Ethiopia Doctors advice
105 subscribers
1 photo
1 link
Download Telegram
Channel created
እንቁላል(Egg)
እነዚህ የጤናማ እንቁላል አስገራሚ እውነታዎች ናቸዉ ፦
1-ለመፈጨት ቀላል ነው
እንቁላል ፍርፍር ወይም ቅቅል ከተመገብነው በሃላ ለከርሳችን/ሆዳችን/ አይከብድም።ሰውነታችን በሽታ የመከላከል አቅሙ ከፍተኛ ነው።
2-ለጡት ካንሰር የመጋለጥ እድልን ይቀንሳል
የተለያዩ ጥናቶች እንደሚያመለክቱት ቢያንስ በሳምንት 6 እንቁላል መመገብ በጡት የካንሰር የመጋለጥ እድላችንን 44% ይቀንሳል ።
3-ለአይን ጤንነት ይጠቅማል
ሁለት ካሮቲኖይድ፣ሉቲይን እና ዜክሳንቲን የጠራ እይታ እና ጤናማ እይታ እንዲኖረን ይረዳል።
4-የፀጉሩ እና የጥፍር ጤንነትን ይጨምራል
በሰልፈር/ድኝ/የበለፀገ አሚኖ አሲድ በእንቁላል ውስጥ ይገኛል። የጥፍርን ጤንነት እና ጥራት ይጨምራል።ሌሎች ሚኒራሎች እንደ ብረት ዚንክ እና ሴሊኒየም ለፀጉር ጤንነት የበኩላቸውን ድርሻ ይወጣሉ።
5-የሰውነት ክብደትን ያመጣጥናል
የሰውነት ክብደታቸውን መጨመር የሚፈልጉ ሰዎች እንቁላል ትክክለኛ ምርጫ ሲሆን በፕሮቲን የበለፀገ ነው።እንቁላል ምንጠቀም ከሆነ ከመጥን በላይ እንዳንመገብ አስተዋጽኦ ያደርጋል ሰለዚህ በቀላሉ የሰውነት ክብደታችንን አመጣጠንን ማለት አደለም።
6-አጥንታችን ጠንካራ እንዲሆን ያደርጋል
ካልስየም በሰውነታችን እንዲዲመጠጥ እና እንዲዋሀድ ቫይታሚን ዲ በጣም አስፈላጊ ነው።እንቁላል ከፍተኛ ቫይታሚን ዲ ፎስፈረስ ና ካልስየም መጠን አለው እነዚህ በአንድነት በመሆን የአጥንት ችግርን ይከላከላሉ።
7-ለአይምሮ ጤንነት አስፈላጊ ነው
እንቁላል ክሎሪንን ለአይምሮ በመመገብ ጤንነቱን ይጨምራል /ይጠብቃል።ክሎሪን መልዕክት አስተላላፊ በመሆን ያገለግላል።በእንቁላል አስኳል ውስጥ የሚገኝ ፎሌት የተባለ ንጥረ ነገር የነርቭ ሴሎችን በመጠበቅ አእምሮ ተግባሩን በትክክል እንዲወጣ ያደርገዋል።


መልካም ጤንነት
👍3
#ማይግሬን(migraine head ache)

