የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) መልእክት
ዛሬ፣ የቀጨኔ–አምባሳደር–ጊዮን-ኢሬቻ–ባምቢስ የወንዝ ዳርቻ ልማትን መርቀን ለአገልግሎት አብቅተናል፤ ይህ የ351 ሄክታር አጠቃላይ ስፋት እና የ10 ኪ.ሜ ርዝማኔ ያለውን የኮሪደር ልማት ዘመናዊ፣ አረንጓዴ እና ሁሉንም አካታች የሆነች አዲስ አበባን የመገንባት ራዕያችንን እውን የሚያደርግ ትልቅ ፕሮጀክት ነው።
የእግረኛ መንገዶችን፣ የብስክሌት መንገዶችን እና የተቀናጁ የትራንስፖርት መሠረተ ልማቶችን ያካተተ በመሆኑ፣ ይህ ልማት ይበልጥ ተደራሽ እና ለኑሮ ተስማሚ የሆነ የከተማ ከባቢን ይፈጥራል። የልጆች መጫወቻ ስፍራዎች፣ ፕላዛዎችና አምፊ ቲያትሮች፣ የስፖርት ማዘውተሪያዎች፣ እንዲሁም የውሃ ትርዒት ማሳያዎች ለመዝናኛና ማህበራዊ ግንኙነት አዳዲስ ዕድሎችን ያበረክታሉ። የመኪና ማቆሚያ ስፍራዎች እና ከ100 በላይ መኪኖችን በአንድ ጊዜ መሙላት የሚያስችሉ ስምንት የኤሌክትሪክ መኪና መሙያ ማዕከላት የዘመናዊ መሠረተ ልማቱን አቅም ይበልጥ ያጠናክራሉ። በወንዝ አስተዳደር፣ በአፈርና ውሃ ጥበቃ፣ እንዲሁም በወንዝ ዳርቻ አረንጓዴ ስፍራዎች አማካኝነት የአካባቢ ጥበቃን ከከተማ ገፅታ ለውጥ ጋር እያቀናጀን እንገኛለን።
በተመሳሳይ መልኩ ይህ ልዩ የኮሪደር ልማት አዳዲስ የኢኮኖሚ ዕድሎችን መፍጠር ያስቻለ ነው። የተዘጋጀው የገበያ ማዕከል ቀደም ሲል በወንዝ ዳርቻው አካባቢ ይኖሩ ለነበሩ ነዋሪዎች የዕደ ጥበብ ምርቶችን እንዲያመርቱ፣ ለማሳያና ለመሸጫ እንዲጠቀሙበት የሚያስችል ሲሆን፣ የግብርና ምርት መሸጫ ማዕከ ደግሞ የግብርና አምራቾችን ከገበያው ጋር ያገናኛል።
የእኛ ርዕይ ለዛሬውና ለሚቀጥሉት ትውልዶች ውብ ብቻ ሳትሆን ምርታማና ሁሉንም አካታች እንዲሁም ህዝቧን የምትመጥን ከተማ መገንባት ነው!

❤1👍1
የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ መልእክት
ዛሬ የእንጦጦ ፒኮክ የወንዝ ዳርቻ ልማት አካል የሆነው፣ ከቀጨኔ በአምባሳደርና በኢሬቻ እስከ ባምቢስ የተዘረጋው የወንዝ ዳርቻ ልማት ፕሮጀክት በጠቅላይ ሚኒስትራችን ተመርቆ ለሕዝብ ክፍት ሆኗል።
ይህ ታላቅ ልማት የአዲስ አበባን ውበት፣ የነዋሪዎቿን የኑሮ ጥራት፣ የከተማዋን የቱሪዝም መዳረሻነትና የኢኮኖሚ እንቅስቃሴ የሚያሳድግ ወሳኝ ሥራ ነው።
የወንዝ ዳርቻዎቻችንን ከብክለት፣ ከተፈጥሮ መራቆትና ከአደጋ ተጋላጭነት በማውጣት፣ ለአረንጓዴ ልማት፣ ለመዝናኛ፣ ለስፖርት፣ ለንግድና ለማኅበራዊ ትስስር ምቹ ስፍራዎችን እየፈጠርን ነው። ይህ ሥራ የወንዞቻችንን ተፈጥሯዊ ይዘት ከመመለስ ባለፈ፣ ከተማችንን ለነዋሪዎቿ የበለጠ ምቹ፣ ማራኪና ለኑሮ የተሻለች እያደረጋት ነው።
የፕሮጀክቱ ዋና ዋና ውጤቶች
ከቀጨኔ በአምባሳደርና በኢሬቻ እስከ ባምቢስ የተዘረጋው ይህ ፕሮጀክት 351 ሄክታር ስፋትና 10 ኪሎ ሜትር ርዝመት የሚሸፍን ሲሆን፣ የተለያዩ ዘመናዊ መሠረተ ልማቶችንና የሕዝብ መገልገያዎችን አካትቷል።https://www.ena.et/web/amh/w/amh_9809852

👍1👏1