Ethiopian Broadcasting corporation ®
8.86K subscribers
17.9K photos
205 videos
14 files
1.62K links
Ethiopian broadcasting corporation is a 24 working public media.

https://telega.io/c/EBC_TV
ማንኛውም አይነት አስተያየት እና ጥቆማ ካላችሁ በዚህ ላኩልን እንቀበላለን!!
https://t.me/+G7d4hSzJEhViMzQ0
Download Telegram
Ethiopian Broadcasting corporation ®
Photo
ሁለት ወንዶች ከ2 ሰዓት በታች የገቡበት፤ ሦስቱ ደግሞ በአንዴ የዓለምን ሪከርድ የሰበሩበት የለንደኑ ማራቶን
********************
ሁለት ወንዶች ከ2 ሰዓት በታች የገቡበት፤ ሦስቱ ደግሞ በአንዴ የዓለምን ሪከርድ የሰበሩበት የለንደኑ ማራቶን አዲስ ታሪክ ጽፏል።
እነ ማን ታሪክ ሠሩ?
ኬንያዊው አትሌት ሰባስቲያን ሳዌ በይፋዊ የውድድር መድረክ የ2 ሰዓት የጊዜ ገደብን በመስበር የመጀመሪያው ሰው ሆኗል።
አትሌቱ 1 ሰዓት ከ59 ደቂቃ ከ30 ሰከንድ በማጠናቀቅ ዓለምን አስገርሟል።
የኛው ዮሚፍ ቀጄልቻ በመጀመሪያው የማራቶን ተሳትፎው፣ ሌላው ከ2 ሰዓት በታች የገባ ድንቅ አትሌት ሆኗል።
ዮሚፍ ቀጄልቻ ውድድሩን የጨረሰው 1 ሰዓት 59.41 ደቂቃ ነው፤ ይህም አትሌቱ ከወዲሁ በማራቶኑ ዓለም አዲስ ታሪክ እንደሚጽፍ ተገማች አድርጎታል።
ለብዙ ዘመናት የሰው ልጅ በማራቶን ከ2 ሰዓት በታች ሊገባ አይችልም ተብሎ ይታሰብ ነበር፤ ዛሬ ግን ያ የማይቻል የሚመስለው ግድግዳ በሳዌ እና በዮሚፍ ተሰባብሯል።
የማራቶን ሩጫ አዲስ ምዕራፍ ገብቷል፤ ይህንን ለማመን ምናልባት ጥቂት ቀናት ሊወስድብን ይችላል።
ዪጋንዳዊው አትሌት ጃኮብ ኪፕሊሞም 2 ሰዓት፣ ከ28 ሰከንድ በመግባት ቀድሞ የነበረውን የዓለም ክብረ ወሰን በማሻሻል ሦስተኛ ወጥቷል።
በሌላ በኩል በለንደን ታሪክ ራሱን ደግሟል፤ የሀገራችን ኩራት የሆነችው አትሌት ትዕግሥት አሰፋ የለንደን ማራቶን ክብሯን በብቃት አስጠብቃለች።
አትሌት ትዕግሥት ክብራን ማስጠበቋ ብቻ ሳይሆን ባለፈው ዓመት እዚሁ ለንደን ላይ ያስመዘገበችውን የሴቶች ብቻ ማራቶን የዓለም ክብረ ወሰን በ9 ሰከንድ በማሻሻል፣ 2 ሰዓት 15.41 ደቂቃ በመግባት አዲስ ታሪክ ጽፋለች።
ኬንያዊቷ ሔለን ኦቢሪ 2 ሰዓት 15.53 ,ደቂቃ በመግባት ሁለተኛ ስትወጣ፣ ጆይሲሊን ጄፕኮስጌ ሦስተኛ ሆና አጠናቅቃለች።
ይህ ክስተት የሰው ልጅ አቅም ወሰን እንደሌለው የታየበት፣ ኢትዮጵያዊያን እና ጎረቤቶቻችን ኬንያውያን ዓለምን ያስደመሙበት ታላቅ ክስተት ሆኗል።
እናንተስ በዮሚፍ ቀጄልቻ እና በትዕግሥት አሰፋ ድል ምን ተሰማችሁ? ደስታችሁን በአስተያየት መስጫው ላይ ግለጹላቸው።
በዮናስ በድሉ
🕊1
Ethiopian Broadcasting corporation ®
Photo
አትሌት ዮሚፍ ቀጀልቻ ማራቶንን ከ2 ሰዓት በታች የገባ የመጀመርያው ኢትዮጵያዊ አትሌት ሆነ
***************
በለንደን ማራቶን ለመጀመርያ ጊዜ የተወዳደረው አትሌት ዮሚፍ ቀጀልቻ ማራቶንን ከ2 ሰዓት በታች መግባት የቻለ የመጀመርያው ኢትዮጵያዊ አትሌት ሆኗል።
