St.Paul's Hospital Millennium Medical College
22.1K subscribers
3.67K photos
39 videos
23 files
583 links
St. Paul's is a leading public hospital and medical college in Addis Ababa, Ethiopia.
Download Telegram
ስለ ቅድመ የማህፀን ጫፍ ካንሰር ምርመራ….

የቅድመ የማህፀን ጫፍ ካንሰር ምርመራ ማለት አንድ ህመሙ ተከስቶ ከፍተኛ ደረጃ ከመድረሱ በፊት በማወቅ አስፈላጊውን ህክምና ወይንም ጥንቃቄ ማድረግ ማለት ነው፡፡

ምርመራው በተለይ ለማን የስፈልጋል?
1. እድሜዋ ከ21 ዓመት በላይ የሆነና ወንድ የምታውቅ
2. ከዚህ በፊት ተመረምራ ነፃ ከተባለች 3 ዓመት ያለፋት
3. የሰውነትን በሽታ የመከላከል አቅምን የሚያዳክሙ መድኃኒቶችን የምትወስድ ወይም የኤች አይ ቪ (HIV) ቫይረስ በደሟ ውስጥ ያለ።

ምርመራ ምን ይጠቅማል?
1. ካንሰር አለመኖሩን ማረጋገጥ
2. የቅድመ ካንሰር ምልክቶች ካሉ ባግባቡ ለመታከም
3. የተረጋገጠ ካንሰር ከተገኘ በወቅቱ ህክምናውን በመውሰድ ለመዳን
4. ውጤትን አውቆ አስፈላጊውን ጥንቃቄ ለማድረግ።

መረጃዎች ምን ያሳያሉ?
በሀገራችን ውስጥ በየዓመቱ ሆስፒታል ለህክምና መጥተው ሲመረመሩ ከ7000 በላይ ሴቶች የማህፀን ጫፍ ካንሰር ተጋልጠው ተገኝተዋል፡፡ ከነኚሁ ውስጥ ከ6000 በላይ የሚሆኑት በዛው ዓመት ይሞታሉ። ይህ ስሌት የሚያመለክተው ህመም ኖሯቸው ለመታከም ወደ ህክምና ማእከል የመጡትን ሴቶች ብቻ ነው።

ይህን ጽሁፍ ያዘጋጁልን ዶ/ር ቤቴል ደረጀ- የማህጸን እና የጽንስ ስፔሺያሊስት ናቸው፡፡
ለጤናሽ
ጎንሽን የምታሳርፊው እንዴት ነው ?

እርግዝና ተከትለው ከሚከሰቱ አካላዊ ለውጦች መካከል የማሕጸን እና የጽንስ ክብደት መጨመር ይጠቀሳል፡፡ ለምሳሌ ከእርግዝና በፊት 30 ግራም ያህል ብቻ ይመዝን የነበረ ማኅጸን (ጽንሱን ሳይጨምር) ከእርዝና በኋላ 1 ኪሎ ያህል ሊመዝን ይችላል፡፡ ይህ በሆድሽ አከባቢ እርግዝናን ተከተሎ የተከሠተው ክብደት የመኝታ አቅጣጫሽን በጥንቃቄ ካልመረጥሽ እስከሞት ሊደርስ የሚችል የከፋ ጉዳት ሊያጋልጥሽ ይችላል፡፡
በምን ምክንያት ቢባል፡-
ለታችኛው የሰውነታችን ክፍል የተጣራ በንጥረ ነገር እና በኦክሲጂን የበለጸገውን ደም የሚያደርሰው ትልቁ የደም ሥር (Aorta) እና ከታችኛው የሰውነታችን ክፍል ተመላሽ የሚሆነውን ደም የሚመልሰው ትልቁ የደም ሥር (Vena Cava ) የሚገኙት ከሆዳችን ጀርባ ህብለ ሠረሠራችንን (Spinal cord) ተከትለው ሲሆን በእርግዝና ወቅት በጀርባሽ ስንትተኚ እነዚህን ትላልቅ የደም ሥሮች ጽንሱ እና ማሕጸን ስለሚጫኗቸው የደም ዝውውር ሥርዓትሽን ያዛባዋል፡፡ ይህም ማለት ሰውነትሽ በቂ ደም እየተዳረሰ አይደለም ማለት ነው፡፡ (ከታች ያለው ስእል ተመልከቺ) ፡፡
ችግሩ
ለሰውነትሽ አስፈላጊ በሆኑ ንጥረ ነገሮች እና በኦክሲጂን የበለጸገ ደም ለሰውነት ክፍሎችሽ በበቂ ሁኔታ ስለማይደርስ
• ማፈን
• ከወገብ በላይ የሰውነት ክፍል በላብ መጠመቅ
• ራስን መሳት ሊከሰት ይችላል፡፡
መፍትሔውስ፡-
መፍትሔው በእጅሽ ነው፡፡ ጎንሽን ስታሳርፊ (ስትተኚ) በጎንሽ በኩል ይሁን፡፡ ቀደም ባሉት ጊዜያ የጤና ባለሙያዎች እርጉዞችን በግራ ጎን በኩል ብቻ እንዲተኙ የሚመክሩ ቢሆንም ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ የተደረጉ ጥናቶች ግን በግራም ሆነ በቀኝ በኩል መተኛት እንደሚቻል አረጋግጠዋል፡፡

