ግዮን አማራ / GION AMHARA
378 subscribers
141 photos
19 videos
65 links
Download Telegram
የተዋጊ መሀንዲስ አመራሩ ፋኖን ተቀላቀለ❗️

የአፄ አምደ ጽዮን ኮር ምኒሊክ ክፍለጦር ለተከታታይ ቀናት በሰራው ከፍተኛ የደሕንነት ስራ እራሱን "ልዩ ዘመቻ ኮማንዶ 104ኛ ክፍለጦር" ብሎ የሚጠራው  ሁለተኛ (2ኛ) ሻለቃ የተዋጊ መሀንዲስ አመራሩ ከነ ሙሉ ትጥቁ ጀግናው ሰራዊታችንን በሰላም ተቀላቅሏል።

የአማራ ፋኖ ሕዝባዊ ድርጅት (አፋሐድ) ሸዋ ጠቅላይ ግዛት ዕዝ አፄ አምደ ጽዮን ኮር የምኒሊክ ክፍለጦር ሰሞኑን በተለያዩ ሁለት ግንባሮች ማለትም በመንዝ ቀያ ወረዳ ዘመሮ ከተማ እና በእንሳሮና ዋዩ ወረዳ በበልበሊት ቀጠና በአገዛዙ ዙፋን አስጠባቂ ስብስብ ላይ ከፍተኛ ድል ከመቀዳጀቱም በተጨማሪ ከፍተኛ የከተማ ውስጥ የደሕንነት ስራ በመስራት የብርሀኑ ጁላን የሰራዊት ቁመና የሌለውን የዘራፊ ስብስብ እያፈራረሰው ይገኛል።

ዛሬ ነሐሴ 29 ቀን 2017ዓ.ም የእምየ ምኒሊክ ልጆችን የተቀላቀለው የተዋጊ መሀንዲስ አመራሩ በቀጣይ እሱ የሚመራው ሰራዊት ሙሉ በሙሉ ፈርሶ ፋኖን እንደሚቀላቀል የተናገረ ሲሆን እራሱንም ለዝሕ ውሳኔ ያበቃው በተቋሙ ውስጥ የሚታዩ ብሄር ተኮር የሆነ አድሏዊ አሰራሮች በተለይ በደቡብ እና በአማራ ብሔር ተወላጆች ላይ ያነጣጠረ ግፍና በደል እየተፈፀመ መሆኑን ለአፄ አምደ ጽዮን ኮር ሚዲያና ኮሙኒኬሽን ክፍል በሰጠው የስልክ ማብራሪያ አረጋግጧል።

ከነ ሙሉ ትጥቁ ፋኖን የተቀላቀለው የአገዛዙ ዙፋን አስጠባቂ የልዩ ዘመቻ ኮማንዶ 104 ኛ ክፍለጦር አባሉ:-
   ~ አንድ ዘመናዊ ጥርጥር ክላሽ (ሞረት ክላሽ)
   ~ 150 የክላሽ ጥይት
   ~ 5 ካዝና 
   ~ በርካታ ምስጥራዊ ዶክመንቶች እና
   ~ የደረት ትጥቅ ለምኒሊክ ክፍለጦር አስረክቧል።

ላለፉት 321 ቀናቶች ቆይታውን ከፋኖ ጋር ያደረገው በጥቅምት 20 ቀን 2017ዓ.ም ከተመሳሳይ የልዩ ዘመቻ ኮማንዶ 104ኛ ክፍለጦር በመውጣት የምኒሊክ ክፍለጦርን ተቀላቅሎ እስካሁኗ ሰዓት ድረስ እየታገለ ያለው የደቡብ ኢትዮጵያው ተወላጁ ዛሬ ፋኖን ለተቀላቀለው የአገዛዙ ወታደር አባል በሰላም ወጥቶ ፋኖን እንዲቀላቀል ትልቁን ሚና መወጣቱን በመግልፅ ለቀድሞ የትግል አጋሩና ለምኒሊክ ክፍለጦር የፋኖ አባላትና አመራሮች ላደረጉለት ደማቅ አቀባበል ታላቅ ምስጋናውን አቅርቧል።

በመጨረሻም የኮሩ ሚዲያና ኮሙኒኬሽን ክፍል "ወቅታዊ የአገዛዙ ሰራዊት ቁመና ምን ይመስላል?" በሚል ፋኖን ለተቀላቀለው የሰራዊቱ አባል ጥያቄ ያቀረበ ሲሆን በምላሹም "በተለይ ሰሞኑን በአገዛዙ ቤት ከፍተኛ ትርምስ እና መደናገጥ እንዲሁም አብዛኛው ሰራዊት ከሚቀርበው የትግል ጓዱ  በተናጠል ተቀምጦ እንዴት ተቋሙን ለቆ የሚጠፋበትን መንገድ ብቻ ነው የሚያወራው ሲል ይመልሳል።