¤ማይግሬን ለማስታገስ ጠቃሚ ምክሮች

የተረጋጋ እና ፀጥ ያለ ቦታ ይምረጡ
በአካባቢዎ የሚገኝ መብራት ማጥፋት እና ከተቻለ እንቅልፍ መተኛት,የሞቀ
ወይንም የቀዘቀዘ ውኃን በላስቲክ በማድረግ በእራስዎ እና በአንገትዎ ላይ
ማስቀመጥ, ይህ ማለት ደግሞቅዝቃዜው በማደንዘዝ ሕመም እንዳይሰማዎ
ሲያደርግ ሙቀቱ ደግሞ የራስና የአንገት ጡንቻዎችን እንዲፈታቱ
ያደርጋልሕመም የሚሰማዎ ቦታ ላይ በቀላሉ ማሸት አንገትዎን እና ትከሻዎን
ማሸትገላዎን በሙቅ ውሀ መታጠብ
በቂ እረፍት ማድረግ
መደበኛ የእንቅልፍ ሰዓት ይኑርዎሁሌም በተመሳሳይ ሰዓት የመተኛት ልምድ
ያዳብሩበቀን እንቅልፍ መተኛት ያስለመዱ ከሆነ ከ20-30 ደቂቃ ብቻ ቢሆን
ይመከራል. ከዛ በላይ እንቅልፍ ከወሰዱ የለሊት እንቅልፍዎን ሊያዛባ
ይችላልእንቅልፍዎ ያልመጣ ከሆነ እራስዎን አያስገድዱ መጽሐፍ በማንበብ
ራስዎን ያድክሙ
አመጋገብዎን ያስተካክሉ
መደበኛ የሆነ የምግብ ሰዓት ይኑርዎቁርስዎን መመገብ አይዘንጉማይግሬን
ቀስቃሽ የሆኑ ምግቦችን ያስወግዱ (እንደ ቼኮሌት, አይብ, ቡና እና የአልኮል
መጠጦች)
የአካል ብቃት እንቅስቃሴ
የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ማድረግ የማይግሬን ራስ ምታትን ይቀሰቅሳል ነገር
ግን ሐኪምዎን በማማከር ቀለል ያሉ እንቅስቃሴዎችን ያድርጉ (ለምሳሌ እንደ
ውሃ ዋና; የእግር ጉዞ የመሳሰሉትን ማድረግ ይችላሉ)
ጭንቀትዎን ይቆጣጠሩ
ጭንቀት የማይግሬን ራስ ምታትን ይቀሰቅሳል. በዕለት ተዕለት የኑሮ ሁኔታዎች
የሚያጋጥሙንን አስጨናቂ ነገሮች መከላከል ባይቻልም ከዚህ በታች
የተዘረዘሩትን በመፈፀም መቀነስ ይችላሉ.ቀለል ያለ የኑሮ ዘይቤ ይኑርዎጊዜዎን
በአግባቡ ይጠቀሙየዕረፍት ጊዜ ይኑርዎለነገሮች በጎ አመለካከት ይኑርዎራስዎን
ዘና ያድርጉ
የራስ ምታትዎን በተመለከተ የግል ማኅደር ይኑርዎ
በግል ማኅደር መመዝገብ ራስምታትዎን የሚያስነሳውን ሁኔታ ለማወቅ እና ምን
እንደሚያስታግስልዎም ለማጤን ይረዳል።
የሚጥል በሽታ(Epilepsy)


በሃገራችን በብዛት እንደሚታሰበው የክፉ መንፈስ ሳይሆን፣ የአእምሮአችን ህዋሳት ከትክክለኛው ስርአት በተለየና በበዛ መልኩ ሲነቃቁ የሚከሰት በሽታ ነው። 

አንድ ሰው የሚጥል በሽታ አለበት ለማለት ምልክቶቹ ቢያንስ ሁለት ጊዜ መከሰት ይኖርባቸዋል። በሽታው መታከም የሚችል ችግር ማሆኑን አውቆ ታማሚን ወደ ህክምና ቦታ ማምጣት ብልህነት ነው።

የሚጥል በሽታ ምልክቶቹ ምንድናቸው?

የበሽታው አገላለጽ ከበሽታው አይነት ሊለያይ ይችላል። በብዛት የሚታየው የበሽታው አይነት ጠቅላላ ሰውነትን የሚያንዘፈዝፍ ሲሆን በዚህ ጊዜ ታማሚዎች ራሳቸውን ይስታሉ። ታማሚው ከዚህም በተጨማሪ አይን ወደላይ ሲሰቅል እና አረፋ ሲደፍቅ ይታያል። በአንዳንድ የበሽታው አይነቶች ላይ ምልክቱ ከመታየቱ በፊት ራስ ምታት፣ የልብ የመምታት ስሜት፣ የእይታ ብዥታ ሊታዩት ይችላሉ። ይህም ከ አንድ እስከ ሁለት ደቂቃ ሊቆይ ይችላል። ታማሚዎቹ ከነቁ በኋላ የሁነውን ነገር ለማወቅ እና ለማስታወስ ይሳናቸዋል። ለተከታይ ደቂቃዎችም ሽንትና ሰገራቸውን መቆጣጠር ይሳናቸዋል።

ለበሽታው እንዴት ልጋለጥ እችላለሁ?

ለአብዛኛው የሚጥል በሽታ ተጠቂዎች የበሽታውን መነሻ ለማወቅ ይቸግራል። ነገር ግን የሚከተሉት ችግሮች ለበሽታው መከሰት የራሳቸውን አስተዋጾ ያበረክታሉ።

በቅርብ የቤተሰብ አባላት ላይ ተመመሳሳይ በሽታ መኖርበእናት የእርግዝና ወራት የተከሰቱ ችግሮችበጭንቅላት ላይ የደረሰ ጉዳት ወይም አደጋወደ ጭንቅላት የተሰራጨ ካንሰርየደም ውስጥ ስኳር መጠን ማነስየአደንዛዥ ዕፆች ተጠቃሚነትተደራቢ በሽታዎች፡ ለምሣሌ፦ የጭንቅላት ወባ

