Great Ethiopian Run (ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ)
6.21K subscribers
2.5K photos
190 videos
6 files
279 links
Official Great Ethiopian Run Telegram Channel.

Call 0116635757 for more details.
Download Telegram
አትሌት ሴና ገመቹ እና ራሔል እምቢበል የኢትዮ ቴሌኮም ታላቁ ሩጫ በሐረር አሸናፊዎች ሆኑ

መነሻ እና መድረሻውን ሐረር በር ላይ በማድረግ ፕሮፌሽናል አትሌቶችእና ከአዲስ አባባ ተጓዥ ተሳታፊዎችን ያካተተ ልዩ የ10ኪ.ሜ. ውድድር የተደረገ ሲሆን በወንዶች አትሌት ሴና ገመቹ በ32:04:77 በመግባት የአንደኛነት ደረጃን ሲይዝ ምህረት አወቀ ሁለተኛ እና ኢብራሒም መሐመድ ሶስተኛ ደረጃን ይዘው ውድድራቸውን ጨርሰዋል።

በሴት አትሌቶች ውድድር ራሔል እምቢበል በ41:43:23 በመግባት ቀዳሚውን ደረጃ ይዛ ስታጠናቅቅ አምራን ሸምሱ ሁለተኛ እና አዚዛ ሙክታር ሶስተኛ ደረጃ ተከታትለው ገብተዋል።
 
በተመሳሳይ ርቀት ውድድራቸውን ያደረጉት የልወቅሽ ኢትዮጵያ ክላሲክስ ተጓዥ ተሳታፊዎች መሐከል በተካሔደው ውድድር በወንዶች ዮሐንስ አየልኝ እንዲሁም በሴቶች ርብቃ ግርማ አሸናፊዎች ሆነዋል።

ዛሬ በድምቀት በተከናወነው ውድድር ላይ የሐረሪ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ኦርዲን በድሪ ፣ የባህልና ስፖርት ሚኒስቴር ሚኒስትር ዲኤታ መኪዩ መሀመድ፣ የቱሪዝም ሚኒስቴር ሚኒስትር ዲኤታ እንደገና አበበ (ዶ/ር)፣ እንዲሁም ሌሎች ከፍተኛ የመንግስት ሃላፊዎች በክብር እንግድነት ታድመዋል።

ከ16 አመት በታች ታዳጊ አትሌቶች የተሳተፉበት የ1.5 ኪ.ሜ.ውድድር እና ከ11 አመት በታች ልጆች የተሳተፉበት የ1 ኪ.ሜ.ውድድር ሌላው የዕለቱ ድምቀት ነበር፡፡

ሐረር የልወቅሽ ኢትዮጵያ ክላሲክስ ስድስተኛ እና የመጨረሻዋ መዳረሻ ከተማ ስትሆን ዛሬ ከተካሔደው የሩጫ ውድድር ባሻገር ትናንት የጀጎል ግቢ የተጎበኘበት የእግር ጉዞ ተካሂዷል፡፡ በተጨማሪም ምሽት ላይ በዘንድሮው የልወቅሽ ኢትዮጵያ ክላሲክስ በሁሉም ከተሞች በስኬት እና በድምቀት ለመካሄዱ አስተዋፅዖ ላበረከቱ አካላት እና ግለሰቦች የምስጋና፣ ዕውቅና እና ሽልማት ምሽት ተካሂዷል፡፡

የ2018 ልወቅሽ ኢትዮጵያ ክላሲክስ መነሻውን ደብረብርሃን በማድረግ በሐዋሳ፣ ጅማ፣ ቦቆጂ፣ አርባምንጭ እና ዛሬ ማጠቃለያውን ሐረር ላይ አድርጓል። በስድስቱም ከተሞች ላይ በመገኘት ዉድድሮቻቸውን ላደረጉ 43 ተወዳዳሪዎች ሲገጣጠም የኢትዮዽያ ካርታ ቅርፅ ያለው ልዩ ሜዳሊያ ተበርክቶላቸዋል።

