EBC (Ethiopian Broadcasting Corporation)
✔
132K subscribers
45.6K photos
484 videos
80 files
13.7K links
EBC (Ethiopian Broadcasting Corporation) @etvafaanoromoo1
@ETVkidschannel
@EBCWORLD1
@etventertainment1
Download Telegram
የመገጭ ግድብ እውነታዎች

‎👉በአማራ ክልል ማዕከላዊ ጎንደር ዞን የሚገኝ የውኃ ማጠራቀሚያ እና የመስኖ ልማት ፕሮጀክት ነው
‎
‎ 👉 ጥቅምት 13 ቀን 2019 ዓ.ም በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ተመርቋል::

‎
‎👉 ውኃ የመያዝ አቅም 185 ሚሊዮን ኪዩቢክ ሜትር ነው
❤6🙏1
አረንጓዴ ዐሻራ፡- ኢትዮጵያ ለዓለም ያበረከተችው ብቸኛው የፈተና ማለፊያ

የዓለም የአየር ንብረት ለውጥ ጉዳይ ከንግግር ወደ ተጨባጭ ተግባር እንዲሸጋገር ግንባር ቀደም ሚና እየተጫወተች የምትገኘው ኢትዮጵያ የ32ኛው አየር ንብረት ለውጥ ጉባኤ (COP32) አዘጋጅነትን ስትረከብ ይዛው የቀረበችው ዋነኛ ስንቅ በተግባር የተፈተነውን የአረንጓዴ ዐሻራ ታሪካዊ ድል ነው::

ዓለም በአስቸጋሪ የአየር ንብረት መዛባት እየተፈተነች ባለችበት ወቅት፣ ኢትዮጵያ ተግባራዊ እርምጃን በመውሰድ ለአፍሪካ ብሎም ለተቀረው ዓለም ትልቅ አብነት መሆን ችላለች
❤5🙏4
በመቐለ ከተማ 5 ሺህ 500 የቀድሞ ታጣቂዎች ለአንድ ወር ሲሰጥ የቆየውን የተሃድሶ ሥልጠና አጠናቀቁ

በመቐለ ከተማ ለአንድ ወር የተሃድሶ ሥልጠና ሲወስዱ የቆዩ 5 ሺህ 500 የቀድሞ ታጣቂዎች ሥልጠናቸውን አጠናቅቀዋል::

በትግራይ ክልል ከ47 ሺህ በላይ የቀድሞ ታጣቂዎች ለተሃድሶ ሥልጠና መመዝገባቸው ይታወቃል
❤27🙏1
የአዲስ አበባ ነዋሪዎችን ክብር የመለሰው የልማት ጉዞ

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በከተማዋ እየተከናወኑ ባሉ ሰፊ የመልሶ ማልማት ሥራዎች የዜጎችን ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት እና የኑሮ ጥራት ማሻሻል ላይ ከፍተኛ ትኩረት ሰጥቶ እየሠራ ይገኛል::

እነዚህ ሁለገብ የልማት እርምጃዎች የከተማዋን ነዋሪዎች ማኅበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ህይወት ከፍ የሚያደርጉ አዳዲስ መሠረተ ልማቶችን እውን እያደረጉ ናቸው
🙏7
COP32 እና የአየር ንብረት ዲፕሎማሲ ለሀገራችን ልማትና ኢንቨስትመንት ያለው አበርክቶ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በዛሬው ዕለት የ32ኛው የተባበሩት መንግሥታት የአየር ንብረት ለውጥ ጉባኤ (COP32) ብሔራዊ አስተባባሪ ኮሚቴን በመሰብሰብ አጠቃላይ የሥራ ሂደት መገምገማቸውን ገልጸዋል::

