Ethiopian Broadcasting corporation ®
8.86K subscribers
17.9K photos
205 videos
14 files
1.62K links
Ethiopian broadcasting corporation is a 24 working public media.

https://telega.io/c/EBC_TV
ማንኛውም አይነት አስተያየት እና ጥቆማ ካላችሁ በዚህ ላኩልን እንቀበላለን!!
https://t.me/+G7d4hSzJEhViMzQ0
Download Telegram
ከውጭ የሚገቡ ምርቶችን ከመተካት ባለፈ የወጪ ንግድ ገቢን እያሳደገ ያለው የኢትዮጵያ የግብርና ኢንቨስትመንት
*************

ኢትዮጵያ በአስር ዓመቱ የግብርና መሪ ዕቅድ ውስጥ በትኩረት እንዲሰራባቸው ካስቀመጠቻቸው ስትራቴጂካዊ ዘርፎች መካከል አንዱ የሆነው የግብርና ኢንቨስትመንት የምግብ ዋስትናን የማረጋገጥ፣ ከውጭ የሚገቡ ምርቶችን በሀገር ውስጥ የመተካት እና የውጪ ምንዛሪን የማሳደግ ሀገራዊ ግቦችን በላቀ ስኬት እያሳካ ይገኛል።

የሀገራችንን ሰፊ የግብርና አቅም በመጠቀም በርካታ የሀገር ውስጥና የውጭ ባለሃብቶች በስፋት ተሰማርተው ወደ ልማት ገብተዋል።

በአሁኑ ወቅት በሀገር አቀፍ ደረጃ በእርሻ ኢንቨስትመንት ብቻ ከ2 ነጥብ 3 ሚሊዮን ሄክታር በላይ መሬት በ8 ሺህ 904 ባለሀብቶች እጅ ላይ እንደሚገኝ የግብርና ሚኒስቴር መረጃ ያመላክታል።

መንግሥት ይህንን ዘርፍ ይበልጥ ለማሳደግ በመሬት አቅርቦት፣ የፋይናንስ አገልግሎትን ተደራሽ በማድረግ፣ በውል እርሻ እና በመሰረተ-ልማት ማመቻቸት ረገድ በርካታ...https://web.facebook.com/EBCzena/posts/pfbid0XuvHdboxNg7cbVgLLAFExSs4pcZVJaqhj2bffnrgWWQSF7G29nAHSABodApxhLshl
👏1
ፊፋ ከ2026ቱ የዓለም ዋንጫ 14 ቢሊዮን ዶላር ገቢ ለማግኘት አቅዷል
****

ከሶስት ቀናት በኋላ በሚጀምረው የ2026ቱ ዓለም ዋንጫ፣ ፊፋ በታሪክ ከፍተኛ የተባለውን የ14 ቢሊዮን ዶላር ገቢ ያገኛል ተብሎ ይጠበቃል።

ይህም በ2022 በኳታር ከተካሄደው የዓለም ዋንጫ ከተገኘው ገቢ ጋር ሲነጻጸር በእጥፍ የሚጨምር ሲሆን፤ አሜሪካ፣ ካናዳ እና ሜክሲኮ በጋራ የሚያዘጋጁት ይህ ውድድር በታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ በሶስት ሀገራት አስተናጋጅነት የሚካሄድ የመጀመሪያው የዓለም ዋንጫ በመሆን አዲስ ታሪክ ይጽፋል።

ይህ በዓይነቱ ትልቁ የተባለው የዘንድሮው ዓለም ዋንጫ የተሳታፊ ሀገራትን ቁጥር ወደ 48 ያሳደገ ሲሆን፣ በአጠቃላይ 104 ጨዋታዎች ይደረጉበታል።

ይህ የተሳትፎ መጠን ውድድሩን በታሪክ ትልቁ ከማድረጉም በላይ፣ በዓለም እግር ኳስ ታሪክ ከፍተኛ ትርፍ የሚመዘገብበትና በገንዘብ ረገድ እጅግ ስኬታማው የስፖርት ሁነት እንደሚያደርገው ታውቋል።

በዘረንቶስ ሰለሞን

#worldcup #sport #EBC
👏1
የኢትዮጵያ የህልውና እና የፍትሕ ጉዞ ወደ ቀይ ባሕር ዳርቻ
*************

ኢትዮጵያ በታሪክ ውስጥ ስሟ በገዘፈው ልክ በመልክዓ-ምድራዊ እስር ውስጥ እንድትማቅቅ የተፈረደባት ሀገር ሆና እንድትቆይ የተደረገው በድንገቴ የታሪክ አጋጣሚ አይደለም።

ከጀርባው የረቀቀ የባዕዳን ሴራ እና የውስጥ ባንዳዎች የታሪክ ክህደት ጭምር እንደነበረበት ዛሬ ላይ የሀቅ ፀሐይ የሞቀው የአደባባይ ምስጢር ሆኗል።

ሀገራችን የባሕር በሯን ስታጣና የየብስ እስረኛ ስትሆን ጉዳቱ የገባቸው ጥቂት አርቆ አሳቢዎች ብቻ ነበሩ። ዛሬ ግን ያ የታፈነና የታመቀ ታሪክ የትንፋሽ ማስተንፈሻ አግኝቶ ወደ ዓለም አቀፍ አጀንዳነት ተሸጋግሯል።