ለዝሕ መደናገጥ ዋና ምክነያት የሆነው ደግሞ በዝሕ ሰዓት በሰራዊቱ ውስጥ "የአማራ ፋኖ አንድ ሆኗል!" የሚል አስደንጋጭ ነገር የሰራዊቱን ካምፕ አምሶታል በዝሕ የተነሳ በርካታ የሰራዊቱ አባላት ከነ ሙሉ ትጥቃቸው እየጠፉ ይገኛሉ ሲል በተቋሙ ውስጥ ያለውን አሁናዊ መረጃ አጋርቶናል።

   ════❁✿❁════

የአማራ ፋኖ ህዝባዊ ድርጅት ሸዋ ጠቅላይ ግዛት ዕዝ!!
❤4🙏1
Forwarded from 
የአርበኛ እስክንድር ነጋ የስራ ሃላፊነቶች በዝርዝር'

"በአንድ የፖለቲካዊ የትጥቅ ትግል እንቅስቃሴ ውስጥ የፖሊሲ እና ስትራቴጂ መምሪያ የድርጅቱ "አንጎል" ወይም አቅጣጫ ጠቋሚ ተደርጎ ይወሰዳል። ይህ መምሪያ የትግሉን የረጅም ጊዜ ግብና ያንን ግብ ለማሳካት የሚከተሉትን መንገዶች የመንደፍ ከፍተኛ ስልጣን አለው።

የዚህ መምሪያ ዋና ዋና ሚናዎች እና የስልጣን ወሰን እንደሚከተለው ይጠቃለላሉ፦
1. ርዕዮተ-ዓለማዊ አቅጣጫን መቅረጽ (Ideological Leadership)

መምሪያው ድርጅቱ ለምን እንደሚታገል፣ ጠላቱ ማን እንደሆነ እና በትግሉ መጨረሻ ምን ዓይነት ሥርዓት መገንባት እንደሚፈልግ ትርጓሜ ይሰጣል። ይህ ስልጣን በድርጅቱ ውስጥ ያሉ ሌሎች ክፍሎች (ወታደራዊ፣ የህዝብ ግንኙነት፣ ፋይናንስ) የሚመሩበትን መሰረታዊ መመሪያ ያወጣል።

2. ስትራቴጂያዊ እቅድ ማውጣት (Strategic Planning)
የትጥቅ ትግሉ ከየት ተነስቶ የት መድረስ እንዳለበት ደረጃዎችን (Phases) ይነድፋል። ለምሳሌ፦
* መቼ መከላከያ ላይ መሆን እንዳለበት።
* መቼ ማጥቃት እንደሚጀመር።
* ከሌሎች ሃይሎች ጋር የሚደረጉ ጥምረቶችን አይነት መወሰን።

3. የፖሊሲ ቀረጻ (Policy Formulation)
በትጥቅ ትግል ወቅት የሚያጋጥሙ ማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ጉዳዮች ላይ መመሪያ ያወጣል።

* የቁጥጥር ስር አካባቢዎች አስተዳደር ድርጅቱ በተቆጣጠራቸው አካባቢዎች ህዝቡን እንዴት እንደሚያስተዳድር፣ ግብር እንዴት እንደሚሰበስብ እና ፍትህ እንዴት እንደሚሰፍን ፖሊሲ ያወጣል።
* የውጭ ግንኙነት ፖሊሲ፦ ከጎረቤት ሀገራት እና ከአለም አቀፍ ማህበረሰብ ጋር የሚኖረውን ግንኙነት መርህ ያስቀምጣል።

4. የውሳኔ ሃሳብ ማመንጨት (Advisory Power)
ይህ መምሪያ ለድርጅቱ ከፍተኛ አመራሮች (ሊቀመንበሩ ወይም ስራ አስፈፃሚው) ውሳኔዎችን እንዲያሳልፉ መረጃዎችን የማሰባሰብ፣ የመተንተን እና የውሳኔ ሃሳቦችን የማቅረብ ስልጣን አለው። ይህም በትግሉ ውስጥ ስህተቶች እንዳይፈጠሩ የጥንቃቄ ስራዎችን ይሰራል::

ለድርጅቱ ያለው ቁልፍ ሚና
* አንድነትን መፍጠር፦ ሁሉም የድርጅቱ አባላት አንድ አይነት አላማ እና ግብ እንዲኖራቸው በማድረግ የውስጥ መከፋፈልን ይከላከላል።

* ሃብትን በአግባቡ መጠቀም፦ የትጥቅ ትግል ውስን ሃብት (ሰው፣ መሳሪያ፣ ገንዘብ) የሚጠይቅ በመሆኑ፣ ያንን ሃብት የትኛው ግብ ላይ ቢውል የተሻለ ውጤት እንደሚያመጣ ቅድሚያ የሚሰጣቸውን ነገሮች ይለያል።

* ተለዋዋጭ ሁኔታዎችን መተንበይ፦ በጦርነት ወይም በፖለቲካ ውስጥ የሚከሰቱ ድንገተኛ ለውጦችን (ለምሳሌ የመንግስት መቀየር ወይም የውጭ ጣልቃ ገብነት) አስቀድሞ በመገመት ለድርጅቱ አማራጭ መውጫ መንገዶችን ያዘጋጃል።