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በዚሁ ወቅት ጉባኤው ለኢትዮጵያ ያለውን ዘርፈ ብዙ ፋይዳ አስመልክተው በሰጡት ማብራሪያ፣ COP32 ታላቅ ዓለም አቀፍ መድረክ ከመሆኑ ባለፈ ሀገራችን የአየር ንብረትና የአካባቢ ጥበቃ አጀንዳዎቿን የምታራምድበት፣ ዓለም አቀፍ አጋርነቷን የምታጠናክርበት፣ ኢንቨስትመንትን የምትስብበት እንዲሁም ብሔራዊ ጥረቶቿን ወደ ዘላቂ ውጤት የምትለውጥበት ትልቅ ዕድል እንደሚፈጥር አስገንዝበዋል
❤14👍2
የአጉል ተልዕኮ ሰለባ እየሆኑ ያሉ ወጣቶች ወደ ሰላማዊ መንገድ እንዲመጡ አቶ ጌታቸው ረዳ ጥሪ አቀረቡ

የጠቅላይ ሚኒስትሩ የምስራቅ አፍሪካ ጉዳዮች አማካሪ ሚኒስትር ጌታቸው ረዳ በህገ ወጡ የህወሓት ቡድን አጉል ተልዕኮ ሰለባ እየሆኑ ያሉ ወጣቶች ወደ ሰላማዊ መንገድ እንዲመጡ ጥሪ አቅርበዋል::

አቶ ጌታቸው ይህንን ያሉት በመቐለ የተሃድሶ ማሰልጠኛ ማዕከል ሥልጠና ሲወስዱ የነበሩ የቀድሞ ታጣቂዎች ሥልጠና ማጠናቀቂያ መርሐ ግብር ላይ በተገኙበት ወቅት ነው
❤13🙏5👍1
በመቐለ የተሃድሶ ሥልጠና የወሰዱ የቀድሞ ታጣቂዎች የሥራ ዕድል እንዲያገኙ ይሠራል - አቶ አወሉ አብዲ

በመቐለ የተሃድሶ ሥልጠና የወሰዱ የቀድሞ ታጣቂዎች በሀገር ውስጥ እና በውጭ ሀገራት ባሉ የሥራ ዕድሎች ተጠቃሚ እንዲሆኑ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመተባበር እንደሚሠሩ የሥራና ክህሎት ሚኒስትር አቶ አወሉ አብዲ ተናግረዋል::

ሚኒስትሩ ይህን የገለጹት ከጠቅላይ ሚኒስትሩ የምሥራቅ አፍሪካ ጉዳዮች አማካሪ ሚኒስትር አቶ ጌታቸው ረዳ ጋር በመቐለ የተሃድሶ ሥልጠናቸውን ያጠናቀቁ የቀድሞ ታጣቂዎችን በጎበኙበት እና ከተሳታፊዎቹ ጋር በተወያዩበት ወቅት ነው
👏8❤2
በመቐለ የተሃድሶ ሥልጠና የወሰዱ የቀድሞ ታጣቂዎች የሥራ ዕድል እንዲያገኙ ይሠራል - አቶ አወሉ አብዲ

በመቐለ የተሃድሶ ሥልጠና የወሰዱ የቀድሞ ታጣቂዎች በሀገር ውስጥ እና በውጭ ሀገራት ባሉ የሥራ ዕድሎች ተጠቃሚ እንዲሆኑ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመተባበር እንደሚሠሩ የሥራና ክህሎት ሚኒስትር አቶ አወሉ አብዲ ተናግረዋል::

ሚኒስትሩ ይህን የገለጹት ከጠቅላይ ሚኒስትሩ የምሥራቅ አፍሪካ ጉዳዮች አማካሪ ሚኒስትር አቶ ጌታቸው ረዳ ጋር በመቐለ የተሃድሶ ሥልጠናቸውን ያጠናቀቁ የቀድሞ ታጣቂዎችን በጎበኙበት እና ከተሳታፊዎቹ ጋር በተወያዩበት ወቅት ነው
👍5❤3
የቦረና ብሔራዊ ፓርክ፡ ሌላው የኢትዮጵያ የቱሪዝም ሀብት መገለጫ

