Ethiopian Broadcasting corporation ®
8.86K subscribers
17.9K photos
205 videos
14 files
1.62K links
Ethiopian broadcasting corporation is a 24 working public media.

https://telega.io/c/EBC_TV
ማንኛውም አይነት አስተያየት እና ጥቆማ ካላችሁ በዚህ ላኩልን እንቀበላለን!!
https://t.me/+G7d4hSzJEhViMzQ0
Download Telegram
ጋሞ ጨንቻ ለመጀመሪያ ጊዜ ወደ ኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ አደገ
*********************

በኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ ምድብ "ሀ" የመጨረሻ ሳምንት ጨዋታ ዛሬ በጅማ ስታዲየም የተካሄደ ሲሆን፣ ጋሞ ጨንቻ ቡራዩ ከተማን 3 ለ 0 በሆነ ሰፊ ውጤት አሸንፏል።

በዚህም ክለቡ ነጥቡን ወደ 41 በማሳደግ፣ ወደ ኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ማደጉን ያረጋገጠ የመጀመሪያው ቡድን ለመሆን በቅቷል።

በፍራፍሬ ሀብቷ በስፋት የምትታወቀው ጨንቻ፣ በታሪኳ ለመጀመሪያ ጊዜ በኢትዮጵያ ከፍተኛው የደረጃ እርከን (ፕሪሚየር ሊግ) የሚወክላት ክለብ በማግኘቷ ስኬቱ ለከተማዋና ለደጋፊዎቿ ልዩ ትርጉም የሚሰጥ ሆኗል።

የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ጥላሁን ከበደ የጋሞ ጨንቻ እግርኳስ ክለብ ወደ ፕሪሚየር ሊግ በማደጉ የተሰማቸውን ደስታ ገልጸው፤ ክለቡ በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ሶስተኛው የክልሉ ተወካይ ለመሆን መብቃቱ ክልሉ በርካታ የእግርኳስ ተጫዋቾች መፍለቂያ ስለመሆኑ ማሳያ ነዉ ብለዋል።

የጋሞ ጨንቻ እግርኳስ ክለብ በውድድር ዓመቱ በነበረው ጠንካራ አቋም ለዚህ ታሪካዊ ድል መብቃቱ ተገልጿል።

በሰለሞን አባቡ

#EBC #Ethiopia #GamoChencha #EthiopianPremierLeague #HigherLeague #FootballNews
👏1
የሆርሙዝ የባህር ወሽመጥ ያለፉ ሰዓታት ሁኔታ፦ የሰላም ጥረቶች መሰናከል እና የዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ ምላሽ
**************

በመካከለኛው ምሥራቅ ያለው ወታደራዊ ውጥረት ዛሬ ወደ አዲስ እና አደገኛ ምዕራፍ ተሸጋግሯል።

በፓኪስታን፣ ኢስላማባድ ለ21 ሰዓታት የተካሄደው የሰላም ድርድር ያለምንም ስምምነት መጠናቀቁን ተከትሎ፣ የዩናይትድ ስቴትስ ማዕከላዊ ዕዝ (CENTCOM) ዛሬ ከቀኑ 5፡00 ሰዓት ጀምሮ በኢራን ወደቦች ላይ መደበኛ የባሕር ከበባ መጀመሩን አስታውቋል።

ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ኢራን በሆርሙዝ ወሽመጥ ላይ የምታስከፍለውን ክፍያ “ዓለም አቀፍ ዝርፊያ” ሲሉ በመኮነን፣ ክፍያውን የሚፈጽም ማንኛውም መርከብ በአሜሪካ ቁጥጥር ሥር እንደሚውል አስጠንቅቀዋል።

በሌላ በኩል፣ ኢራን ሆርሙዝ ወሽመጥ ሙሉ በሙሉ በቁጥጥሯ ሥር መሆኑን በመግለጽ፣ የባሕር ከበባውን እንደማትቀበልና ማንኛውም ወታደራዊ እርምጃ ከባድ አጸፋዊ ምላሽ እንደሚያስከትል አሳውቃለች።

