ዘርፍ በዘላቂነት ለማዘመን እና ምርታማነትን በከፍተኛ ደረጃ ለማሳደግ ለዓመታት ትልቅ ተግዳሮት ሆኖ የቆየው የአፈር ማዳበሪያ አቅርቦት እጥረት ነው
❤15
ነጋድራስ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የሥራ ፈጠራ ውድድር የአሸናፊዎች መመዘኛ መስፈርቶች
👍6❤3
የዛሬዋ ታዳሚ የነገዋ አዘጋጅ ሀገር ኢትዮጵያ ከኮፕ 31 ጉባኤ እየቀሰመች ያለው ልምድ

በቱርክዬ አንታሊያ እየተካሄደ የሚገኘው 31ኛው የተባበሩት መንግሥታት የአየር ንብረት ለውጥ ጉባኤ COP31፣ ኢትዮጵያ በመጪው ዓመት በአዲስ አበባ ለምታስተናግደው COP32 ጉባኤ ወሳኝ የልምድ ማግኛ እና ስትራቴጂያዊ የዝግጅት ምዕራፍ ሆኗል::

በጉባኤው ላይ የተገኙት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የኢትዮጵያን የአረንጓዴ አሻራ መርሐ ግብር ስኬቶች፣ የንጹህ ኢነርጂ መሠረተ ልማት ግንባታ ተሞክሮዎች እንዲሁም የቀጣይ በካይ ጋዝ ልቀት ስጋቶችና መፍትሄዎችን ለዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ አጋርተዋል
🔥8❤1
በትግራይ ክልል በተፈጠረው ሰላም የተቋረጡ አገልግሎቶች በመመለሳቸው ደስተኞች ነን፡- ነዋሪዎች

በትግራይ ክልል የመንግሥት ሠራተኞች ደመወዝ መከፈል መጀመሩን ጨምሮ፣ ለተፈናቃዮች ሰብዓዊ እርዳታ ለማዳረስ ቅድመ ዝግጅቶች መደረጋቸው በነዋሪዎች ዘንድ ትልቅ ደስታን ፈጥሯል::

በመቐሌ ከተማ በተካሄደ ሕዝባዊ ውይይት ላይ የተገኙ ነዋሪዎች እና የሃይማኖት አባቶች ባለአደራ አስተዳደሩ እና መንግሥት የጀመሩት የሰላም ጉዞ አበረታች መሆኑን አንስተዋል
❤33👍7
በሳዑዲ ዓረቢያ በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ የነበሩ 2 ሺህ 86 ኢትዮጵያውያን ወደ ሀገራቸው ተመለሱ

በሳዑዲ ዓረቢያ በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ የነበሩ 2 ሺህ 86 ኢትዮጵያውያን ወደ ሀገራቸው ተመልሰዋል::

በሳምንቱ ውስጥ በተደረገ 9 ዙር በረራ የተመለሱት 1 ሺህ 664 ወንዶች፣ 387 ሴቶች እና 35 ህፃናት ሲሆኑ ከተመላሾች መካከል 63 እድሜያቸው ከአስራ ስምንት ዓመት በታች የሆኑ ታዳጊዎች ይገኙበታል
❤12🙏3
ልማት በሰው ልጅ ክብር ሲለካ

የአንድ ሀገር ዕድገት እና ብልጽግና የሚለካው ባላት የተፈጥሮ ሀብት እና በምትገነባቸው ግዙፍ ፕሮጀክቶች ብቻ አይደለም::

እነዚህ ሀብቶች እና መሠረተ ልማቶች የዜጎችን የዕለት ተዕለት ሕይወት፣ ክብር እና መሠረታዊ ፍላጎት የሚመልሱ ሰው ተኮር ሲሆኑ ብቻ ሀገር በትክክለኛው የብልጽግና ጎዳና ላይ ትራመዳለች
❤8🙏1
የኢትዮጵያ የማይናወጥ የዲፕሎማሲ ጉዞ እና ቀጣናዊ የልዕልና ምዕራፍ

ኢትዮጵያ የአፍሪካ የነፃነት እና የሉዓላዊነት ምልክት ሆና በጽናት በመዝለቅ ከዘመናዊው ዓለም አቀፍ የዲፕሎማሲ ሥርዓት ጋር በጥልቀት ተሳስራ ታሪካዊ የዲፕሎማሲ ማዕከልነቷን አስቀጥላለች::