ከአዲስ አበባ ከተማ 640 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ የሚገኘው የቦረና ብሔራዊ ፓርክ፣ በደቡባዊ ኦሮሚያ ዞን በሰፊ መልክዓ ምድሩ እና በበለጸገ የዱር እንስሳት ሀብቱ የኢትዮጵያ ድንቅ የተፈጥሮ ስጦታ ነው::

የመደመር መንግሥት የቱሪዝም ዘርፉን ከኢኮኖሚው ዋና ምሰሶዎች አንዱ በማድረግ የተፈጥሮና የባህል ሀብቶችን ለማልማት በሰጠው ልዩ ትኩረት፣ እንደ ቦረና ብሔራዊ ፓርክ ያሉ ያልተነኩ የቱሪስት መዳረሻዎችን የመጠበቅና የማስተዋወቅተግባር ተጠናክሮ ቀጥሏል
❤8👍4👌1
አዲስ አበባ በተለይ በህጻናት መዝናኛ ረገድ በአጭር ጊዜ ያከናወነችው የአካቶ ትግበራ ሥራ አርዓያነት ያለው ነው - የጀርመኗ ላይፕዚሽ የልዑካን ቡድን አባላት

አዲስ አበባ በአካታች የከተማ ልማት ሥራዎች ያላትን ተሞክሮ ለጀርመኗ እህት ከተማ ላይፕዚሽ የምታጋራበት የልምድ ልውውጥ መድረክ በመካሄድ ላይ ይገኛል::

በመዲናዋ አስተዳደር ሴቶችና ወጣቶችን እንዲሁም አካል ጉዳተኞችን ጨምሮ ልዩ ፍላጎት ያላቸውን የኅብረተሰብ ክፍሎች በልማት፣ በትምህርትና በሥራ ዕድል ፈጠራ ተጠቃሚ ለማድረግ የአካቶ ትግብራ ሥራዎች በትኩረት እየተከናወኑ ይገኛሉ
❤4👏4
ኢትዮጵያ የኮፕ 32 ጉባኤን በተሳካ ሁኔታ የማስተናገድ አቅም አላት - አምባሳደሮች

ኢትዮጵያ በቀጣይ ዓመት የሚካሄደውን 32ኛውን የተባበሩት መንግሥታት የአየር ንብረት ለውጥ ጉባኤ (COP32) በብቃት እና በስኬት የማስተናገድ ሙሉ አቅም እንዳላት በኢትዮጵያ የቱርክዬ እና የአውስትራሊያ አምባሳደሮች ገልጸዋል::

ዘንድሮ 31ኛው ምዕራፍ ላይ የደረሰው ዓመታዊው የተባበሩት መንግሥታት የአየር ንብረት ለውጥ ጉባኤ (COP31) በቱርክዬ አንታሊያ እየተካሄደ ይገኛል
👏9
ብልጽግና ፓርቲ እና የሩስያው ‘ዩናይትድ ራሽያ’ ፓርቲ የተፈራረሙት የስትራቴጂያዊ አጋርነት ስምምነት

የስትራቴጂያዊ አጋርነት ስምምነቱን የብልጽግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዚዳንት እና የዋና ጽህፈት ቤት ኃላፊ አደም ፋራህ እና የ‘ዩናይትድ ራሽያ’ ፓርቲ ጠቅላይ ምክር ቤት ጸሐፊ እና የፓርቲው ጽ/ቤት ኃላፊ ቭላድሚር ያኩሼቭ ፈርመውታል::

