Ethiopian Broadcasting corporation ®
8.87K subscribers
17.9K photos
205 videos
14 files
1.62K links
Ethiopian broadcasting corporation is a 24 working public media.

https://telega.io/c/EBC_TV
ማንኛውም አይነት አስተያየት እና ጥቆማ ካላችሁ በዚህ ላኩልን እንቀበላለን!!
https://t.me/+G7d4hSzJEhViMzQ0
Download Telegram
የ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ የውጤት ቆጠራ እና የማዳመር ስራ ተጠናቅቆ በሁሉም ምርጫ ክልሎች ውጤት ተለጥፏል - ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ
****************
የ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ የውጤት ቆጠራ እና የማዳመር ስራ ተጠናቅቆ በሁሉም ምርጫ ክልሎች ውጤት መለጠፉን የብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ሰብሳቢ ወይዘሮ ሜላትወርቅ ኃይሉ ገልፀዋል።

የቦርዱ ሰብሳቢ ከምርጫ ክልሎች የተዳመሩ ውጤቶች ወደ ቦርዱ ማዕከል መጥተው የማጣራት ስራ እየተሰራ እንደሚገኝም ነው የገለፁት።

በትናንትናው ዕለት በነበረው መግለጫ ከሁለት ምርጫ ክልል በስተቀር የምርጫ ክልል ደረጃ ውጤት አለመለጠፉን ገልጸን ነበር ያሉት ወይዘሮ ሜላትወርቅ ዛሬ በአንደኛው በሃላባ 1 ተለጥፏል፣ የቀብሪ በያ አሁንም የማዳመሩ ሥራ በተወሰነ ደረጃ ጊዜ ፈጅቶባቸዋል ብለዋል።

የብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ሰብሳቢ ወይዘሮ ሜላትወርቅ በመግለጫቸው ምርጫ ክልሎች ማዕከል ላይ ደርሰው የማረጋገጡ ሥራ የተጀመረላቸው ከ1ሺህ 139 ውስጥ 1ሺህ 8ቱ በቦርዱ…https://web.facebook.com/EBCzena/posts/pfbid02gCmhXCHgEHRD4RJf7MVkn4VorFyp6yPqSjLniTdjwLvLi7sENxrERQKWFYaTz1vCl
👏1
ኤቨርተን ለበርንሌይ 35 ሚሊዮን ፓውንድ እንዲከፍል ተወሰነ

ኤቨርተን የፋይናንስ ደንብ (PSR) በመጣሱ ምክንያት ለበርንሌይ 35 ሚሊዮን ፓውንድ እንዲከፍል የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ልዩ ኮሚሽን ወስኗል።

ይህ ውሳኔ አንድ የፕሪሚየር ሊግ ክለብ ከሌላው በታሪክ የጠየቀውና የተፈቀደለት ትልቁ የካሳ ክፍያ ሆኖ ተመዝግቧል።

መነሻ ምክንያቱ የሚያያዘው ከ2021/22 የውድድር ዘመን ጋር ነው። በወቅቱ ኤቨርተን የትርፍና ዘላቂነት ደንብ (PSR) በመጣሱ በ2023/24 የውድድር ዘመን የአስር  ነጥብ ቅጣት ተጥሎበት እንደነበር ይታወሳል።

ነገር ግን በርንሌይ "ኤቨርተን ደንቡን በጣሰበት የ2021/22 የውድድር ዘመን የነጥብ ቅጣቱ ተፈጻሚ ቢሆን ኖሮ እኛ ከሊጉ አንወርድም ነበር፤ በመውረዳችን ምክንያት ከፍተኛ የፋይናንስ ኪሳራ ደርሶብናል" በማለት የካሳ ክስ መስርቷል።

በወቅቱ ኤቨርተን 16ኛ ደረጃን ይዞ ሲተርፍ፣ በርንሌይ 18ኛ ደረጃ ሆኖ መውረዱ ይታወሳል።

ኤቨርተን ውሳኔውን "ህጋዊ ያልሆነ፣ መሰረት የሌለው እና ፍጹም የተሳሳተ" ነው ሲል የገለጸው ሲሆን፣ ወዲያውኑ ይግባኝ ማለቱን አስታውቋል። ይህ ውሳኔ ከጸና ለሊጉ ትልቅ መነጋገርያ ይሆናል።

