Ethiopian Broadcasting corporation ®
8.86K subscribers
17.9K photos
205 videos
14 files
1.62K links
Ethiopian broadcasting corporation is a 24 working public media.

https://telega.io/c/EBC_TV
ማንኛውም አይነት አስተያየት እና ጥቆማ ካላችሁ በዚህ ላኩልን እንቀበላለን!!
https://t.me/+G7d4hSzJEhViMzQ0
Download Telegram
የባሕር በር ደኅንነት ጉዳይ ከምንጊዜውም በላይ አንገብጋቢ ሆኗል - ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)
*******************

የዓለም የንግድ እና የኢንዱስትሪ ትሥሥር በአየር፣ በየብስ እና በባሕር ሎጂስቲክስ ስጋቶች ውስጥ መውደቁን ተከትሎ የባሕር በር ደኅንነት ጉዳይ ከምንጊዜውም በላይ አንገብጋቢ መሆኑን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ገልጸዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ እንደገለጹት፣ መንግሥት ከዓመታት በፊት የባሕር ላይ እንቅስቃሴ አደጋ ሊገጥመው እንደሚችል በመተንበይ "ከባሕር ከራቅን 130 ሚሊዮን ሕዝብ አደጋ ውስጥ ይወድቃል" የሚል የጸና አቋም ሲያራምድ ቆይቷል።

ምንም እንኳን በወቅቱ ለዚህ ጉዳይ በቂ ትኩረት ባይሰጠውም፣ አሁን ላይ ግን ሀገራት የንግድ መስመሮችን ለጥቅማቸውም ሆነ ተቀናቃኞቻቸውን ለመጉዳት ሲሉ በከፍተኛ ደረጃ እየተቆጣጠሩት ይገኛሉ።

በመሆኑም ከባሕር መራቅም ሆነ በአንድ መስመር ላይ ብቻ ጥገኛ መሆን አዋጭ ባለመሆኑ፣ ኢትዮጵያ ለዚህ የሎጂስቲክስ አለመረጋጋት አስቀድሞ መተንበይን ‘ፕሮአክቲቭ የሆነ መፍትሔ’ መከተሏን ጠቅላይ ሚኒስትሩ አብራርተዋል።

#EBC #Ethiopia #PMAbiyAhmed #SeaAccess
👏2
ሀገርን መገንባት የሚቻለው በጥግግት የሚኖር ማኅበረሰብ ሲፈጠር ነው:- ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)
**********************
ሀገርን መገንባት የሚቻለው በ"ጥግግት" (Agglomeration) የሚኖር ማኅበረሰብ ሲፈጠር መሆኑን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) አስታወቁ።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ "ከተማ አያስፈልገኝም፣ ደጋፊዬ አርሶ አደር ነው" የሚለው እሳቤ ልማትን እንደማያመጣ ገልጸው፣ ከተሜነት ለኢኖቬሽን፣ ለውድድር እና ለተሻለ የመንግሥት አገልግሎት ወሳኝ መሆኑን አስረድተዋል።

በትምህርት ዘርፍም ሰፊ የእሳቤ ለውጥ መደረጉን ጠቁመው፤ ዩኒቨርሲቲዎችን እንደ ኮንዶሚኒየም በየዞኑ በመበተን ጥራት የሌለው ትምህርት ከመስጠት ይልቅ...https://web.facebook.com/EBCzena/posts/pfbid0VN21yvz6i7bpiLQqoUArXVjxcYNYBn74uG4QYUAtXxmSTzS5Ly2xWq8aNB6p1ErWl
👍1🕊1
ሩስያ በብሪክስ ሀገራት መካከል የጋራ የመጠባበቂያ ምግብ ክምችት ዘዴ እንዲመሠረት ሐሳብ አቀረበች
***********************

በዓለም አቀፍ ደረጃ እየታየ የመጣውን የምግብ ዋስትና ስጋት ለመቀነስ እና የገበያ መረጋጋትን ለመፍጠር ሩስያ በብሪክስ ሀገራት እና በቀጣናዊ አጋሮች በጋራ የሚመራ የመጠባበቂያ ምግብ ክምችት ዘዴ እንዲመሰረት የሚያስችል ሐሳብ አቀረበች።

