የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ልዑካን እና የተለያዩ ሀገራት አምባሳደሮች በመቐለ ከተማ ከባለአደራ አስተዳደር አመራሮች ጋር እየተወያዩ ነው
የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት (ተመድ) ልዑካን እና የተለያዩ ሀገራት አምባሳደሮች በመቐለ ከተማ ከትግራይ ክልል ባለአደራ አስተዳደር አመራሮች ጋር ውይይት እያካሄዱ ይገኛሉ::
በውይይቱ ላይ የክልሉ ባለአደራ አስተዳደር ዋና ሥራ አስፈጻሚዎች፣ የመቐለ ከተማ ከንቲባ ሺሻይ አማረ (ዶ/ር) እንዲሁም ሌሎች ከፍተኛ የአስተዳደሩ አመራሮች ተገኝተዋል

❤11👍2
ኮፕ 32ን በድምቀት ለማስተናገድ የተጀመረው ሁሉን አቀፍ ዝግጅት
ትላልቅ ሀገራዊ እና ዓለም አቀፍ ሁነቶችን በላቀ ድምቀት እና በስኬት ለመወጣት፣ የተናጠል ተቋማዊ ጥረት ብቻውን በቂ ባለመሆኑ የሁሉም ባለድርሻ አካላት፣ ተቋማት እና ግብረ ኃይሎች ተናብቦ እና ተቀናጅቶ መሥራት ወሳኝ ነው::
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የ32ኛው የተመድ አየር ንብረት ጉባኤ (COP32) ብሔራዊ አስተባባሪ ኮሚቴን በመሰብሰብ የሰጡት ስትራቴጂያዊ አቅጣጫ ኢትዮጵያ ይህንን ታላቅ ዓለም አቀፍ ጉባኤ በብቃት ለማስተናገድ የያዘችውን የላቀ ዝግጁነት በግልጽ የሚያሳይ ነው

❤5🔥1👌1
የአፍሪካን የቴክኖሎጂ መሪነት ለመጨበጥ የሚደረግ የዲጂታል ኢትዮጵያ ስትራቴጂያዊ ጉዞ
ከ130 ሚሊዮን በላይ ሕዝብ ባለቤት የሆነችው እና አብዛኛው ቁጥር ወጣት የሆነባት ኢትዮጵያ፣ ባለፉት ጥቂት ዓመታት የኢኮኖሚ ዕድገቷን በቴክኖሎጂ እና በዲጂታል ሽግግር ለማዘመን መሠረታዊ ለውጦችን በማድረግ ላይ ትገኛለች::
በአፍሪካ ቀንድ ብሎም በመላው አህጉሪቱ የቴክኖሎጂ እና የኢኖቬሽን ማዕከል የመሆን ራዕይ ሰንቃ እየተንቀሳቀሰች ያለችው ኢትዮጵያ፣ ዲጂታል ሽግግርን የቅንጦት ጉዳይ ሳይሆን የሕልውና፣ የኢኮኖሚ ሉዓላዊነት እና የዘላቂ ልማት ቁልፍ መሣሪያ አድርጋ ወስዳዋለች

❤15🙏1
አዲስ አበባ ከዓለም ባንክ ጋር ያላትን ትብብር ወደ ላቀ ምዕራፍ ለማሸጋገር እንሠራለን - ከንቲባ አዳነች አቤቤ
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ ከዓለም ባንክ ቡድን ጋር ያለውን የረጅም ጊዜ አጋርነት ይበልጥ ለማጠናከር እና ወደ ከፍተኛ ደረጃ ለማሳደግ ያለመ ፍሬያማ ውይይት ማድረጋቸውን ገለጹ::
ከንቲባዋ እስካሁን በከተማው የውኃ አቅርቦት መሠረተ ልማት ማስፋፊያ እና ማሻሻያ፣ በፍሳሽ መሰብሰቢያ እና ማጣሪያ ተቋማት ግንባታ፣ እንዲሁም በትራንስፖርት እና በሌሎች ቁልፍ የልማት ዘርፎች ከዓለም ባንክ ቡድን ለተገኘው ድጋፍ ከፍተኛ ምስጋና አቅርበዋል

❤5🙏5
ካሉብ የተፈጥሮ ጋዝ ማውጫና ማጣሪያ ፕሮጀክት ሥራ መጀመሩ ለኢንዱስትሪዎች መነቃቃት ትልቅ ምዕራፍ ነው
የኢትዮጵያን የማድረግ አቅም ከቃል ወደ ተግባር የቀየረው ካሉብ የተፈጥሮ ጋዝ ማውጫና ማጣሪያ ፕሮጀክት ሥራ መጀመሩ ለሀገር ውስጥ ኢኮኖሚ፣ ለኢንዱስትሪዎች መነቃቃት እና ለቀጣናዊ ትሥሥር ትልቅ ምዕራፍ ነው::
በካሉብ የጋዝ ማውጫና ማጣሪያ ኩባንያ የውጭ ክፍል የሥራ ሂደት ኦፕሬተር አስፋው ወርቁ የፕሮጀክቱን መጀመር አስመልክቶ ከኢቢሲ ጋር ባደረጉት ቆይታ፣ ኢትዮጵያ ውስጥ የነዳጅ ዋጋ መናር ትልቅ ጫና እንደነበረውና አሁን ላይ ጋዝ ማምረት መጀመሩ በትራንስፖርት ዘርፍ ትልቅ መፍትሔ እንደሚያመጣ ገልጸዋል

