We have held discussion on traffic accidents with representatives of the community discussion. It is well known that traffic accidents are increasing in our country. We have also carried out awareness raising programs on the issue. (AaBET Hospital, which is a branch of our college, is known for treating victims of traffic accidents.)
#WorldDayofRemembranceforTrafficVictims
#WorldDayofRemembranceforTrafficVictims
የአልትራሣውንድ ጥቅም ከእናቶች ጤና አንጻር
*********************************
አልትራሣውንድ በአሁኑ ወቅት አልትራሣውንድ በድንገተኛ ክፍልና በተለያዩ አፋጣኝ የህክምና ድጋፍ ለሚያስፈልጓቸው ህሙማን አገልግሎት ለመስጠት ጠቃሚ መሳሪያነው፡፡ይሰጣል፡፡
አልትራሣውንድ የእርግዝና ምዕራፎችን ለመከታተል ጉልህ ሚናን አለው፡፡ለአብነትም፡-
በተለይ .በመጀሪመያው የእርግዝና ምዕራፍ ወቅት / ከ1-3ኛው ወር/
1. ትክክለኛ እርግዝና መኖሩንና ፅንስ መፈጠሩን ለማረጋገጥ
2. የተፈጠረው ፅንስ እድሜው ምን ያህል እንደሆነ ለመገመት
3. እርግዝናው በማህፀን ውስጥ ወይም ከማህፀን ውጪ መፈጠሩንና አለመፈጠሩን ለማረጋገጥ ይረዳል፡፡ ምክንያቱም ከማህፀን ውጪ የሚፈጠር እርግዝና ለእናትየው ጤንነት አስጊ በመሆኑ በአፋጣኝ እርምጃ ለመውሠድና የእናትየውን ጤንነት ለመጠበቅ ይረዳል፡፡
4. የፅንሱን የልብ ምት ለማረጋገጥና በህይወት መኖሩን ለማየት
5. በአጠቃላይ እርግዝናው ትክክለኛና ተፈጥሮአዊ በሆነ መንገድ መቀጠሉን ለማረጋገጥ ያስችላል፡፡ በሁለተኛው የእርግዝና ምዕራፍ ወቅት /
አቀማመጡን ከማህፀን በር አንፃር ለመገምገም - የፅንሱን እንቅስቃሴ ለመቆጣጠር - የፅንሱን እድገት ለመከታተልና በማህፀን ውስጥ መታፈንን፣ የእድገት መቋረጥ ወይም መቀነስ እንደሌለ ለማወቅ - የእናትየው ማህፀንና አካባቢው በአግባቡ በጥሩ ጤንነት ላይ እንደሚገኝ ለማወቅና የተከሠተ ችግር ካለ አፋጣኝ እርምጃ ለመውሰድ ይረዳል፡፡
በአጠቃላይ አልትራሣውንድ በእርግዝና ወቅት ከ12ኛው ሣምንት በኋላ የፅንሱን ፆታ ለመለየት ብሎም የሚወለድበትን ቀን ለመገመት ያስችላል፡፡

ማሕበራዊ ሚድያ ድረገጾችን መጠቀም የአመጋገብ ሥርዓትን እንደሚያቃውስ ተገለጠ
ወላጆች ልብ በሉ። ማሕበራዊ ድረ ገጾች በተለይም ምስሎችን ማየት እና ማጋራት ትኩረት የሚሰጥባቸው መድረኮች ላይ ረጅም ጊዜ ማሳለፍ በልጆችና በታዳጊ ወጣቶች ላይ የአመጋገብ ሥርዓት መቃወስን እንደሚያስከትል ተመራማሪዎች ይፋ አድርገዋል። አንድ ሺ የሚያህሉ የ7ኛ እና የ8ኛ ክፍል ተማሪዎች ላይ የተደረገው ጥናት በኢንተርናሽናል ጆርናል ኦቭ ኢቲንግ ዲስኦርደር ላይ በታተመው ጽሁፍ በማሕበራዊ ድረገጾችና በአስተሳሰብ እንዲሁም በባሕርይ መለወጥ መካከል ዝምድና መኖሩን አመላክቷል።

እንቅልፍ ማብዛት ለእስትሮክ ሊያጋልጥ ይችላል
በዓለም ዙርያ በተለይም በአሜሪካ እስትሮክ ዋነኛው የሞት እና የአካል ጉዳት መንስኤ ነው። አዲስ ጥናት እንዳስታወቀው እንቅልፍ ማብዛት ለዚህ አይነቱ የልብ በሽታ ተጋላጭነትን በ85 በመቶ ከፍ ያደርገዋል። በዓለም ዙርያ በየዓመቱ 15 ሚሊዮን ሰዎች ለእስትሮክ ይጋለጣሉ። ከእነዚህም ውስጥ 6 ሚሊዮን የሚሆኑት በእስትሮክ ምክንያት ሲሞቱ አምስት ሚሊዮን የሚያህሉት ደግሞ የአካል ጉዳተኛ ሆነው ይኖራሉ።