ይህን ውድድር ከታላቁ ሩጫ በኢትዮዽያ ጋር በመሆን በስያሜ አጋርነት አብሮ የሚሰራው ኢትዮ ቴሌኮም ነው። በተጨማሪም የቱሪዝም ሚኒስቴር፣ ዳሽን ባንክ፣ ፔፕሲ፣ ፋብ ሳሙና፣ ቶፕ ውኃ፣ አፍራን ሆስፒታል፣ ቻናል 1 ቲቪ እና የሐረር ቱሪዝም ኮሚሽን የውድድሩ አጋሮች ናቸው።
👍7❤5🤩1
ለታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ - በቴሌብር ይመዝገቡ!

ከ60ሺህ ተሳታፊዎች መሐከል አንዱ ይሁኑ!

የምዝገባ ዋጋ
- ከመስቀል አደባባይ ለሚጀምረው ቀይ መነሻ 790 ብር
- ከግዮን ሆቴል ፊት ለፊት ለሚጀምረው እና የመሮጫ ቁጥር ለሚኖረው አረንጓዴ መነሻ 950 ብር

የ2019 ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ 10ኪ.ሜ. በባንክ ኦፍ አሜሪካ የቀረበ ✨

ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ ✨

#GreatEthiopianRun #MyRunMyColor
❤15🔥3
የታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ 10ኪ.ሜ. ምዝገባ ነገ ይጠናቀቃል።

ምዝገባው በቴሌብር በኩል ብቻ እየተከናወነ ሲሆን ያሉን ጥቂት ቀሪ ቦታዎች ሳይሞሉ በፊት ይመዝገቡ።

✨ሩጫዬ ቀለሜ ✨

✨ 2019 ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ 10ኪ.ሜ. በባንክ ኦፍ አሜሪካ የቀረበ ✨

#GreatEthiopianRun #MyRunMyColor #Telebirr
👍11❤7
የ2019 ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ 10 ኪ.ሜ. የመደበኛ ምዝገባ በሰባት ቀናት ጊዜ ውስጥ ተጠናቀቀ

60,000 ሯጮችን የሚያስተናግደው ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ 10ኪ.ሜ. ምዝገባ ባለው ከፍተኛ ፍላጎት ምክንያት በግለሰቦች እና ድርጅቶች የሚደረገው የምዝገባ ጊዜ እያጠረ መጥቷል።

በኢትዮጵያ ሕዝብ ዘንድ ካለው ከፍተኛ ምላሽ የተነሳ በባንክ ኦፍ አሜሪካ የስያሜ አጋርነት የሚቀርበው የ2019 ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ 10ኪ.ሜ. መደበኛ ምዝገባ ተጠናቋል።

ከማክሰኞ እስከ ማክሰኞ የዘለቀው የሰባት ቀናት የምዝገባ ጊዜ ውድድሩ ከተጀመረበት 1994ዓ.ም. ጀምሮ ባሉት የ26 ዓመታት ታሪክ ውስጥ አጭሩ የምዝገባ ጊዜ ሆኖ ተመዝግቧል።

የዘንድሮው ምዝገባ ይበልጥ የቀለለው ግለሰቦች በቴሌብር (telebirr) መተግበሪያ በኩል በመጠቀም እና ሙሉ በሙሉ ዲጂታል በሆነ የምዝገባ ሂደት ነው። ነፃ የውድድር ምዝገባ፣ የበጎ አድራጎት ስራዎች ገቢ ማሰባሰብ እና የሰዓት መቆጣጠሪያ ቴክኖሎጂን በስፋት መጠቀም ከባንክ ኦፍ አሜሪካ ጋር በተደረገው አጋርነት የመጡ አዳዲስ ስኬቶች አንዱ ተደርጎ ተወስዷል።