❤4🔥3
ኢትዮጵያ በሰላም ማስከበር ተልዕኮ ለዓለምና ለቀጣናው ሰላም ያላትን ቁርጠኝነት በተግባር አሳይታለች
ኢትዮጵያ ላለፉት ሰባት አሥርት ዓመታት በሰላም ማስከበር ተልዕኮ ላይ በመሳተፍ ለዓለም አቀፍና ለቀጣናዊ ሰላምና ደኅንነት ያላትን ጠንካራ ቁርጠኝነት በተግባር ማሳየቷን የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት የመከላከያ ሎጂስቲክስ ዋና መምሪያ ኃላፊ ሌተናል ጄኔራል አብዱራህማን እስማኤል ገለጹ::
ኢትዮጵያ በሰላም ማስከበር ዘርፍ የዓለምንና የቀጣናውን ሰላም በመጠበቅ ላለፉት ሰባት አስርት ዓመታት የበኩሏን ሚና ስትወጣ መቆየቷን ጠቅሰዋል፡፡
የኢፌዴሪ ዓለም አቀፍ የሰላም ማስከበር ማሠልጠኛ ተቋምና የኢትዮጵያ ብሔራዊ መከላከያ ኮሌጅ በጋራ ባዘጋጁት መድረክ፣ ኢትዮጵያ በዓለም ሥርዓት ለውጥና በባለብዙ ወገን ትብብር መዳከም ተግዳሮቶች ውስጥ የሰላም ማስከበር ሚናዋን የምታስቀጥልባቸው ስትራቴጂዎች ላይ ውይይት እየተካሄደ ነው

👍5❤3🙏1
ጦርነት ከውድመት፣ ከሞት እና ከአካል ጉዳት ውጪ ምንም ጥቅም እንደሌለው ተገንዝበናል - የቀድሞ የትግራይ ክልል ታጣቂዎች
ጦርነት ከውድመት፣ ከሞት እና ከአካል ጉዳት ውጪ ምንም ጥቅም እንደሌለው መገንዘባቸውን የተሃድሶ ሥልጠናቸውን ያጠናቀቁ የቀድሞ የትግራይ ክልል ታጣቂዎች ተናግረዋል::
"ጦርነት ይበቃናል፤ ሰላም ይሻለናል" በሚል ትጥቃቸውን በማውረድ መቐለ በሚገኘው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ተሃድሶ ማዕከል ሥልጠና ሲወስዱ የቆዩ ከ7 ሺህ 200 በላይ የቀድሞ ታጣቂዎች ሥልጠናቸውን አጠናቅቀዋል

🙏5❤1
ኢትዮጵያ በዓለም አቀፍ የሰላም ማስከበር ተልዕኮ ያላትን ሚና አጠናክራ ትቀጥላለች፡- ቫይስ አድሚራል ክንዱ ገዙ
ኢትዮጵያ ተቋማዊ አቅሟንና አጋርነቷን በማጎልበት በዓለም አቀፍ ደረጃ ያላትን የሰላም ማስከበር ሚና ይበልጥ አጠናክራ እንደምትቀጥል የኢትዮጵያ ባሕር ኃይል ዋና አዛዥ ቫይስ አድሚራል ክንዱ ገዙ ገለጹ::
ኢትዮጵያ ተቋማዊ አቅሟን በማዘመን፣ የሠራዊቷን ዝግጁነት ማሳደግና ቀጣናዊ ብሎም ዓለም አቀፋዊ አጋርነቷን በማስፋት በዓለም የሰላም ማስከበር ሚናዋን እንደምትወጣም ተናግረዋል

👍3🔥3
የአየር ንብረት ፋይናንስ ለታዳጊ ሀገራት ቅድሚያ ፍላጎቶች ምላሽ በሚሰጥና ተደራሽ በሆነ መልኩ ሊቀርብ ይገባል - ጌዲዎን ጢሞቲዎስ (ዶ/ር)
ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር እና የCOP32 ተመራጭ ፕሬዚዳንት ጌዲዎን ጢሞቲዎስ (ዶ/ር)፣ የአየር ንብረት ፋይናንስ በሚያስፈልገው ደረጃ፣ በተደራሽ መንገዶች እና ለታዳጊ ሀገራት ቅድሚያ ፍላጎቶች ምላሽ በሚሰጥ መልኩ እንዲቀርብ ጥሪ አቀረቡ::
ሚኒስትሩ ይህንን ያሉት በCOP31 ላይ "ከውጥን ወደ ተግባር፡ በዓለም አቀፍ የአካባቢ ጥበቃ ተቋም (GEF)፣ በዝቅተኛ የዕድገት ደረጃ ላይ ለሚገኙ ሀገራት ፈንድ (LDCF) እና በልዩ የአየር ንብረት ለውጥ ፈንድ (SCCF) አማካኝነት የገንዘብ ድጋፍ ማሰባሰብ" በተሰኘው የከፍተኛ ኃላፊዎች ውይይት ላይ ባደረጉት ንግግር ነው