በአውሮፓ የቅኝ ግዛት ማዕበል መካከል በዓድዋ ድል ነፃነቷን በማስከበር ለዓለም አቀፍ ሕግና ለጋራ ደኅንነት የነበራትን ቁርጠኝነት በተግባር አሳይታለች
❤7🙏5
መርካቶ የበጎነት መንደር፦ ማኅበራዊ ፍትህ በተግባር፣ የዜጎች ሕይወት በእውነት ሲቀየር

በመርካቶ የበጎነት መንደር/በቅጠል ተራ የተገነቡት ዘጠኝ የመኖሪያ ቤት ሕንፃዎች ከተራ የግንባታ ሥራ በላይ፣ የዜጎችን የኑሮ ሁኔታ የሚቀይሩ፣ የቤተሰቦችን ተስፋ የሚያድሱና የማኅበራዊ ፍትህን በተግባር የሚያረጋግጡ የመደመር መንግሥት ቁርጠኝነት ማሳያዎች ናቸው::

የቤት ችግርን መቅረፍ ማለት የአንድን ቤተሰብ ነገ መገንባት፣ የልጆችን የተሻለ ዕድል ማረጋገጥ፣ የኑሮ ደኅንነትን ማጠናከርና የአካባቢውን ማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ ኑሮ ማነቃቃት ነው
❤12🙏3
ወደ ልማት ምዕራፍ እየተሸጋገረች የምትገኘው ትግራይ

ህገ-ወጡ የሕወሓት ቡድን በትግራይ ሕዝብ ላይ የፈጸመው ጥፋትና ያስከተለው የፈተና ጊዜ እጅግ ከባድ ነበር::

ይሁን እንጂ ዛሬ የትግራይ ሕዝብ ከዚህ የጥፋት አዙሪት በመውጣት ለሰላም እና ለልማት አዲስ ምዕራፍ ከፍቷል
❤9🙏1
የኢትዮጵያን ዓለም አቀፍ ገጽታና የኢንቨስትመንት መስህብ እየቀየሩ የሚገኙ ሀገራዊ ፕሮጀክቶች

ኢትዮጵያ የዘመናት ታሪክ፣ የደመቀ ባህል እና የበለጸገ የተፈጥሮ ሀብት ባለቤት ብትሆንም፣ እነዚህን ጸጋዎች ወደ ተጨባጭ የኢኮኖሚና የቱሪዝም ገቢ በመቀየር ረገድ የመሠረተ ልማት ውስንነትና የመዳረሻዎች አለመልማት ዓብይ ማነቆ ሆነው ቆይተዋል::

ባለፉት ጥቂት ዓመታት ግን ይህንን ነባራዊ ሁኔታ ለመለወጥ ያለሙት የኮሪደር ልማት፣ ገበታ ለሀገር እና ገበታ ለትውልድ የተሰኙ ሦስት የተሳሰሩ ሀገራዊ ኢኒሼቲቮች በኢትዮጵያ የልማት ምኅዳር ላይ አዲስ ምዕራፍ ከፍተዋል
❤5🔥5🙏1
COP32 ብሔራዊ ጥረቶቻችንን ወደ ዘላቂ ውጤት ለመለወጥ ትልቅ ዕድል ይፈጥራል፡- ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ዛሬ ጠዋት የCOP32 ብሔራዊ አስተባባሪ ኮሚቴን በመሰብሰብ አጠቃላይ የሥራ ሂደት መገምገማቸውን አስታውቀዋል::

ጠቅላይ ሚኒሰትሩ በማኅበራዊ ትሥሥር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት፣ በግምገማው ወቅት የCOP32 ዝግጅቶችን ከፈትሽን በኋላም ሥራዎች የሚመሩበት ስትራቴጂካዊ አቅጣጫ ሰጥቻለሁ ብለዋል
👍10❤6
በመቐለ ከተማ በሚከናወነው የኮሪደር ልማት ፕሮጀክት ዙሪያ ከመቐለ ዩኒቨርሲቲ ምሁራን እና አመራሮች ጋር ውይይት ተካሄደ

በመቐለ ከተማ በሚከናወነው የኮሪደር ልማት ፕሮጀክት ዙሪያ ከመቐለ ዩኒቨርሲቲ ከተውጣጡ ምሁራን፣ ተመራማሪዎች እና የዩኒቨርሲቲው አመራር አካላት ጋር ውይይት ተካሂዷል::

ውይይቱ የከተማዋን ነባራዊ ገጽታ ማሻሻል፣ የዕድገት ፍጥነቷን ማሳደግ እና ለነዋሪዎች ምቹ የሆነ ዘመናዊ መሠረተ ልማት እውን ማድረግ በሚያስችሉ ሐሳቦች ላይ ያተኮረ ነው
❤18👏7