ይህን ጽሁፍ ዶ/ር ቤተል ደረጀ- የማሕጸን እና የጽንስ ስፔሺሊስት ያዘጋጁልን ነው፡፡
አስምና እርግዝናሽ

አስም ያለባት ሴት ማርወገዝ ትችላለች፡፡ ይሁን እንጂ በሽታው በእርግዝና ላይ የሚያስከትለው ችግርም አለ፡፡
አስም ያለባት እናት ከጤነኛዋ በበለጠ
· ለደም ግፊት
· ያለጊዜው መውለድ
· ክብደቱ ትንሽ የሆነ ወይም በማህፀን ውስጥ የቀጨጨ ህፃን ለመውለድ
· ሲወለዱ የመታመምና የመሞት እድላቸው ከፍ ያሉ ህፃናትን የመውለድ እድል አላት።
አስም ካለባቸው ነፍሰ-ጡሮች ውስጥ
· ሲሶዎቹ (1/3)- ከበፊቱ የተለየ ህመም አይታይባቸውም
· ሲሶዎቹ - ይሻላቸዋል
· ሲሶዎቹ - ደግሞ በጣም ይታመማሉ።
አስም ያለባት እናት በእርግዝና ጊዜ መድኃኒቷን እንዳታቋርጥ ይመከራል።
መፍትሄው ፦ አስሙን በተቻለ አቅም እየተቆጣጠሩ ጥሩ የሆነ የእርግዝና ክትትል ማድርግ ይኖርባታል።

የሐኪም ምክር፡በባልደረባችን ዶ/ር ቤቴል ደረጀ- የማህጸን እና የጽንስ ስፔሺያሊስት
በእርግዝና ወቅት ለስኳር ህመም የሚጋለጡት እነ ማን ናቸው?

በእርግዝና ወቅት በሴቶች ላይ ከሚከሰቱ የጤና እክሎች አንዱ የስኳር ህመም ነው፡፡ በዓለም አቀፍ ደረጃ 6-7% የሚሆኑት ነፍሰጡሮች የስኳር ህመም አላቸው፡ ከነዚህ ውስጥ ደግሞ 90% በእርግዝና ወቅት ብቻ የሚከሰተው የስኳር ህመም ይኖራቸዋል። ለመሆኑ በእርግዝና ወቅት ይበልጥ ለስኳር ህመም ተጋላጭ የሚሆኑ እነ ማን ናቸው?