❤5🙏3
የብሔር ብሔረሰቦች መስተጋብር ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጠነከረ መጥቷል -- አቶ ትግሉ መለሰ
በኢትዮጵያ በተሠሩ ሰፊ ሥራዎች የብሔር ብሔረሰቦች መስተጋብር ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጠነከረ መምጣቱን የፌዴሬሽን ምክር ቤት ጽሕፈት ቤት ኃላፊ አቶ ትግሉ መለሰ ገልጸዋል::
የፌዴሬሽን ምክር ቤት፣ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እና የሕገ መንግሥትና ፌዴራሊዝም አስተምህሮ ማዕከል በመተባበር 21ኛውን የኢትዮጵያ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ቀን በማስመልከት ለሦስቱ ተቋማት አመራሮች እና ሠራተኞች በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አዳራሽ የግንዛቤ ማስጨበጫ ሥልጠና ሰጥተዋል

❤12🥰2
ታዳጊ አትሌቶቻችን የኢትዮጵያን የድል ጉዞ የምታድሱ ሀገራዊ ኩራቶቻችን ናችሁ - ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ
ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ በሴኔጋል ዳካር በተካሄደው የ2026 የዓለም ወጣቶች ኦሎምፒክ ጨዋታዎች ኢትዮጵያን በአትሌቲክስ የሜዳሊያ ሰንጠረዥ በአንደኝነት እንድታጠናቅቅ ያስቻሉ ታዳጊ አትሌቶችን በአካል አግኝተው አበረታተዋል::
ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ አትሌቶቹ በአፍላ ዕድሜያቸው በዓለም መድረክ ባሳዩት ብቃትና ባስመዘገቡት ድል የሀገራቸውን ሰንደቅ በክብር ከፍ ማድረጋቸውን ገልጸዋል

🙏14👏2
ኢትዮጵያ ለአዳጊ ሀገራት የአቪዬሽን ትስስርን ለማጠናከር ያላትን ቁርጠኝነት አረጋገጠች
ኢትዮጵያ ለዳጊ ሀገራት (LLDCs) የአቪዬሽን ትስስርን ለማሻሻል እና ዓለም አቀፍ ትብብርን ለማጠናከር ያላትን ቁርጠኝነት፣ በዓለም አቀፉ የአየር ትራንስፖርት ኮንፈረንስ ጎን ለጎን በተካሄደው የዓለም አቀፉ የሲቪል አቪዬሽን ድርጅት (ICAO) የልማት አጋሮች ውይይት ላይ በድጋሚ አረጋግጣለች::
የዓለም አቀፉን የሲቪል አቪዬሽን ድርጅት (ICAO) እና ቀጣናዊ ጽሕፈት ቤቶቹን፣ አባል ሀገራትን፣ የሲቪል አቪዬሽን ባለሥልጣናትን፣ የአፍሪካ ሲቪል አቪዬሽን ኮሚሽንን፣ ቀጣናዊ ድርጅቶችን፣ የዓለም ባንክን፣ ዓለም አቀፍ የፋይናንስ ተቋማትን፣ የልማት ኤጀንሲዎችን፣ ለጋሽ ሀገራትን፣ የኤርፖርት ኦፕሬተሮችን፣ አየር መንገዶችን እንዲሁም የግል ዘርፍ ባለሀብቶችን ጨምሮ ቁልፍ ዓለም አቀፍ የአቪዬሽን ባለድርሻ አካላት በውይይቱ ላይ ተሳትፈዋል

❤9
ከኢትዮጵያ ጋር ሁለንተናዊ የትብብር አድማስ በማስፋት የዲፕሎማሲ ግንኙነትን ለማጎልበት እንሰራለን - የተለያዩ ሀገራት አምባሳደሮች
የኢትዮጵያንና የየሀገራቸውን ሁለንተናዊ የትብብር አድማስ በማስፋት የዲፕሎማሲ ግንኙነትን ለማጎልበት በቁርጠኝነት እንደሚሰሩ በኢትዮጵያ አዲስ የተሾሙ የተለያዩ ሀገራት አምባሳደሮች ገለጹ::
ፕሬዚዳንት ታዬ አጽቀሥላሴ ከአፍሪካ፣ እስያ፣ መካከለኛው ምሥራቅ፣ አውሮፓ እና ካሪቢያን ሀገራት በኢትዮጵያ አዲስ የተሾሙ የ16 ሀገራት አምባሳደሮችን የሹመት ደብዳቤ በትናንትናው ዕለት ተቀብለዋል

❤6🙏3💯1