ጤና፣ ደስታ እና አዲስ ትዝታ ሁሉም በአንድ ሩጫ!
ምዝገባ ነገ ይጀመራል
እንጦጦ ፓርክ ሲቢኢ ሩጫ
መስከረም 30 እንገናኝ!
#GreatEthiopianRun #EntotoParkCBERun
ምዝገባ ነገ ይጀመራል
እንጦጦ ፓርክ ሲቢኢ ሩጫ
መስከረም 30 እንገናኝ!
#GreatEthiopianRun #EntotoParkCBERun
❤6👍3
ምዝገባ በሲቢኢ ብር ፕላስ ላይ ተጀምሯል ✍️
ጤና፣ ደስታ እና አዲስ ትዝታ ሁሉም በአንድ ሩጫ!
አሁኑኑ በመመዝገብ በነፋሻማው እንጦጦ ፓርክ አስደሳች ጊዜን ከእኛ ጋር ያሳልፉ
እንጦጦ ፓርክ ሲቢኢ ሩጫ
ቅዳሜ መስከረም 30 እንገናኝ!
📱 በቀላሉ በሲቢኢ ብር ፕላስ ይመዝገቡ
#GreatEthiopianRun #EntotoParkCBERun
ጤና፣ ደስታ እና አዲስ ትዝታ ሁሉም በአንድ ሩጫ!
አሁኑኑ በመመዝገብ በነፋሻማው እንጦጦ ፓርክ አስደሳች ጊዜን ከእኛ ጋር ያሳልፉ
እንጦጦ ፓርክ ሲቢኢ ሩጫ
ቅዳሜ መስከረም 30 እንገናኝ!
📱 በቀላሉ በሲቢኢ ብር ፕላስ ይመዝገቡ
#GreatEthiopianRun #EntotoParkCBERun
❤10👍2
በሩጫ አንድ ሆነን፣ በቀለማት ደምቀን፣ አብረን የማይረሳን ጊዜ እንፍጠር። ❤️💛💚
50 ቀናት ብቻ ቀርተውናል! 🏃🏾♀️🏃🏾♂️🔥
#GreatEthiopianRun #MyRunMyColor #8WeekToGo

