Ethiopian Broadcasting corporation ®
8.85K subscribers
17.9K photos
205 videos
14 files
1.62K links
Ethiopian broadcasting corporation is a 24 working public media.

https://telega.io/c/EBC_TV
ማንኛውም አይነት አስተያየት እና ጥቆማ ካላችሁ በዚህ ላኩልን እንቀበላለን!!
https://t.me/+G7d4hSzJEhViMzQ0
Download Telegram
የመደመር አንቀፅ
ከአምራች ኢንዱስትሪው ዝግጁነት መገለጫዎች መካከል መሠረተ ልማት ዋነኛው ነው። ኢትዮጵያ ለአመታት በኢኮኖሚ መሠረተ ልማቶች ላይ ከፍተኛ ኢንቨስትመንት ስታደርግ ቆይታለች፡፡ አሁን በግንባታ ሂደት ላይ የሚገኙትን ጨምሮ ከዚህ በፊት የተገነቡት የትራንስፖርት እና የቴክኖሎጂ መሠረተ ልማቶች፣ የኃይል ማመንጫዎች፣ የኢንዱስትሪ ፓርኮችና ዞኖች፣ የጉምሩክና ሎጅስቲክስ መሠረተ ልማቶች፣ ሀገራችን ለአምራች ኢንዱስትሪው ዕድገት ያሳካችው ዝግጁነት መገለጫ ተደርገው የሚቀርቡ ናቸው።
የኤሌክትሪክ ኃይል አቅርቦትን ለማስፋፋት ባለፉት ዓመታት ሰፊ ኢንቨስትመንት ተካሂዷል። ለአምራች ኢንዱስትሪው የሚቀርበው የኤሌክትሪክ ኃይል አቅርቦትም ከፍተኛ ለውጥ አሳይቷል። የሕዳሴ የኃይል ማመንጫን ጨምሮ ሌሎች በጅምር ያሉና በሚገባ አገልግሎት እየሰጡ ያልነበሩ ማመንጫዎችን ወደ መስመር ለማስገባት ተችሏል።
በዚህም ሀገራችን ለአምራች ኢንዱስትሪው የሚያስፈልጋትን የኃይል አቅርቦት በሚገባ መሸፈን ችለናል።
የመደመር መንግስት
ገፅ 206
👏1
ፓኪስታን በአሜሪካ እና ኢራን መካከል የሚደረግ ሁለተኛ ዙር ድርድርን ለማስተናገድ ሐሳብ አቀረበች
*******************

ፓኪስታን የ15 ቀኑ የተኩስ አቁም ስምምነት ከማብቃቱ በፊት በአሜሪካ እና በኢራን መካከል የሚደረግ ሁለተኛ ዙር ድርድር በኢስላማባድ ለማስተናገድ ሐሳብ ማቅረቧን አሶሺየትድ ፕሬስ ዘግቧል።

የዜና ወኪሉ ስማቸው እንዳይጠቀስ የፈለጉ ሁለት የፓኪስታን ባለሥልጣናትን ጠቅሶ እንደዘገበው፣ ሀገሪቱ ይህንን ጥያቄ ያቀረበችው ውጥረቱን በዘላቂነት ለመቀነስ ካላት ፍላጎት በመነሣት ነው።

የሐሳቡ ተግባራዊነት የሚወሰነው ተደራዳሪ ወገኖቹ ሌላ የተለየ ቦታ እንዲመቻችላቸው የሚጠይቁ መሆን አለመሆኑ ላይ እንደሆነ ባለሥልጣናቱ መግለጻቸው ተጠቁሟል።

በኢራን እና በአሜሪካ መካከል ሁለተኛው ዙር ድርድር በቅርብ ቀናት ውስጥ፣ ምናልባትም ሐሙስ ዕለት ሊደረግ እንደሚችል ተዘግቧል።

#EBC #middleeast #iran #usa #peace
👍1
የኢትዮጵያ የኢንደስትሪ ጉዞ አዲስ ምዕራፍ እየተራመደ ይገኛል

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ከኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን ጋር ባደረጉት የሁለት ክፍሎች ቃለምልልስ ኢትዮጵያ የአዲሱ ዘመን የኢንደስትሪ መስፋፋትን እንዴት እየበየነች እንደሆነ አብራርተዋል።

የመጀመሪያውን ክፍል ዛሬ ምሽት 2:30 በኢቢሲ የተለያዩ አማራጮች ይጠብቁ።
#PMOEthiopia #PMAbiyAhmed #EBC
👏1
ፓኪስታን በአሜሪካ እና ኢራን መካከል የሚደረግ ሁለተኛ ዙር ድርድርን ለማስተናገድ ሐሳብ አቀረበች
*******************

ፓኪስታን የ15 ቀኑ የተኩስ አቁም ስምምነት ከማብቃቱ በፊት በአሜሪካ እና በኢራን መካከል የሚደረግ ሁለተኛ ዙር ድርድር በኢስላማባድ ለማስተናገድ ሐሳብ ማቅረቧን አሶሺየትድ ፕሬስ ዘግቧል።

የዜና ወኪሉ ስማቸው እንዳይጠቀስ የፈለጉ ሁለት የፓኪስታን ባለሥልጣናትን ጠቅሶ እንደዘገበው፣ ሀገሪቱ ይህንን ጥያቄ ያቀረበችው ውጥረቱን በዘላቂነት ለመቀነስ ካላት ፍላጎት በመነሣት ነው።

የሐሳቡ ተግባራዊነት የሚወሰነው ተደራዳሪ ወገኖቹ ሌላ የተለየ ቦታ እንዲመቻችላቸው የሚጠይቁ መሆን አለመሆኑ ላይ እንደሆነ ባለሥልጣናቱ መግለጻቸው ተጠቁሟል።

