St.Paul's Hospital Millennium Medical College
22.1K subscribers
3.67K photos
39 videos
23 files
583 links
St. Paul's is a leading public hospital and medical college in Addis Ababa, Ethiopia.
Download Telegram
St. Paul’s gave a half-day training on PMTCT to 24 journalists from various government and private media organizations. The purpose of the training was to give media professional’s awareness of that sought to raise awareness about Mother-to-child transmission of HIV is the spread of HIV from a woman living with HIV to her child during pregnancy, childbirth mother.
Thank you #SPHMMC'sDepartmentofObstetricsandGynecology
ክቡር ዶ/ር አሚን አማን በጤናው ዘርፍ ስኬት እንዲመጣ በእጅጉ ሰርተዋል፡፡ እናመሰግናለን! ወደፊትም በስራዎ መከናወን እንዲሆንልዎት መልካሙን ሁሉ አንመኛለን፡፡
t.me/spmmc
ጤናማው የወር አበባ ዑደትሽ
t.me/spmmc

አንዲት ሴት የወር አበባ ማየት በጀመረች 2 ዓመት ጊዜ ውስጥ ዑደት መስተካከል ይጀምራል። የጤናማ የወር አበባ ዑደት መገለጫዎች ደግሞ የሚከተሉት ናቸው፡፡
· ወቅቱን ጠብቆ የሚመጣ (21-35 ቀናት ውስጥ)
· መጠኑ በየወቅቱ የማይለዋወጥ (20-80 ሚ.ሊ)
· ከ2- 7 ቀን የሚፈስ
· የማይረጋ ደም
ከዚህ የተለየ የወር አበባ መምጣት ከጤናማነት የወጣ ሁኔታ መሆኑን ማስተዋል እና አስፈላጊ የሆነውን የጤና እርዳታ መሻት ያስፈልጋል።
የፈተና ጊዜን ስለማሳውቅ
የፈተና ጊዜን ስለማሳውቅ
በነርሲንግ ትምህርት ክፍል 2012 ዓ.ም በየካርዲዮ ቫስኩለር ነርሲንግ የ2ኛ ዲግሪ ትምህርት ፕሮግራም አመልካቾች ጥር 4 ቀን 2012 የጽሁፍ ፈተና ይሰጣል፡፡ ጥር 5 ቀን 2012 ደግሞ ቃለ መጠይቅ ይቀርባሉ፡፡
St. Paul's Hospital Millennium Medical College-SPHMMC - Hero#Gynecology&ObstetricsPhysician#SafeMotherhoodMonth During this Safe Motherhood Month, we recognize Dr. Ayele Teshome for his voluntary services to improve maternal health care services. Dr. Ayele is an Obstetrics and Gynecology Physician who has worked on improving the maternal health services when he was working in St. Peter’s specialized hospital. He has worked on quality improvement so that mothers could be served without a hassle. He has arranged for surgery through an association of voluntary physicians for mothers who had complications at Alem ketema. He has coordinated such voluntary services in two rounds ensuring that the country woman benefits from the services. He has also coordinated blood donation for mothers who suffer from bleeding copiously. Dr. Ayele has developed various documents which are important for improving maternal healthcare services. He also organized short term training programs to enhance the quality of services by healthcare professionals. Thank you, Dr. Ayele, for all you have done. (He is currently working as Provost for Yekatit 12 Medical Collage)
ለመላው ባለሙያዎቻችን እንኳን ደስ ያላችሁ! ለተገልጋዮቻችችን እንኳን ደስ ያላችሁ!

በመካንነት ሕክምና ማእከል ህክምናቸውን ሲከታተሉ የነበሩ ጥንዶች በ ` intro vitro fertilization’ ህክምና ልጅ ማግኘት ችለዋል፡፡
ጥንዶቹ ለሰባት ዓመታት በጋብቻ ሲኖሩ ልጅ ማፍራት አልቻሉም ነበር፡፡ እነዚህ ባልና ሚስት የቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሊኒየም ሕክምና ኮሌጅ ማእከሉ ባለፈው ሚያዚያ 2011 ተመርቆ ከተከከፈተ በኃላ የመጀመሪዎቹ በ IVF ሕክምና ልጃቸውን የታቀፉ ወላጆች ሆነዋል፡፡ ለመላው ባለሙያዎቻችን እንኳን ደስ ያላችሁ! ለተገልጋዮቻችችን እንኳን ደስ ያላችሁ!