የበሽታው መዘዞች

በሽታው በተደጋጋሚ በሚከሰትበት ወቅት ሌሎች ችግሮችን አያይዞ ያመጣል። እነዚህም የሚከተሉት ናቸው።

ከ30 ደቂቃ በላይ የሚቆይ ማንቀጥቀጥ መገለልና መድሎ የግጭት አደጋዎች የአእምሮ ዘገምተኝነት ድንገተኛ ሞት

እነዚህን አስከፊ ችግሮች ከመከሰታቸው በፊት ለመቆጣጠር ምልክቶቹ በታዩበት ጊዜ በአፋጣኝ አቅራቢያ ወደሚገኝ የጤና ተቋም በመሄድ አስፈላጊውን ህክምና ማግኘት ያስፈልጋል።

የሚጥል በሽታ ህክምና ምንድነው?

የተለያዩ የላብራቶሪ ምርመራዎች ከተደረጉ በኋላ የኢኢጂ እና እንዳስፈላጊነቱ ደግሞ የኤም አር አይ ምርመራዎች የደረጋሉ። እነዚህ ምርመራዎች ለሐኪሙ የችግሩን መንስኤ እንዲረዳና ከዚህም ተነስቶ ትክክለኛውን መድሃኒት ለማዘዝ ያስችሉታል። ከዚህም በተጨማሪ በሽታውን የሚያባብሱትንና የሚያስነሱትን መንስኤዎች በመረዳት ማስወገድ ያስፈልጋል። የሚሰጠው መድሃኒት እንደየበሽታው አይነት የሚለያይ በመሆኑ ምርመራዎችን ማድረግ አስፈላጊ ነው። መድሃኒት መውሰድ ከጀመርክ የመድሃኒቱን ስራ ከሚያስትጓጉሉ ነገሮች እና ለአደጋ ከሚያጋልጡ ባህሪዎች መጠበቅ ይኖርብሃል። እነዚህም፡

አልኮል መጠጥአደንዛዥ ዕጽ ለምሣሌ፦ ጫትከፍተኛ ቦታዎችዋና … ናቸው።

በበሽታው ህክምና ጥሩ ልውጥ ለማግኘት ከተፈለገ ሐኪም ጋር ክትትል ማድረግ ያስፈልጋል። በቀጠሮ ቀን በመሄድ በሽታው ያሳየውን መሻሻል መገምገም ይኖርበታል። በበሽታው የተያዘ ማንኛውም ሰው በትምህርት ራሱን ማሳደግ፣ ማግባት፣ መውልድ እና ቤተሰብ መመስረት ይችላል።

የሚጥል በሽታ ያለበትን ሰው እንዴት ልረዳው እችላለሁ?

በሃገራችን ውስጥ የሚዘውተሩት ባህላዊ መንገዶች ማለትም ክብሪት መጫርም ሆነ ውሃ መርጨት፣ ለህመምተኛው የሚሰጡት ጥቅም የለም። እነዝህ መንገዶች የሚጠቅሙ የሚመስለን ችግሩ ሲከሰት የሚፈጀው ጥቂት ደቂቃ በመሆኑ ነው። በመጀመሪያ መረጋጋት ያስፈልጋል። ከዚያም በአፋጣኝ የህክምና ሰጪ አካላት ጋር (ለምሳሌ፡ ቀይ መስቀል) በመደወል እገዛ እንዲደረግ ማስታወቅ ይኖርብሃል። በመቀጠልም ህመምተኛው የወደቀበት ስፍራ አደጋ ሊያስከትሉ የሚችሉ እንደ ድንጋይ፣ የመስታወት ስባሪ የመሳሰሉ ነገሮችን ከአካባቢው በማራቅ ህመምተኛውን ከተጨማሪ አደጋዎች መጠበቅ ትችላለህ። ልብሱን በመከፋፈትም ጭንቀቱን መቀነስ ትችላለህ። ከዚያም ወደጎን በማስተኛት ወደአፍ የሚገቡ ነገሮችን እንዳይውጥ መከላከል ይቻላል። ይህንን በመድረግ የመታነቅ ችግር እንዳይገጥመው ትከላከላለህ። ምላሱም ወደ ውስጥ ገብቶ መተንፈስ እንዳስቸገረው ከተመለከትክ ፣ ምላሱን በማስወጣት ሰላሙን ላትመልስላት ትችላለህ። የተጠሩት የጤና ባለሙያዎች በአካባቢው ሲደርሱ የተመለከትከውን በሙሉ በአግባቡ በመግለጽ ለመዳን ያለውን ተስፋ መጨመር ትችላለህ።
❤2👍1
የማህፀን ኢንፌክሽን