የሩስያ የደህንነት ምክር ቤት ከፍተኛ ባለስልጣን እንደገለጹት፤ በአሁኑ ወቅት በዓለም አቀፍ ደረጃ እየተስተዋለ ያለው የነዳጅ እና የማዳበሪያ ምርት አቅርቦት መስተጓጎል በግብርናው ዘርፍ ላይ እያሳደረው ያለውን ጫና ለመቋቋም በአጋር ሀገራት መካከል ጠንካራ ቅንጅት መፍጠርን አስፈላጊ አድርጎታል።

በተለይም በመካከለኛው ምስራቅ ያገረሸው ግጭት የማዳበሪያ ንግድ ዋነኛ መስመር የሆነው የሆርሙዝ የባሕር ወሽመጥ እንዲዘጋ በማድረጉ፣ ለሰብል ምርታማነት ወሳኝ በሆነው የማዳበሪያ አቅርቦት ላይ ከፍተኛ ተጽእኖ ማሳረፉ ተመልክቷል።

ሩስያ ይህን ስጋት በዘላቂነት ለመቀነስ የጋራ የመጠባበቂያ ምግብ ክምችት ዘዴ እንዲኖር ሐሳብ ያቀረበች ሲሆን፣ በተጨማሪም እ.አ.አ እስከ 2030 ድረስ የግብርና ምርት ወጪ ንግዷን በ50 በመቶ በማሳደግ በዓለም አቀፍ የምግብ አቅርቦት ሰንሰለት ውስጥ ተምትጫወተውን ቁልፍ ሚና ይበልጥ ለማጠናከር በቁርጠኝነት እየሠራች መሆኑን አስታውቃለች።

በሰለሞን ገዳ

#Russia #BRICS #FoodReserve #FoodSecurity #EBC
👍1👏1
"ኢራን የኑክሌር ጦር መሣሪያ ፍላጎቷን ከተወች፣ በኢኮኖሚ እንድትበለጽግ እናደርጋለን" - አሜሪካ
*****************

በአሜሪካ እና በኢራን መካከል ያለው ውጥረት ባለበት ሁኔታ፣ የምክትል ፕሬዚዳንት ጄዲ ቫንስ አዲስ መግለጫ የብዙዎችን ትኩረት ስቧል።

ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕም የሰላም ንግግሩ በሚቀጥሉት ሁለት ቀናት ውስጥ ሊቀጥል እንደሚችል ፍንጭ ሰጥተዋል።

በፓኪስታን የተደረገው የመጀመሪያ ዙር ንግግር ያለምንም ስምምነት ቢጠናቀቅም፣ ቫንስ አሁን ስላለው ሂደት "ጥሩ ስሜት ይሰማኛል" ብለዋል።

በሀገራቱ መካከል ያለው ጥልቅ አለመተማመን በአንድ ጀንበር እንደማይፈታም አክለዋል።

ትራምፕ የሚፈልጉት ተራ ስምምነት ሳይሆን ለውጥ የሚያመጣ ትልቅ ስምምነት ስለመሆኑ ቫንስ ገልጸዋል።

ትራምፕ፣ "ኢራን የኑክሌር ጦር መሣሪያ የማምረት ሐሳቧን ከተወች፣ ኢራን እንድትበለጽግና የዓለም ኢኮኖሚ አካል እንድትሆን እናደርጋለን" ብለዋል።

ለአሜሪካ የ"ብልጽግና" ግብዣ ኢራን የምትሰጠው ምላሽ በጉጉት እየተጠበቀ ነው።

በሌላ በኩል ካናዳ፣ እንግሊዝ፣ አውስትራሊያ እና ሌሎች 7 ሀገራት በሊባኖስ ያለው ግጭት በአስቸኳይ እንዲቆም በጋራ መግለጫ ጠይቀዋል።

ከሦስቱ ሀገራት በተጨማሪ መግለጫውን ብራዚል፣ ኮሎምቢያ ኢንዶኔዥያ፣ ጃፓን፣ ዮርዳኖስ፣ ሴራሊዮን እና ስዊዘርላንድ ፈርመውታል።

ሀገራቱ በሊባኖስ እየተባባሰ ባለው የሰብዓዊ ቀውስ እና የተፈናቃዮች ቁጥር መጨመር ከፍተኛ ስጋት እንዳላቸው ገልጸዋል።

በተለይም ባለፈው መጋቢት ወር ሦስት የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የሰላም አስከባሪዎች መገደላቸውን አውግዘዋል።

