Ethiopian Broadcasting corporation ®
8.86K subscribers
17.9K photos
205 videos
14 files
1.62K links
Ethiopian broadcasting corporation is a 24 working public media.

https://telega.io/c/EBC_TV
ማንኛውም አይነት አስተያየት እና ጥቆማ ካላችሁ በዚህ ላኩልን እንቀበላለን!!
https://t.me/+G7d4hSzJEhViMzQ0
Download Telegram
ኢትዮጵያና ላይቤሪያ ከጋራ የጽናት ታሪክ የሚመነጭ ጥልቅ ግንኙነት አላቸው - ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)
***********************

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የላይቤሪያ ሪፐብሊክ ፕሬዝደንት ጆሴፍ ንዩማ ቦአካይን በብሔራዊ ቤተ-መንግሥት አቀባበል አድርገዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው ባስተላለፉት መልእክት፤ ለይፋዊ የሥራ ጉብኝት ኢትዮጵያ የገቡትን የላይቤሪያ ሪፐብሊክ ፕሬዝደንት ጆሴፍ ንዩማ ቦአካይ በብሔራዊ ቤተ-መንግሥት አቀባበል በማድረጌ ታላቅ ክብር ይሰማኛል ብለዋል።

ኢትዮጵያ እና ላይቤሪያ በቅኝ ግዛት ያልተገዙ፣ ለአኅጉሩ ነፃነትና አንድነት ድምፅ በመሆን ከጋራ የጽናት ታሪክ የሚመነጭ ጥልቅና ዘመናትን የተሻገረ ግንኙነት እንዳላቸውም አስታውቀዋል።

ዛሬም እንደ ሁሌው ኢትዮጵያ ከሰፊ ገበታዋ ያላትን ታላቅ ዐቅምና ዘላቂ ወዳጅነት፣ አብረዋት ለሚጓዙ ሁሉ ለማካፈል ዝግጁ መሆኗን ጠቅላይ ሚኒስትሩ አረጋግጠዋል።

በዚህ መንፈስ ይህ ጉብኝት በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለውን ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት በማጠናከር፤ የጋራ ህልሞቻችንን በማይናወጥ መሠረት እና የመፈጸም ቁርጠኝነት ወሳኝ ምዕራፍ እንደሚሆን ጽኑ እምነት እንዳላቸውም ገልጸዋል።

#EBC #Ethiopia #Liberia #Diplomacy #AbiyAhmed #JosephBoakai #PanAfricanism #BilateralRelations
👏1
የቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው የርህራሄ ዓሻራዎች
*****************

በኢትዮጵያ ፖለቲካዊ እና ማህበራዊ ታሪክ ውስጥ "ቀዳማዊት እመቤት" የሚለው ስያሜ ከግርማዊነትና ከክብር ባለፈ፣ አዲስ ትርጉም እየያዘ መጥቷል። ይህ ስያሜ ዛሬ ላይ የዝምታ አገልግሎት፣ የትህትና ጉዞ እና የሰብዓዊነት መገለጫ ሆኖ በብዙዎች ልብ ውስጥ ሰርጿል።

ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው ባለፉት ጥቂት ዓመታት ያሳዩት የማይነጥፍ ቁርጠኝነት አንድን ትልቅ እውነት በተግባር አረጋግጧል፤ "እናትነት በቤት ውስጥ አይወሰንም፤ የሀገር እናትነት ማለት የሌሎችን ህመም መጋራት፣ የጎደለውን መሙላት ነው" የሚለውን እውነት።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) "መደመር" በሚለው ፍልስፍናቸው ኢትዮጵያውያን ተደጋግፈውና ተሳስረው እንዲያድጉ እንደሚወተውቱት ሁሉ፣ ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸውም ይህንን ራዕይ ወደ ማዕድ ማጋራት ተግባር ቀይረውታል። በመላው ኢትዮጵያ የተገነቡት 14 ግዙፍ የዳቦና የዱቄት ፋብሪካዎች የዚህ የ"መደመር" ፍሬ ህያው ምስክሮች ናቸው።
https://web.facebook.com/EBCzena/posts/pfbid02wG6LAy54EYfZ8oCz3paD8Hf3oZtf8LkX3tYBaXPQ8AggjSYQ8TjwWE8CjsCRPXkLl
👏1
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከላይቤሪያ ፕሬዝደንት ጆሴፍ ንዩማ ቦአካይ ጋር ተወያዩ
***********************

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከላይቤሪያ ፕሬዝደንት ጆሴፍ ንዩማ ቦአካይ ጋር ፍሬያማ የሁለትዮሽ ውይይት ማድረጋቸውን ገልጸዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባስተላለፉት መልእክት፤ በውይይታቸው በተለያዩ ዘርፎች ያላቸውን የቆየ አጋርነት ይበልጥ ለማጠናከርና ለማስፋት ወሳኝ ምዕራፍ መከፈቱን አስታውቀዋል።

ከሁለትዮሽ ስብሰባው በመቀጠልም፣ በሁለቱ ሀገራት በኩል ቅድሚያ የሚሰጣቸውን ጉዳዮች ለማሳካት ያለውን ቁርጠኝነት የሚያረጋግጡ የመግባቢያ ስምምነቶች እንዲፈረሙ መደረጉን ጠቁመዋል።

እነዚህ ስምምነቶች ኢትዮጵያ በፈጣን የለውጥ ጉዞ ያካበተችውን ልምድ ለሌሎች የአፍሪካ ሀገራት ለማካፈል፤ እንዲሁም ከአጋሮቻቸው የተለያዩ ዕይታዎችን በመቅሰም ለአኅጉሩ ዕድገት ዘላቂና አፍሪካዊ መፍትሄዎችን በጋራ ለማፍለቅ እንደ ወሳኝ መሠረት እንደሚያገለግሉ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ገልጸዋል።
👏1