Ethiopian Broadcasting corporation ®
8.86K subscribers
17.9K photos
205 videos
14 files
1.62K links
Ethiopian broadcasting corporation is a 24 working public media.

https://telega.io/c/EBC_TV
ማንኛውም አይነት አስተያየት እና ጥቆማ ካላችሁ በዚህ ላኩልን እንቀበላለን!!
https://t.me/+G7d4hSzJEhViMzQ0
Download Telegram
ከንቲባ አዳነች አቤቤ በበጎነት መንደር የተገነባውን 29ኛውን የተስፋ ብርሃን የምገባ ማዕከል መርቀው ሥራ አስጀመሩ
*****************
የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ በልደታ ክፍለ ከተማ የተገነባውንና ለከተማዋ 29ኛ የሆነውን "የተስፋ ብርሃን" የምገባ ማዕከል መርቀው ሥራ አስጀመሩ።

ማዕከሉ ማኅበራዊ ፍትህን ለማንገሥ የሚከናወኑ የበጎነት ተግባራት አካል ሲሆን፣ በተለይም በልማት ምክንያት ተነስተው በተገነቡ 492 ቤቶች ውስጥ ለሚኖሩ 2 ሺህ 460 ነዋሪዎች ትልቅ እፎይታ እንደሚሆን ከንቲባዋ ገልጸዋል።

በተለይ አረጋውያን፣ ለማኅበራዊ ችግር የተጋለጡና ድጋፍ የሚሹ ወገኖች በሚኖሩበት በዚህ "የበጎነት መንደር" ውስጥ የተከፈተው ማዕከል፤ ነዋሪዎች ንጹሕና ትኩስ ምግብ በቀን አንድ ጊዜ…https://web.facebook.com/EBCzena/posts/pfbid0NS2qrQcPKze7yTj8Qc6hVjXEz61mmd7Kxfpsj7GJiUXNivrXJMSTdJKaTXCjbfjFl
👏1
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ልዩ የኤር ትርዒት ለጎብኚዎች ክፍት አደረገ
*******************
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ 80ኛ ዓመት የምሥረታ በዓሉን ምክንያት በማድረግ ያዘጋጀው ልዩ የማይንቀሳቀስ የኤር ትርዒት (Static Air Show) ዛሬ በቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ በድምቀት ተከፍቷል።

ይህንን የማይንቀሳቀስ የኤር ትርዒት የትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ሚኒስትር ዓለሙ ስሜ (ዶ/ር) እና የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ መስፍን ጣሰው በጋራ መርቀው ከፍተውታል።

የአፍሪካ ኩራትና የደንበኞቹ የልብ አድራሽ የሆነው የኢትዮጵያ አየር መንገድ…https://web.facebook.com/EBCzena/posts/pfbid02LgFKcJJGeqVs7rQKpKY9Au2sDKgae3s99x2aCBHGt89FyDmNzc4DNSuhLGxkqwcAl
👏1
የአትሌት ሻምበል ባሻ የብርጓል መለሰ ሥርዓተ ቀብር ተፈጸመ
*********************
በሀገር ውስጥና በዓለም አቀፍ መድረኮች የሀገሯን ሰንደቅ ዓላማ ከፍ ስታደርግ የቆየችው አትሌት ሻምበል ባሻ የብርጓል መለሰ ሥርዓተ ቀብር ዛሬ ግንቦት 6 ቀን 2018 ዓ.ም በመንበረ ፀባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ተፈጽሟል።

በሥርዓተ ቀብሩ ላይ ከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች፣ ታዋቂ አትሌቶች፣ አሰልጣኞች፣ የመከላከያ ሠራዊት አመራሮችና አባላት እንዲሁም ቤተሰብና ወዳጅ ዘመዶቿ በተገኙበት በመከላከያ የክብር ዘብ እና በማርሽ ባንድ ታጅቦ በክብር ተሸኝታለች።

አትሌት ሻምበል ባሻ የብርጓል መለሰ በ2015 በመላ አፍሪካ ጨዋታዎች የግማሽ ማራቶን የነሐስ ሜዳሊያ፣ በ2013 ደግሞ በዓለም አገር አቋራጭ ውድድር የብር ሜዳሊያ ባለቤት…https://web.facebook.com/EBCzena/posts/pfbid0GtjeCvYLDrgirFp3AVDY1ENksMSas6jJg8M28tPg2o284WNCg1WqznaCYviVrj9xl
😢1
የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጌድዮን ጢሞቲዎስ (ዶ/ር) ከደቡብ አፍሪካ አቻቸው ጋር ተወያዩ
**************
የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጌዲዮን ጢሞቲዎስ (ዶ/ር) ከደቡብ አፍሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሮናልድ ላሞላ ጋር ተወያይተዋል።

ሚኒስትሮቹ በሕንድ ኒው ዴልሂ እየተካሄደ ከሚገኘው የብሪክስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች ጉባኤ ጎን ለጎን ባደረጉት ውይይት በሁለትዮሽ ጉዳዮች ላይ መክረዋል።

በተለይም ሚኒስትሮቹ በውይይታቸው በደቡብ አፍሪካ በኢትዮጵያውያን ዜጎች…https://web.facebook.com/EBCzena/posts/pfbid02XENSEFb4Ag8GnappYBjUNG2dyPWmUw3tvHYjqEgbmGhgY6MEEmLAxvHbjF4YB1bfl
👏1
ፕሬዚዳንት ትራምፕ በቻይና ያደረጉት ጉብኝት ‘የጋራ መግባባትንና መተማመንን የሚያጎለብት’ ነው፦ ፕሬዚዳንት ሺ ጂንፒንግ
***********************
የቻይናው ፕሬዚዳንት ሺ ጂንፒንግ፣ የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ወደ ቤጂንግ ያደረጉት የ3 ቀን ጉብኝት “በሁለቱ ሀገራት መካከል መግባባትንና መተማመንን ያጠናክራል” ሲሉ ገልጸውታል።
ሺ ጂንፒንግ የትራምፕን ጉብኝት "ሁሉም አካላት አሸናፊ የሚሆኑበት፣ ታሪካዊ፣ አስፈላጊ እና ወቅቱን የጠበቀ” ነው ሲሉ ገልፀውታል።
ሁለቱ መሪዎች የተረጋጋ የኢኮኖሚ እና የንግድ ግንኙነትን ለመጠበቅ፣ በተለያዩ መስኮች ተግባራዊ ትብብርን ለማስፋፋት እና የጋራ ስጋቶችን በአግባቡ ለመፍታት ስምምነት ላይ ደርሰዋል።
ፕሬዝዳንት ሺ እንደገለጹት፣ ጉብኝቱ በጋራ መከባበር ላይ የተመሰረተ ሰላማዊ አብሮ መኖር እና የሁለቱንም ሀገራት ተጠቃሚነት ማረጋገጥ የዓለም አቀፉ ማህበረሰብ የሚጠብቀው ጉዳይ ነው።
ፕሬዚዳንት ሺ ጂንፒንግ በተጨማሪም ቻይናና አሜሪካ በዓለም አቀፍና በቀጣናዊ ጉዳዮች ላይ ትብብራቸውን እንዲያጠናክሩ መስማማታቸውን ጠቁመዋል።
ይህ ጉብኝት በ9 ዓመታት ውስጥ ወደ ቻይና የተጓዘ የመጀመሪያው በሥልጣን ላይ ያለ የአሜሪካ ፕሬዚዳንት ያደርጋቸዋል።
Ethiopian Broadcasting Corporation #China #USA #Beijing #ChinaUSRelations #WorldNews #Geopolitics
See less
👏1