¶የማህፀን ኢንፌክሽን ማለት በተለያዩ ባክቴርያዎች፣ ቫይረሶች፣ ፓራሳይቶች እና ፈንገሶች ምክንያት የማህፀን መግቢያ ብልት(vaginal canal) ሲቀጥልም ማህፀን፣ የማህፀን ቱቦ እና የእንቁለል ማምረቻው (ovary) ሲጠቃ ነው።

¶በማህፀን መግቢያ ብልት (Vagina canal)ውስጥ ከሰውነት ጋር ተግባብተው የሚኖሩ ጥሩ ባክቴሪያዎች(lactobacilus) ሲኖሩ እነኝህ አሲድ በማመንጨት(lactic acid) ከውጭ ወደውስጥ የሚገቡ ተህዋስያንን ለምሳሌ ሌሎች ከሰውነት ውጭ የሚገኙ ባክቴሪያዎችን፣ ቫይረሶችን እና ፈንገሶችን የሚገድሉልን ሲሆን ነገር ግን እነኝህ ጥሩ የሚባሉ ባክቴሪያዎች በተለያዩ ምክንያቶች በብልት ውስጥ ሳይገኙ ወይም ሲጎዱ አሲዳማ የነበረው የብልት ክፍል ወደ ቤዛማነት ስለሚቀየር ለኢንፌክሽን የመጋለጥ ሁኔታ በከፍተኛ ሁኔታ ሊጨምር ይችላል።

¶ኢንፌክሽንን የሚጨምሩ ሁኔታዎች

☘️ ከብዙ ወንዶች ጋር ጥንቃቄ የጎደለው(ያለ ኮንዶም) ግንኙነት ማድረግ። ይህ ከውጭ ያሉትን ባክቴሪያዎች እና ሌላ ተህዋስያን እንደ ቫይረስ እና ፈንገስ የመሳሰሉት ወደማህፀን ሊያስገባ ይችላል።

☘️ አንዳንድ የንፅህና መጠበቂያ ሞዴሶች የሚይዟቸው ንጥረ ነገሮች ወይም ደግሞ ሴቶች የሚጠቀሟቸው የተለያዩ የንፅህና መጠበቂያ ኬሚካሎችና ሳሙናዎች ከብልት ጫፍ ወይም ከብልት የውስጠኛው ሽፋን ጋር ሲገናኙ ጥሩ የሚባሉትን ባክቴሪያዎች ሊጎዱ ይችላሉ።

☘️ በሳሙና ወይም ብልት ውስጥ ውሀ አስገብቶ መታጠብ - ይህ ጥሩ የሚባሉትን ባክቴሪያዎች ከቦታቸው አጥቦ ሊያወጣ ይችላል

☘️ በወር አበባ ጊዜ የሚደረግ የግብረ ስጋ ግንኙነት የማህፀን በር ክፍት ስለሚሆን ተህዋስያን በቀላሉ ወደማህፀን እንዲገቡ ሊያረግ ይችላል

☘️ የመራቢያ አካባቢ ንፅህናን በተገቢው ሁኔታ አለመጠበቅ

☘️ ንፅህናውን ያልጠበቀ የወሊድ አገልግሎት እና ውርጃ ማድረግ

☘️ በለጋ እድሜ የግብረ ስጋ ግንኙነት መጀመር (ከ19 አመት እድሜ በታች)

ከላይ የተጠቀሱት ምክንያቶች ጥሩ የሆኑትን ባክቴሪያዎች በመጉዳትና በማስወገድ በመጥፎ ባክቴሪያ እንዲተኩ ሊያደርጉ ይችላሉ። ይህም ለአኢንፌክሽን ያጋልጣል።

¶ ምልክቶች

☘️ የመጀመሪያው ምልክት በመጠን በዛ ያለ እና ከወትሮው ወይም ከተለመደው የተለየ ሽታ ያለው ፈሳሽ መታየት መጀመር ነው

☝️ ወደህክምና ካልሄዱና ችላ ካሉት ደግሞ

☘️ በማህፀን መግቢያ አካባቢ ማቃጠል፣ ማሳከክ እና ማበጥ
☘️ በግንኙነት ጊዜ ማቃጠል
☘️ ሽንት በሚሸናበት ጊዜ ማቃጠል ስሜት

☝️ አሁንም ችላ ካልሺውና ወደጤና ተቋም ካልሄድሽ ሊከሰት የሚችሉ ችግሮች

☘️ ኢንፌክሽኑ ከታችኛው የማህፀን መግቢያ ብልት (vaginal canal) በማለፍ ወደ ላይኛው የማህፀን ክፍል የማህፀንን በርን (cervix) በማለፍ ኢንፌክሽኑ መዛመቱን ይቀጥላል። ይህም በመቀጠል-

