በሮም የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ኤምባሲ የዘንድሮን የአረንጓዴ አሻራ ንቅናቄ በመቀላቀል ሰራተኞችን እና የኢትዮጵያ ዲያስፖራ አባላትን ያካተተ የችግኝ ተከላ መርሀ-ግብር ለምግብነት የሚወሉ ፍራፍሬዎችን በመትከል ተካሄደ
=============================
(ሐምሌ 03 ቀን 2017 ዓ.ም)፡ "በመትከል ማንሰራራት" በሚል መሪ ቃል ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ ያስጀመሩትን የዘንድሮውን የአረንጓዴ አሻራ ፕሮግራምን መነሻ በማድረግ በሮም የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ኤምባሲ ባልደረቦች እና የዲያስፖራ አባላት በጋራ በኤምባሲው መኖሪያ ቤት የችግኝ ተከላ አካሂደዋል::
በአገራችን የአረንጓዴ አሻራ ፕሮግራም ይፋ ከሆነበት ጊዜ አንስቶ የኤምባሲው አባላት መርሀግብሩን በመቀላቀል በየአመቱ የችግኝ ተካላ በማካሄድ የሚገኙ ሲሆን የዘንድሮውን የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር ምክንያት በማድርግ በሀገራችን ድጋፍ ለሚያስፈልጋቸው ወገኖች እንዲውል የገንዘ ድጋፍ ተሰባስቧል።
እየተካሄደ ያለው የአረንጓዴ ልማት ሀገራችን በምግብ ራሷን በማስቻል ኢኮኖሚያዊ ዕድገቷን ከማፋጠኑም በተጨማሪ በአለም አቀፍ ደረጃ የካርቦን ልቀትን ለመቀነስ ለሚካሄደው ጥረት ትልቅ አበርክቶ ያለው ነው።

👍7👎1
Channelling the change በሚል መሪ ቃል በክሮሺያ እየተካሄደ ባለው የDubrovnik 2025 ፎረም በኢትዮጵያ በኩል ተሳትፎ ተደረገ፣
===============
(ነሃሴ 4 ቀን 2017 ዓ.ም) “Channelling the change” በሚል መሪ ቃል በክሮዚያ እየተካሄደ ባለው የDubrovnik 2025 ፎረም በኢትዮጵያ በኩል ተሳትፎ ተደርጓል። ፎረሙ በጂኦፖለቲካዊ ለውጦች እና ለተሻለ ዓለም አቀፍ የትብብር መንገዶች ላይ ለመመከር የተለያዩ አገራት አመራሮች፣ የፖሊሲ አማካሪዎች እና ኤክስፐርቶችን ያሳተፈ ነው።
በዚህም አምባሳደር ሲራጅ ረሺድ ኢትዮጵያን ወክለው “African’s progress with the global reshuffle” በሚል ርዕስ በተዘጋጀ የፓናል ውይይት መድረክ ላይ ተሳትፎ አድረገዋል። በውይይቱም የአፍሪካ አንድነት እያደገ የመጣውን የዓለም አቀፋ የሃይል አስተላለፍ ለመቋቋም ያለውን ጠቀሜታ አጽንኦት ሰጥተው አንስተዋል። ኢትዮጵያ ቀጣናዊ ውህደትን እና የአፍሪካን አንድነት በማጠናከር ረገድ ያላትን ሚና በማሳየት አህጉሪቱ በአለም አቀፍ መድረክ ያላትን ተፅእኖ ለማሳደግ የኢኮኖሚ ትስስር ወሳኝ መሆኑን አስረድተዋል።

