Ethiopian Broadcasting corporation ®
8.86K subscribers
17.9K photos
205 videos
14 files
1.62K links
Ethiopian broadcasting corporation is a 24 working public media.

https://telega.io/c/EBC_TV
ማንኛውም አይነት አስተያየት እና ጥቆማ ካላችሁ በዚህ ላኩልን እንቀበላለን!!
https://t.me/+G7d4hSzJEhViMzQ0
Download Telegram
የመካከለኛው ምስራቅ ውጥረት፣ የትራምፕ ቀነ-ገደብ እና የዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ ስጋት
***********

በአሜሪካ እና በኢራን መካከል ያለው ወታደራዊ እና ዲፕሎማሲያዊ ፍጥጫ እያየለ በመጣበት በዚህ ወቅት፣ የኢራኑ ፕሬዚዳንት መስዑድ ፔዜሽኪያን ሀገራቸው ለማንኛውም ኃይል እጅ እንደማትሰጥ አረጋግጠዋል።

ፕሬዚዳንቱ፣ ኢራንን በማስገደድ ለማንበርከክ የሚደረግ ማንኛውም ሙከራ ውጤቱ ውድቀት ብቻ ይሆናል ሲሉ አስጠንቅቀዋል።

በሌላ በኩል የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ለኢራን የሰጡትን የተኩስ አቁም ቀነ-ገደብ የማራዘም ፍላጎት እንደሌላቸው አስታውቀዋል።

ትራምፕ፣ የሰሜን አትላንቲክ ጦር ቃል ኪዳን ድርጅት (NATO) በሆርሙዝ ወሽመጥ ጉዳይ አሜሪካን ባለመደገፉ ዳግም ወቅሰዋል።

የቻይና የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ፣ የአሜሪካና የኢራንን ግጭት ለማስቆም የሚደረጉ ማናቸውንም ጥረቶች ሀገራቸው እንደምትደግፍ አስታውቀዋል።

ማሌዥያ በበኩሏ፣ አሜሪካ በሆርሙዝ ወሽመጥ ላይ የጣለችውን የባሕር ትራንስፖርት እገዳ በድጋሚ እንድታጤነው እና እንድታነሳው ጥሪ አቅርባለች።

#MiddleEast #Iran #USA #Trump #Pezeshkian #China #Malaysia #Hormuz #BreakingNews
👏1
ሃላባ ከተማ ለመጀመሪያ ጊዜ ወደ ኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ አደገ
*************

በኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ ምድብ ለ ላይ የነበረው ሃላባ ከተማ በ19ኛ ሳምንት ተከታዩ ደሴ ከተማን 1 ለ 0 በማሸነፍ ወደ ኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ለመጀመርያ ጊዜ አድጓል።

በሐዋሳ በተደረው ጨዋታ እስራኤል ሸጎሌ የሃላባን የማሸነፊያ ግብ አስቆጥሯል። ሃላባ ከተማ ሊጉ ሊጠናቀቅ አንድ ጨዋታ እየቀረው ነው ወደ ሊጉ ማደጉን ያረጋገጠው።

#EBC #Ethiopia #football
“ጦርነቱ ሊያበቃ ተቃርቧል” - ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ
*****************

የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ከኢራን ጋር ያለው ጦርነት ወደ ማብቂያው እየተቃረበ መሆኑን ገለጹ።

ፕሬዚዳንቱ ከፎክስ ኒውስ ጋር ባደረጉት ቆይታ፣ አሜሪካ ገና ሥራዋን ባታጠናቅቅም ስድስት ሳምንታትን ያስቆጠረው ይህ ጦርነት ወደ ማጠናቀቂያው መስመር እየደረሰ መሆኑን ተናግረዋል።

ይሁን እንጂ የፖለቲካ ተንታኞች እንደሚሉት የፕሬዚዳንት ትራምፕ ንግግር በሀገር ውስጥ ያለውን ፖለቲካዊ ጫና ለመቀነስ የታለመ እና የጦርነቱን መቆም የሚፈልግ ስሜት የተንጸባረቀበት ነው።

አሁን ባለው ሁኔታ ለሁለት ሳምንታት የተቆረጠው የተኩስ አቁም ጊዜ ግማሽ ላይ የደረሰ ሲሆን በሆርሙዝ ወሽመጥ ላይ ያለው ውጥረት ግን እንደቀጠለ ይገኛል።

እንደ ባለሙያዎቹ ገለጻ፣ ፕሬዚዳንቱ ግጭቱን ለመፍታት ያላቸው ጊዜ እያለቀ ቢመስልም በሁለቱ ሀገራት መካከል ስምምነት ላይ ለመድረስ የሚያስችሉ ዕድሎች እንዳሉ ጠቁመዋል።

#Trump #IranWar #MiddleEastCrisis #BreakingNews #USA #Iran
👏2👍1
ኢትዮጵያ የወርቅ ማጣሪያ ፋብሪካ በቅርቡ ታስመርቃለች - ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)
***************************

ኢትዮጵያ የሀብት ምንጮቿን እሴት በማሳደግ እና የኢንዱስትሪ አቅሟን በማጎልበት ረገድ ወሳኝ ምዕራፍ ላይ መድረሷን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ገለጹ።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ አክለውም፣ በሀገራችን ለመጀመሪያ ጊዜ እየተገነባ ያለው የወርቅ ማጣሪያ ፋብሪካ በቀጣዮቹ ጥቂት ወራት ውስጥ ተጠናቅቆ ይመረቃል ብለዋል።

ሀገራችን እስካሁን ጥሬ ወርቅን ...