ለዘንድሮው ውድድር ከተዘጋጁት ጠቅላላ 60,000 ቦታዎች ውስጥ 3000 የሚሆኑት ዘንድሮ የ12ኛ ክፍል ፈተናን ለሚወስዱ ተማሪዎች በነፃ የሚሰጡ ሲሆን፣ ይህም አጋርነቱ ሰፊ የኅብረተሰብ ክፍል በውድድሩ ላይ እንዲሳተፍ ለማድረግ ያለውን ዓላማ የሚያሳይ ነው።

በተጨማሪም በሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ለተመረጡ ሦስት የበጎ አድራጎት ድርጅቶች ገቢ ለማሰባሰብ የታለመውን ‘ሌሎችን ለመርዳት ሮጣለሁ’ የገንዘብ ማሰባሰብ ዘመቻ በጥቅምት ወር 2019ዓ.ም. መጀመሪያ ላይ ይጀመራል። ቀሪ ጥቂት የምዝገባ አማራጮች የዚሁ ዘመቻ አካል ለሆኑት እና ለሽያጭ ከሚቀርቡት የበጎ አድራጎት ቦታዎች ላይ ይደረጋል።

ሁሉም የበጎ አድራጎት ቦታዎች ሙሉ በሙሉ ሲያዙ፣ ውድድሩ በአጠቃላይ 60,000 ተመዝጋቢዎች ይኖሩታል።
❤14👍7
🔥እየደረሰ ነው⏳ 100 ቀናት ብቻ ቀርተዋል! 🔥

በ100 ቀናት ውስጥ የአፍሪካ ትልቁ 10 ኪ.ሜ. የጎዳና ላይ ሩጫ ይከሔዳል 🇪🇹

እርስዎም ሌላ የማይረሳ የሩጫ ቀን ለማሳለፍ ይዘጋጁ! 🏃🏾‍♀️🏃🏾‍♂️

2019 ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ 10ኪ.ሜ. በባንክ ኦፍ አሜሪካ የቀረበ 💫

#GreatEthiopianRun #MyRunMyColor #100DaysToGo #Ethiopia
❤20🔥4
የአትሌቶች ምዝገባ ዛሬ ተጀምሯል! 🏆

ለ2019 ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ 10ኪ.ሜ. በባንክ ኦፍ አሜሪካ የቀረበ ውድድር የአትሌቶች ምዝገባ ላምበረት በሚገኘው የታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ ቢሮ እየተካሄደ ይገኛል።

🪪 ለምዝገባ ሲመጡ፦ መታወቂያ ፣ ፋይዳ ወይም ፓስፖርት ይዘው መምጣትዎን አይዘንጉ።

#GreatEthiopianRun #Registration #Athletes
❤8
እንኳን ለ1501ኛው የነቢዩ ሙሐመድ (ሰ.ዓ.ወ.) መውሊድ በሰላም አደረሳችሁ።

ታላቁ ሩጫ በኢትዮዽያ በዓሉ የሰላምና የፍቅር እንዲሆንላችሁ ይመኛል።

#GreatEthiopianRun #Mewlid
❤13👍6
🌼እንኳን ለ2019ዓ.ም. አዲሱ ዓመት በሰላም አደረሳቸሁ 🌼

ታላቁ ሩጫ በኢትዮዽያ ዓመቱ የሰላምና የፍቅር እንዲሆንላችሁ ይመኛል።

#GreatEthiopianRun #NewYear
❤23👍4👏2
የምንወደው እና የምንናፍቀው እንጦጦ ፓርክ ሲቢኢ ሩጫችን ተመልሷል።

እንጦጦ ፓርክ ሲቢኢ ሩጫ

መስከረም 30 እንገናኝ!

#GreatEthiopianRun #EntotoCBERun
👍11❤2
እንኳን ለ2019 የመስቀል ደመራ በዓል በሰላም አደረሳችሁ!

✨ መልካም የደመራ በዓል!