በIVF ሕክምና የሚወልዱ ቁጥራቸው 70 የሚደርሱ ነፍሰጡር እናቶችም በቀጣይ ወራቶች ልጃቸውን ለማቀፍ ይበቃሉ፡፡ በኢትዮጵያ ያለመውለድ ችግር/ መሃንነት/ ስርጭት ከፍተኛ መሆኑ ቢታመንም በተወሰነ መልኩ ምርመራዎችን ከማድረግ የዘለለ በበቂ ሁኔታ የህክምና መፍትሔ ለመስጠት የሚያስችል የተደራጀ የህክምና ተቋም አልነበረም፡፡ በመንግስት የጤና ተቋም የጳውሎስ የመጀመሪያው ነው፡፡

ከዚህ ቀደም ብዙ ጥንዶች ወደ ውጪሃገር ሄደው በከፍተኛ ወጪ ለመታከም ይገደዱ ነበር፡፡በዚህም ሀገራችን ከፍተኛ የሆነ የውጭ ምንዛሪ ይባክን ነበር፡፡

የቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሊኒየም ሕክምና ኮሌጅ በመጪው ሁለት ዓመታት በሀገር ውስጥ የማይገኙ ሌሎች የሕክምና አገልግሎቶችን ለመጀመር በሂደት ላይ ነው፡፡
የቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሊኒየም ህክምና ኮሌጅ ። ያስገነባው የእናቶችና ህፃናት ልዩ ሆስፒታል አገልግሎት ተመረቀ።
የክብር እንግዶቹ የጤና ሚኒስትር ዴኤተ ዶር ሊያ ታደሠ አና የሱዛን ቶምሰን ቡፌት ፋውንዴሽን የዓለም ዓቀፍ ፕሮግራም ዳይሬክተር ፕሮፌሰር ሠናይት ፍስሐ በተገኙበት ተመርቆ ተከፍቷል።
ጥቂት ስለ ሆስፒታሉ :-
***
+++ሆስፒታሉ በሁለት ሺ ካሬ ሜትር ላይ ነው ያረፈው +++የግንባታ ወጪው 450 ሚ. ብር ነው።
+++456, አልጋዎች አሉት።
+++ ይህ ሆስፒታል በእናቶችና ህፃናት ጤና ላይ ብቻ ትኩረት ሰጥቶ የሚሠራ ነው።
+++የማዋለድ አገልግሎትን ጨምሮ የሴቶች የካንሰር ህክምና፣ የጡትና የማህፅን በር ጫፍ ካንሰር ልየታና ሕክምና ይሠጣል።
+++መደበኛ የጨቅላ ህፃናት ህክምና እስከ ልብ ቀዶ ህክምና ድረስ የዘለቁ ሙሉ የህፃናት ህክምና ይሠጣል።

+++ ሆስፒታሉ በቀን ከሁለት ሺ አምስት መቶ በላይ ለሚሆኑ እናቶችና እስከ ሶስት መቶ ለሚጠጉ ጨቅላ ህፃናት የህክምና አገልግሎት መሥጠት ይችላል።
13 የቀዶ ህክምና አገልግሎት የሚሰጡ ሰፋፊ ክፍሎችና 16 የህጻናት የጽኑ ህሙማን አገልግሎት መስጫ ክፍሎች አሉት።
A foundation stone has been laid for the construction of a new Center of Excellence for reprductive Health building within the St.Paul's compound.

Proffessor Senait Fisha of International Director Susan Thompson Buffet Foudation and State Minister Health Dr.Leah Tadesse laid the cornerstone for the Center of reproductive health to be built next to MCH hospital.
የጤና ጥበቃ ሚንስቴር ዛሬ በሰጠው መግለጫ በኮሮና ቫይረስ ሳይያዙ አይቀሩም ተብለው የተጠረጠሩ አራት ሰዎች በኢትዮጵያ መገኘታቸውን አሳውቋል።