1) እድሜዋ ከ35 ዓመት በላይ ከሆነ
2) ከዚህ በፊት - ከ4ኪ.ግ. በላይ የሚመዝን ልጅ ወልዳ ከነበረ
- እርግዝናዋ ወቅት የስኳር በሽታ አጋጥሟ ትከነበረ
- የአፈጣጠር ችግር ያለበት ጽንስ ከነበራት
3) ባልታወቀ ምክንያት ጽንሷ ሞቶባት ከነበረ
4) የቅርብ ቤተሰቧ ውስጥ የስኳር ታማሚ ካለ
5) ከመጠን በላይ ወፍራም ከሆነች (BMI>30)
6) በምርመራ ላይ በሽንቷ ውስጥ የስኳር መጠን ከጨመረ

ለስኳር ህመም የመጋለጥ እድሏ ከፍኛ ነው፡፡ ይህች ሴት ከእርግዝና በፊትም ሆነ በእርግዝናዋ ወቅት በሚደረግላት ክትትል እና ህክምና ለስኳር ህመም እንዳትጋለጥ መከላከል ይቻላል፡፡

ይህን ጽሁፍ ያዘጋጁልን የማህፀን እና ጽንስ ስፔሺያሊስት የሆኑት ባልደረባችን ዶ/ር ቤቴል ደረጀ ናቸው፡፡
ጽሑፉን ከወደዱት share በማድረግ ለሌሎችም የጋሩት፡፡
ክብር ለኢትዮጵያ ጀግኖች!

#አድዋ ! #ክብር ለኢትዮጵያ ጀግኖች #ታላቅመስዋዕትነት#የጥቁርሕዝቦችድል
#የአፍሪካዊያንኩራት
#HumanitarianHero
Professor Senait Fissha was named Humanitarian hero by the Global Humanitarian Community. Congratulations, Professor Senait!
የዓለም የኩላሊት ጤና ቀን ምክንያት በማድረግ ነጻ ምርመራ አዘጋጅተንልዎታል፡፡
ሰዓት፡ 3፡00- 6፡30
We have organized health awareness day with health checkups for the community at St. Paul’s Transplant center. We will be testing for Blood pressure, urine and heart rate on the day.
Time: 9:00- 12:30
#worldkidneyday2020#SPHMMCethiopia
Congratulations #Dr_Lia_Tadesse, on your well deserved appointment as the Minister of Health of Ethiopia.

ክብርት ዶር ሊያ ታደሠ የጤና ሚኒስቴር ሆነው በመሾምዎ በእጅጉ ደስ ብሎናል። መልካም የሥራ ዘመን ይሁንልዎ።

SPHMMC
እንዲህ ሰላም ይባባሉ!( መጨባበጥ ይቅርና)
St. Paul’s celebrated world kidney day with a free health screening and Health education and a press conference to a private and governmental media journalists on Kidney health and the transplant cen
የየዓይን ግፊት ህመም (ግላኮማ) ምንድን ነዉ?

ግላኮማ በብርሃን አማካኝነት ዓይናችን የሚቀበለዉን መረጃ ለአንጎላችን የሚያደርሰዉን የእይታ ነርቭ የሚያጠቃ የዓይን ጤና ችግር ነዉ።
የዓይን ብርሃንን (እይታን) የሚያጠፋ ወይም የሚሰርቅ አስከፊ የዓይን ህመም ነዉ። ቀስ በቀስ የእይታ አድማስን እያጠበበና የቀጥታ እይታን እያዳከመ ለዓይነ ስዉርነት የሚዳርግ በሽታ ነው፡፡ብቸኛዉ መፍትሄ ግላኮማዉ የከፋ ጉዳት ሳያደርስ እንዲታወቅ ወቅታዊና ተገቢ የዓይን ምርመራ ማድረግና ጉዳቱንም ለመቀነስ የሚያስችሉ የተለያዩ የህክምና አማራጮችን መጠቀም ነዉ።