#GreatEthiopianRun
❤12👍4
ጤና፣ ደስታ እና አዲስ ትዝታ ሁሉም በአንድ ሩጫ!

ምዝገባ ነገ ይጀመራል

እንጦጦ ፓርክ ሲቢኢ ሩጫ

መስከረም 30 እንገናኝ!

#GreatEthiopianRun #EntotoParkCBERun
❤6👍3
ምዝገባ በሲቢኢ ብር ፕላስ ላይ ተጀምሯል ✍️

ጤና፣ ደስታ እና አዲስ ትዝታ ሁሉም በአንድ ሩጫ!

አሁኑኑ በመመዝገብ በነፋሻማው እንጦጦ ፓርክ አስደሳች ጊዜን ከእኛ ጋር ያሳልፉ

እንጦጦ ፓርክ ሲቢኢ ሩጫ

ቅዳሜ መስከረም 30 እንገናኝ!

📱 በቀላሉ በሲቢኢ ብር ፕላስ ይመዝገቡ

#GreatEthiopianRun #EntotoParkCBERun
❤10👍2
በሩጫ አንድ ሆነን፣ በቀለማት ደምቀን፣ አብረን የማይረሳን ጊዜ እንፍጠር። ❤️💛💚

50 ቀናት ብቻ ቀርተውናል! 🏃🏾‍♀️🏃🏾‍♂️🔥

#GreatEthiopianRun #MyRunMyColor #8WeekToGo
👏14❤9🔥3
ለ2026 የህፃናት ሩጫ ምዝገባ ተጀመረ

በአፍሪካ ትልቁ የጎዳና ላይ ሩጫ ጎን ለጎን በአዲስ አበባ የሚካሄደው የህፃናት ሩጫ፣ የመጪውን ትውልድ ሯጮች ለማነሳሳት በተዘረጋው
ሰፊ ፕሮግራም ላይ አንድ አካል በመሆን የተሳታፊዎችን ቁጥር ለማሳደግ ይሰራል፡፡

ጋዜጣዊ መግለጫ
ማክሰኞ ፤ መስከረም 26 ቀን 2019 - አዲስ አበባ

ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ ከ10 ኪሎ ሜትር የጎዳና ላይ ሩጫው አንድ ቀን ቀደም ብሎ ቅዳሜ ህዳር 12 ቀን 2019 ለሚካሄደው የ2026 የህፃናት ሩጫ ምዝገባ ዛሬ መጀመሩን ይፋ አደረገ።

ሁለቱም ሩጫዎች የተሳታፊዎችን ቁጥር እድገት የሚያሳዩ ሲሆን፣ ለህፃናቱ ውድድር 5,000 ቲሸርቶች ለሽያጭ ቀርበዋል።

ዕድሜያቸው 11 ዓመት እና ከዚያ በታች ለሆኑ ህፃናት ክፍት የሆነውና ከ4 ዓመት ጀምሮ በሦስት የዕድሜ ክልሎች የሚካሄደው ይህ ውድድር፣ ዘንድሮ በቦሌ ክፍለ ከተማ በሚገኘው አዲሱ አደይ አበባ ስታዲየም የውድድር ቦታውን አዘዋውሯል።

የውድድሩ ኦፊሴላዊ ሆቴል በሆነው ሀያት ሬጀንሲ በዛሬው ዕለት በተካሄደው የምዝገባ ማስጀመርያ መርሃ ግብር ላይ፣ የልጆች ሩጫ
የረጅም ጊዜ አጋር የሆነው ዩኒሴፍ (UNICEF) “ውሃን እንጠብቅ፣ የሕፃናትን መጻኢ እድል እንጠብቅ” የሚለውን የውድድሩን ዓመታዊ መልእክት አስተላልፏል።

