የኢትዮጵያ የኢንደስትሪ ጉዞ አዲስ ምዕራፍ እየተራመደ ይገኛል።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ከኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን ጋር ባደረጉት የሁለት ክፍሎች ቃለምልልስ ኢትዮጵያ የአዲሱ ዘመን የኢንደስትሪ መስፋፋትን እንዴት እየበየነች እንደሆነ አብራርተዋል።
የመጀመሪያውን ክፍል ማክሰኞ ሚያዚያ 6/ 2018 ዓመተ ምህረት ከምሽቱ 2:30 ይጠብቁ።
Ethiopian Broadcasting Corporation #Ethiopia #EBC
#PMOEthiopia

👏1
ኢትዮጵያ የዓለም አቀፉ ስፖርት ጋዜጠኞች ማህበር ጉባኤን ለማስተናገድ ተመረጠች
*****
በስዊዘርላንድ ሉዛን በተካሄደው 88ኛው የዓለም አቀፉ ስፖርት ጋዜጠኞች ማህበር ጉባኤ ላይ በተሰጠ ድምፅ ኢትዮጵያ የ2027ቱን ታላቅ መድረክ እንድታስተናግድ በሙሉ ድምፅ መመረጧን የኢትዮጵያ ስፖርት ጋዜጠኞች ማህበር በይፋ አስታውቋል።
ይህ ስኬት የሀገሪቱን ስም በዓለም አቀፍ ስፖርት መድረክ ዳግም ከፍ የሚያደርግ ሲሆን በሚቀጥለው ዓመት በሚካሄደው በዚህ ጉባኤ ላይ ከ300 በላይ አንጋፋና ስመ ጥር የዓለም ስፖርት ጋዜጠኞች ወደ ሯጮቹ ምድር አዲስ አበባ የሚመጡበትን ዕድል አመቻችቷል።
በጉባኤው ላይ የሚሳተፉት ባለሙያዎች በዓለም አቀፍ ደረጃ ከፍተኛ ተቀባይነት ያላቸውና በታላላቅ የሚዲያ ተቋማት ውስጥ የስፖርቱን ዓለም የታሪክ ማህደር የፃፉ ናቸው።
ከእነዚህም መካከል የአበበ ቢቂላን በባዶ እግር የመሮጥ ገድል እስከ ኃይሌ ገብረ ሥላሴና ቀነኒሳ በቀለ የድል ታሪኮች ለዓለም ያስተዋወቁ አንጋፋ ጋዜጠኞች ይገኙበታል። እንዲሁም የማራዶናን ታሪካዊ ግቦች በወጣትነታቸው የዘገቡና አሁን ደግሞ እንደ ላሚን ያማል ያሉ ወጣት ከዋክብትን ቃለ-መጠይቅ ያደረጉ አንጋፋ የስፖርት መጽሐፍት ደራሲያንና ጋዜጠኞች የኢትዮጵያን እንግዳ ተቀባይነት ለማየት ወደ መዲናዋ ይተማሉ።
እንዲሁም የዓለም አቀፉ ኦሊምፒክ ኮሚቴ፣ የፊፋ እና የካፍ ፕሬዝዳንቶችን ጨምሮ የሌሎች ዓለም አቀፍ ስፖርት ተቋማት መሪዎች በዚሁ መድረክ ላይ እንደሚታደሙ ይጠበቃል።
ይህንን ታላቅ ዝግጅት ማስተናገድ ለኢትዮጵያ ስፖርት ጋዜጠኞች ማህበር ብቻ ሳይሆን ለሀገሪቱ ስፖርት ዕድገት ትልቅ ትርጉም አለው።
በተለይም ለወጣት ጋዜጠኞች አዳዲስ የሥራ ዕድሎችን ከመፍጠር ባሻገር ከዓለም አቀፍ ባለሙያዎች ጋር ጠንካራ ግንኙነት በመመሥረት ልምድ እንዲቀስሙ ሰፊ በር ይከፍታል።