“ለሕዝቦች ነፃነት!” ከተሰኘው ሩስያ መራሽ የፓርቲዎች የጋራ ንቅናቄ ጠቅላላ ጉባኤ ጎን ለጎን በሞስኮ የተፈረመው ስምምነት፣ ከዓድዋ ድል ጀምሮ የዘለቀውን የኢትዮጵያና የሩስያ ታሪካዊ ወዳጅነት እና በሉዓላዊነት ላይ የተመሠረተ አጋርነት ወደ ላቀ ተቋማዊ ምዕራፍ ለማሸጋገር ያለመ ነው
❤24👍5🔥3
ኢትዮጵያ ያስመዘገበቻቸውን የአየር ንብረት ለውጥ ምላሽ ውጤቶች በዓለም አቀፍ መድረክ አቀረበች

በቱርክ አንታሊያ እየተካሄደ በሚገኘው 31ኛው የተባበሩት መንግሥታት የአየር ንብረት ለውጥ ጉባኤ (COP31) ላይ ኢትዮጵያ ባለፈው አንድ ዓመት ውስጥ ዝቅተኛ የካርቦን ልቀት እና የአየር ንብረት ተቋቋሚነት ያለው ኢኮኖሚ በመገንባት ረገድ ያስመዘገበቻቸውን ተጨባጭ ውጤቶችና የቀጣይ የትኩረት አቅጣጫዎች ይፋ አድርጋለች::

በCOP31 የኢትዮጵያ ፓቪሊዮን በብሔራዊ ስትራቴጂ ሚኒስቴር አዘጋጅነት “ከቤሌም እስከ አንታሊያ፦ ዝቅተኛ የካርቦን ልቀትና የአየር ንብረት ተቋቋሚ ኢኮኖሚ በመገንባት የኢትዮጵያ ጉዞ” በሚል መሪ ቃል በተካሄደው ከፍተኛ የግምገማ መድረክ፣ የኢትዮጵያ መንግሥት እና የልማት አጋሮች ተወካዮች ተገኝተዋል
❤14🙏2
የኢትዮጵያን ምርት እና አገልግሎት ለአሜሪካዊያን እና የቢዝነስ ማኅበረሰብ ለማስተዋወቅ ያለመ የቡና ፌስቲቫል ተካሄደ

የኢትዮጵያን ቡና የሚያስተዋውቅ “Taste of Ethiopian Coffee” የተባለ ፌስቲቫል ዋሽንግተን ዲሲ በሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ የአሜሪካ ዜጎች እና ትውልደ ኢትዮጵያውያን በተገኙበት በድምቀት ተካሂዷል::

ፌስቲቫሉ የኢትዮጵያን ምርት እና አገልግሎት ለአሜሪካዊያን ዜጎች እና የቢዝነስ ማኅበረሰብ የማስተዋወቅ እና የገበያ ትሥሥር ለመፍጠር ያለመ መሆኑ ተገልጿል
❤9🙏2
የዋልያዎቹን የአፍሪካ ዋንጫ ጉዞ መልክ የሚቀይረው ጨዋታ ዛሬ ይደረጋል

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ከሞዛምቢክ ጋር የሚያደርገውን ወሳኝ ጨዋታ ዛሬ በባሕር ዳር ዓለም አቀፍ ስታዲየም ያደርጋል::

በምድብ 10 የተደለደለው ብሔራዊ ቡድኑ የማጣሪያ ውድድሩን በመጀመሪያዎቹ ሁለት ጨዋታዎች ተሸንፎ መጀመሩ በብዙ መልኩ ተስፋ ሚያስቆርጥ ይመስል ነበር
❤8🔥2👏1
የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ልዑካን እና የተለያዩ ሀገራት አምባሳደሮች መቐለ ገቡ

‎ልዑካኑ በአሉላ አባነጋ ዓለም አቀፍ መቐለ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ የትግራይ ክልል ባለአደራ አስተዳደር ዋና ሥራ አስፈፃሚዎች እና የመቐለ ከተማ ከንቲባ ሺሻይ አማረ (ዶ/ር) እና ሌሎች የባለአደራ አስተዳደሩ ከፍተኛ አመራሮች አቀባበል አድርገውላቸዋል::