* የህዝብ ድጋፍን ማረጋገጥ፦ ትግሉ በህዝብ ዘንድ ተቀባይነት እንዲኖረው የሚያደርጉ ማራኪ ፖሊሲዎችን በመንደፍ የህዝብን ድጋፍ (Mass Mobilization) ያጠናክራል።

ባጠቃላይ፡ የፖሊሲ እና ስትራቴጂ መምሪያ ከሌለ የትጥቅ ትግሉ ግልጽ አቅጣጫ የሌለው፣ በስሜት የሚመራ እና በቀላሉ የሚፈርስ ሊሆን ይችላል።

በአንድ የፖለቲካዊ የትጥቅ ትግል ውስጥ በፖሊሲ እና ስትራቴጂ መምሪያ (ሲቪል/ፖለቲካዊ አመራር) እና በወታደራዊ ክንፉ መካከል ያለው ግንኙነት እጅግ ስስ እና ወሳኝ ነው። ይህ ግንኙነት በሳይንሳዊ አጠራሩ "Civil-Military Relations" ይባላል።

በስኬታማ የትጥቅ ትግሎች ውስጥ ያለው የግንኙነት መዋቅር የሚከተሉትን ዋና ዋና ነጥቦች ያካትታል

1. የፖለቲካ የበላይነት (Political Supremacy)
በትጥቅ ትግል መመሪያ ውስጥ "ጠመንጃ ፖለቲካን መምራት የለበትም፤ ፖለቲካ ጠመንጃውን መምራት አለበት" የሚለው መርህ ቀዳሚ ነው።

* ውሳኔ ሰጪነት ጦርነት መቼ እንደሚጀመር፣ መቼ እንደሚቆም እና መቼ ወደ ድርድር እንደሚገባ የሚወስነው የፖሊሲ እና ስትራቴጂ መምሪያው እንጂ ወታደራዊ አዛዦች አይደሉም።

* አላማ ወታደራዊ እርምጃዎች ሁሉ የፖለቲካ ግብን ለማሳካት የሚደረጉ መሳሪያዎች ብቻ ናቸው።

2. የስትራቴጂ እና የታክቲክ ልዩነት
በሁለቱ መካከል ግልጽ የሆነ የስራ ክፍፍል አለ
* የፖሊሲ መምሪያ (ስትራቴጂ)"ምን መደረግ አለበት? ለምንስ?" የሚለውን ይወስናል። ለምሳሌ "በዚህ አመት የጠላትን የኢኮኖሚ መሰረት ማዳከም አለብን" የሚል ስትራቴጂ ያወጣል።

* ወታደራዊ ክንፍ (ታክቲክ)"እንዴት መደረግ አለበት?" የሚለውን ይተገብራል። የፖሊሲ መምሪያው የሰጠውን ግብ ለመምታት የትኛው ጦር የት ቦታ መዋጋት እንዳለበት ዝርዝር ወታደራዊ እቅድ ያወጣል።

3. የፖለቲካ ኮሚሽነሮች ሚና (Political Commissioners)
በብዙ የትጥቅ ትግል መዋቅሮች ውስጥ የፖሊሲ መምሪያው የራሱን ተወካዮች (ፖለቲካዊ መኮንኖችን) በየክፍለ ጦሩ ውስጥ ይመድባል።

* ተልዕኮአቸው ተዋጊው ሰራዊት የድርጅቱን ፖሊሲና ስነ-ምግባር እየተከተለ መሆኑን ማረጋገጥ ነው።
* ጥቅሙ ወታደራዊ አዛዦች ከድርጅቱ አላማ ወጥተው የራሳቸውን አምባገነናዊ ስልጣን እንዳይገነቡ ይቆጣጠራሉ።

4. መረጃ እና ግብረ-መልስ (Feedback Loop)
ግንኙነቱ ወደ አንድ ወገን ብቻ የሚፈስ አይደለም
* መምሪያው ከወታደራዊ ክንፉ የሚመጣውን መረጃ (ለምሳሌ የጠላት ጥንካሬ፣ የሰራዊቱ ስሜት፣ የህዝብ ድጋፍ) መሰረት አድርጎ ፖሊሲዎቹን ይከልሳል።

* ወታደራዊ ክንፉም ያለ ፖሊሲ መምሪያው የገንዘብ፣ የትጥቅ እና የዲፕሎማሲ ድጋፍ መንቀሳቀስ አይችልም።
ግንኙነቱ ካልተጠበቀ ምን ይከሰታል?
ሁለቱ ክፍሎች ተናበው ካልሰሩ የሚከተሉት አደጋዎች ይፈጠራሉ
* ወታደራዊ መፈንቅለ መንግስት ወታደራዊ ክንፉ የፖለቲካ የበላይነቱን ጥሶ ስልጣን ለመያዝ ሊሞክር ይችላል።
* የአላማ መጥፋት ሰራዊቱ ለምን እንደሚዋጋ ካላወቀ እንደ ወንበዴ ቡድን ንብረት ማጥፋትና ህዝብን ማሰቃየት ሊጀምር ይችላል።