ግላኮማን የሚያመጣዉ ምንድን ነዉ?
እንደማንኛዉም የአካል ክፍል ዓይናችንም የሚጠበቅበትን የማየት ሥራ እንዲከዉን የተለያዩ ነገሮች (አየር፣ ዉኃ፣ ምግብና ሌሎች የተለያዩ ንጥረ ነገሮች) ያስፈልጉታል። ዓይናችን የያዘዉን የኳስ መሰል ቅርጽ እንዲይዝ ያስቻለዉ ዓይናችን ዉሥጥ ያለዉ ዉኃ መሰል ፈሳሽ /ዓይነ ዉኃ/ ሲሆን ይህ ፈሳሽ የዓይንን ቅርጽ ከመጠበቅ በተጨማሪ ለተለያዩ የዓይን ክፍሎች አስፈላጊ ንጥረ ነገሮችን የማድረስና በገንባንደት ሂደት የሚፈጠሩ (ጥቅም ላይ የዋሉ) ንጥረ ነገሮችን ከዓይን የማስወገድ ሥራ ይሠራል።
ኳስ እንደ ኳስ የሚጠበቅበትን አገልግሎት ለመስጠት ከዉሥጥ በቂ የሆነ የግፊት ኃይል (አየር) ሊኖረዉ ይገባል። ኳሱ ዉስጥ ያለዉ የግፊት መጠን ከበዛ ወይም ካነሰ በኳሱ ላይ ጉዳት ይደርሳል። በተመሳሳይም ዓይናችን ዉሥጥ ያለዉ ፈሳሽ ሲበዛ ወይም ሲያንስ ዓይን ሥራዉን በአግባቡ የማይወጣ ከመሆኑም ባሻገር በዓይናችን ላይ አካላዊ ጉዳት ይደርሳል።
ግላኮማ የሚከሰተዉ በዓይናችን ዉሥጥ ያለዉ ዓይነ ዉኃ ከሚፈለገዉ በላይ ተጠራቅሞ (የዓይን ግፊት ጨምሮ) ከዓይን ወደ አንጎል መረጃ በሚያስተላልፈዉ (በሚያቀብለዉ) ነርቭ ላይ ጉዳት ሲያደርስ ነዉ። በአጭሩ ግላኮማ የሚከሰተዉ በዓይን ዉሥጥ የሚገኘዉ የፈሳሽ መጠን የግለሰቡ ዓይን ከሚቋቋመዉ በላይ ተጠራቅሞ የዓይን ግፊት በእይታ ነርቭ ላይ ጉዳት ሲያደርስ ነዉ።

ለግላኮማ የሚያጋልጡ ነገሮች አሉ?
ሁሉንም የኅብረተሰብ ክፍል የሚያጠቃ ቢሆንም ለዚህ ችግር ሊያጋልጡ የሚችሉ ዋና ዋና ነገሮች የሚከተሉት ናቸዉ።
1. የእድሜ መጨመር (አርባ ዓመትና ከዚያ በላይ)፡- እድሜ እየገፋ በሄደ ቁጥር ለግላኮማ ተጋላጭነቱ እየጨመረ ይሄዳል፤
2. የጥቁር (የአፍሪካ) ዝርያ፤
3. ከቤተሰብ (እህት፣ ወንድም፣ እናት፣ አባት) በግላኮማ የተያዘ ሰዉ ከነበረ /ካለ/፤
4. አጠቃላይ የሰዉነት ህመሞች (የስኳር ህመም፣ ደም ግፊት፣ የልብ ህመም፣ ራስ ፍልጠት (‹‹ሚግሬይን››)፤
5. በመነጽር ሊሰተካከል የሚችል የእይታ ችግር (በቅርብ፣ በርቀት የማየት ችግር)፤
6. በአደጋ ወይም በሌሎች ህመሞች ምክንያት ጉዳት የደረሰበት ዓይን፤
7. የዓይነ መስታወት ዉፍረት መቀነስ (ስስ ዓይነ መስታወት)፤
8. ለረጅም ጊዜ የሚወሰዱ መድኃኒቶች (በተለይም ኮርቲዞን /ስቴሮይድ/ ያላቸዉ )።
ግላኮማ መኖሩ የሚታወቀዉ እንዴት ነዉ?
አንድ ግለሰብ ግላኮማ እንዳለበት ሊያዉቅ የሚችልበት ብቸኛዉ መንገድ ዓይን ሐኪም ዘንድ ቀርቦ ሙሉ የዓይን ምርመራ ሲያደርግ ብቻ ነው፡፡ አንድ ሰዉ ግላኮማ እንዳለበት ወይም እንደሌለበት ለማወቅ የሚከተሉት መሠረታዊ ምርመራዎች ይደረጋሉ።
1. የዓይን ግፊት መለካት፤
2. የዓይነ መስታወት ዉፍረት መለካት፤
3. እይታይ ነርቭን በልዩ መሣሪያ ማየትና ጉዳት ካለም የጉዳቱን መጠን መለካት፤
4. የእይታ አድማስን በልዩ መሣሪያ መለካት።
ከላይ የተጠቀሱት ምርመራዎች ከተደረጉ በኋላ አንድ ሰዉ ግላኮማ እንዳለበትና እንደሌለበት ይታወቃል፡፡የጉዳቱ መጠን ምን ደረጃ ላይ እንደሚገኝ ገምግሞ የሚያስፈልገዉን የህክምና አማራጭ ከህመምተኛዉ ጋር በመወያየትና በመምክርም ሀኪም ዉሳኔ ይሰጣል። በምርመራዉ ወቅት ግላኮማ የሌለባቸዉ ነግር ግን በግላኮማ የመያዝ እድላቸዉ ከፍተኛ ለሆነ ሰዎች መደበኛ የሆነ ዓመታዊ የዓይን ምርመራ እንዲያደርጉ ምክር ይሰጣቸዋል።