ለሙሉ መረጃው https://web.facebook.com/EBCzena/posts/pfbid0s38rt5Nw1b2UruBVMuNvMvmDqf1oDf3PCF1KG2vsDez7e93EywWjL45pepxZJwVal
👏3
“ኢትዮጵያን የባሕር በር አልቦ አድርጎ መቀጠል በየትኛውም ዘመን አዋጭ አይደለም” - ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

#EBC #Ethiopia #PMAbiyAhmed #SeaAccess
👏2
ነፃ ንግድ ቀጣና የሎጀስቲክስ ሥርዓቱን በማዘመን ረገድ የላቀ ፋይዳ አለው - ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)
*************

ኢትዮጵያ ውስጥ የሚገኙ የኢንዱስትሪ ፓርኮች ወደ ነፃ ንግድ ቀጣና ማደጋቸው፣ ከምርት ተግባር ባለፈ የንግድ እና የሎጀስቲክስ ሥርዓቱን በማዘመን ረገድ ወሳኝ ሚና እንደሚኖራቸው ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ገለጹ።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከኢቢሲ ጋር በነበራቸው ቆይታ እንደገለጹት፣ የኢንዱስትሪ ፓርኮች ቀደም ሲል ትኩረታቸው በአምራች ዘርፍ ላይ ብቻ የነበረ ቢሆንም፣ ወደ ነፃ ንግድ ቀጣና ሲቀየሩ ግን የንግድ እንቅስቃሴን የማሳለጥ ሰፊ አቅም ይኖራቸዋል።

ለሙሉ መረጃው

https://web.facebook.com/EBCzena/posts/pfbid02TvufdiNYdGpt8kNhqBP66o2ncxbHaFu9JkaAYfoajZhRbfq2h3gX1gQuUDFspmaCl
👏2
ኢትዮጵያ አትቆምም፤ ሸብረክ አትልም፤ ትበለጽጋለች - ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)
**************

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከኢቢሲ ጋር ባደረጉት ቆይታ፣ ኢትዮጵያ በሚቀጥሉት ዐሥር ዓመታት ውስጥ ያለ ጥርጥር የአፍሪካ አውራ ሀገር እንደምትሆን ያላቸውን ጽኑ እምነት ገልጸዋል።

ይህንን ታላቅ ራዕይ እውን ለማድረግ ግን በምኞት እና በልመና ሳይሆን፣ ችግርን ላለመውረስ ሌት ተቀን ያለመታከት መሥራት እንደሚገባ አስገንዝበዋል።

ለሙሉ መረጃው ... https://web.facebook.com/EBCzena/posts/pfbid02PpPn9rPfEH4YF2NcqeXhJWaXDXeN8v5oou9LPhtjFvakbPJ6RJMiDkH7PYqv7tw8l
👍2👏1
ኢትዮጵያ ከባሕር በር ተነጥላ እስከ ወዲያኛው ትኖራለች ብሎ የሚያስብ ሰው ካለ የዋህ ነው - ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)
******************

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የኢትዮጵያ የባሕር በር ባለቤትነት ጥያቄ ወደኋላ የማይባል፣ በምንም ሁኔታ የማይቀለበስ እና የሀገራችን የኅልውና ጉዳይ መሆኑን ተናግረዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከኢቢሲ ጋር በነበራቸው ልዩ ቆይታ፣ ይህንን የኅልውና ጉዳይ ወደ ጎን በመተው የሀገራችንን ብልጽግና ማሰብ እንደማይቻል አስገንዝበዋል።

ሀገራችን በቀይ ባሕር እና በኤደን ባሕረ ሰላጤ ለሚሰነዘሩ ጥቃቶች በቀጥታ ተጋላጭ መሆኗን ገልጸው ...

ለሙሉ መረጃው ... https://web.facebook.com/EBCzena/posts/pfbid027TMhafk9hWdSuuN7o7JNptBBdD9JKMKcfzUYZKbdDihoWBkBF5ymSDsnvLDMqoe6l
👍4👏2
"ሐዋሳ የውበት፣ የዓሣ እና የቡርሰሜ ብቻ ሳትሆን ለኢትዮጵያ እና ለአፍሪካ ብርሃን የሚያመነጭ፣ በአፍሪካ ትልቁ የሶላር ሴል የሚመረትባት ከተማ ሆናለች።" - ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)
👍1👏1🕊1