አካላዊ እንቅስቃሴ ከፕሮስቴት ካንሰር ይከላከላል
ለፕሮስቴት ካንሰር የሚያጋልጡ የአኗኗር ዘይቤዎች ላይ ጥናት ሲያደርጉ የነበሩ ተመራማሪዎች አካላዊ እንቅስቃሴ አለማድረግ እና ለፕሮስቴት ካንሰር ተጋላጭ መሆን ዝምድና እንዳላቸው ደርሰውበታል። ፕሮስቴት ካንሰር በአሜሪካ እና በዓለም ዙርያ በስርጭቱ በሁለተኛ ደረጃ የሚገኝ የካንሰር አይነት ነው። በአሜሪካ የሚገኘው የናሽናል ካንሰር ኢንስቲትዩት እንደዘገበው በ2019 መጨረሻ አካባቢ አሜሪካ ውስጥ ብቻ 175 ሺ ሰዎች በፕሮስቴት ካንሰር ይያዛሉ። በዚህ በሽታ የሚያዙ ሰዎች ብዙ ቢሆኑም ሳይንቲስቶች ለበሽታው መከሰትና መባባስ መንስኤው ምን እንደሆነ እስካሁን አጥርተው ሊያውቁ አልቻሉም። በቅርቡ በእንግሊዝ አንድ የአጠኚዎች ቡድን ለየት ያለ የጥናት ስልት በመጠቀም ኢንተርናሽናል ጆርናል ኦቭ ኢፒደሚዮሎጂ ላይ እንዳሳተሙት አካላዊ እንቅስቃሴ ማድረግ ለፕሮስቴት ካንሰር ተጋላጭነትን እንደሚቀንስ ገልጸዋል።

ሞባይል ስልክ መጠቀም ለጭንቅላትና ለአንገት ጉዳት ያጋልጣል
በመንገድ ላይ እየሄዱ በሞባይል አጭር የጽሁፍ መልእክት ማስተላለፍ ጠጥቶ ከመንዳት እንደማይለይ አንዳንድ ሰዎች ይናገራሉ። በቅርብ የተደረገ ጥናት እንደሚጠቁመው መንገድ ላይ እየሄዱ በሞባይል የጽሁፍ መልእክት ማንበብና ማስተላለፍ ባለፉት ሃያ ዓመታት ውስጥ ለተከሰቱ ብዙ የጭንቅላት እና የአንገት ጉዳቶች መንስኤ ሆኗል። በ2017 ብቻ መኪና እያሽከረከሩ ስልክ መደወል፣ ኢሜይል ማንበብ፣ ወይም አጭር የጽሁፍ መልእክት መቀበልና ማስተላለፍ 400 ከባድ የመኪና አደጋዎችን አስከትሏል። ነገር ግን መኪና እየነዱ ብቻ ሳይሆን በእግር እየሄዱም ሞባይል ስልክ መጠቀም ለአደጋ እንደሚያጋልጥ ተረጋግጧል።

ከምግብ ላይ በቀን 300 ካሎሪ መቀነስ ለልብ ጤና ይጠቅማል
አንድ ሰው ፍጹም ጤናማ የሆነ የሰውነት ክብደት ቢኖረውም እንኳ በቀን ከምግቡ ላይ 300 ካሎሪ ቢቀንስ ለልቡ ጤና ትልቅ አስተዋጽኦ እንዳለው ተገለጸ። በቀን የተጠቀሰውን ያህል ምግብ ለመቀነስ አልፎ አልፎ መጾም ወይም ከምግብ በኋላ የሚበሉትን ቺዝ ኬክ መተው ይቻላል። በጥናቱ ወቅት ጥናቱ የተደረገባቸው ሰዎች ለሁለት ዓመት ምግብ በመቀነሳቸው የደም ግፊታቸው ሲወርድ በደማቸው ውስጥ ያለው ቅባት ደግሞ በ24 በመቶ ዝቅ ብሏል።

ማስታወቂያ
የቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሊኒየም ሕክምና ኮሌጅ በ 2012 ዓ.ም በካርዲዮ ቫስኩላር ነርሲንግ በሁለተኛ ዲግሪ ትምህርት ሰልጣኞችን ተቀብሎ ማሰልጠን ይፈልጋል፡፡
ስለዚህ በትምህርት መስኩ መሰልጠን የሚፈልጉ የሚከተለውን መስፈርት ማሟላት አለባቸው፡፡
የቅበላ መስፈርት
• እውቅና ካለው ዩንቨርስቲ (የትምህርት ተቋም) በነርሲንግ የመጀመሪያ ዲግሪ ያለው /ያላት
• በሙያው ሁለት አመት ያገለገለ /ያገለገለች
• ከሚሰሩበት ድርጅት የስፖንሰርሽፕ ደብዳቤ ማምጣት የሚችል /የምትችል
• ከተማሩበት የትምህርት ተቋም ኦፊሻል ትራንስክሪፕት ማምጣት የሚችል /የምትችል
• ሁለት የድጋፍ ደብዳቤ የሚሰራበት መስሪያ ቤት ማምጣት የሚችል /የምትችል
• የመግቢያው ፈተና ማለፍ የሚችል /የምትችል
የምዝገባ ቦታ
በኮሌጁ ሬጅስትራል ጽ/ቤት
የምዝገባ ቀን ፡
ከታህሳስ 13 እስከ ታህሳስ 24 201ዓ/ም ድረስ ዘወትር በስራ ሰዓት መመዝገብ ይችላሉ፡፡
የፈተናው ቀን በኮሌጁ የፌስቡክና ቴሌግራም ገጽ ይገለጻል፡፡
የቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሊኒየም ሕክምና ኮሌጅ