እንግሊዝ እና ፈረንሳይ የአሜሪካን የባሕር ከበባ እንደማይደግፉ በማስታወቅ፣ ከጦርነቱ ተሳታፊዎች ነጻ የሆነ እና ጥብቅ የመከላከል ዓላማ ያለው ሰላማዊ ዓለም አቀፍ የባሕር ኃይል ጥምረት ለማቋቋም የጋራ ጉባኤ ጠርተዋል።

ቻይና እና ሩስያ መፍትሔው ወታደራዊ ኃይል ሳይሆን በአስቸኳይ ተኩስ አቁም ላይ መድረስ መሆኑን በማስገንዘብ፣ ከበባው የዓለም አቀፍ ንግድ መስመርን እንደሚያስተጓጉል አስጠንቅቀዋል።

ሳውዲ ዓረቢያ ከደኅንነት ስትራቴጂ አኳያ ጥንቃቄ የተሞላበት ዝምታን ስትመርጥ፣ ኳታር ቀጣናው ከቁጥጥር ውጪ ወደሆነ ጦርነት እያመራ ነው በማለት ስጋቷን ገልጻለች።

ፓኪስታን እና ኦማን በበኩላቸው የተጀመረውን የሽምግልና ጥረት አጠናክረው እንደሚቀጥሉ ሲያረጋግጡ፣ እስራኤል የአሜሪካን ውሳኔ ሙሉ በሙሉ ደግፋለች።

እንደ ዎል ስትሪት ጆርናል እና ሌሎች ሁነኛ የመረጃ ምንጮች፣ በኢስላማባድ የተካሄደው የሰላም ድርድር ላለመሳካቱ ዋናው ምክንያት የኢራን የኑክሌር መርሐ ግብር እና የሆርሙዝ ወሽመጥ የቁጥጥር ሥልጣን ጉዳይ ነው።

የአሜሪካ ምክትል ፕሬዚዳንት ጄዲ ቫንስ ኢራን የኑክሌር ፍላጎቷን እንድታቆም ያቀረቡትን ጥያቄ አለመቀበሏን ሲገልጹ፤ የኢራን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አባስ አራቅቺ በበኩላቸው የአሜሪካ ከፍተኛ ጫና እና የከበባ ዛቻ ለስምምነት ተቃርቦ የነበረውን ድርድር እንዳደናቀፈው ገልጸዋል።

የፖለቲካ እና የኢኮኖሚ ተንታኞች የቀጣዩን ጊዜ ሁኔታ በከፍተኛ ስጋት እየተመለከቱት ነው። የስትራቴጂያዊ እና ዓለም አቀፍ ጥናቶች ማዕከል (CSIS) ተንታኞች እንደሚሉት፣ ይህ ጫና ኢራን በየመን የሚገኙ የሁቲ ኃይሎችን በመጠቀም በባቢል መንደብ ወሽመጥ ላይ ተጨማሪ ጥቃቶች እንድትሰነዝር ሊገፋት ይችላል።

ይህ ከሆነ እና በአንድ ጊዜ ሁለት ዋና ዋና የነዳጅ ማስተላለፊያ መስመሮች ከተዘጉ፣ ከ100 ዶላር በላይ የዘለለው የነዳጅ ዋጋ እስከ 150 ዶላር ሊያሻቅብ እንደሚችል የገበያ ተንታኞች ይገምታሉ።

የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት በበኩሉ፣ ጦርነቱ እና የኢኮኖሚ መናጋቱ በዓለም ዙሪያ 32 ሚሊዮን ሰዎችን ወደ ድህነት ሊገፋ እንደሚችል ስጋቱን ገልጿል።

ከነዚህ አስተያየቶች በመነሳት የተጀመረው የሰላም ጥረት እና የኦማን የሽምግልና ሚና አሁንም ብቸኛው የቀውሱ መውጫ ተስፋ ተደርጎ እየታየ ይገኛል።

ለሚ ታደሰ

#MiddleEastCrisis #StraitOfHormuz #NavalBlockade #EnergySecurity #Diplomacy
👏1
አሜሪካ በሆርሙዝ ወሽመጥ ላይ የጣለችው “ሕገ-ወጥ” እገዳ የራሷን እና የዓለምን ኢኮኖሚ በእጅጉ የሚጎዳ ነው - ኢራን
*********************************

የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ፣ አሜሪካ ወደ ሆርሙዝ ወሽመጥ የሚገቡም ሆነ የሚወጡ መርከቦችን በይፋ ማገድ መጀመሯን አስታውቀዋል።

ፕሬዚዳንት ትራምፕ በ‘ትሩዝ ሶሻል’ የማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው ባስተላለፉት መልዕክት፣ የኢራን የባህር ኃይል ባለፈው ወር በተፈጸመበት ጥቃት መዳከሙን የገለጹ ሲሆን፤ ከጥቃቱ የተረፉ የኢራን መርከቦች አሜሪካ እገዳ ወደጣለችበት የውሃ አካል ከቀረቡ የማያዳግም እርምጃ እንደሚወሰድባቸው አስታውቀዋል።

ቴህራን በበኩሏ የአሜሪካ ድርጊት “ሕገ-ወጥ” ነው ስትል አውግዛለች። የኢራን ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ኢስማኤል ባጋኢ፣ አሜሪካ ኢራንን ለመጉዳት እየፈጸመችው ባለው ድርጊት የራሷን እና የዓለምን ኢኮኖሚ እየጎዳች ነው ሲሉ ገልጸዋል። የአሜሪካ ድርጊት በተለይ በዓለም አቀፍ የነዳጅ ገበያ ላይ ከፍተኛ ቀውስ እንደሚያስከትልም አስጠንቅቀዋል።

በአሜሪካና በኢራን መካከል በኢስላማባድ የተደረገው የሰላም ድርድር ያለምንም ውጤት መጠናቀቁን ተከትሎ፣ የአሜሪካ ጦር ከሰኞ ጀምሮ ወደ ኢራን ወደቦች የሚገቡና የሚወጡ ማናቸውንም መርከቦች እንቅስቃሴ ለማገድ መዘጋጀቱን አሳውቆ የነበር ሲሆን፤ የዚህ እርምጃ ዋና ዓላማ የኢራንን ወታደራዊ እና ኢኮኖሚያዊ አቅም ሙሉ በሙሉ ለመገደብ እንደሆነ ተመላክቷል።

በሆርሙዝ ወሽመጥ ጉዳይ ላይ የተለያዩ ሀገራትም ሐሳባቸውን እየገለጹ ሲሆን፤ የዓለማችን ቀዳሚ የድፍድፍ ነዳጅ አስመጪ የሆነችው ቻይና በሆርሙዝ ወሽመጥ ላይ የሚደረግ ማንኛውም እገዳ የዓለም አቀፉን ማኅበረሰብ ጥቅም የሚጎዳ ነው ብላለች።

አያይዛም፣ እገዳው በራሷ የኢነርጂ ዋስትና ላይ ሊፈጥረው የሚችለው ጫና በእጅጉ እንዳሳሰባት ገልጻ፤ ሁሉም ወገኖች ትዕግሥትን እንዲላበሱ አሳስባለች።


የአውሮፓ ኅብረትም በተመሳሳይ በመካከለኛው ምስራቅ ቀጣና ያለው አለመረጋጋት እንዳሳሰበው ገልጿል።፤ የኅብረቱ የውጭ ጉዳይ ፖሊሲ ኃላፊ ካያ ካላስ፣ አሁን እየታየ ያለው ሁኔታ በቀጣናው “ጠንካራ ዓለም አቀፍ የባህር ላይ ደህንነት ጥምረት” አስፈላጊ መሆኑን አመላካች ነው ብለዋል።

በሀብተሚካኤል ክፍሉ

#MiddleEast #StraitOfHormuz #USA #Iran #EnergySecurity #GlobalEconomy #EBC
👏1
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የላይቤሪያ ፕሬዝዳንት ጆሴፍ ንዩማ ቦአካይን ተቀበሉ
*********************************

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የላይቤሪያ ፕሬዝዳንት ጆሴፍ ንዩማ ቦአካይን ተቀብለዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በመልዕክታቸው "የነገ ብሩህ ተስፋ እየተሰራባት ወደ ምትገኘው ምድረቀደምት ኢትዮጵያ እንኳን በሰላም መጡ" ብለዋቸዋል።