☘️ እንቁላሉን የሚያመርተው ክፍል (ovary) እና እንቁላሉን ወደ ማህፀን የሚወስደውን ቱቦ (Fallopian tube) በመድፈን ውሀ እና መግል እንዲቋጥር በማድረግ ከፍተኛ የሆነ ከእምብርት በታች ህመም ማምጣት ፣ ቀጥሎም ትኩሳት፣ ብርድ ብርድ ማለት ፤ ይህ በተገቢው ሁኔታ ካልታከመ መግል የያዘው ከረጢት መፈንዳት እና ለከፍተኛ የሆነ የኢንፌክሽን አደጋ መጋለጥ

☘️ ቱቦው ከተዘጋ ደግሞ እርግዝና እንዳይከሰት ማድረግ እና መካንነትን ማስከተል
በቱቦው ኢንፌክሽን ምክንያት ከማህፀን ውጭ ለሚፈጠር እርግዝና መጋለጥ (Ectopic pregnancy)

☘️ በማህፀንና ዙሪያው አካባቢ በኢንፌክሽኑ ምክንያት መጠባበቅን መፍጠር (adhesion) ይህም ለብዙ ጊዜ የሚቆይ የጀርባና ዳሌ አካባቢ ከፍረኛ የሆነ ህመም፤ በተጨማሪም በግንኙነት ጊዜ ህመም መሰማት

¶እንዴት እንከላከለው?

☘️ በወር አበባ ጊዜ ንፅህና መጠበቂያ ሞዴሶችን በተቻለ አቅም ቶሎ ቶሎ ሳይሞላ መቀየር

☘️ እንቅስቃሴ ወይም ስፓርት ካደረግሽ በውሀላ የውስጥ ልብስሽን መቀየር

☘️ በተቻለ አቅም በወር አበባ ጊዜ የግብረ ስጋ ግንኙነት አለማድረግ

☘️ ማህፀን ውስጥ ሳሙና ወይም ውሀ አስገብቶ አለመታጠብ

☘️ በተለምዶ የሚባሉ “በጨው ታጠቢው” የሚባል ምክሮችን ህመሙ እንዳይድን እና በተለይ ወደላይኛው የማህፀን ክፍል ዘልቆ እንዲገባ ስለሚያደርግ ከዚህ አይነት ድርጊት መቆጠብ

☘️ ከብዙ ወንዶች ጋር የሚደረግ ልቅ ከሆነ የግብረ ስጋ ግንኙነት መቆጠብ ፤ በብልት ውስጥ የሚገቡ የተለያዩ የወሲብ ቁሳቁሶችን አለመጠቀም፤

☘️ በግንኙነት ጊዜ ኮንዶም መጠቀም

☘️ እንደዚህ አይነት ከማህፀን የሚወጣ ፈሳሽ ወይንም ማሳከክ ካለ ይድናል እስኪልየው ሳይሉ ወደጤና ተቋም በመሄድ ህክምና ማግኘት።

☘️ ጤናው በተጠበቀ ቦታ የወሊድ አገልግሎት ማግኘት

☘️ ጤናው በተጠበቀ ቦታ የውርጃ አገልግሎት መፈፀም

¶ገና የህመሙ ምልክት ሲታይሽ ወደ ጤና ተቋም ከሄድሽ ቀላል የሆኑ የደም፣ የሽንት እና የማህፀን ምርመራዎች እና ተጨማሪ የአባላዘር ምርመራ ተደርጎልሽ በቀላሉ ህክምናው ሊሰጥሽና ከፍተኛ ከሆኑ የማህፀን አደጋዎች ሳይከሰትብሽ ወደ ቀድሞው የጤና አቋምሽ መመለስ ትችያለሽ።
👍2
ሾተላይ (Rh-isoimmunization)

💥 ሾተላይ የሚባለው በሽታ ከሁለተኛ ጀምሮ የሚወለዱ ህፃናትን የሚያጠቃ በሽታ ሲሆን ይህም በእናትና በፅንሱ መሀከል የደም አይነት አለመጣጣም(Rh incompatability) ምክንያት የሚከሰት ነው።

💥 ሾተላይ የሚከሰተዉ የሴቲቱ የደም አይነት Rh negative ፣ የባል የደም አይነት Rh positive እና የፅንሱ ደግሞ Rh positive ከሆነ ሲሆን በተጨማሪም በተለያዩ ምክንያቶች Rh positive ደም ወደ ሴቲቱ ደም ከገባ ወይም ከወሰደች ነው።


💥 ሚስት Rh negative መሆን ይኖርባታል እና ፅንሱ Rh positive መሆን ይኖርበታል
💥 ባል Rh negative ከሆነ ሾተላይ አይከሰትም

¶ሾተላይ ለምን ይከሰታል?