አራቱም ኢትዮጵያዊያን መሆናቸው የተነገረ ሲሆን፤ ሦስቱ ቫይረሱ በተከሰተበት ዉሃን ግዛት ተማሪ የነበሩ ናቸው ተብሏል።

4ቱ ሰዎች በለይቶ ማከሚያ ማዕከል ተለይተው ክትትል እየተደረገላቸው እንደሆነ ታውቋል። ከተለዩት ተጠርጣሪዎች ሁለቱ የሳል እና የሙቀት ምልክት አሳይተዋል። ሁለቱ ተጠርጣሪዎች ደግሞ ምንም አይነት የህመም ምልክት ባያሳዩም፤ ወረርሺኙ ከተከሰተበት ስፍራ የመጡ በመሆናቸው እና ምልክቱ ከታየባቸው ሰዎች ጋር ግነኙነት ስለነበራቸው ተለይተው ክትትል እየተደረገላቸው ነው ሲል ጤና ጥበቃ አስታውቋል።
የጤና ጥበቃ አመራሮች በሰጡት መግለጫ፤ ለተጠርጣሪ ህመምተኞቹ የላብራቶሪ ናሙና ተወስዶ ለምረመራ ወደ ደቡብ አፍሪካ መላኩን ተናግረዋል።

በቦሌ ዓለም አቀፍ አየር ማረፊያ የመንገደኞች የሰውነት ሙቀት መለካት ከተጀመረበት ጊዜ ጀምሮ እስካሁን 21ሺህ ሰዎች ሙቀት መለካቱም ተነግሯል።

እስካሁን በቻይን ከ100 በላይ ሰዎች በቫይረሱ ምክንያት ህይወታቸው አልፏል።




የኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ከቫይረሱ ጋር የተያያዙ ጠቃሚ መረጃዎችን ለህብረተሰቡ የሚከተለውን መረጃ ከቀናት በፊት አስተላልፏል።

ኮሮና ቫይረስ ምንድነው?

የኮሮና ቫይረስ ከቀላል እስከ ከባድ የመተንፈሻ አካል ሕመም የሚያስከትል የቫይረስ ዝርያ ሲሆን ሞትን ሊያስከትል የሚችል ህመም ነው።

የቫይረሱ መተላለፊያ መንገዶች

በሽታው ያለበት ሰው ሲያስነጥስ ወይም ሲያስል፣ ባልበሰሉ ምግቦች፣ ከታማሚው ሰው ጋር በሚደረግ የቅርብ ንክኪ ይተላለፋሉ።

የበሽታው ምልክቶች

በበሽታው የተያዙ ሰዎች ትኩሳት፣ ሳል፣ የትንፋሽ መቆራረጥ እና የመተንፈስ ችግር ምልክቶች ይታይባቸዋል።

በሽታው የጠናባቸው ሰዎች ላይ ደግሞ እንደ የሳምባ ምች እና ከባድ የመተንፈሻ አካላት ህመም ይስተዋልባችዋል።
በበሽታው መያዛቸውን የጠረጠሩ ሰዎች ምን ማድረግ አለባቸው?

ከላይ የተጠቀሱት ምልክቶች ካለብዎ ወዲያውኑ በአቅራቢያዎ ወደሚገኝ የጤና ተቋም ይሂዱ።

የበሽታው ስሜት ከመፈጠሩ አስራ አራት ቀናት በፊት በሽታውን ሪፖርት ወዳደረጉ አገራት ሄደው ከነበረም ይህንንም ለጤና ባለሙያ ያሳውቁ።

በሚያስሉበት እና በሚያስነጥሱበት ጊዜ በሽታው ወደ ጤነኛ ሰው እንዳይተላለፍ አፍና አፍንጫን በክንድ፣ በመሃረብ ወይም በሶፍት ይሸፍኑ።

አፍን አፍንጫን ለመሸፈን የተጠቀምንበትን ሶፍት በአግባቡ በቆሻሻ መጣያ ውስጥ ማስወገድ እና እጅን ሁልጊዜ በውሃ እና በሳሙና መታጠብ ያስፈልጋል።

በበሽታው መያዝዎን ሪፖርት ለማድረግ በነጻ የስልክ መስመር
8335 ወይም የመደበኛ ስልክ 0112765340 መጠቀም ይችላሉ

በሽታው ወዳለባቸው ሃገራት ሲጓዙ ሊወሰዱ የሚገቡ ጥንቃቄዎች

ትኩሳት እና የሳል ምልክት ከሚያሳዩ ሰዎች ጋር ንክኪ አለማድረግ

በተለይ ደግሞ ከታመሙ ሰዎች ወይም ከአካባቢያቸው ጋር ንክኪ ከፈጠሩ እጅን በሳሙናና ውሃ መታጠብ

ያልበሰሉ የእንስሳት ተዋጽኦዎችን አለመመገብ

በሕይወት ካሉም ሆነ ከሞቱ የቤት እና የዱር እንስሳት ጋር ንክኪ አለማድረግ