‎"በቆይታዎ እጅግ ፍሬያማ ውይይት እንደሚኖረን እምነቴ ነው" ሲሉም ጠቅላይ ሚኒስትሩ ገልጸዋል።

#Ethiopia #Liberia #bilateral #diplomacy #EBC
🕊3👏2
የመደመር አንቀፅ
ከአምራች ኢንዱስትሪው ዝግጁነት መገለጫዎች መካከል መሠረተ ልማት ዋነኛው ነው። ኢትዮጵያ ለአመታት በኢኮኖሚ መሠረተ ልማቶች ላይ ከፍተኛ ኢንቨስትመንት ስታደርግ ቆይታለች፡፡ አሁን በግንባታ ሂደት ላይ የሚገኙትን ጨምሮ ከዚህ በፊት የተገነቡት የትራንስፖርት እና የቴክኖሎጂ መሠረተ ልማቶች፣ የኃይል ማመንጫዎች፣ የኢንዱስትሪ ፓርኮችና ዞኖች፣ የጉምሩክና ሎጅስቲክስ መሠረተ ልማቶች፣ ሀገራችን ለአምራች ኢንዱስትሪው ዕድገት ያሳካችው ዝግጁነት መገለጫ ተደርገው የሚቀርቡ ናቸው።
የኤሌክትሪክ ኃይል አቅርቦትን ለማስፋፋት ባለፉት ዓመታት ሰፊ ኢንቨስትመንት ተካሂዷል። ለአምራች ኢንዱስትሪው የሚቀርበው የኤሌክትሪክ ኃይል አቅርቦትም ከፍተኛ ለውጥ አሳይቷል። የሕዳሴ የኃይል ማመንጫን ጨምሮ ሌሎች በጅምር ያሉና በሚገባ አገልግሎት እየሰጡ ያልነበሩ ማመንጫዎችን ወደ መስመር ለማስገባት ተችሏል።
በዚህም ሀገራችን ለአምራች ኢንዱስትሪው የሚያስፈልጋትን የኃይል አቅርቦት በሚገባ መሸፈን ችለናል።
የመደመር መንግስት
ገፅ 206
👏1
ፓኪስታን በአሜሪካ እና ኢራን መካከል የሚደረግ ሁለተኛ ዙር ድርድርን ለማስተናገድ ሐሳብ አቀረበች
*******************

ፓኪስታን የ15 ቀኑ የተኩስ አቁም ስምምነት ከማብቃቱ በፊት በአሜሪካ እና በኢራን መካከል የሚደረግ ሁለተኛ ዙር ድርድር በኢስላማባድ ለማስተናገድ ሐሳብ ማቅረቧን አሶሺየትድ ፕሬስ ዘግቧል።

የዜና ወኪሉ ስማቸው እንዳይጠቀስ የፈለጉ ሁለት የፓኪስታን ባለሥልጣናትን ጠቅሶ እንደዘገበው፣ ሀገሪቱ ይህንን ጥያቄ ያቀረበችው ውጥረቱን በዘላቂነት ለመቀነስ ካላት ፍላጎት በመነሣት ነው።

የሐሳቡ ተግባራዊነት የሚወሰነው ተደራዳሪ ወገኖቹ ሌላ የተለየ ቦታ እንዲመቻችላቸው የሚጠይቁ መሆን አለመሆኑ ላይ እንደሆነ ባለሥልጣናቱ መግለጻቸው ተጠቁሟል።

በኢራን እና በአሜሪካ መካከል ሁለተኛው ዙር ድርድር በቅርብ ቀናት ውስጥ፣ ምናልባትም ሐሙስ ዕለት ሊደረግ እንደሚችል ተዘግቧል።

#EBC #middleeast #iran #usa #peace
👍1
የኢትዮጵያ የኢንደስትሪ ጉዞ አዲስ ምዕራፍ እየተራመደ ይገኛል

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ከኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን ጋር ባደረጉት የሁለት ክፍሎች ቃለምልልስ ኢትዮጵያ የአዲሱ ዘመን የኢንደስትሪ መስፋፋትን እንዴት እየበየነች እንደሆነ አብራርተዋል።

የመጀመሪያውን ክፍል ዛሬ ምሽት 2:30 በኢቢሲ የተለያዩ አማራጮች ይጠብቁ።
#PMOEthiopia #PMAbiyAhmed #EBC
👏1