በተመሳሳይ ሁኔታ ሊድስ ዩናይትድ ቀደም ብሎ ከኤቨርተን ጋር ከፍርድ ቤት ውጭ ስምምነት ማድረጉ ሲነገር፣ እንደ ቼልሲ እና በ115 ክሶች የተጠረጠረው ማንችስተር ሲቲ ያሉ ክለቦች ጥፋተኛ ሆነው ከተገኙ፣ ሌሎች ክለቦችም በተመሳሳይ መልኩ በሚሊዮን የሚቆጠር የካሳ ይገባኛል ክስ እንዲመሰርቱባቸው ትልቅ በር ሊከፍት ይችላል ሲል ስጋቱን ያስቀመጠው ቢቢሲ ነው።

በአዲስ የሺዋስ

#EthiopianBroadcastingCorporation
👏1
ሁሉም የዓለም ዋንጫ ጨዋታዎች በምልክት ቋንቋ ይተረጎማሉ
****

ይህን እንቅስቃሴ ዓለም አቀፉ የእግር ኳስ አስተዳዳሪ አካል ፊፋ በመላው ዓለም ለሚገኙ ደጋፊዎች ይበልጥ አካታች የሆነ የውድድር ተሞክሮ ለመፍጠር የታቀደ ትልቅ እርምጃ ሲል ገልጾታል።

የአካል ጉዳት ያለባቸው ደጋፊዎች በስታዲየም ውስጥም ሆነ በሩቅ መመልከቻ አማራጮች አማካኝነት በውድድሩ ሙሉ በሙሉ መደሰት እንዲችሉ ማድረግን ዓላማው አድርጓል።

ማኅበሩ በመግለጫው “ፊፋ አካል ጉዳተኞችን እና ቤተሰቦቻቸውን እንዲሁም ጓደኞቻቸውን ጨምሮ ሁሉም ደጋፊዎች በዘንድሮው የዓለም ዋንጫ ላይ ግሩም ተሞክሮ እንዲኖራቸው ለማድረግ ቁርጠኛ ነው” ብሏል።

ሙሉውን የጨዋታ እንቅስቃሴ በመተርጎም መስማት ለተሳናቸው እና የመስማት ችግር ላለባቸው ደጋፊዎች መሳጭ ተሞክሮ ይሰጣል።

በፊፋ የተመደቡ አስተርጓሚዎች የየደቂቃውን እንቅስቃሴ ማስተላለፍ ብቻ ሳይሆን እንደ ዳኛ ፊሽካዎች፣ የደጋፊዎች የድጋፍ ድምፅ እና በስታዲየሙ ድባብ ውስጥ ያሉ ድምፆችን ያጋራሉ፤ ይህም ደጋፊዎች እያንዳንዱን የጨዋታውን ቅጽበት እንዲከታተሉ ያደርጋቸዋል ነው የተባለው።

የእግር ኳስ ደጋፊዎችን በተሻለ ሁኔታ ለማገልገል፣ በዩናይትድ ስቴትስ እና በካናዳ የሚደረጉ ሁሉም የምድብ ጨዋታዎች የአሜሪካ የምልክት ቋንቋ (ASL) ትርጉም የሚኖራቸው ሲሆን፣ በሜክሲኮ የሚደረጉ ጨዋታዎች ደግሞ የሜክሲኮ የምልክት ቋንቋ (LSM) ይኖራቸዋል።