#MiddleEast #Iran #USA #negotiation #Trump #Vance #Lebanon
🕊1
ሰላምን ማጽናት ከእያንዳንዱ ዜጋ የሚጠበቅ ተግባር ነው፡- ሊቀ ትጉሃን ቀሲስ ታጋይ ታደለ
*****************
7ኛው ሀገር አቀፍ የሰላም ጉባዔ "ሰላምን ይበልጥ ለማስፋት እና ለማስረፅ የሃይማኖቶች ሚና" በሚል መሪ ሀሳብ በአሶሳ ከተማ እየተካሄደ ነው።

የኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባዔ ጠቅላይ ጸሐፊ ሊቀ ትጉሃን ቀሲስ ታጋይ ታደለ፣ ሰላምን ማጽናት ከሁሉም ዜጋ እንደሚጠበቅ ተናግረዋል።ሆኖም የእምነት አባቶች እና ምእመናን በዚህ ረገድ ያላቸው ኃላፊነት ከፍ ያለ መሆኑን አብራርተዋል።

ባለፉት የሰላም ኮንፈረንሶች ሰላምና አንድነትን በሚያጠናክሩ ጉዳዮች ላይ በመምከር በርካታ ውጤቶች መገኘታቸውን ቀሲስ ታጋይ አስታውሰዋል።

በአሶሳ እየተካሄደ ያለው 7ኛው ሀገር አቀፍ ጉባዔም ሀገራዊ አንድነትን ለማምጣት ትልቅ አቅም እንደሚፈጥር ጠቁመዋል።

በጉባዔው ላይ የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት ፕሬዚዳንት…https://web.facebook.com/EBCzena/posts/pfbid02aBvW5P7QXcNfZQtiQ8LZL66treWVx1p6SZpGTyUA3C25rEDgJyPRgVmTCoxSeeyul
👎1
የመካከለኛው ምስራቅ ውጥረት፣ የትራምፕ ቀነ-ገደብ እና የዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ ስጋት
***********

በአሜሪካ እና በኢራን መካከል ያለው ወታደራዊ እና ዲፕሎማሲያዊ ፍጥጫ እያየለ በመጣበት በዚህ ወቅት፣ የኢራኑ ፕሬዚዳንት መስዑድ ፔዜሽኪያን ሀገራቸው ለማንኛውም ኃይል እጅ እንደማትሰጥ አረጋግጠዋል።

ፕሬዚዳንቱ፣ ኢራንን በማስገደድ ለማንበርከክ የሚደረግ ማንኛውም ሙከራ ውጤቱ ውድቀት ብቻ ይሆናል ሲሉ አስጠንቅቀዋል።

በሌላ በኩል የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ለኢራን የሰጡትን የተኩስ አቁም ቀነ-ገደብ የማራዘም ፍላጎት እንደሌላቸው አስታውቀዋል።

ትራምፕ፣ የሰሜን አትላንቲክ ጦር ቃል ኪዳን ድርጅት (NATO) በሆርሙዝ ወሽመጥ ጉዳይ አሜሪካን ባለመደገፉ ዳግም ወቅሰዋል።

የቻይና የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ፣ የአሜሪካና የኢራንን ግጭት ለማስቆም የሚደረጉ ማናቸውንም ጥረቶች ሀገራቸው እንደምትደግፍ አስታውቀዋል።

ማሌዥያ በበኩሏ፣ አሜሪካ በሆርሙዝ ወሽመጥ ላይ የጣለችውን የባሕር ትራንስፖርት እገዳ በድጋሚ እንድታጤነው እና እንድታነሳው ጥሪ አቅርባለች።

#MiddleEast #Iran #USA #Trump #Pezeshkian #China #Malaysia #Hormuz #BreakingNews
👏1
ሃላባ ከተማ ለመጀመሪያ ጊዜ ወደ ኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ አደገ
*************

በኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ ምድብ ለ ላይ የነበረው ሃላባ ከተማ በ19ኛ ሳምንት ተከታዩ ደሴ ከተማን 1 ለ 0 በማሸነፍ ወደ ኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ለመጀመርያ ጊዜ አድጓል።

በሐዋሳ በተደረው ጨዋታ እስራኤል ሸጎሌ የሃላባን የማሸነፊያ ግብ አስቆጥሯል። ሃላባ ከተማ ሊጉ ሊጠናቀቅ አንድ ጨዋታ እየቀረው ነው ወደ ሊጉ ማደጉን ያረጋገጠው።

#EBC #Ethiopia #football