Ethiopian Broadcasting corporation ®
8.85K subscribers
17.9K photos
205 videos
14 files
1.62K links
Ethiopian broadcasting corporation is a 24 working public media.

https://telega.io/c/EBC_TV
ማንኛውም አይነት አስተያየት እና ጥቆማ ካላችሁ በዚህ ላኩልን እንቀበላለን!!
https://t.me/+G7d4hSzJEhViMzQ0
Download Telegram
የትንሣኤ በዓል የሕይወት አሸናፊነትና የጥሩነት መገለጫ ነው” - ፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑቲን
************

የሩሲያው ፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑቲን የክርስቶስን የትንሣኤ በዓል ለሚያከብሩ የኦርቶዶክስ ክርስቲያኖችና ለመላው የሩሲያ ሕዝብ የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል።

ፕሬዝዳንቱ በመልዕክታቸው፣ ታላቁ የትንሣኤ በዓል በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ሰዎችን ልብ በእውነተኛ ደስታ፣ በሕይወት አሸናፊነት እንዲሁም በፍቅርና በፍትህ ድል አድራጊነት እንደሚሞላ ገልጸዋል።

በዓሉ ሕዝቡን ከቆዩት የቀድሞ አባቶች ወጎችና መንፈሳዊ እሴቶች ጋር የሚያስተሳስር ታላቅ ዕለት መሆኑንም አክለዋል።

የሩሲያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያንና ሌሎች የክርስትና እምነት ተከታዮች ታሪካዊና ባህላዊ ቅርሶችን በመጠበቅ፣ የቤተሰብን ተቋም በማጠናከርና ወጣቱን ትውልድ በትክክለኛ ሥነ-ምግባር በማነጽ ረገድ የሚጫወቱትን አርዓያነት ያለው ሚና ፕሬዚዳንቱ አድንቀዋል።

በተለይም ሃይማኖታዊ ተቋማት ከመንግሥት አካላት ጋር በመቀናጀት ለሀገራዊ አንድነት፣ ለሃይማኖቶች የጋራ ውይይት እንዲሁም በወታደራዊ ዘመቻ ላይ ለሚገኙ ዜጎችና ለቤተሰቦቻቸው እያደረጉት ያለው ድጋፍ የሚደነቅ መሆኑን ጠቁመዋል።

ፕሬዚዳንት ፑቲን ለመላው ሕዝብ መልካም ጤንነትን እና ብልጽግናን በመመኘት፣ በዓሉ የሰላምና የደስታ እንዲሆንላቸው መልካም ምኞታቸውን አስተላልፈዋል።

#Russia #Orthodox #Easter #VladimirPutin #Goodwill #HappyEaster
👏1