የወር አበባሽ ተዛብቶብሽ ይሆን?
የወር አበባ ዑደት መዛባት ማለት አንዲት ሴት ወትሮ ከምታየው የተለየ ጠባይ ሲገጥማት ነው፡፡
1) የወር አበባ መዛባት ዓይነቶች የምንላቸው የሚከተሉት ናቸው፡፡ እነሱም
· የፍሰት መጠን መብዛት
· የፍሰት መጠን ማነስ
· መቅረት
· የቀኑ መዛባት
· ቶሎ ቶሎ መምጣት
2) የወር አበባ መዛባት መገለጫዎች
የፍሰት መጠን መብዛት- ከዚህ በፊት ይፈስሽ ከነበረው መጠን በላይ ሲበዛ፣ ከ7 ቀናት ባላይ ሲፈስሽ፣ ብዙ የንጽሕና መጠበቂያ ለመጠቀም ስትገደጂ፣ ሲፈስሽ የሚረጋ ከሆነ፣ የድካም ስሜት ካለሽ፣ የማዞር ስሜት ካለሽ እና ራስን እስከ መሳት ስትደርሺ ፍሰቱ ተዛብቷል ማለት ነው፡፡
መንስኤው ምን ሊሆን ይችላል?
የማህፀን እጢዎች፣ የሆርሞን መዛባት፣ ጭንቀት፣ መድሀኒቶች፣ የደም መርጋት ችግር ሊሆን ይችላል።
የፍሰት መጠን ማነስ፡- ከ35 ቀናት በላይ እየቆየ የሚመጣ ከሆነ፣ ከሁለት ቀናት ባነሰ ጊዜ ብቻ በመጠኑ የሚፈስሽ ከሆነ ይሄ የማነስ ምልክት ነው።
ሌላው መንስኤ ደግሞ ፡- የእንቁላል አመራረት ሂደት መዛባት(PCOD)ነው፡፡
መቅረት፡- ለ3 ተከታታይ ዑደት ወይም ለ6 ወራት የወር አበባ መቅረት፤ መንስኤውም
· እርግዝና፣ የማኅጸን ጠባሳ፣ የማኅጸን ኢንፌክሽን፣ የሆርሞን መዛባት
· ጭንቀት፣ ከባድ የሆነ የስፖርት እንቅስቃሴ ወይም ማረጥ ሊሆኑ ይችላሉ።
ቀኑን ማዛባት፡- ወቅቱን ጠብቆ የማይፈስ የወር አበባ ዑደት
መንስኤዎች፡- የማኅጸን ዕጢዎች፣ የማህጸን ጫፍ ካንሰር
ቶሎ ቶሎ መጣ የምንለው፡- ከ21 ቀናት በታች ተደጋሞ የሚመጣ ከሆነ ነው።
መንስኤዎች፡- ማህፀን እጢዎች፣ የሆርሞን መዛባት፣ ጭንቀት፣ መድሀኒቶች፣ የማረጥ እድሜ ላይ መድረስ ሊሆኑ ይችላሉ።
መፍትሔዎች እንደ መንስኤዎች ዓይነት ይለያያል።
(ይህን መረጃ የሰጡን ዶ/ር ቤቴል ደረጀ- የማህጸን እና የጽንስ ስፔሺያሊስት ሐኪም ናቸው፡፡)
ለተጨማሪ የጤና መረጃ፡የቴሌግራም ገፀጻችንን ይከታተሉ፡፡
t.me/spmmc

የምዝገባ ቀን ተራዝሟል!
በሚከተሉት ትምህርቶች የምዝገባ ቀን ተራዝሟል! የስፖንርሺፕ ደብዳቤ የመግቢያ ፈተና ካለፉ በኋላ ማምጣት ይቻላል፡፡፡
Emergency and critical care nursing
2. Operating theater nurse
3. Neonatal nursing
4. Pediatric nursing
5. Surgical nursing
የምዝገባ ቀን፡- ከዘሬ ጀምሮ እስከ ታህሳሥ 24 ቀን 2012
የስፖንርሺፕ ደብዳቤ የመግቢያ ፈተና ካለፉ በኋላ ማምጣት ይቻላል፡፡፡

From December 9-14 2019 GC, a group of Indian higher delegates, participants of the India Innovation and Technology Expo and Conference hosted by the Ministry of Innovation and Technology, led by the honorable Mr. Munish Gupta -Program Advisor to the India-Ethiopia Innovation & Technology Commercialization Programme- visited SPHMMC on December 12 and was hosted by the SPHMMC Office of ISO led by Dr. Rania Ibrahim. They had a productive dialogue which led to the initiation of new innovative and strategic partnerships with 5 Indian based companies.