* ውጤት አልባ መስዋዕትነት ወታደራዊ ድል ቢገኝም፣ ያ ድል ወደ ፖለቲካዊ ትርፍ (ለምሳሌ ወደ ድርድር ወይም አስተዳደር) ካልተቀየረ ትግሉ ይከሽፋል።
ለማጠቃለል የፖሊሲ እና ስትራቴጂ መምሪያው "አንጎል" ሲሆን፣ ወታደራዊ ክንፉ ደግሞ ስራውን የሚያከናውነው "ጡንቻ" ነው። ጡንቻው ያለ አንጎል መሪነት አውዳሚ ነው፤ አንጎሉም ያለ ጡንቻው ረቂቅ ሃሳብ ብቻ ሆኖ ይቀራል።

https://t.me/AmharaFanoNationalMovement
❤4
Forwarded from 
ጥር 10 ቀን 2018 ዓ.ም
የከተራ እና ጥምቀት በዓልን አስመልክቶ ከአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ የተሰጠ መግለጫ

የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ ለመላው ኢትዮጵያዊያን እና የኦርቶዶክስ እምነት ተከታዮች እንኳን ለ2018 የከተራ እና ጥምቀት በዓል በሰላም አደረሳችሁ ይላል።

የድርጅታችንን መመስረት ተከትሎ ሰራዊታችን፣ መላው የአማራ ህዝብ፣ የዳያስፖራው ማህበረሰብ እና የትግሉ ደጋፊወች በከፍተኛ ስሜት እና ደስታ መቀበላቸውን ስናረጋግጥ ከፍተኛ ኩራት ይሰማናል። በአንድነታችን ከፍተኛ ልባዊ ደስታን የተጎናፀፈው ሰራዊት እና ህዝብ የድሉን ፅዋ ያነሳ ዘንድ የጠላትን አከርካሪ መስበር የሚችል ስልታዊ አመራር ለመስጠት መዘጋጅታችንን በዚህ አጋጣሚ እናረጋግጣለን።

የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ የሀገራችን ባህል እና ትውፊት እንዲጠበቅ እና ሁሉም ኢትዮጵያዊ ባህሉን እና እምነቱን በነፃነት የሚያራምድበት ሀገር እንዲኖረን የጀመረውን ፀረ አገዛዝ ተጋድሎ በአዲስ መንፈስ አጠናክሮ የሚቀጥል መሆኑንም በዚህ አጋጣሚ እንገልፃለን።

መላው ሰራዊታችን እና አመራሩ በተቆጣጠርናቸው አካባቢዎች ሁሉ በዓሉ በሰላም እንዲከበር ከህብረተሰቡ ጋር በትብብር እንድትሰሩ እናሳስባለን።

በድጋሚ መልካም የከተራ እና የጥምቀት በዓል!

የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ
❤1
Forwarded from 
የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ ፖሊት ቢሮ የመጀመሪያ ስብሰባውን አደረገ።

ጥር 09 ቀን 2018 ዓ. ም በይፋ መመስረቱ የተገለፀው የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ የፖሊት ቢሮ ጥር 12 ቀን 2018 ዓ.ም በተለያዩ አጀንዳወች ላይ ውይይት አድርጎ ውሳኔወችን አሳልፏል።

የድርጅቱ ስራ አመራር አባላት በተገኙበት በዚህ የውይይት መድረክ ላለፉት 30 ወራት በነበረው የትግል ሂደት በነበሩ የእርስ በእርስ ሽኩቻወች እና አለመግባባቶች እንዲሁም የአደረጃጀት ልዩነቶች ምክንያት ለተፈፀሙ ጥፋቶች የእርስ በእርስ የይቅርታ መርሀ ግብር በማከናወን ውይይቱ ተጀምሯል።

በፍፁም መተማመን እና ጓዳዊነት የተጀመረው ውይይትም የድርጅቱ ቀሪ የአመራር መዋቅር ስለሚዋቀሩበት ሁኔታ፣ የወለጋ ክፍለ ሀገር ፋኖ እዝ (ቢዛሞ) ያቀረበውን የአደረጃጀት ጥያቄ፣ የቀጠና እና የዕዝ ስያሜወችን በተመለከተ፤ የሰራዊት እና የነባር ዕዞችን ውህደት እንዲሁም የወታደራዊ እና ፖለቲካዊ ፍኖተ ካርታ ዝግጅትን በተመለከተ ሰፊ ውይይት አድርጎ የስራ መመሪያወችን ሰጥቷል።

የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ የሕዝብ ግንኙነት መምሪያ
https://www.facebook.com/profile.php?id=61586961050047
❤2
በሆዳቸው ወድቀው ለብልፅግና መገረድን  ምርጫቸው ያደረጉ (ትግሉን የከዱ ባንዳወችም፣ ቀድመው የፈረሙቱ የአብን ሰወችም ሆኑ ሌሎች ከህሊናቸዉ የተፋቱ የአብይ አማሮች) የሚግባቡበት የጋራ ቋንቋ አላቸው።  ፋኖን በተላላኪነት መፈረጅ።

