ደቂቃዎችን የወሰደው የሰሜን ኮሪያውን መሪ አሻራ እና ዲኤንኤ የማጥፋት ሥራ
*****************
ትናንት በቻይና ቤጂንግ ተካሂዶ በነበረው ታላቅ ወታደራዊ ሰልፍ ላይ ተጋብዘው ቤጂንግ ከተገኙት የሀገራት መሪዎች መካከል የሩሲያው ፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑቲን እና የሰሜን ኮሪያው ኪም ጆንግ ኡን ይገኙበታል።
በቻይና የተገናኙት እነዚህ መሪዎች የሁለትዮሽ ውይይት ያደረጉ ሲሆን ውይይታቸው ሲጠናቀቅ የሰሜን ኮሪያው መሪ ኪም ጆንግ ኡን የፀጥታ ሰዎች፣ እርሳቸው ተቀምጠውበት የነበረውን ወንበር እና በእጃቸው ነክተዋቸዋል ብለው ያሰቡትን የወንበር መደገፊያ፣ ጠረጴዛ እና ሌሎች እቃዎችን በኬሚካል ሲያፀዱ ታይተዋል።
በዚህ በከፍተኛ ሁኔታ በጥንቃቄ በተካሄደ ዱካን የማጥፋት ሥራ ሁለት የፀጥታ ሠራተኞች በስብሰባው አዳራሽ ያሉትን ነገሮች በሚገባ ካፀዱ በኋላ ኪም ጆንግ ኡን የጠጡበትን ብርጭቆ በሌላ አካል እጅ እንዳይገባ ይዘውት ሄደዋል።
ሰሜን ኮሪያ በተለያየ ጊዜያት የኪም ጆንግ ኡን አሻራ እና ዲኤንኤ ወደ ሌሎች ሀገራት የስለላ ድርጅቶች እጅ እንዳይገባ ከፍተኛ ጥንቃቄ ታደርጋለች።
ከእነዚህ መካከልም እ.አ.አ በ2019 በቪዬትናም ሃኖይ ከአሜሪካው ፕሬዚዳንት ትራምፕ ጋር በተወያዩበት ወቅት፣ ከስብሰባው መጠናቀቅ በኋላ ኪም ጆንግ ኡን የነኳቸውን እቃዎች እንዲሁም ያረፉበትን ክፍል ለሰዓታት ያፀዱ ሲሆን፣ የተኙበትን ፍራሽ እና አንሶላ እንዲወገዱ አድርገዋል።
በዋሲሁን ተስፋዬ
#EBC #ebcdotstream #putin #kim #DNA #security

👍1
ፕሬዚዳንት ሺ ጂንፒንግ ለባሕረ ሰላጤው ሀገራት ሉዓላዊነት እና ደኅንነት ተገቢው ክብር እንዲሰጥ አሳሰቡ
*************************
የቻይናው ፕሬዚዳንት ሺ ጂንፒንግ ከአቡ ዳቢው አልጋ ወራሽ መሐመድ ቢን ዛይድ ጋር ባደረጉት ውይይት በመካከለኛው ምሥራቅ ሰላም እና መረጋጋትን ለማጠናከር የሚያስችል ባለ አራት ነጥብ የውሳኔ ሐሳብ ማቅረባቸውን ሺንዋ ዘግቧል።
የውሳኔ ሐሳቡ በሰላም አብሮ መኖር፣ ብሔራዊ ሉዓላዊነት እና ዓለም አቀፍ የሕግ የበላይነት መርሆዎች ላይ ትኩረት የሚያደርግ ሲሆን፣ ለደኅንነት እና የልማት ቅንጅት አስፈላጊነትም አፅንዖት ይሰጣል።
ፕሬዚዳንቱ፣ “በመካከለኛው ምሥራቅ የሚገኙ የባሕረ ሰላጤው ሀገራት ሉዓላዊነት፣ ደኅንነት እና የግዛት አንድነት በቅንነት ሊከበር ይገባል” ማለታቸውን የቻይና የቴሌቪዥን ጣቢያ (CCTV) ዘግቧል።
#EBC #Ethiopia #middleeast #china #sovereignty #security

👏1