10 ሚሊዮን ብር የሚያሸልመው የትንሣኤ ሎተሪ እጣ ወጣ
******************
የኢትዮጵያ ሎተሪ አገልግሎት 10 ሚሊዮን ብር የሚያሸልመውን የትንሣኤ ሎተሪ ዕጣ የታዛቢዎችና የተቋሙ ከፍተኛ አመራሮች በተገኙበት በዛሬው ዕለት በይፋ አውጥቷል።
በወጣው የዕጣ ውጤት መሠረት 10 ሚሊዮን ብር የሚያሸልመው አንደኛ ዕጣ ቁጥር 1017459 ሆኖ የወጣ ሲሆን፣ 7 ሚሊዮን ብር የሚያሸልመው ሁለተኛው ዕጣ ደግሞ በቁጥር 0709265 ላይ አርፏል።
በተጨማሪም 3.5 ሚሊዮን ብር የሚያስገኘው ሦስተኛው ዕጣ ቁጥር 0730432 ሆኖ ሲመዘገብ፣ 1.5 ሚሊዮን ብር የሚያሸልመው አራተኛው ዕጣ ደግሞ ቁጥር 0341593 ሆኗል።
በመጨረሻም አገልግሎቱ የማስተዛዘኛ ቁጥሩ 4 ሆኖ መውጣቱን አስታውቋል።
ዕድለኞች በሕጉ መሠረት በተቀመጠው የጊዜ ገደብ ውስጥ ወደ ተቋሙ በመቅረብ ሽልማታቸውን መረከብ እንደሚችሉ ተገልጿል።
በሳምሶን በላይ
#EthiopianBroadcastingCorporation #Ethiopia #Lottery #EasterLottery #EthiopianLottery

👍1
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) እና ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው በአንድነት ፓርክ ዓመታዊውን የፋሲካ መዐድ ማጋራት አከናወኑ
**************
በመላው ኢትዮጵያ በክርስትና ጥላ ውስጥ በሚገኙ ቤተ-እምነቶች ያሉ ክርስቲያኖች የትንሳኤን በዓል በተስፋ፣ በመስዋዕትነት እና በአዲስ መነሳት መንፈስ በአንድነት ያከብራሉ።
ከሳምንታት የፆም፣ ጥሞና እና ራስን የመመልከት ጊዜ በኋላ ፋሲካ በእውነተኛ አምልኮ፣ መንፈስን አድሶ፣ ቤቶችንም በደስታ ይሞላል። በዘመድ አዝማድ መጠያየቅ እና ማዕድ መካፈልም ፍቅርን ያዳብራል።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) እና ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው ዓመታዊውን የፋሲካ መዐድ ማጋራት ከተለያዩ የኅብረተሰብ ክፍሎች ጋር በአንድነት ፓርክ በጋራ መታደማቸው ለእውነተኛው የአንድነት መንፈስ ጉልህ ማሳያ ነው።
በዓለ ትንሳኤው በመላው ኢትዮጵያ የእምነት፣ ቤተሰባዊነት እና የመታደስ መንፈስ የሚታይበት ጊዜ ነው። ሁላችንም በዚህ የትንሳኤ መንፈስ ዛሬም፣ ነገም፣ ሰርክ ቤታችንን፣ ልባችንንም ለተቸገሩ ወገኖች እንክፈት!
መልካም በዓል።
#PMOEthiopia

👏1
አሜሪካ እና ኢራን የተኩስ አቁም ስምምነታቸውን እንዲያከብሩ ፓኪስታን ጠየቀች
********************
በመካከለኛው ምስራቅ ያለውን ውጥረት ለማርገብ በአሜሪካ እና በኢራን መካከል በፓኪስታን አስተናጋጅነት ሲካሄድ የቆየው የሰላም ንግግር ለጊዜው ያለስምምነት መጠናቀቁ ይታወቃል።
የፓኪስታን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ኢሻቅ ዳር፤ ሁለቱም ወገኖች የገቡትን የሁለት ሳምንት የተኩስ አቁም ስምምነት እንዲያከብሩ እና ለቀጣይ ዲፕሎማሲያዊ ጥረቶች ዝግጁ እንዲሆኑ አሳስበዋል።
ፓኪስታን ለ24 ሰዓታት በዘለቀው በዚህ ከፍተኛ ድርድር ላይ የጦር ኃይሎች ኢታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ሰይድ አሲም ሙኒርን ጨምሮ ከፍተኛ አመራሮቿን በማሳተፍ የሽምግልና ሚናዋን ተወጥታለች።
የአሜሪካው ምክትል ፕሬዚዳንት ጄዲ ቫንስ ንግግሩ ያለምንም ስምምነት መጠናቀቁን ገልጸው ከኢስላማባድ ወደ ዋሽንግተን ተመልሰዋል።
በኢስላማባድ በተካሄደው በዚህ ንግግር የአሜሪካው ልዑክ በጄዲ ቫንስ፣ የኢራኑ ደግሞ በፓርላማ አፈ-ጉባኤው ባገር ጋሊባፍ ተመርቷል።
ፓኪስታን በቀጣይም በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለውን ልዩነት በውይይት ለመፍታት የምታደርገውን ጥረት እንደምትቀጥል አስታውቃለች።
#MiddleEast #Diplomacy #Pakistan #USA #Iran #negotiation #EBC