ይህንን ነገር ደጋግመው የሚያጮሁት መደበቂያ ፍለጋ ነው። የዘር ማጥፋት ጦርነት ታውጆበት እየተጨፈጨፈ ያለን ህዝብ በመካዳቸው እርቃናቸውን ቆመዋል። ከሞራል፣ ከህሊና እና ከታሪክ ጥያቄወች የሚሸሸጉበት ዋሻ ፈልገዋል። ይህንን ዋሻ ያጡ ባንዳወች እና የተላላኪነት ምልክቶች ህይወቱን እየሰጠ ህዝቡን ከጥፋት በማዳን ላይ ያለን ታጋይ በማጠልሸት እና አቻ ፍለጋ ላይ በመሰማራት ራሳቸውን ሊያስደስቱ እየደከሙ ነው።
እነሱ እርቃናቸውን ስለቆሙ ከትግላችን አነሳስ እና ባህሪ ጋር በማይገናኝ መንገድ ፋኖን የሆነ አካል ይመራዋል ብሎ በመፈረጅ እንደነሱ ህሊናችን እንዲታረዝላቸው ይፈልጋሉ።

ፋኖ በታሪክ ፊት በክብር የሚያቆመዉን ፀረ- አገዛዝ ተጋድሎ እያደረገ ነው። መላላክ እና በራስ ህዝብ ላይ መቆመር የባንዳወች የህይወት መመሪያ ነው። ፋኖ የአማራን ህዝብ ከመጥፋት ለመታደግ ክቡር መስዋዕትነት የሚከፍል በዚህ ዘመን ካሉ ግዙፍ የነፃነት፣ የሰብአዊ መብት ታጋዮች ቀዳሚው ነው።

የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ የሚያስከትለው ወይም በጋራ የሚያሰልፈው እንጅ ለብልፅግና እንዳደሩቱ የሚገብርለት ወይም ጁኒየር የሚሆንለት አጋር የለዉም። በህልውናችን ላይ በመጣ ግዜ ህወሃትን ጨምሮ የትኛውንም አካል ለመዋጋት የሚቀድመን እንደሌለ ህዝባችን ጠንቅቆ ያውቃል። ይህንን ደግሞ ከአብይ ጉያ ስር ተወሽቀን ሳይሆን በራሳችን መንገድ ያደረግነው፣ ማድረግም የምንችለው እንደሆነ በተግባር አረጋግጠናል።

የህልዉና ጦርነት ውስጥ የከተተን የብልፅግና አገዛዝ ፕሮፖጋንዳም የውጊያ መስመርም ሊያዘጋጅልን አይችልም። በUAE ጀት እና ድሮን አማራን ለሚጨፈጭፈው አብይ አህመድ ስልጣን በፈቃደኝነት የሚፈስ የአማራ ደም አይኖርም። መስዋዕትነት የምንከፍለው አረመኔውን አገዛዝ በማስወገድ የህልውና ጥያቄያችንን በምሉዕነት ለማረጋገጥ ነው።

የአፍሪካ ቀንድ ሰላም የሚመጣው ብልፅግና ሲወገድ ብቻ ነው።

የአፋብን ሕዝብ ግንኙነት መምሪያ ኃላፊ አርበኛ አስረስ ማረ ዳምጤ
https://t.me/Gionamhara
የአማራ ህዝብ ማወቅ ያለበት ራያ አካባቢ ያለው ነባራዊ ሁኔታና እውነታ!

አላማጣ ከተማ ራያ አላማጣ እና ኮረም ዙሪያ የነበረው የፋሽስቱ አገዛዝ ብልፅግና መከላከያ ሰራዊት እና ፌደራል ፖሊስ ያለ ምንም የጥይት ተኩስ ጥር 21/2018 ዓ.ም አካባቢውን ለቆ ወጥቷል::

ፋሽስቱ የብልፅግና አገዛዝ ሚያዚያ 2016 ዓ.ም ራያ ላይ የነበረውን መዋቅር በሴራ አፍርሶ አካባቢውን አሳልፎ በመስጠት በኋላም የተወሰነ ሃይሉን የተለያዩ ቦታዎች ላይ በማስፈር አካባቢውን ከትግራይ ሃይሎች ጋር ይዞ መቆየቱ የሚታወቅ ነው::

ፋሽስቱ አገዛዝ ብልፅግና በተጠቀሱት የራያ አካባቢዎች ከሚያዚያ 2016 ዓ.ም ጀምሮ ከትግራይ ሃይሎች ጋር በጋራ ሰፍሮ ይኖር የነበረውን ሰራዊቱን ጥር 21/2018 ዓ.ም ያለ ምንም የጥይት ተኩስ ለቆ እንዲወጣ አድርጎ ቦታውን ሙሉ ለሙሉ ለትግራይ ሃይሎች አስረክቧል::