በታሪኩ በማራቶን ለመጀመርያ ጊዜ የተወዳዳረው ዮሚፍ ቀጀልቻ 2ኛ ደረጃን ይዞ ሲያጠናቅቅ የገባበት 1 ሰዓት 59.41 ደቂቃ የኢትዮጵያ አዲስ ክብረ ወሰን ሆኖ ተመዝግቧል
ኬንያዊው አትሌት ሰባስቲያን ሳዌ ውድድሩን በበላይነት ሲያጠናቅቅ የገባበት ሰዓት አዲስ የዓለም ክብረ ወሰን ሆኗል።
የባለፈው ዓመት የለንደን ማራቶን አሸናፊው ሰባስቲያን ሳዌ 1 ሰዓት 59.30 ደቂቃ ርቀቱን ለማጠናቀቅ የወሰደበት ሰዓት ሆኗል።
የ30 ዓመቱ አትሌት ከሦስት ዓመት በፊት በሀገሩ ልጅ ኬልቪን ኪፕቱም ተይዞ የነበረውን የ2 ሰዓት 00.35 ደቂቃ ክብረ ወሰን በመስበር አዲስ ታሪክ ሠርቷል።
በአንተነህ ሲሳይ
👍1👏1
Ethiopian Broadcasting corporation ®
Photo
አትሌት ትግስት አሰፋ በለንደን ማራቶን ክብረ ወሰን በማሻሻል ለ2ኛ ተከታታይ ጊዜ አሸነፈች
*************
ለ49ኛ ጊዜ በተደረገው የለንደን ማራቶን አትሌት ትግስት አሰፋ በበላይነት ስታጠናቅቅ የገባችበት ሰዓት በሴቶች ብቻ በራሷ ተይዞ የነበረውን የዓለም ክብረወሰን አሻሽላለች።
በዓለም አትሌቲክስ የፕላቲኒየም ደረጃ ባለው ማራቶን ትግስት አሰፋ እስከ መጨረሻው እልህ አስጨራሽ ፉክክር በማድረግ የገባችበት 2 ሰዓት 15.41 ደቂቃ አዲስ ክብረ ወሰን ሆኖም ተመዝግቧል።
የፓሪስ ኦሊምፒክ የብር ሜዳሊያ ባለቤቷ ትግስት አሰፋ ባለፈው ዓመት በተደረገው የለንደን ማራቶን በሴቶች ብቻ ማራቶን የዓለም ክብረ ወሰን ባለቤት ናት፡፡
የሁለት ጊዜ የበርሊን ማራቶን አሸናፊዋ አትሌት ትግስት፣ የለንደን ማራቶንን ለ2ኛ ተከታታይ ጊዜ ያሸነፈችበት ሆኗል፡፡
ኬንያውያኑ አትሌቶች ሄለን ኦቢሪ እና ጆይስሊን ጅፕኮስጊ 2ኛ እና3ኛ ደረጃን ይዘው አጠናቀዋል፡፡
በአንተነህ ሲሳይ
👏1
ከለውጡ ወዲህ የተመዘገቡ ስኬቶች የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ሕዝብን የልማት ተጠቃሚነት ወደ ላቀ ደረጃ አሸጋግረዋል - አቶ አሻድሊ ሀሰን
***********************
የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል መንግሥት ከኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት ጋር በመተባበር "ከዳር እስከ መሐል፦ የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የልማት ትንሣዔ" በሚል መሪ ቃል በአሶሳ ከተማ የፓናል ውይይት አካሂዷል።
የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አቶ አሻድሊ ሀሰን በውይይቱ ላይ እንደገለጹት፣ ክልሉ ከዚህ ቀደም "ዳር" ተብሎ ፍትሐዊነት በጎደለው አሠራር ሳይለማ የቆየ ቢሆንም፣ ከለውጡ ወዲህ በተከናወኑ ተግባራት የሕዝቡን የልማት ተጠቃሚነት ወደ ላቀ ደረጃ ያሻገሩ ተጨባጭ ስኬቶች ተመዝግበዋል።
ርዕሰ መስተዳድሩ አክለውም የክልሉን ሰላም እና ፀጥታ በማስፈን የተከናወኑ ተግባራት ተጠናክረው በመቀጠላቸው የዜጎችን ተጠቃሚነት ማረጋገጥ መቻሉን ገልጸዋል።
ክልሉ ያለውን የተፈጥሮ ጸጋ በመጠቀም ባለሀብቶች ከራሳቸው አልፎ ለሀገራችን የኢኮኖሚ ዕድገት አስተዋፅኦ እያበረከቱ መሆኑን እና ሕዝቡም የዚህ ሂደት ቀጥተኛ ተጠቃሚ እንደሆነ ተመላክቷል።