በኢራን እና በአሜሪካ መካከል ሁለተኛው ዙር ድርድር በቅርብ ቀናት ውስጥ፣ ምናልባትም ሐሙስ ዕለት ሊደረግ እንደሚችል ተዘግቧል።

#EBC #middleeast #iran #usa #peace
👍1
ፕሬዚዳንት ሺ ጂንፒንግ ለባሕረ ሰላጤው ሀገራት ሉዓላዊነት እና ደኅንነት ተገቢው ክብር እንዲሰጥ አሳሰቡ
*************************

የቻይናው ፕሬዚዳንት ሺ ጂንፒንግ ከአቡ ዳቢው አልጋ ወራሽ መሐመድ ቢን ዛይድ ጋር ባደረጉት ውይይት በመካከለኛው ምሥራቅ ሰላም እና መረጋጋትን ለማጠናከር የሚያስችል ባለ አራት ነጥብ የውሳኔ ሐሳብ ማቅረባቸውን ሺንዋ ዘግቧል።

የውሳኔ ሐሳቡ በሰላም አብሮ መኖር፣ ብሔራዊ ሉዓላዊነት እና ዓለም አቀፍ የሕግ የበላይነት መርሆዎች ላይ ትኩረት የሚያደርግ ሲሆን፣ ለደኅንነት እና የልማት ቅንጅት አስፈላጊነትም አፅንዖት ይሰጣል።

ፕሬዚዳንቱ፣ “በመካከለኛው ምሥራቅ የሚገኙ የባሕረ ሰላጤው ሀገራት ሉዓላዊነት፣ ደኅንነት እና የግዛት አንድነት በቅንነት ሊከበር ይገባል” ማለታቸውን የቻይና የቴሌቪዥን ጣቢያ (CCTV) ዘግቧል።

#EBC #Ethiopia #middleeast #china #sovereignty #security
👏1
"ሕልሜ መኪና በአነስተኛ ዋጋ እና በብዛት ሲመረት ማየት ነው" - የራሱን መኪና የሠራው ወጣት
******************

ወጣት ብሩክ ወንድይፍራው ይባላል፤ በልጅነቱ ከአባቱ እግር ሥር የማሽን ብየዳ እና የሞዲፊኬሽን ሥራ ከመቅሰም ተሻግሮ፣ ሙያውን በትምህርት ለማጠናከር በማሰብ በባሕር ዳር ቴክኒክ እና ሙያ ኮሌጅ በአውቶ ኤሌክትሪክ ዘርፍ ተመርቋል።

የአባቱን ፈለግ የመከተል ሕልም እንደነበረው የሚናገረው ብሩክ፣ ግዙፍ የሳሙና መሥሪያ፣ የመኖ ማቀነባበሪያ እና ልዩ ልዩ የፋብሪካ ማሽኖችን ከማምረት ተሻግሮ፣ ባለ አራት እግር 300 ሲሲ (cc) ሞተር ያላት የራሱን መኪና መሥራት ችሏል።

እንደ ብሩክ ገለጻ፣ ተሽከርካሪዋ ሙሉ በሙሉ በሀገር ውስጥ ጥሬ ዕቃዎች የተሠራች እና ከ400 ኪሎ ግራም በላይ ክብደት ያላት ሲሆን፣ ሥራውን ለማጠናቀቅም ስምንት ወራት ወስዶበታል። ...

ለሙሉ መረጃው https://web.facebook.com/EBCzena/posts/pfbid025EVMsXA6DrPMkyNvtaKWqN2SocdZq7MDgjygifRChYz1yn3UXRDWyhDDZWLMTFYel
👏1
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከፖርቹጋል የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጋር ተወያዩ
********************

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የፖርቹጋል የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ፓውሎ ራንገልን ተቀብለው አነጋግረዋል።

በውይይታቸውም በኢትዮጵያ እና በፖርቹጋል መካከል ያለውን የሁለትዮሽ ግንኙነት ይበልጥ ማጠናከር በሚቻልባቸው ሁኔታዎች ላይ መክረዋል።

በተጨማሪም በሁለቱ ሀገራት መካከል የሚደረጉ ቀጣይ ትብብሮችን ይበልጥ ለማሳደግ በሚያስችሉ ቁልፍ መስኮች ዙሪያ ሰፊ ምክክር ማድረጋቸውን ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማኅበራዊ ትስስር ገጽ ገልጸዋል።
#Ethiopia #Portugal #Diplomacy #Cooperation #AbiyAhmed #EthiopianBroadcastingCorporation
👏1
ኢትዮጵያ እና ፖርቹጋል በንግድ፣ በቱሪዝም እና በዲፕሎማሲ መስኮች በጋራ ለመሥራት ከስምምነት ደረሱ
*************

ጌዲዎን ጢሞቲዎስ (ዶ/ር) ከፖርቹጋል ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ፓውሎ ሬንጄል ጋር በጽሕፈት ቤታቸው ተወያይተዋል።

በውይይታቸውም ኢትዮጵያ እና ፖርቹጋል ረጅም ዘመናትን ያስቆጠረ ታሪካዊ ግንኙነት ያላቸው ሀገራት መሆናቸውን ዶ/ር ጌዲዎን ገልጸዋል።

ይህንን ግንኙነት በንግድ፣ በኢንቨስትመንት፣ በቱሪዝም እና በአካባቢ ጥበቃ ዘርፎች ይበልጥ ማጠናከር እንደሚገባም አመልክተዋል።

የፖርቹጋል ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ፓውሎ ሬንጄል በበኩላቸው...https://web.facebook.com/EBCzena/posts/pfbid0aSSxb67Pknw9ky7fvAXDaePq47VY8BmUPKWJkTZiFC3BkvhgsWTXLnYSXzFaks8El
👏1