St.Paul's Hospital Millennium Medical College
22.1K subscribers
3.67K photos
39 videos
23 files
583 links
St. Paul's is a leading public hospital and medical college in Addis Ababa, Ethiopia.
Download Telegram
በዚህ የዓለም የቲቢ ቀን ለማክበር በዝግጅት ላይ ባለንበት ወቅት ፡ ከቲቢ ሕመም የዳኑ ሰዎች እንዲህ ይናገራሉ፡፡ ሙሉዓለም ታለ ምስክርነት አነሆ!
ሁለት ጊዜ በሳንባ በሽታ ተይዛለች በዚህም ምክንያት መስራት እየፈለገች እንዳትሰራ እንደ ልቤ መንቀሳቀስ እየፈለኩን እንዳልንቀሳቀስ አድርጎኛል ትላለች፡፡ በአንዲት ትንሽ ቤት ከእህቷና ከእህቷልጅ ጋር ኑሮን የምትገፋው የ23 ዓመቷ ሙሉአለም ታለ ትውልድና እድገቷ በአማራ ክልል መንዝ ማማ ነው፡፡
በ2012 ወደአዲስ አበባ ስትመጣ ስራ እየሰራች የተሸለ ኑሮ ለመስራት ነበር፡፡ ምንም እንኳን መድሃኒቱን በትክክል ብወስድም ሁለቴ ከመያዝ አላመለጠችም፡፡ እህቷም በዚሁ በሽታ ተይዛ እንደነበር በማስታወስ ያሳለፈችውን ከበድ ወቅት አትረሳውም፡፡
"የምንኖርባት ቤት በጣም ትንሽ መሆኗ አየር እንደልብ እንዲገባ አያደርግም ፡፡በዛም ምክንያት ይመስለኛል እህቴ የተያዘቸው "ስትል ታስረዳለች፡፡ ም የሚኖሩበት አካባቢ ምን ያህል አስቸጋሪ እንደሆነ ትገልጻለች፡፡
መጠንቀቅ እየተቻለ አለመጠንቀቅ ምንያህል ኑሮን እንደሚያመሰቃቅል እኔ ማሳያ ነኝ የምትለው ወጣቷ በበሽታው ከተያዙ በኋላም መድሃኒተን በአግባቡ አለመውሰድ ዋጋ ሲያስከፍል በሌሎች አይቻለው ትላለች፡፡ የሳንባ በሽታ ስራዬን አሳጥቶኛል ባልወድም የሰው እጅ ጠባቂ አድርኛል የምትለው ሙሉአለም ታሞ ከመማቀቅ አስቀድሞ መጠንቀቅ ነውና ነገሩ ሰዎች በተለይም በሳንባ በሽታ ተጠቅተው እጅግ ከባድ ጊዜ ከሚያሳልፉ እና በመድሀኒቱ በሚመጣ የጎንዮሽ ጉዳት ሰለባ ከመሆናቸው በፊት ይጠንቀቁ ስትልም መልክቷን አስተላፋለች ፡፡አሁን ላይም በሰለጠነችበት የሙያ መስክ ስራ አግኝታ መስራት የልብ ምኞቷ መሆኑን በመግለጽ ታሪኳን ትደመድማለች፡፡
A half day awareness raising training about Tuberculosis in relation to the World TB Day was given to journalists drawn from private and public owned media houses. The training was organized in collaboration with WHO and VHS.
27ኛው የአለም የቲቢ ቀን እና 18ኛው ዓመታዊ የቲቢ ምርምር ጉባኤ ዛሬ በይፋ ተከፍቷል።
ይህ ዓመታዊ የቲቢ ምርምር ጉባኤም በቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሊኒየም ሕክምና ኮሌጅ እና በአዲስ አበባ ጤና ቢሮ አዘጋጅነት በመካሄድ ላይ ነው።
ለሁለት ቀናት በሚቆየው በዚህ ጉባዔ ተገኝተው የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የጤና ሚኒስትርዋ ዶ/ር መቅደስ ዳባ እንዳሉት መንግስት ለቲቢ ትኩረት በመስጠቱ ከለጋሾች የሚገኘውን የገንዘብ መጠን ያክልም መንግስት ከራሱ በጀት እየመደበ የበሽታውን ስርጭት ለመግታት እየሠራ ነው ብለዋል።
በጉባዔው ከክልል ጤና ቢሮ ኃላፊዎች: የሕክምና ኮሌጆች: ተመራማሪዎች እና ከተለያዩ የአፍሪካ ሀገራት የመጡ እና መንግስታዊ ካልሆኑ ተቋማት የመጡ ተሳትፈዋል ።
Today is world TB day ! Let's come together to raise awareness about TB and towards its eradication .
#sphmmc
የዓለም ቲቢ ቀንን ምክንያት በማድረግ በቲቢ ዙሪያ የሚሰሩ ድርጅቶችና ግለሰቦች ከአትዮጵያ ፌዴራል ሪፐብሊክ ተወካዮች ምክር ቤት ህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የጤና፣ ማህበራዊ ልማት፣ ባህልና ስፖርት ቋሚ ኮሚቴ አባላት ጋ አባለት ጋር ውይይት አድርገናል፡፡ በሀገር ዐቀፍ ደረጃ የቲቢን በሽታ በ2030 ለማጥፋት ያለውን እቕድ ለመሳካት ውይይት ተደርጓል፡፡
SPHMMC and AA Health Bureau organized a 3km Anti TB (tuberculosis) walk to celebrate World TB Day in Addis Ababa on the 24th of March 2024. The walk, which intended to increase public awareness about TB, called for active community engagement in the fight against the disease in Ethiopia.
St Paul Hospital Millennium Medical College is excited to announce that training in acupuncture has started in partnership with Acupuncture Without Borders ( a French organization) in October 2022. The 1st group of trained students is now able to start a clinic in St Paul Hospital to treat patients with all kinds of pain and functional problems, efficiently and without negative side effects.
The clinic is now open twice a week.