‎የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ልኡካን ከዛሬ ኅዳር 8 ጀምሮ ለሁለት ቀናት የሚቆይ ኦፊሴላዊ የሥራ ጉብኝት በመቐለ ከተማ ያካሂዳሉ
🙏5❤3
ፕሬዚዳንት ታዬ አጽቀ ሥላሴ በኢትዮጵያ አዲስ የተሾሙ የ16 ሀገራት አምባሳደሮች የሹመት ደብዳቤ ዛሬ ይቀበላሉ

የኢፌዴሪ ፕሬዚዳንት ታዬ አጽቀ ሥላሴ በኢትዮጵያ አዲስ የተሾሙ የ16 ሀገራት አምባሳደሮች የሹመት ደብዳቤ ዛሬ በብሔራዊ ቤተመንግሥት ይቀበላሉ::

በመርሐ ግብር ከአፍሪካ፣ ከእስያ፣ ከመካከለኛው ምሥራቅ፣ ከአውሮፓ እና ከካሪቢያን ሀገራት የተወከሉ ተሿሚ አምባሳደሮች በክብር ዘብና በማርሽ ባንድ ሥነ ሥርዓት ታጅበው ደብዳቤያቸውን ያቀርባሉ
👏5👍3
በመቐለ ከተማ የተጀመረውን የንግድ እንቅስቃሴ በዘላቂነት ለማስቀጠል ውይይት ተካሄደ

በመቐለ ከተማ ከተማዋ የተጀመረውን የንግድ እንቅስቃሴ በዘላቂነት ለማስቀጠል፣ ሕገወጥ ንግድን ለመከላከል እና የንግዱ ማኅበረሰብ በሙሉ አቅሙ ወደ ሥራ እንዲገባ የሚያስችሉ ጉዳዮች ላይ ከሰባቱ ክፍለ ከተሞች የንግድ እና የመንግሥት አገልግሎት ኃላፊዎች ጋር ውይይት ተካሂዷል::

በውይይቱ ላይ የተገኙት በትግራይ ክልል ባለአደራ አስተዳደር የመቐለ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ እና የመንግሥት አገልግሎት ዘርፍ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ አቶ ገብረሕይወት ገብረሥላሴ ናቸው
❤6👍2
የነዋሪዎችን የኑሮ ጫና በተግባር የሚቀንሱ የገበያ ማዕከላት

በከተማችን አዲስ አበባ የዜጎችን የዕለት ተዕለት ፍጆታ በተመጣጣኝ ዋጋ ማሟላት የሚያስችል ሁኔታ እየተመቻቸ ነው::

ይህንን መርህ በተግባር የሚያሳየው የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር፣ በከተማዋ በተለያዩ አካባቢዎች የግብርናና የኢንዱስትሪ ምርቶች በቀጥታ ለሸማቾች የሚቀርቡባቸውን የገበያ ማዕከላትንና የቅዳሜና እሑድ ገበያዎች ተደራጅተዋል
👍5
የኢትዮጵያን የሰላም ማስከበር ሚና ለማስቀጠል የሚያስችሉ ስትራቴጂያዊ አቅጣጫዎች ላይ ምክክር እየተደረገ ነው

የኢትዮጵያን የሰላም ማስከበር ሚና ለማስቀጠል የሚያስችሉ ስትራቴጂያዊ አቅጣጫዎች ላይ ምክክር እየተደረገ ይገኛል::

ምክክሩን በመከላከያ ሠራዊት የሰላም ማስከበር ማዕከል የዓለም አቀፍ ሰላም ማስከበር ማሰልጠኛ ኢስቲትዩት ከኢትዮጵያ ብሔራዊ መከላከያ ኮሌጅ ጋር በመተባበር ነው ያዘጋጁት
👏6❤2👍2