የባሕር በር ጉዳይ ለኢትዮጵያ የቅንጦት ወይም የፍላጎት ጥያቄ ሳይሆን፣ ከብሔራዊ ህልውና ጋር የተቆራኘ የሞትና የሽረት ጉዳይ መሆኑን መላው የኢትዮጵያ ሕዝብና መንግሥት በአንድ ድምፅ እያስተጋቡት ይገኛሉ።

ይህ የታሪክ ጠባሳ የስሌት ስህተት ሳይሆን ሆን ተብሎ የተቃኘ ሀገራዊ አቅምን የማዳከም ስትራቴጂ ውጤት ነበር። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በቁርጠኝነት እንደገለጹት ኢትዮጵያ የባሕር በር ባለቤት ካልሆነች ልማቷ ብቻ ሳይሆን ዘላቂ ሰላሟም አደጋ ላይ መውደቁ አይቀሬ ነው።

ከ130 ሚሊዮን በላይ ሕዝብ ያቀፈች ግዙፍ ሀገር፣ የዓለም የንግድ መስመር በሆነው በቀይ ባሕር…https://web.facebook.com/EBCzena/posts/pfbid02Uzruaeafpmk8urBwC38qVBigACtVqpxv8Bk91cZa2GBSMWvNVTm48hGhqwH4CjeFl
👏1
ዘመኑን የዋጀው ፌዴራል ፖሊስ፤ ከሀገራዊ ሪፎርም እስከ ድንበር ተሻጋሪ ወንጀሎች መከላከል ስኬት
***************

የሀገራችንን ታሪክና ልዕልና የሚመጥን ዘመናዊ የፖሊስ ተቋም ለመገንባት የተጀመረው ሀገራዊ ሪፎርም፣ የኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስን ወንጀልን አስቀድሞ የመከላከል ቁመና ወደ ላቀ ደረጃ አሸጋግሮታል።

የፌዴራል ፖሊስ ጠቅላይ አዛዥ ኮሚሽነር ጄኔራል ደመላሽ ገብረሚካኤል እንደገለጹት፤ ተቋሙ የሀገራዊ ለውጡን ተከትሎ ባካሄደው ጥልቅ የሪፎርም ትግበራ አሁን ላይ ዘመኑን የዋጀና ውጤታማ ተግባራትን የሚያከናውን ጠንካራ አቅም መገንባት ችሏል።

ይህ አዲስ ተቋማዊ ቁመናም ፖሊስ ከተለዋዋጭ ሁነቶች እና ከዲጂታሉ ዓለም ፈጣን ዕድገት ጋር እኩል እንዲጓዝ ትልቅ አቅም የፈጠረለት ሲሆን፣ በተለይም በዓለም አቀፍና ድንበር ተሻጋሪ ወንጀሎችን በመከላከል ረገድ በርካታ ስኬታማ ተግባራትን ለማስመዝገብ እንዳስቻለው ተናግረዋል።

ተቋሙ በስኬት ከተወጣቸው ተልዕኮዎች መካከል በየአቅጣጫው መረባቸውን ዘርግተው በሕገ-ወጥ የሰዎች ዝውውር…(15) ዘመኑን የዋጀው ፌዴራል ፖሊስ፤ ከሀገራዊ... - Ethiopian Broadcasting Corporation | Facebook
👏1
ሁለት ትሪሊዮን 339 ቢሊዮን 268 ሚሊዮን 126 ሺህ 738 ብር!

የሚኒስትሮች ምክር ቤት ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እንዲቀርብ የወሰነው የ2019 ዓ.ም ረቂቅ በጀት።

#Ethiopia #EBC #budget #2019budget
👏1
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ለሕንድ ጠቅላይ ሚኒስትር የእንኳን ደስ አለዎት መልዕክት አስተላለፉ
**************
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ለሕንድ ጠቅላይ ሚኒስትር ናሬንድራ ሞዲ የእንኳን ደስ አለዎት መልዕክት አስተላልፈዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በመልዕክታቸው ናሬንድራ ሞዲ በሕንድ ታሪክ ለረጅም ጊዜ ያገለገሉ ጠቅላይ ሚኒስትር በመሆን ታሪካዊ ምዕራፍ ማስመዝገባቸውን ገልጸዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በማኅበራዊ ትስስር ገጽ ባስተላለፉት መልዕክት፤ "ታላቅ ወንድሜ እና ውድ ወዳጄ ክቡር ናሬንድራ ሞዲ፣ የዓለማችንን ትልቁን እና እጅግ ንቁ የሆነውን የዲሞክራሲ ማህበረሰብ ዘላቂ እምነት በማግኘት፣ ህንድን በራዕይ እና በቁርጠኝነት በተከታታይ ሶስት የዲሞክራሲያዊ የስልጣን ዘመናት በመምራት ላስመዘገቡት ታሪካዊ ስኬት የተሰማኝን ደስታ እገልጻለሁ" ብለዋል።

የጠቅላይ ሚኒስትር ናሬንድራ ሞዲ አመራር በሚሊዮን የሚቆጠሩ…
https://web.facebook.com/EBCzena/posts/pfbid0Lm4viS9wUnEwibGuRNxiuhnL3g1KHb7MCSLNmofzxrWUvf3CVFE3iydSXhLVfuodl
👏1