👉 የሰው ልጅ ከወላጆቹ ዘረመል ተነስቶ ከ4 የደም አይነቶች ውስጥ አንዱን ሊይዝ ይችላል። እነኝህም
1. “A”
2. “B”
3. “AB”
4. “O” ተብለው ይጠራሉ።

👉 በሰውነት ውስጥ የሚገኙ ቀይ የደም ህዋሶች(RBCs) የላይኛው ሽፋናቸው ላይ Rh የተባለ ፕሮቲን (protein) ካላቸው ሴቲቱ Rh positive ናት ማለት ሲሆን እነኚህ ፕሮቲኖች ከሌሉ ደግሞ Rh negative ናት ማለት ነው።

ለምሳሌ:- ሴቲቱ የደም አይነቷ B ቢሆንና ቀይ የደም ሴሎቿ ላይ Rh ፕሮቲን ካለ B Positive ናት ማለት ነው፤ እነኚህ Rh ፕሮቲኖች ከሌሉ ደግሞ B Negative ናት ይባላል።

👉 አንዲት ሴት ሾተላይ የሚባለው ችግር ሊከሰትባት የሚችለው እሷ Rh negative ሆና በተለያዩ አጋጣሚዎች Rh positive የሆነ ደም ወደሰውነቷ ሲገባ ሰውነቷ እነኚህን Rh positive የደም አይነቶች የሚያጠፉ(የሚገሉ) ንጥረ ነገሮች (Antibodies) ሲያመነጭ (ሲያመርት) ነው። እነኚህም እስከ እድሜልክ በሰውነቷ ይቆያሉ።

👉 እነኚህ የተመረቱት ተከላካይ ንጥረ ነገሮች(Antibodies) የመጀመሪያው ልጅ ላይ ምንም ተፅዓኖ ሳይኖራቸው ልጁ በሰላም ሊወለድ ይችላል ነገር ግን የሁለተኛው ፅንስ የደም አይነቱ Rh positive ከሆነ ወደ ፅንሱ በማለፍ የፅንሱን Rh positive የቀይ የደም ህዋሶች ያጠቃሉ ማለት ነው፤ ይህም ፅንሱን ለተለያየ አደጋዎች ሊያጋልጠው ይችላል።

👉 ይህም ችግር ፅንሱ ላይ የተለያዩ ጉዳቶችን ሊያመጣ ይችላል ፤ እነኚህም

☘️ በፅንሱ የተለያዩ የአካል ክፍሎች ውሀ መቋጠር - Fetal hydrops
☘️ በተደጋጋሚ የፅንስ መውረድ - Miscarriage
☘️ የፅንሱ የደም ማነስ - Fetal anemia
☘️ ፅንሱ በማህፀን ውስጥ እንዳለ ጊዜው ሳይደርስ ህይወቱ ማለፍ
☘️ ህፃኑ ከተወለደ በውሃላ ቆዳው ቢጫ መሆን እና የጨረር ህክምና ማስፈለግ(phototherapy)
☘️ በከፍተኛ ደም ማነስ ምክንያት ደም ለመውሰድ መጋለጥ

¶ሾተላይ እንዴት ይታከማል?

👉 Rh negative የሆነችው እናት ከዚህ ቀጥሎ የተዘረዘሩት ነገሮች ከገጠሟት
☘️ ባለቤቷ Rh positive ከሆነ
☘️ ውርጃ ካጋጠማት
☘️ ከማህፀን ውጭ እርግዝና ካጋጠማት
☘️ ከእንግዴ ልጅ ላይ የሚነሳ እጢ(Gestation trophoblastic disease) ካጋጠማት
☘️ በእርግዝና ወቅት አደጋ ከደረሰባት፤
☘️ በክትትል ወቅት ከእንግዴ ልጅ ወይም ከሽርት ዉሃ በመሳሪያ ናሙና ከተወሰደ

👉👉 Anti D የተባለ ኢሚውኖግሎቡሊን (immunoglobulin) መድሀኒት በመውሰድ ሾተላይን መከላከል ይቻላል።

☘️ በእርግዝና ጊዜ Anti D የተባለውን መድሃኒትን በ 7 ወር(28 ሳምንት) ላይ እና ህፃኑ በተወለደ ቢቻል እስከ 72 ሰዓት ውስጥ በመስጠት የሾተላይ በሽታን መከላከል ይቻላል።