👏14❤9🔥3
ለ2026 የህፃናት ሩጫ ምዝገባ ተጀመረ
በአፍሪካ ትልቁ የጎዳና ላይ ሩጫ ጎን ለጎን በአዲስ አበባ የሚካሄደው የህፃናት ሩጫ፣ የመጪውን ትውልድ ሯጮች ለማነሳሳት በተዘረጋው
ሰፊ ፕሮግራም ላይ አንድ አካል በመሆን የተሳታፊዎችን ቁጥር ለማሳደግ ይሰራል፡፡
ጋዜጣዊ መግለጫ
ማክሰኞ ፤ መስከረም 26 ቀን 2019 - አዲስ አበባ
ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ ከ10 ኪሎ ሜትር የጎዳና ላይ ሩጫው አንድ ቀን ቀደም ብሎ ቅዳሜ ህዳር 12 ቀን 2019 ለሚካሄደው የ2026 የህፃናት ሩጫ ምዝገባ ዛሬ መጀመሩን ይፋ አደረገ።
ሁለቱም ሩጫዎች የተሳታፊዎችን ቁጥር እድገት የሚያሳዩ ሲሆን፣ ለህፃናቱ ውድድር 5,000 ቲሸርቶች ለሽያጭ ቀርበዋል።
ዕድሜያቸው 11 ዓመት እና ከዚያ በታች ለሆኑ ህፃናት ክፍት የሆነውና ከ4 ዓመት ጀምሮ በሦስት የዕድሜ ክልሎች የሚካሄደው ይህ ውድድር፣ ዘንድሮ በቦሌ ክፍለ ከተማ በሚገኘው አዲሱ አደይ አበባ ስታዲየም የውድድር ቦታውን አዘዋውሯል።
የውድድሩ ኦፊሴላዊ ሆቴል በሆነው ሀያት ሬጀንሲ በዛሬው ዕለት በተካሄደው የምዝገባ ማስጀመርያ መርሃ ግብር ላይ፣ የልጆች ሩጫ
የረጅም ጊዜ አጋር የሆነው ዩኒሴፍ (UNICEF) “ውሃን እንጠብቅ፣ የሕፃናትን መጻኢ እድል እንጠብቅ” የሚለውን የውድድሩን ዓመታዊ መልእክት አስተላልፏል።
መልእክቱ ንጹህ የመጠጥ ውሃ የማግኘት መብት የማንኛውም ህፃን መሰረታዊ መብት መሆኑን
በማስገንዘብ ህፃናትን የውሃ ዋስትና እና የአየር ንብረት ለውጥ ውይይት ማዕከል ያደርጋል።
የታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ አዘጋጆች በዛሬው መርሃ ግብር ላይ በሴቶች እና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር የተመረጡ ሶስት ሀገር በቀል የበጎ አድራጎት ድርጅቶችን የሚደግፈውን ዓመታዊ የገንዘብ ማሰባሰብያ ዘመቻ አስተዋውቀዋል።
አሁን 22ኛ ዓመቱ ላይ የሚገኘው
የ‘ሌሎችን ለመርዳት እሮጣለሁ’ (Run For A Cause) ዘመቻ ዘንድሮ ለአለምፍሬ ፒንክ ሀውስ የካንሰር ፋውንዴሽን (APCF)፣ ፍቅር
ኢትዮጵያ የአዕምሮ እድገት ውስንነት ያለባቸው ልጆች ብሄራዊ ማህበር (FENAID) እና ማረፊያ የአረጋውያን እንክብካቤ እና ድጋፍ ማህበር ገቢ ያሰባስባል።
የገቢ ማሰባሰቡን ለማጠናከር 5,000 የበጎ አድራጎት የመሮጫ ቲሸርቶች ለሽያጭ ቀርበዋል።
“ዘንድሮ ከማጠናቀቂያ መስመሩ ባሻገር ትርጉም ያለው ተፅዕኖ ለመፍጠር ከበፊቱ ይበልጥ ጠንክረን እየሰራን እንገኛለን፤” ያሉት
የታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያሥራ አስኪያጅ ዳግማዊት አማረ አክለውም “የውድድሮቻችንን ተደራሽነት እና ተፅዕኖ ለመጨመር የሚረዱ
አዳዲስ እድሎች በመፈጠራቸው ደስተኛ ነን።” ብለዋል።
የሴቶች እና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስትሯ ተወካይ ዶክተር ሀና የሺንጉስ ይህንን ሃሳብ በማጠናከር፣ ሩጫው ለሌሎች ድጋፍ መስጫ መንገድ በመሆኑ ያለውን አስፈላጊነት ገልጸዋል፦ “ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ 10 ኪሎ ሜትር በአንድ ድንጋይ ሁለት ወፍ ይመታል፤ ከቤተሰብ እና ከጓደኞቻችን ጋር እየሮጥን እንዝናናለን፣ በተመሳሳይ ጊዜ ደግሞ ድጋፋችን ለሚያስፈልጋቸው ወገኖች እጃችንን
እንዘረጋለን።
”ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ በማህበረሰቡ ውስጥ ጤናን እና አካል ብቃት እንቅስቃሴን በማስፋፋት ረገድ የሚያደርገው አስተዋፅኦ፣ በስራ
ቦታ ላይ ጤናማ የአኗኗር ዘይቤን ለሚያስፋፉ “ወርቃማ ደንበኞች” ድርጅቶች በተሰጡ ልዩ ልዩ እውቅናዎች በፕሮግራሙ ላይ
ተመስግነዋል።
የዛሬው መርሃ ግብር በተጨማሪም ለ2026 የታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ 10 ኪሎ ሜትር ተሳታፊዎች ለውድድሩ እንዲሰለጥኑ እና ሩጫን የዘወትር ልማዳቸው እንዲያደርጉ የታሰበ አዲስ የስልጠና መተግበሪያ (App) ይፋ ሆኗል።
መተግበሪያው ውድድሩ እ.ኤ.አ. በ2001 ከተጀመረበት ጊዜ አንስቶ ለዕድገቱ ትልቅ አስተዋፅኦ ካደረጉት ቁልፍ ስዎች አንዱ በሆኑት በኃይሌ ገብረስላሴ የተሰጡ ምክሮችን ያካተተ
ነው።

❤14
ምዝገባ ተጀምሯል!
ልጆች በጉጉት የሚጠብቁት ቀን እነሆ
አሁኑኑ ልጆችዎን በላምበረት ማራቶን ህንፃ 4ኛ ፎቅ በሚገኘው ቢሮ ወይም አለም ሲኒማ ጀርባ በመገኘት ያስመዝግቡ
ንፁህ ውሃ ለሁሉም ህፃናት
ውሃን እንንከባከብ፤ የልጆች ነገን እንጠብቅ።
#childrenrace #UNICEF

❤3👍1
በአዲስ ጅማሮ፣ በአዲስ መንፈስ እንጦጦ ፓርክ ሲቢኢ ሩጫ ተመልሷል።
ነገ ማለዳ እንጦጦ ፓርክ እንገናኝ
እንጦጦ ፓርክ ሲቢኢ ሩጫ✨
#GreatEthiopianRun #EntotoParkCBERun #CBE

❤10🔥2
👏አሸናፊዎች ሁላችሁም እንኳን ደስ ያላችሁ 👏#ውጤታችሁን ለማግኘት ማስፈንጠሪያውን ተጠቀሙ!
https://result.greatethiopianrun.org/results/entotoparkrun/mass
https://result.greatethiopianrun.org/results/entotoparkrun/cbe
እንጦጦ ፓርክ ሲቢኢ ሩጫ✨
#ENTOTO #CBE #Greatethiopianrun

❤3