የትንሣኤ በዓል የሕይወት አሸናፊነትና የጥሩነት መገለጫ ነው” - ፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑቲን
************
የሩሲያው ፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑቲን የክርስቶስን የትንሣኤ በዓል ለሚያከብሩ የኦርቶዶክስ ክርስቲያኖችና ለመላው የሩሲያ ሕዝብ የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል።
ፕሬዝዳንቱ በመልዕክታቸው፣ ታላቁ የትንሣኤ በዓል በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ሰዎችን ልብ በእውነተኛ ደስታ፣ በሕይወት አሸናፊነት እንዲሁም በፍቅርና በፍትህ ድል አድራጊነት እንደሚሞላ ገልጸዋል።
በዓሉ ሕዝቡን ከቆዩት የቀድሞ አባቶች ወጎችና መንፈሳዊ እሴቶች ጋር የሚያስተሳስር ታላቅ ዕለት መሆኑንም አክለዋል።
የሩሲያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያንና ሌሎች የክርስትና እምነት ተከታዮች ታሪካዊና ባህላዊ ቅርሶችን በመጠበቅ፣ የቤተሰብን ተቋም በማጠናከርና ወጣቱን ትውልድ በትክክለኛ ሥነ-ምግባር በማነጽ ረገድ የሚጫወቱትን አርዓያነት ያለው ሚና ፕሬዚዳንቱ አድንቀዋል።
በተለይም ሃይማኖታዊ ተቋማት ከመንግሥት አካላት ጋር በመቀናጀት ለሀገራዊ አንድነት፣ ለሃይማኖቶች የጋራ ውይይት እንዲሁም በወታደራዊ ዘመቻ ላይ ለሚገኙ ዜጎችና ለቤተሰቦቻቸው እያደረጉት ያለው ድጋፍ የሚደነቅ መሆኑን ጠቁመዋል።
ፕሬዚዳንት ፑቲን ለመላው ሕዝብ መልካም ጤንነትን እና ብልጽግናን በመመኘት፣ በዓሉ የሰላምና የደስታ እንዲሆንላቸው መልካም ምኞታቸውን አስተላልፈዋል።
#Russia #Orthodox #Easter #VladimirPutin #Goodwill #HappyEaster

ከንቲባ አዳነች በመዲናዋ 27ኛውን የተስፋ ብርሃን የምገባ ማዕከል ሥራ አስጀመሩ
*************************
ከንቲባ አዳነች አቤቤ በዛሬው ዕለት በጉለሌ ክፍለከተማ ተገኝተው በክፍለ-ከተማው 3ኛውን፣ በመዲናዋ 27ኛውን የተስፋ ብርሃን የምገባ ማዕከል ሥራ በማስጀመር ከማዕከሉ ተጠቃሚዎች ጋር የትንሳዔ በዓልን በጋራ አክብረዋል።
“የምገባ ማዕከሉ ተጠቃሚ የሆኑ፣ ለማህበራዊ ችግር የተጋለጡ፣ አልባሽ አጉራሽ የሌላቸው፣ ድጋፍ የሚሹ አረጋውያን እና አካል ጉዳተኛ የሀገር ባለውለታ ወገኖቻችንን እንኳን አደረሳችሁ ብለን በዓሉን በጋራ አክብረናል” ብለዋል ከንቲባዋ።
በዓሉ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ያለአንዳች ልዩነት ለሰው ልጆች ሁሉ ራስን እስከ መስጠት ያሳየንን ፍቅር ምሳሌነቱን በመከተል በአብሮነት እና በመተሳሰብ ልንኖር እንደሚገባ የሚስተምር በዓል ነው ብለዋል።
እኛም በ28ቱም የተስፋ ብርሃን የምገባ ማዕከል በዚሁ በትንሳኤ በዓል ብቻ ሳይሆን ሁሌም ወገኖቻችን ስንመግብ ለዜጐቻችን ክብራችንና ፍቅራችንን የምንገልጥበትና ማህበራዊ ፍትህን የምናነግስበት ተግባር ነው ብለዋል ከንቲባ አዳነች።
በዓሉን ምክንያት በማድረግ በሁሉም ክፍለ ከተሞች በማዕከላቱ መዓድ የማቋደስ መርሐ-ግብር እየተከናወኑ መሆኑን ከንቲባዋ በማኅበራዊ ትስስር ገፃቸው ባጋሩት መልዕክት ጠቅሰዋል።
“መስጠት አያጎድልም በሚል መርሕ የተደረገላቸውን ጥሪ በመቀበል ለገነቡት በጎ ፈቃደኛ የአዲስ ቪው ሆቴል ባለቤት አቶ አብይ አበራ እና በየቀኑ ለመመገብ ለተረከበው የአኳስ ኮንስትራክሽን ፒኤልሲ ባለቤት አቶ ወሰን በተጠቃሚው ወገን፣ በከተማ አስተዳደሩና በራሳቸው ስም ምስጋና አቅርበዋል።
በዓሉ የመተባበር፣ የመደጋገፍ እና የፍቅር በዓል እንዲሆንም መልካም ምኞታቸውን ገልጸዋል።
#Ethiopia #AddisAbaba #Easter #sharingmeal #communalfeeding #EBC