ለዚህም እንዲረዳ የሞባይል መተግበሪያ መዘጋጀቱን ነው ፊፋ ያስታወቀው።

በእስከዳር ይኩኖአምላክ

#FIFAWorldCup #Ebc #sport
👏1
ኮሚሽኑ "የኢትዮጵያ ሕዝብ የምክክር ጉባኤ" የሚጀመርበትን ቀን ዛሬ ይፋ ያደርጋል
************
የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ለመላው የኢትዮጵያ ሕዝብ የምክክር ጉባኤ የሚጀመርበትን ቀን ዛሬ ሰኔ 5 ቀን 2018 ዓ.ም. ይፋ እንደሚያደርግ አስታወቀ።
ኮሚሽኑ ባወጣው መረጃ መሠረት፣ ይህ ታሪካዊ የምክክር ሂደት የሚጀመርበትን ዝርዝር መርሃ-ግብር ከምሽቱ 1፡30 ጀምሮ በሁሉም የመገናኛ ብዙሃን አማካኝነት ለሕዝብ ይፋ ያደርጋል።
ኮሚሽኑ "ኢትዮጵያ እየመከረች ነው!" በሚል መሪ ቃል እያከናወነ ያለው ይህ ተግባር፣ በሀገራዊ ጉዳዮች ላይ የጋራ መግባባት ለመፍጠር ያለመ መሆኑ ይታወቃል።
#NationalDialogueEthiopia #Ethiopia #PeaceAndDialogue #EthiopianBroadcastingCorporation
👏1
ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ በኢራን ላይ እወስዳለው ያሉትን ጥቃት እንደተዉት አስታወቁ
**************
የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ከኢራን ጋር የሚደረገው ውይይት መሻሻል እንዳሳየ እና ከስምምነት ሊደረስ እንደሚችል በመግለፅ በኢራን ላይ ሊሰነዝሩት ያሰቡትን ጥቃት ማቋረጣቸውን አስታውቀዋል።
ትራምፕ ትናንት ሐሙስ ኻርግ ደሴት ላይ ኢራንን “ክፉኛ እንመታለን” ብለው ቢዝቱም፤ ሊያደርሱት የነበረውን ጥቃት ለመሰረዝ መወሰናቸውን ነው የተናገሩት።
ከኢራን ጋር የሚፈረመው የመግባቢያ ሰነድ “የመጨረሻ ደረጃ” ላይ መድረሱን ጠቅሰው በዚህ ሳምንት ስምምነቱ ሊገባደድ እንደሚችል አስረድተዋል። ስምምነቱ የሚፈረመው አውሮፓ ውስጥ እንደሚሆን ጠቁመዋል።
ስምምነቱ ኢራን የኒውክሌር መሣሪያ እንዳይኖራት የሚያግድ እንዲሁም በአፋጣኝ የሆርሙዝ ወሽመጥ እንዲከፈት የሚያስገድድ እንደሚሆን ትራምፕ አስረግጠው ተናግረዋል።
ትራምፕ ይህንን ቢሉም የኢራን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ስምምነት ላይ ለመድረስ አለመቃረባቸውን አስታውቀዋል።
አሜሪካ በድርድሩ “ከልክ ያለፈ ጥያቄ” እያቀረበች እንደሆነም ጠቅሰዋል።
ኳታር ሁለቱን አገራት ለማሸማገል ጥረት እያደረገች እንደሆነ ተጠቁሟል።
ትራምፕ ኢራን ላይ ጥቃት እንደማይፈጸም መግለጻቸውን ተከትሎ የድፍድፍ ነዳጅ ዋጋ ቅናሽ ማሳየቱን የዘገበው ቢቢሲ ነው ።
Ethiopian Broadcasting Corporation #ኢራን #አሜሪካ #ትራምፕ #ሆርሙዝ
👍2😁1
"የኢትዮጵያ ሕዝብ የምክክር ጉባኤ" ሐምሌ 8 በይፋ ይጀመራል፡- የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን
***********

በኢትዮጵያ በሂደት ላይ በሚገኘው ሀገራዊ ምክክር ሀገራችን ወደ አዲስ የፖለቲካ የታሪክ ምዕራፍ የምትሻገርበት ወሳኝ ድልድይ እየተገነባ ይገኛል።

የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን፣ በሀገራችን ስር የሰደዱና ለዘመናት የቆዩ የቅራኔ ምንጮችን በጠረጴዛ ዙሪያ ውይይት ለመፍታት ታሪካዊ ኃላፊነት ተረክቦ እየተንቀሳቀሰ ነው።

ዋነኛ ግቡም በፖለቲካው ሳቢያ የሚስተዋሉ መሠረታዊ ልዩነቶችን በውይይት መፍታት ነው። ይህም ብሔራዊ መግባባትን ለማምጣት፣ ማኅበራዊ መተማመንን ለማደስ እና የሀገርን አንድነት በጽኑ መሠረት ላይ ለመገንባት ያለመ ነው።

ኮሚሽኑ “ኢትዮጵያ እየመከረች ነው!” በሚል መሪ ቃል እያከናወነ ያለው ተግባር…https://web.facebook.com/EBCzena/posts/pfbid0HLrTEJEJ1UuXeqxuU7MrkeFjVKetQHyD6yxp4TMx9W6tFAZCudZ8rXxi1i1z2kVLl
👏1
መላው የኢትዮጵያ ሕዝብ በከፍተኛ ተስፋና ጉጉት የሚጠብቀው ታሪካዊው ሀገራዊ የምክክር ጉባኤ ከሐምሌ 8 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ በአዲስ አበባ ይካሄዳል -
የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን

"ኢትዮጵያ እየመከረች ነው"

Ethiopian Broadcasting Corporation #ምክክር #ሐምሌ8 #ኢትዮጵያ
👏1
አረንጓዴ አሻራ የ7 ዓመታት ጉዞ
***********

✅ ጠቅላላ የተተከሉ ችግኞች ➡️ ከ48 ቢሊዮን በላይ

✅ የችግኞች የመጽደቅ ምጣኔ ➡️ 84% (ከ40 ቢሊዮን በላይ የጸደቁ)

