Ethiopian Broadcasting corporation ®
8.86K subscribers
17.9K photos
205 videos
14 files
1.62K links
Ethiopian broadcasting corporation is a 24 working public media.

https://telega.io/c/EBC_TV
ማንኛውም አይነት አስተያየት እና ጥቆማ ካላችሁ በዚህ ላኩልን እንቀበላለን!!
https://t.me/+G7d4hSzJEhViMzQ0
Download Telegram
51ኛው የአዲስ አበባ ደርቢ በኢትዮጵያ ቡና አሸናፊነት ተጠናቀቀ
************
በ20ኛ ሳምንት ሲቢኢ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ተስተካካይ ጨዋታ ኢትዮጵያ ቡና ቅዱስ ጊዮርጊስን 3 ለ 1 አሸንፏል።
በአዲስ አበባ ስታዲየም የሁለቱም ቡድን በርከታ ደጋፊዎች በታደሙበት ጨዋታ ኦካይ ጁል፣ ቢኒያም ጌታቸው እና ዘላለም አባተ የኢትዮጵያ ቡናን ግቦች አስቆጥረዋል።
ፍጹም ጥላሁን የቅዱስ ጊዮርጊስን አንድ ግብ አስቆጥሯል። ፈረሰኞቹ ከአራት ተከታታይ ጨዋታዎች ያለመሸመፍ ጉዞ በኋላ በከተማ ተቀናቃኛቸው ተሸንፈዋል።
ኢትዮጵያ ቡና ነጥቡን 41 ሲያደርስ ቅዱስ ጊዮርጊስ በ35 ነጥብ 10ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል።
በአንተነህ ሲሳይ
👍5
በሁለት የድምፅ መስጫ ወረቀቶች ላይ ድምፅ እንደሚሰጥ ያውቃሉ?
**************

1) ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ምርጫ - ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ዕጩ ድምፅ ሲሰጡ በሀገር አቀፍ ደረጃ የሚወክልዎን ተወካይ ይመርጣሉ።

2) ለክልል ምክር ቤት ምርጫ - ለክልል ምክር ቤት ዕጩ ድምፅ ሲሰጡ በክልል ደረጃ የሚወክልዎን ተወካይ ይመርጣሉ።

#EBC #Ethiopia #በምርጫብቻ
👍2
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከIMF ዋና ዳይሬክተር ክርስታሊና ጆርጂየቫ ጋር ተወያዩ
***********

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከዓለም አቀፉ የገንዘብ ተቋም (IMF) ዋና ዳይሬክተር ክርስታሊና ጆርጂየቫ ጋር በኢኮኖሚያዊ ዕድገት፣ በአጋርነት እና ቅድሚያ በሚሰጣቸው የጋራ ጉዳዮች ላይ ሰፊ ውይይት ማድረጋቸውን ገለጹ።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማኅበራዊ ትሥሥር ገጽ ባሰፈሩት መልዕክት፣ ‎”ለነበረን ጠቃሚ የሐሳብ ልውውጥ እና ቀጣይነት ላለው አጋርነት ምስጋናዬ የላቀ ነው” ብለዋል።

#EBC #Ethiopia #PMAbiyAhmed #IMF
👏1
ኢትዮጵያ ለትውልድ ግንባታ እና ለህፃናት ሁለንተናዊ እድገት ልዩ ትኩረት ሰጥታለች፦ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ
******************
ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ በአዲስ አበባ እየተካሄደ የሚገኘውን ዓለም-አቀፍ የቀዳማይ ልጅነት ጉባዔ አስጀምረዋል።

መንግስት ድሃ-ተኮርና የሰውን ልጅ ልማት ቅድሚያ የሚሰጥ ፖሊሲ በመከተል ላይ እንደሚገኝ የጠቆሙት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ የቀዳማይ ልጅነት እድሜ ክልል ለበለፀገ ማህበረሰብና ለጠንካራ አገር መሰረት መሆኑን በጥልቀት በመረዳት ከፍተኛ ኢንቨስትመንት እየተደረገ መሆኑን አብራርተዋል።

​በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፋና ወጊነት የተጀመሩት በህፃናት ሁለንተናዊ እድገት ላይ ያተኮሩ ስትራቴጅካዊ እርምጃዎች ውጤታማ መሆናቸውን በመጥቀስ በከተማዋ የተገኘውን ልምድ በመቀመር ወደ ሌሎች የሀገሪቱ ክልሎች ለማስፋት የሚያስችል ስርዓት መዘርጋቱንም አረጋግጠዋል።