መልእክቱ ንጹህ የመጠጥ ውሃ የማግኘት መብት የማንኛውም ህፃን መሰረታዊ መብት መሆኑን
በማስገንዘብ ህፃናትን የውሃ ዋስትና እና የአየር ንብረት ለውጥ ውይይት ማዕከል ያደርጋል።

የታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ አዘጋጆች በዛሬው መርሃ ግብር ላይ በሴቶች እና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር የተመረጡ ሶስት ሀገር በቀል የበጎ አድራጎት ድርጅቶችን የሚደግፈውን ዓመታዊ የገንዘብ ማሰባሰብያ ዘመቻ አስተዋውቀዋል።

አሁን 22ኛ ዓመቱ ላይ የሚገኘው
የ‘ሌሎችን ለመርዳት እሮጣለሁ’ (Run For A Cause) ዘመቻ ዘንድሮ ለአለምፍሬ ፒንክ ሀውስ የካንሰር ፋውንዴሽን (APCF)፣ ፍቅር
ኢትዮጵያ የአዕምሮ እድገት ውስንነት ያለባቸው ልጆች ብሄራዊ ማህበር (FENAID) እና ማረፊያ የአረጋውያን እንክብካቤ እና ድጋፍ ማህበር ገቢ ያሰባስባል።

የገቢ ማሰባሰቡን ለማጠናከር 5,000 የበጎ አድራጎት የመሮጫ ቲሸርቶች ለሽያጭ ቀርበዋል።

“ዘንድሮ ከማጠናቀቂያ መስመሩ ባሻገር ትርጉም ያለው ተፅዕኖ ለመፍጠር ከበፊቱ ይበልጥ ጠንክረን እየሰራን እንገኛለን፤” ያሉት
የታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያሥራ አስኪያጅ ዳግማዊት አማረ አክለውም “የውድድሮቻችንን ተደራሽነት እና ተፅዕኖ ለመጨመር የሚረዱ
አዳዲስ እድሎች በመፈጠራቸው ደስተኛ ነን።” ብለዋል።

የሴቶች እና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስትሯ ተወካይ ዶክተር ሀና የሺንጉስ ይህንን ሃሳብ በማጠናከር፣ ሩጫው ለሌሎች ድጋፍ መስጫ መንገድ በመሆኑ ያለውን አስፈላጊነት ገልጸዋል፦ “ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ 10 ኪሎ ሜትር በአንድ ድንጋይ ሁለት ወፍ ይመታል፤ ከቤተሰብ እና ከጓደኞቻችን ጋር እየሮጥን እንዝናናለን፣ በተመሳሳይ ጊዜ ደግሞ ድጋፋችን ለሚያስፈልጋቸው ወገኖች እጃችንን
እንዘረጋለን።

”ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ በማህበረሰቡ ውስጥ ጤናን እና አካል ብቃት እንቅስቃሴን በማስፋፋት ረገድ የሚያደርገው አስተዋፅኦ፣ በስራ
ቦታ ላይ ጤናማ የአኗኗር ዘይቤን ለሚያስፋፉ “ወርቃማ ደንበኞች” ድርጅቶች በተሰጡ ልዩ ልዩ እውቅናዎች በፕሮግራሙ ላይ
ተመስግነዋል።

የዛሬው መርሃ ግብር በተጨማሪም ለ2026 የታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ 10 ኪሎ ሜትር ተሳታፊዎች ለውድድሩ እንዲሰለጥኑ እና ሩጫን የዘወትር ልማዳቸው እንዲያደርጉ የታሰበ አዲስ የስልጠና መተግበሪያ (App) ይፋ ሆኗል።

መተግበሪያው ውድድሩ እ.ኤ.አ. በ2001 ከተጀመረበት ጊዜ አንስቶ ለዕድገቱ ትልቅ አስተዋፅኦ ካደረጉት ቁልፍ ስዎች አንዱ በሆኑት በኃይሌ ገብረስላሴ የተሰጡ ምክሮችን ያካተተ
ነው።
❤14