በተጨማሪም 7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ፍትሐዊ ሆኖ እንዲጠናቀቅ መሥራት የሁሉም ኢትዮጵያውያን ኃላፊነት መሆኑን የጠቀሱት አቶ አሻድሊ፣ መድረኩ ክልሉ ትናንት የነበረበትን ሁኔታ፣ በለውጡ የተመዘገቡ ስኬቶችን እና የወደፊት የሥራ አቅጣጫዎችን በመጠቆም ረገድ ትልቅ ፋይዳ እንዳለው አስገንዝበዋል።
በነስረዲን ሀሚድ
👏1
"ኢንዱስትሪ ለመጀመሪያ ጊዜ ግብርናን ተክቶ ከፍተኛውን የኢኮኖሚ ድርሻ የሚይዝበት መዋቅራዊ ሽግግር በጥቂት ዓመታት ውስጥ የሚፈጸም ይሆናል" - ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)
👏1
Ethiopian Broadcasting corporation ®
Photo
“በበጀት ዓመቱ በእቅድ ከያዝናቸው ተግባራት 96 በመቶ መፈፀም ችለናል” - ከንቲባ አዳነች አቤቤ
****************
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የ2018 በጀት ዓመት የ9 ወራት ሥራዎች አፈፃፀም ግምገማ ማካሄድ ጀምሯል።
ከንቲባ አዳነች አቤቤ ይህንኑ አስመልክቶ በማኅበራዊ ትሥሥር ገጽ ባሰፈሩት መልዕክት፣ “በበጀት ዓመቱ በእቅድ ከያዝናቸው ተግባራት 96 በመቶ መፈፀም ችለናል” ብለዋል።
ለሁለት ተከታታይ ቀናት በሚቆየው የግምገማ መድረክ በበጅት ዓመቱ ለመፈፀም ካቀድናቸው ውስጥ በ9 ወራት በጥብቅ ክትትል የተከናወኑትን የምንገመግምበት እና በቀሪ ወራት የትኩረት ማዕከል አድርገን የምንፈፅማቸው በመልካም አስተዳደር ተለይተው ያልተመለሱትን ምላሽ በመስጠት ማጠናቀቅ፣ የኑሮ ውድነትን የሚያባብሱ ችግሮችን በመቀነስ የዋጋ ንረትን መከላከል፣ የገበያ ማዛባት ችግሮችን መከላከል፣ ከአገልግሎት አሰጣጥ ጋር በመሶብ ዲጅታል የአንድ ማዕከል የመንግስት አገልግሎት የጀመርነውን ውጤታማ ሥራ በቀሪ ወራት በተሟላ ሁኔታ በማጠናቀቅና ወደ ሥራ ማስገባት እንዲሁም ቀሪ አገልግሎቶችን ዲጅታላይዝ አድርጎ ወደ መሶብ ማስገባት፣ ተጀምረው በዚህ ዓመት መጠናቀቅ ያለባቸውን ፕሮጀክቶች በፍጥነትና በጥራት ማጠናቀቅ የአፈፃፀም ግምገማ ማዕከላችን ይሆናሉ ሲሉ ገልጸዋል።
ባለፋት አምስት ዓመታት የእቅድ አፈፃፀማችን ከ90 በመቶ በላይ እያደገ መጥቶ በ2018 ደግሞ 96 በመቶ የደረሰበት ውጤታማ አፈፃፀም መኖሩን በመገምገም፣ ይህንን እያደገ የመጣ የመፈፀም ልምድ አጠናክረን መቀጠል እንድንችል በትኩረት እንገመግማለን ነው ያሉት።
በተጨማሪም 7ኛው ሀገራዊ ምርጫ ፍትሃዊ፣ ነፃ፣ ተዓማኒና ገለልተኛ ሆኖ እንዲከናወን ሁሉም አመራራችን ምቹ ሁኔታ ለመፍጠር ትልቅ ሃላፊነት መወጣት እንዲችሉ የግምገማ አቅጣጫ መቀመጡን ጠቁመዋል።
የነበሩ ጥንካሬዎችን ማስቀጠል፣ ጉድለቶችን በመሙላት በቀሪዎች ወራት በላቀ መፈፀም የግምግማችን ማዕከል ይሆናል ሲሉ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።
👏1
Ethiopian Broadcasting corporation ®
Photo
“የኢትዮጵያን ዕምቅ ዐቅሞች በመግለጥ ረገድ ግለሰቦች የማይተካ ሚና አላቸው” - ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ
**********************
የግለሰቦች የቅርስ ጥበቃ ጥረት ለሀገራችን የቱሪዝም ዕድገት ትልቅ አቅም መሆኑን ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ ገለጹ።
ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ በአብዲ ነጋሽ ቅርስ ማሰባሰቢያ እና ማስጎብኛ ቤት ተገኝተው ጎብኝተዋል።
ከጉብኝቱ በኋላ ባስተላለፉት መልዕክትም፣ ኢትዮጵያ የረጅም ዘመናት ሥልጣኔ እና የጥንታዊ ቅርሶች ባለቤት መሆኗን ለማረጋገጥ እንደ አቶ አብዲ ዓይነት የትውልድ አሻራ ጠባቂዎች ሚና የላቀ ነው ብለዋል።
በሥፍራው የተመለከቱት የቅርሶች ስብስብ ለሀገራችን ታሪክ እና ባህል ትልቅ ክብር የሚሰጥ ድንቅ ሥራ መሆኑን ጠቁመው፣ እነዚህ ሀብቶች በሚመጥናቸው ታሪካዊ ሥፍራ ተደራጅተው ለዕይታ መብቃታቸው ለዘርፉ ትልቅ እመርታ ነው ሲሉ ገልጸዋል።
ትውፊታዊ ቅርሶቹ ባለፈው እና በሚመጣው ትውልድ መካከል የቆሙ ሕያው ድልድዮች ናቸው ያሉት አቶ ተመስገን፣ እንደ አቶ አብዲ ዓይነት በፍላጎት እና በሀገር ፍቅር ስሜት የሚሠሩ ሰዎች የኢትዮጵያን ዕምቅ ዐቅም በመግለጥ ረገድ የማይተካ ሚና እንዳላቸው አመልክተዋል።
በአሁኑ ወቅት የቅርሶች ስብስቡ የአዲስ አበባ አንዱ የቱሪስት መስህብ እና የዜጋዊ ዲፕሎማሲ ማሳያ መሆኑን ጠቅሰው፣ በርካታ የሀገር ውስጥ እና የውጭ ቱሪስቶች እየጎበኙት እንደሚገኝም ገልጸዋል።
የመደመር መንግሥት እንዲህ ያሉ የግል ጥረቶችን በማበረታታት እና የታሪክ ሥፍራዎችን መልሶ በማልማት፣ ቅርሶች የኢኮኖሚ ምንጭ እና የሀገር ኩራት እንዲሆኑ የጀመረውን ሥራ አጠናክሮ እንደሚቀጥልም ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ አረጋግጠዋል።
ተቋማት እና ሀገር ወዳድ ዜጎችም እንደ አቶ አብዲ ያሉ ታታሪዎችን እንዲደግፉ ጥሪ አቅርበዋል።
እንዲህ ያሉ የሀገር መዝገቦችን በታሪካዊ ሕንፃዎች ውስጥ ጠብቆ ማቆየት ለብልጽግና የሚደረገውን ጉዞ በእውቀት እና በማንነት ላይ ለመገንባት የሚያግዝ ተደማሪ አቅም መሆኑንም ገልጸዋል።
👍1👏1
የሲቢኢ ኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ 22ተኛ ሳምንት ተከታታይ ጨዋታ !

                    ⏰ ተጠናቀቀ

        ቅዱስ ጊዮርጊስ 1-3 ኢትዮጵያ ቡና
#ፍፁም 24'                            #ኦካይ 45+3'
                                              #ቢኒያም 52'
                                              #ዘላለም 65'

🏟️ | አዲስ አበባ ስታዲየም
👍2
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ቅዳሜ ምሽት ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ እና በርካታ የአሜሪካ ከፍተኛ ባለሥልጣናት በተገኙበት የዋይት ሐውስ ዘጋቢዎች የእራት ግብዣ አዳራሽ ላይ ጥቃት ለማድረስ የጦር መሣሪያ እና ቢላዋ ይዞ የገባ ግለሰብ በአገሪቱ የጸጥታ እና ደህንነት ባልደረቦች በቁጥጥር ስር ዋለ። ተጠርጣሪው ግለሰብ ፕሬዚዳንቱን ለመግደል አቅዶ እንደነበር መናገሩን የአሜሪካ መገናኛ ብዙኃን ዘግበዋል።
🤔1