ለዚህም ተግባር ይረዳ ዘንድ የቴክኒክና ሳይንሳዊ ዕውቀትን ለፖሊሲ ግብዓት የሚያቀርብ "የአፍሪካ ቀዳማይ ልጅነት ልማት ማዕከል" በአዲስ አበባ መቋቋሙ የመንግስትን ቁርጠኝነት የሚያሳይ መሆኑን https://web.facebook.com/share/p/1GHh5gQuco/

#ebcdotstream #አዲስአበባ #ቀዳማይልጅነት #ሕፃናት #ኢትዮጵያ
👏2
የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ቤጂንግ ገብተዋል
*******************
የዓለማችን ሁለቱ ሀያላን አገራት አሜሪካ እና ቻይና በመሪዎች ደረጃ ለሚያደርጉት ውይይት የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ከልዑካን ቡድናቸው ጋር ቤጂንግ ገብተዋል።
ይህ ጉብኝት በሁለቱ ኃያላን ሀገራት መካከል ያለውን ግንኙነት ብቻ ሳይሆን የዓለምን ጂኦፖለቲካዊ ሚዛን የሚወስን ነው የተባለ ሲሆን ዶናልድ ትራምፕ በቻይና ቆይታቸው በመካከለኛው ምስራቅ በተለይም በኢራን እና በሆርሙዝ ሰርጥ ላይ ከፕሬዝዳንት ሺ ጂንፒንግ ጋር እንደሚወያዩ ይጠበቃል።
#USA #China
🤔1
በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የተጻፈው “የመደመር መንግሥት“ መጽሐፍ የዓረብኛ ትርጉም ነገ ይመረቃል
******************
በተባበሩት ዓረብ ኤምሬትስ አቡዳቢ በነገው ዕለት የሚመረቀው የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) “የመደመር መንግሥት“ መጽሐፍ፤ በዋነኛነት በመካከለኛው ምሥራቅ ለሚገኙ ሁሉም ዓረብኛ ቋንቋ ተናጋሪ ሀገራት፣ ሕዝቦች እና መንግሥታት በመደመር እሳቤ የምትመራዋን ኢትዮጵያን በጥልቀት ለማስተዋወቅ ዓላማ ያነገበ መሆኑን በተባበሩት ዓረብ ኤምሬትስ የኢትዮጵያ ባለሙሉ ሥልጣን አምባሳደር ጀማል በከር (ዶ/ር) ገልጸዋል።
መጽሐፉ በዓረቡ ዓለም የኢትዮጵያን ፍላጎቶች እና ብሔራዊ ጥቅሞች የበለጠ ለማስጠበቅ እና ኢትዮጵያም የመካከለኛው ምሥራቅ አድማሷን ለማስፋት የምትጠቀምበትን የጂኦ-ስትራቴጂክ እና የጂኦ-ፖለቲካ የኃይል አሰላለፍ ሚዛኑ የተጠበቀ ሆኖ እንዲቀጥል ካላት ፍላጎት አንጻር የተተረጎመ ነው።
የመደመርን ፍልስፍና ይበልጥ ለቀጣናው ሀገራት ቅርብ በሆነ ቋንቋ ይዞ መምጣት የኢትዮጵያን ትክክለኛ ዕይታ ያሳያል የሚሉት አምባሳደር ጀማል፣ ይህም ሀገራቱ የአዲሲቷን ኢትዮጵያ ተራማጅ የፖለቲካ፣ የኢኮኖሚ እና የሁሉን አቀፍ የለውጥ ማዕቀፎች እንዲረዱ ትልቅ አቅም እንደሚፈጥር አብራርተዋል።
በነገው ዕለት በሚመረቀው የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) “የመደመር መንግሥት“ ዓረብኛ ትርጉም መጽሐፍ ላይ የተባበሩት ዓረብ ኤምሬትስ ከፍተኛ ባለሥልጣናት እና ንጉሣዊ ቤተሰቦች፣ ዲፕሎማቶች፣ አምባሳደሮች፣ የመካከለኛው ምሥራቅ የኢትዮጵያ ወዳጅ ሀገራት፣ ዳያስፖራዎች እና የኢትዮጵያ ኮሙዩኒቲ አባላት ይታደማሉ።
በሰለሞን ኃይለኢየሱስ (ከአቡዳቢ)
#EBC #Ethiopia #medemer
👏1