👍20🙏13😁5👎1
በጣሊያን በሪሚኒ ከተማ አየተካሄደ በሚገኘው SIGEP World የቡና ኤክስፖ ላይ የኢትዮጵያን ቡና በአውሮፓ ገበያ ላይ ለማስፋፋት እየተከናወነ ያለው ስራ ተጠናክሮ ቀጥሏል።
===========================
(ጥር 8 ቀን 2018 ዓ.ም) እ.ኤ.አ. ጃኗዋሪ 16-20 በጣሊያን ሪሚኒ ከተማ የእየተካሄደ በሚገኘው SIGEP - World Expo ላይ የኢትዮጵያ ቡና መህበራት ምርታቸውን ይዘው እየተሳተፉ ይገኛሉ። በኤክስፖው ኢትዮጵያን ወክለው የተሳተፉት መህበራት የኦሮሚያ ቡና ገበሬዎች ህብረት ስራ ማህበር፣ የሊሙ ኢናራ ገበሬዎች ሁለገብ የህብረት ስራ ማህበር፣ የሆማ ሁለገብ የገበሬዎች ህብረት ስራ ማህበር አና የጅማ ገበሬዎች ሁለገብ የግብርና ህብረት ስራ ማህበር ናቸው።
በወቅቱም የጣሊያን የንግድ ኤጀንሲ (ITA) ዳይሬክተር ሚስተር ሎሬንዞ የኢትዮጵያ የቡና ማህበራት ምርታቸውን በአቀረቡበት ስፍራ (ቡዝ) የጎበኙ ሲሆን፣ በወቅቱም ክብርት አምባሳደር ደሚቱ ሃምቢሳ ከዳይሬክተር ጄኔራሉ ጋር ሰፊ ውይይት አድርገዋል።
በውይይቱም ክብርት አምባሳደር በኢትዮጵያና በጣልያን መካከል ያለውን የንግድ ግንኙነት የበለጠ ለማሳደግ እና በተለይም በቡና ዘርፍ በጣሊያን በኩል እየተደረገ ያለውን ድጋፍ አመስግነዋል። በተያያዘም ዳይሬክተር ጄኔራሉ ባደረጉት የቡና ቅምሻ ስነ-ሥርዓት ላይ ለኢትዮጵያ ቡና ያላቸውን አድናቆት ገልጸዋል።
በኤክስፖው እየተሳተፉ ያሉ የኢትዮጵያ ቡና ላኪዎችና አንጋፋ የጣሊያን ቡና ግዢ ኩባንያዎች መካከል አዳድስ የገበያ ትስስሮች እንዲፈጠሩ የማድረግ ስራ በተጠናከረ መልኩ ቀጥሏል።

👍19😁2👎1👏1
በሮም የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ኤምባሲ የ130ኛው የአድዋ ድል በዓል በድምቀት ተከበረ።
=========
(የካቲት 22 ቀን 2018 ዓ.ም) በሮም የኢፌ.ዲ.ሪ ኤምባሲ የ130ኛው የአድዋ ድል በዓል “የዓድዋ እሴት ለሁለንተናዊ ሀገራዊ ማንሰራራት” በሚል መሪ ቃል የካቲት 22 ቀን 2018 ዓ.ም በድምቀት ተከብሯል።
በእለቱ በጣሊያን የኢ.ፌ.ዲ.ሪ. ባለሙሉ ባለስልጣን አምባሳደር ክብርት ደሚቱ ሀምቢሳ በፕሮግራሙ መክፈቻ ላይ ባደረጉት ንግግር የዓድዋ ድል ለኢትዮጵያውያን የታሪክ ማስታወሻ ብቻ ሳይሆን ኢትዮጵያዊያን ለነፃነታችን ያሳየነው ወደር የለሽ ፅናት ለዓለም ያበሰርንበትና ለብሔራዊ ክብራችን ያለንን ቀናኢነት ያስመሰከርንበት ዘመን ተሻጋሪ እሴታችን መሆኑንገልፀው የዛሬው ትውልድ ከዚህ ታሪክ በመማር አንድነታችንን በሚያጠናክሩ ጉዳዮች ላይ እንዲሳተፉ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል::
የዓድዋ ድል በሚመለከት ፅሁፍ ቀርቦ በይነ መረብ በታደሙ ታሳታፊያን ጭምር ውይይት ተደርጎበታል፣ የፕሮግራሙ ታዳሚዎችም በሚደረገው የልማት ጉዞ በጋራ በመንቀሳቀስ አስተዋጽኦቸውን አጠናክረው እንደሚቀጥሉ ቁርጠኝነታቸውን አረጋግጠዋል፣ በመጨረሻም ለበዓሉ የተዘጋጀውን ኬክ በመቁረስ በድምቀት ተከብሯል።

👍18🙏6👎2👏1