👉 Rh negative የሆነች እናት(ባል Rh positive) የእርግዝና ክትትሏ ከሌሎች እናቶች ለየት ያለ እና የሚሰጣትም ቀጠሮ በዛ ያለ ይሆናል።

👉 ይህም በልጇ ላይ ሊከሰቱ የሚችሉትን የሰውነት ውሀ መቋጠር(መጠራቀም) እና የፅንሱ ደም ማነስ ካለ ቀድሞ በማወቅ ህክምናውን በቶሎ ዘመኑ በደረሰበት ቴክኖሎጂ እዛው ማህፀን ውስጥ እንዳለ ደም በመለገስ እና ወቶ ለመኖር ብቁ በሆነበት ጊዜ ቀድሞ እንዲወለድ በማድረግ ተጨማሪ የሆኑ የህክምና እርዳታዎች እንዲደረግለት ማድረግ ይቻላል።
👏2👍1
መካንነት(Infertility)
ትዳር ከመሰረትን 8 አመታት አሰቆጠርን። ልጅ ለመውለድ እስከ አሁን ድረስ ብንሞክርም አልተሳካልንም። ችግሩ ከእኔ ነው ወይስ ከባለቤቴ" የሚል ጥያቄ አንድ ታካሚ አንስቶልኝ ነበር።

ስንቶቻችን ነን መካንነት (infertility) መፍትሄ ሊኖረው እንደሚችል ምናቀው?

መካንነት (Infertility)ምንድን ነው?

-መካንነት የምንለው ጥንዶች አብረው እየኖሩ ምንም አይነት የወሊድ መቆጣጠሪያ ሳይጠቀሙ ለአንድ አመት ልጅ ለመዉለድ ሞክረው ካልቻሉ ነው።

-መካንነት በተለየ መልኩ በታዳጊ ሀገሮች ይስተዋላል።

-እንደ የአለም የጤና ድርጅት (WHO) አገላለፅ ወደ 50 ሚሊዮን ጥንዶች በአለም አቀፍ ደረጃ ተጠቂ ናቸው።

በማን ችግር ምክንያት ሊፈጠር ይችላል?

-የመካንነት ችግር ብዙዎች የሚያስቡት በሴቷ ችግር ብቻ እንደሆነ ነው። ነገር ግን በእርስዎም ፣ ወይም በትዳር አጋርዎ ምክንያት ሊፈጠር ይችላል።

አይነቶቹስ?
1. አንደኛ ጀረጃ መካንነት (primary infertility) የምንለው ጥንዶች የግብረስጋ ግንኙነት ማድረግ ከጀመሩበት ጊዜ ጀምሮ አንድም ጊዜ ቢሆን ፅንስ መፍጠር ሳይችሉ ሲቀር ነው።

2.ሁለተኛ ደረጃ መካንነት (secondary infertility) የምንለው ከጊዜ በዃላ የሚከሰት ሲሆን ከዚህ በፊት ፅንስ መፍጠር ችለው በተለያየ ምክንያት ከዛ በዃላ ድጋሚ መፀነስ (መውለድ) ካልቻሉ ነው።

ምክንያቶቹስ?
-በሴት ምክንያት ፣ በወንድ ምክንያት ፣ በወንድም በሴትም ተጨባጭ የሆነ ምክንያት ያልተገኘላቸው ብለን ማየት እንችላለን።

1.በሴቶች ምክንያት ከሆነ ለምሳሌ በእድሜ መጨመር ምክንያት በተለይ ከ35 አመት በላይ እድሜ ፣ የማህፀን ቱቦ ኢንፌክሽን ፣ የማህፀን ቱቦ መጥበብ (መዘጋት) ፣ የማህፀን ጠባሳ ፣ የማህፀን አፈጣጠር ችግር ፣ ከእንቁላል ጋር የተያያዘ ችግር (polycystic ovarian syndrome) ፣ የሴቷ እንቁላል በቂ አለመሆን ፣ የሳንባ ነቀርሳ ፣ የማህፀን እጢ፣የአልኮል መጠጥ ፣ ሲጋራ ማጨስ ፣ አላሰፈላጊ ውፍረት ፣ ያልታከመ እና በተደጋጋሚ የሚከሰት የአባላዘር በሽታ ፣ የሆድ እና የመራቢያ አካል ቀዶ ጥገና እንደ ምክንያትነት ይጠቀሳሉ።