ከዚህ ጋር ተያይዞም አገዛዙ በዚህ መንገድ ለቆና አስረክቦ የወጣውን የራያ አካባቢዎች የሃሰት ፕሮፓጋንዳና ሴራ ሊሰራበት እንደተዘጋጀ መረጃው አለን:: ይህንን ካሁን በፊት እንዳደረገውና አሁንም እንደሚያደርግ ግን ለህዝብ የተደበቀ አይደለም::

ብልፅግና ይዞት የነበረውን የራያ መሬት በዚህ መንገድ ያስረከበ መሆኑ እየታወቀ ነገር ግን በክልሉ በሁሉም አካባቢዎች ህዝብ ላይ የተለመደ ፀረ ፋኖ የውሸት ፕሮፓጋንዳውን በመስራትና አዲስ የውጊያ አጀንዳ በመፍጠር ብሎም በፀረ-ህዝብና አገር አፍራሽ ሚዲያዎቹ በማስተጋባት ለአማራው ከእልቂት በስተቀር አንዳች መፍትሄ ወደሌለው ጦርነት በማስገባት እድሜውን ለማራዘም እየሰራ ይገኛል::

ከዚህ ጋር ተያይዞም ከደቡብ ወሎ ዞን የተለያዩ ወረዳዎች በሚሊሻ ስም የሰበሰበውን የአማራ ገበሬ እና አድማ ብተና ቀድሞ ወልድያ እና ራያ ቆቦ ዙሪያ ያሰፈረ ሲሆን ከሰሜን ወሎ ሚሊሻ ጋር በማድረግ በቀጣይ ከትግራይ ሃይሎች ጋር ሊያደርገው ባሰበው ጦርነት ከፊት ሊማግዳቸው ዝግጅቱን ጨርሷል::

*ማስታወሻ፦ አገዛዙ ባሁኑ ሰዓት ሰሜን ወሎ ዞን ባሉ ወረዳዎች የግል ታጣቂዎችን ሳይቀር ለጥር 22/2018 ዓ.ም አስቸኳይ ስብሰባ እየጠራ ይገኛል::

እየሆነ ያለው እውነታ ይሄው ነው::
አርበኛ ፋኖ አበበ ፈንታው
ጥር 21/2018 ዓ.ም
https://t.me/Gionamhara
❤3
የምዕራብ ትግራይ(ወልቃይት) ግንባር ውሎ መረጃ!

ጥር 20/05/2018 ዓ.ም በምስራቅ ፀለምቲ እና በምዕራብ ፀለምቲ የኦህዴድ መከላክያ ሰራዊት እና የትግራይ ሰራዊት (TDF) ውጊያ ሲደረጉ ውለዋል::

👉ኦህዴድ ያሰለፋቸው
1,የትግራይ ሰላም ሓይል (TPF) የሚባለው በብልፅግና በብርሓኑ ጁላ ስራዊት ስንቅ ትጥቅ ቀርቦለት የተደራጀው ሓይል ምዕራብ ትግራይ ሔዶ እንዲዋጋ በመታዘዙ ከፊት ሆኖ ብዙ መስዋዕትነት እየከፈለ ነው።

2, የተከዜ ዘብ:- ይሕም ሓይል አራት ኪሎ ባለው ኦህዴድ የተዋቀረ ሲሆን የወለጋ ተፈናቃዮችን ጨምሮ ከሰሜን ጎንደር በሰፈራ የመጡ ምዕራብ ትግራይ ላይ የእርሻ መሬት እና መሳሪያ ተስጥቶት ከትግራይ ጋር እንዲዋጋ የተፈጠረ ታጣቂ ነው። እዛ ባለው ውጊያም ከትግራይ ሰላም ሓይሎች ጋር አንድ ጥምር ጦር ፈጥሮ ከ TDF ጋር እየተዋጋ ይገኛል።

3, 3ተኛው የኦህዴድ ብልፅግና መከላክያ ስራዊት ነው።

1ኛ✅ በማይዳጉሳ ግንባር ፦

ማይዳጉሳ ግንባር ከትግራይ ኣርሚ 35 የተሳተፈ ሲሆን በአካባቢው የነበረው መከላከያ ሰራዊት እና የተከዜ ዘብ ክፋኛ ተመቶ ቦታውን ለቆ ሸሽቷል

2ኛ✅ እምባ-ማድረ እና ዲማ ምጫራይን ግንባር
ከትግራይ የአርሚ 17 ኮር 3ኛ 2ኛ ክ/ጦሮች በዚህ ቦታ ትናንት ከከሰአት ደርሰው ውጊያ ላይ የነበሩ ሲሆን ዛሬ ለሊቱን ቦታውን ተቆጣጥሮታል።