ጋቦን ከ16 ዓመት በታች የሆኑ አዳጊዎች ማህበራዊ ሚዲያ እንዳይጠቀሙ የሚከለክል በአፍሪካ ቀዳሚ የሆነውን ጥብቅ ሕግ አወጣች
*******************
ጋቦን ዕድሜያቸው ከ16 ዓመት በታች የሆኑ አዳጊዎች በማህበራዊ ሚዲያ ላይ አካውንት እንዳይከፍቱ የሚከለክል ጥብቅ ሕግ አውጥታለች።
ይህም ሀገሪቱን አዳጊዎችን ከዲጂታል ዓለም አደጋዎች ለመጠበቅ እንዲህ ዓይነት ሕግ በማውጣት በአፍሪካ ቀዳሚዋ ያደርጋታል።
የጋቦን ከፍተኛ የኮሙኒኬሽን ባለሥልጣን (HAC) ይፋ ባደረገው መረጃ መሠረት፣ ሕጉ በዋናነት አዳጊዎችን በኢንተርኔት አማካኝነት ከሚሰነዘሩ ጥቃቶች፣ ከሐሰተኛ መረጃዎች እና ከማይመጥኑ ይዘቶች ለመከላከል ያለመ ነው።
በአዲሱ ሕግ መሠረት፣ አዳጊዎች ለትምህርታዊ ዓላማ ካልሆነ በቀር በማንኛውም ማህበራዊ ሚዲያም ሆነ የኢንተርኔት መድረኮች ላይ አካውንት እንዳይከፍቱ በሕግ ይከለከላል።
ይህ አዲስ መመሪያ ሕጉን በማያስከብሩ የቴክኖሎጂ ኩባንያዎች እና ልጆቻቸውን በአግባቡ በማይቆጣጠሩ ወላጆች ላይ ጥብቅ ተጠያቂነትን…https://web.facebook.com/EBCzena/posts/pfbid02GJkfGwUUHT6T4QppZ3Cfy4WFKTGhyhE9kqaNMrqjSFwnHqtJeR7Afmb57AziYRhkl

"አሰብ ለእኛ እናታችንና ብርሃናችን ነበረች፤ ያ ታሪካዊ ቀን ሲመለስ ለማየት እንመኛለን" - የቀድሞ የአሰብ ነዋሪዎች
******************
በአሰብ ከተማ ነግደው ያተረፉ፣ ወልደው የከበሩና ከተማዋን ያቀኑ ኢትዮጵያውያን፤ ዛሬ በኮምቦልቻ ከተማ "የአሰብ ተፈናቃዮች" በሚል መጠሪያ በራሳቸው መንደር ማህበር መስርተው ይኖራሉ።
ኢቢሲ የትንሳኤ በዓልን ምክንያት በማድረግ በእነዚህ ነዋሪዎች ዘንድ ተገኝቶ ባደረገው ቆይታ፣ ነዋሪዎቹ ሀብትና ንብረታቸውን በአሰብ ጥለው ቢመጡም አሁንም ድረስ ስለ ከተማዋ ጥልቅ ትዝታና ቁጭት እንዳላቸው ታዝቧል።
የኮምቦልቻ ከተማ የመንግስት ኮሚኒኬሽን መመሪያ ኃላፊ ወይዘሮ ዘሪቱ ሁሴን እንደገለጹት፤ እነዚህ ወገኖች ከ1983 ዓ.ም ጀምሮ በከተማዋ በቋሚነት እየኖሩ ይገኛሉ።
ቀደም ሲል በአሰብ በንግድ ስራ ይተዳደሩ የነበሩት አቶ አሊ ኢድሪስ፣ አሰብ የሁሉም አካባቢ ህዝብ የሚገናኝባት "የፍቅር ከተማ" እንደነበረች ያስታውሳሉ።
አቶ አሊ አክለውም ቀይ ባህር ለኢትዮጵያ እንደ ልብና አእምሮ ትልቅ ዋጋ ያለው መሆኑን ገልጸው፣ ኢትዮጵያ ዳግም የባህር በር ባለቤት ብትሆን የብልጽግና ማማ ላይ ለመድረስ እንደሚያስችላት በልበ ሙሉነት ይናገራሉ።
በወቅቱ በባህር ትራንስፖርት ዘርፍ ያገለግሉ የነበሩት አቶ ሲሳይ አሰፋ፣ የባህር በሩ ለኢትዮጵያ እንደ እናትና እንደ ብርሃን እንደነበር በቁጭት ያወሳሉ።
ኢትዮጵያ የባህር በር በመነጠቋ ምክንያት እንደ ሌሎች የሰለጠኑ ሀገራት እንዳታድግ እንቅፋት እንደሆነባትም ይገልጻሉ።
https://web.facebook.com/EBCzena/posts/pfbid02qgB7LctQrJwwTJMoaRSz5akwEvMkA3GeD8qPP4PtVm5H1ytnKugiSjYSauFDejrol