✅ የሀገራችን የደን ሽፋን ➡️ ከነበረበት 3% ተነሥቶ ወደ 23.6% ደርሷል

✅ ያገገመ የተራቆተ መሬት ➡️ ከ10 ሚሊዮን ሔክታር በላይ

✅ የተፈጠረ ጠቅላላ የሥራ ዕድል ➡️ ከ1.2 ሚሊዮን በላይ ዜጎች

#Ethiopia #EBC #greenlegacy #success
👏1
ኳታር 1 - 1 ስዊዘርላንድ፦ የሙሉ ሰዓት ውጤት
******

በ23ኛው ዓለም ዋንጫ ምድብ ሁለት ኳታር ከ ስዊዘርላንድ ያደረጉት ጨዋታ፤ 1 ለ 1 በሆነ አቻ ውጤት ተጠናቅቋል።

ብሪል ኤምቦሎ 17ኛው ደቂቃ ላይ በፍፁም ቅጣት ምት ለስዊዘርላንድ ሲያስቆጥር፤ ቡዓሊም ኮክሂ ኳታርን አቻ ያደረገች ግብ 95ኛው ደቂቃ ላይ ከመረብ አሳርፏል።

#WorldCup2026 #qatar #switzerland #EBC #sports
👎2👍1
ጀግናዋ አትሌት ጥሩነሽ ዲባባ የረዳት ኮሚሽነርነት ማዕረግ አገኘች
**************

የፌዴራል ማረሚያ ቤት ኮሚሽን የስፖርት ክለብ እንዲሁም የሙዚቃና ቴአትር ቡድን የተመሠረተበት 40ኛ ዓመት ክብረ በዓል ሰኔ 6 ቀን 2018 ዓ.ም በአድዋ ድል መታሰቢያ በድምቀት ተከብሯል። በዚሁ መድረክ ላይ በኦሎምፒክና በዓለም ሻምፒዮና ውድድሮች በርካታ ሜዳሊያዎችን በማምጣት የሀገርን ሰንደቅ ዓላማ ከፍ ላደረገችው ጀግናዋ አትሌት ጥሩነሽ ዲባባ የተቋሙ ከፍተኛ የዕድገት እርከን የሆነው የረዳት ኮሚሽነርነት ማዕረግ ተሰጥቷታል።

በዕለቱም ለክብርት ረዳት ኮሚሽነር ደራርቱ ቱሉ፣ ለኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ፕሬዚዳንት ኮማንደር አትሌት ስለሺ ስህን፣ ለኮማንደር ፋጡማ ሮባ፣ ለኮማንደር አትሌት ሰለሞን ባረጋ እና ለምክትል ኮማንደር ሰንበሬ ተፈሪ የዕውቅናና ሽልማት ፕሮግራም ተካሂዷል። በተጨማሪም በአሰልጣኝነት ከ30 ዓመታት በላይ በማገልገል የላቀ አስተዋጽኦ ላበረከቱት ረዳት ኮሚሽነር ሁሴን ሸቦ የኒሻን ሽልማት የተበረከተላቸው ሲሆን፤ በኪነ-ጥበቡ ዘርፍ ለሀገር ትልቅ አስተዋጽኦ ላበረከቱ የሙዚቃና ቴአትር ቡድኑ አባላትም ዕውቅና ተሰጥቷል።

በክብረ በዓሉ ላይ የተገኙት የፍትሕ ሚኒስትር ሐና አርዓያሥላሴ የኮሚሽኑ የስፖርት ክለብ ባለፉት 40 ዓመታት እውቅ ጀግኖችን በማፍራት በኩል የላቀ ሚና መጫወቱን ጠቅሰው፤ ተቋሙ ይህንኑ አበረታች ሥራውን ይበልጥ ዘመናዊ በማድረግ አጠናክሮ ሊቀጥል እንደሚገባ አሳስበዋል። በበኩላቸው ኮሚሽነር ጄኔራል የኑስ ሙሉ ተቋሙ ታራሚዎችን አምራችና ሕግ አክባሪ ዜጋ አድርጎ የማውጣት ኃላፊነት እንዳለበት ገልጸው፤ ይህንንም ለማሳካት የስፖርት እና የኪነ-ጥበብ ክፍሎቹ ታራሚውን በማዝናናት፣ በማስተማርና የአካል ብቃት በማጎልበት በኩል ግንባር ቀደም ሚና እየተጫወቱ መሆኑን አስታውቀዋል።
👏1