3ኛ✅ ደገብራይን ግንባር

ከትግርይ አርሚ 35 እና 42 እየተሳተፈ ሲሆን ከዛ የተከዜ ዘብና የሓራ መሬት ታጣቂዎች አሁንም ድረስ ውጊያ ላይ ናቸው

👉 በምዕራብ -ደቡብ ትግራይ ማለትም በዋልድብባ ዛሬማ...TDF በደደቢት አርጎ የትግራይ ጦር ዘልቆ ገብቷል።

👉ግዙፉ የትግራይ ሰራዊት ኣርሚ 33 መኾኒ መድረሱን ተከትሎ ኣላማጣ እና ኮረም ላይ ሆኖ የአካባቢውን ስድስት ወረዳዎች ሲያስተዳድር የነበረው የኦህዴድ መከላከያ ሰራዊት ወደ ቆቦ እና አፋር ሸሽቷል።

👉 ኦህዴድ የተማመነባቸው ድሮኖችን ተበታትኖ በመጓዝ አቅማቸውን ማዳከም ተችሏል።

👉ወደ ትግራይ በረራዎች ቆመዋል

👉ሻዕቢያ ጦሩን ወደ ቡሬ አፋር ሰሜን ምዕራብ ትግራይ ኣዲያቦ እና ሑመራ ከተማ አስጠግቷል።

👉ግጭቱ ወደ ሰሜን ወሎ እና አፋር የመስፋፋት እድሉ ሰፊ ነው

ተጨማሪ መረጃ እንደረሰን እናቀርባለን።
ድል ለጭቁን ሕዝቦች!
ውድቀት ለፋሽስቱ ኦህዴድ /ብልፅግና !!
https://t.me/Gionamhara
❤1
ሰበር....ብልፅግና "ስልታዊ ማፈግፈግ" የሚላትን ጨዋታ ጀመረ!
የብልፅግና መከላከያ ሰራዊት "ስልታዊ ማፈግፈግ" በሚል ስም አላማጣንና ኮረም ዙሪያን ለቆ በመሸሽ ላይ ነው።

አላማጣ እና ኮረም ዙሪያ የነበረው የሪፐብሊካን ጋርድና የኮማንዶ ክፍለጦር እንዲሁም መደበኛ ሰራዊቱን ጨምሮ የፌደራል ፖሊስ አባላት ከትናንት ጥር 20/2018 ዓ/ም ምሽት ጀምሮ ጨርቄን ማቄን ሳይሉ አከባቢውን ለቀው በመሸሽ ወደ ቆቦ ከተማ መግባታቸውን የመረብ ሚዲያ የምስራቅ ዐምሓራ ቀጠና ዘጋቢዎች ለማረጋገጥ ችለዋል።

ብልፅግና ከ2013 ዓ/ም ጀምሮ እስከ 2015 ዓ/ም መጀመሪያዎቹ ወራት ድረስ ከሕወሓት ጋር ባደረገው ጦርነት የአማራ ክልልን የመዋጊያ ሜዳው በማድረግ "በስልታዊ ማፈግፈግ" ስም ሕዝቡን ማስጨረሱንና ክልሉን ማውደሙ አይዘነጋም።

ከፋኖ ጋር በሚያደርገው ውጊያም የፋኖን ክንድ መቋቋም ሲያቅተው ከሚፈፅመው የዘቀደ ጥቃት የተረፉ ንፁኋኖችን ለመጨረስ ዛሬም "ስልታዊ ማፈግፈግ" የሚላትን ካርድ በድጋሚ መዟታል።

ብልፅግና በዛው ከሕወሓት ጋር ባደረገው ጦርነት ከባባድ መሣሪያዎችን ተተኳሽ እና ነዳጅ ካፍ እስከ ገደፋቸው እንደሞሉ ጥሎ በመሸሽ "ስልታዊ ማፈግፈግ" በሚል በአማራ ሕዝብ ላይ በሚሳለቅበት ወቅት፡ የአማራ ፋኖ እና የአማራ ልዩ ኃይል እንዲሁም በቀድሞው የአማራ አድማ ብተና እና ሚኒሻ ኃይሉ ባደረጉት ብርቱ ተጋድሎ ሕዝባቸውን ነፃ አውጥተዋል።

በርግጥ የኋላ የኋላ "በስልታዊ ማፈግፈግ" ስም በአማራ ሕዝብ ላይ እየተፈፀመ ያለው የክህደት ደባ የገባቸው ሀገር ወዳድ የመከላከያ ሰራዊት አባላት ከአማራ ሕዝብ ጎን ቆመው ውድ ሕይወታቸው ያለ ስስት እስከ መስጠት የደረሰ መስዋዕትነት በመክፈል ታሪክ የማይዘነጋው ታላቅ ተጋድሎ አድርገዋል።

በወቅቱ በአማራ ሕዝብ ላይ "በስልታዊ ማፈግፈግ" ስም እየተሰራ ያለውን ደባ ያጋለጡ ለአብነትም "ስልታዊ ማፈግፈግ እስከምን ድረስ ነው?" በሚል የሞገተው ጋዜጠኛ ጎበዜ ሲሳይ ዘገየን ጨምሮ ሌሎች የማሕበረሰብ አንቂዎች ከስራ ከመባረር ጀምሮ እስከ እስርና ድብደባ ድረስ ግፍ ተፈፅሞባቸዋል።