2.በወንድ ምክንያት ከሆነ ለምሳሌ የዘር ፍሬ መተላለፊያ መዘጋት ፣ በቂ የሆነ የዘር ፍሬ ህዋስ አለመኖር ፣ የሆርሞን መዛባት ፣ ሲጋራ ማጨስ ፣ አልኮል መጠጥ ፣ አላስፈላጊ ውፍረት ፣ አላስፈላጊ ጭንቀት ፣ የወንድ የዘር ህዋስ (sperm cell) አለመኖር ወይም ማነስ ፣ የሳንባ ነቀርሳ ፣ ኢነፌክሽን ፣ የአባላዘር በሽታ እንዲሁም በአደጋ ምክንያት ሊከሰት ይችላል።

3.በወንድም በሴትም ተጨባጭ የሆነ ምክንያት ያልተገኘላቸው (unexplained infertility) ሊኖር ይችላል።

ምርመራዎቹስ?
- ሀኪምዎት ተገቢውን ታሪክ ከወሰደ እና አካላዊ ምርመራ ካደረገልዎት በዃላ የተለያዩ ምርመራዎች ለምሳሌ ለወንዱም ለሴትም የተለያዩ የደም፣ የሽንት ምርመራ ከዛም ለወንድ የዘር ፈሳሽ ምርመራ (Semen analysis) ይታያል ከዛም አንደ አሰፈላጊነቱ karyotyping ፣ የሆርሞን ምርመራ (FSH, LH, PRL, testesterone)፣ x ray ፣ የሆድ ወይም የዘር ፍሬ አልትራሳውንድ ፣ CT scan
ለሴት ደግሞ HSG ፣ office hysterocopy ፣ የሆድ እና የመራቢያ አካል አልትራሳውንድ ፣ Endometrial biopsy ሊታዘዝ ይችላል።

በማህበረሰባችን የተሳሳቱ አመለካከቶች እና ተያያዥ ጉዳቶችስ ምንድን ናቸው?

-ልጅ ካልተወለደ ትዳር እንደማይባል ተደርጎ ማሰብ
-መካንነት ሲነሳ የሴቷ ችግር ብቻ እንደሆነ ማሰብ
-በማህበረሰባችን ውስጥ ህክምና ወይም መፍትሄ እንደሌለው ተደርጎ ማሰብ እና የግንዛቤ ማነስ

-ተያያዥ ጉዳቶች ለምሳሌ ስነልቦናዊ፣ማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ችግር ያስከትላል።ለምሳሌ በጥነዶች መሀል የጥፋተኝነት ስሜት፣ራስን መውቀስ፣ እስከ ፍቺ የመድረስ ሁኔታ ይስተዋላል።

መፍትሄዎቹስ?

-የወር አበባ ኡደትን ጠብቆ የማይመጣ ከሆነ ባለሙያ በማማከር ማስተካከል
-የሰውነት ክብደትን ማስተካከል
-ሲገራ ፣ አልኮል መጠጥ ማቆም
-ጭንቀት መቀነስ

-ስኳር በሽታ ያለባቸው ሰዎች የደም ስኳር መጠን መቆጣጠር
-በወንዱም በሴቱም ግልፅ የሆኑ የተረጋገጡ ምክንያቶች ካሉ ማከም፣ቀዶ ጥገና

-በቴክኖሎጂ የታገዘ ከማህፀን ውጪ የመካንነት ህክምና (IVF) ይህም ከሴቷ እንቁላል ፣ ከወንዱ የዘር ፈሳሽ ተወስዶ በቤተ ሙከራ ውስጥ ፅንስ እንዲፈጠር የማድረግ ህክምና ነው። የተፈጠረውን ፅንስ በሴቷ ማህፀን ውስጥ ይከተትና እንደ ማንኛውም እርግዝና ፅንሱን ተሸክማ ጊዜው ሲደርስ የምትወልድበት ህክምና ነው።

-የመሀፀን ኪራይ (Serrogacy) ይህ ህክምና በህጋዊ ስምምነት ፅንስ በሌላ ሰው ማህፀን ውስጥ እንዲያድግ ይደረግ እና ከተወለደ በዃላ የልጅ ባለቤት መሆን ማለት ነው።

-እኛ ሀገር ላይ ህክምናው በተወሰኑ የህክምና ቦታዎች ላይ በመሰጠት ላይ ይገኛል።

-ሌላዉ የመጨረሻ አማራጭ በማደጎ ልጅ ማሳደግ (Adoption) ነው።
👍3❤2
https://spinformoney.com/7725543497316988 spinformoney - Super spins, earn money with just one click every day
👍1
The owner of this channel has been inactive for the last 5 months. If they remain inactive for the next 18 days, they may lose their account and admin rights in this channel. The contents of the channel will remain accessible for all users.