ገዢው የብልፅግና ቡድን በስልታዊ ማፈግፈግ ስም ከትግራይ ክልል ጀምሮ በአማራ ክልል ከራያ እስከ ወልድያና ደሴ እንዲሁም እስከ ሸዋ ጣርማበር ድረስ በማፈግፈግ የጦር ሜዳውን አማራ ክልል ላይ አድርጎ የአማራ ሕዝብ እንዲጨፈጨፍ፣ ክልሉ እንዲወድም እንዳደረገው ይታወቃል።

ብልፅግና ይችን ያረጀች ያፈጀት "ስልታዊ ማፈግፈግ" ብሎ የሚጠራት ጨዋታን ዛሬም ለመጫዎት በራያ ግንባር አሃዱ ብሎ ጀምሯል።

አገዛዙ ከዚህ ቀደም በኮረም ዙሪያ እና በአላማጣ አስፍሯቸው የነበሩ ከፌደራል ፖሊስ እስከ ሪፐብሊካን ጋርድና አየር ወለድ ኮማንዶ ክፍለጦሮች እንዲሁም መደበኛ እግረኛ ሰራዊቱን ከነ ሜካናይዝድ ክፍሉ ከትናንት ጥር 20/2018 ዓ/ም ምሽት ጀምሮ ጓዙን ጠቅልሎ ድንገት ሹልክ ብሎ መውጣቱን ጣቢያችን መረብ ሚዲያ ያለማረጋገጥ ችሏል።

በአሁን ሰዓት ቆቦ ከተማ ከአላማጣና ኮረም ሸሽተው በመጡ ወታደሮችና ሜካናይዝድ መሣሪያዎች ተጥለቅልቃለች።

ከፋኖ ጋር እየተካሄደ በሚገኘው ውጊያ አከርካሪው የተሰበረው መከላከያ ሰራዊቱ፡ ይህን በድል ሳይወጣ ሌላ አዲስ ጦርነት በመጀመሩ ለመማረክ እንኳን እድል እንደማያገኝ ስለተረዳ በተስፋ መቁረጥ ስሜት ተውጧል።

ብልፅግና ለምን አስወረርከን በሚል የራያ ማሕበረሰብ ጥያቄ ሲያነሳበትም "እንዳልከላከልላችሁ ፋኖ አጠቃኝ፡ የራሳችሁ ፋኖ ነው ያስወረራችሁ" በሚል የቂል መልስ እንደሚሰጥም ይጠበቃል።

በወልቃይትም እንዲሁ ነው።በአዴን ወብልፅግና በጋራ ሆነው ወልቃይትና ራያን ለዳግም ወረራ በማጋለጥ "ፋኖ ነው ያስወረራችሁ የሚል አጀንዳ ለማራገብ ዝግጅታቸውን ጨርሰዋል።

መረበኞች ነን መረጃ አጥማጆች!

የቴሌግራም ገፃችን👉https://t.me/Gionamhara
❤3
Forwarded from  (Mogesie Shiferaw)
የአገዛዙ ሰራዊት ንፁሃንን ከመግደልና በጅምላ ከመጨፍጨፍ ባለፈ በዚህ መልኩ የአርሶ አደሩን ንብረት እያወደመና እያቃጠለ ይገኛል::

ይህ የሆነው በምስራቅ ዕዝ የአገዛዙ ሰራዊት ሲሆን ቦታውም በጎጃም መተከል ጃዊ ወረዳ ከብተሊ ቀበሌ ነው::
የአብይ የጫካ ቤተመንግስት በሚሳኤል ተመታ❗️

የዘረ ፈጁ አብይ አህመድ መደበቂያ ሊሆን የታሰበው' የጫካ ቤተ መንግሥት ' በትናትናው ምሽት የሚሳኤል ጥቃት እንደደረሰበት ተሰምቷል።

የዛሬውን ማታ ጥቃት ጨምሮ በተከታታይ እየተፈፀሙ ባሉት መሰል ጥቃቶች ከፍተኛ ሽብርና መደናገጥ ውስጥ የገባው የብልፅግናው አገዛዝ የሌሊቱን ጥቃት ተከትሎ በከፍተኛ ደረጃ ውድመት ያስተናገደውን የኦህዴድ ብልፅግናው ቁንጮ አብይ አህመድ የጫካ ቤተ መንግስት በትልልቅ መሸፈኛወች በማጠር ውድመቱን ከህዝብ ዕይታ ለመሸፈን እየተጣጣሩ መሆኑ ተረጋግጧል።

ባሳለፍነው ሳምንት ጨምሮ በተከታታይ እየደረሰ ባለው የድሮን እና የሚሳኤል ጥቃቶች በደብረ ዘይት አየር ኃይል ዋና ማዘዣ ጣቢያ ጨምሮ ወታደራዊ ማዘዣ ጣቢያወችን ኢላማ ያደረጉ እንደነበር ይታወሳል።

(መስከረም 28 ቀን 2019 ዓ.ም)