የግላኮማ ህክምና ምንድን ነዉ?

ለግላኮማ ህመም የሚደረጉ ዋና ዋና የህክምና አይነቶች ሦስት (የመድኃኒት ህክምና፣ የብርሃን ጨረር (ሌዘር) ህክምናና የዓይን ግፊት ቀዶ ህክምና ) ሲሆኑ ዋና አላማቸዉም የዓይን ግፊትን በመቀነስ ተጨማሪ ጉዳት እንዳይደርስ መከላከልና የጉዳቱ መጠን እንዲቀንስ ማድረግ ነዉ።
ግላኮማ የሌለበት ሰዉ ምን ሊያደርግ ይገባል ?
ጠቅለል ባለ መልኩ የሚከተሉትን መሠረታዊ ነጥቦች ልብ ካሉ እይታዎን ለመጠበቅ፤ ግላኮማ ከተከሰተም ጉዳቱን መቀነስ ይችላሉ።
1. እድሜዎ ከአርባ ዓመት በላይ ከሆነ፣ በቤተሰብ የግላኮማ ችግር ካለ ወይንም ያለበት ሰዉ ካለ፣ ሌሎች ለግላኮማ የሚያጋልጡ የጤና ችግሮች ካሉ ግላኮማ የሚያወጣዉን ጉዳት መከላከል ስለሚቻል ቢያንስ በዓመት አንድ ጊዜ የዓይን ምርመራ ማድረግ፤
2. የግላኮማ ምርመራ የሚደረግባቸዉን በአቅራቢያ የሚገኙ የመንግሥትና የግል ጤና ተቋማት ማወቅ፤
3. ስለግላኮማ ያለዎትን እዉቀትና ግንዛቤ ማዳበርና እንዴት እይታዎን ሊጎዳ እንደሚችል መገንዘብ::

ግላኮማ ይድናል?
ግላኮማ በዓለም ላይ ዓይነ ስዉርነት በማምጣት ከዓይን ሞራ ቀጥሎ በሁለተኛ ደረጃ የሚጠቀስ ሲሆን በሀገራችን ኢትዮጵያ ደግሞ ከዓይን ሞራና ዓይን ማዝ በመቀጠል በሦስተኛ ደረጃ ይቀመጣል። አንድ ግላኮማ ያለበት ሰዉ ሊያዉቀዉና አምኖ ሊቀበለዉ የሚገባዉ ጉዳይ በግላኮማ ምክንያት የመጣ የእይታ መቀነስ በምንም አይነት የህክምና ዘዴ ወደ ነበረበት ሊመለስ እንደማይችል ነዉ። ለዚህም ነዉ የግላኮማ ችግር አሳሳቢ የሚሆነዉ። የህክምናዉ ዋና አላማ ህመሙ ከታወቀበት ጊዜ ጀምሮ ተጨማሪ ጉዳት እንዳይደርስና የጉዳቱ መጠን እየከፋ እንዳይሄድ ማድረግ ነዉ። እንደ ዓይን ሞራ በአንድ ጊዜ ህክምና ሊድን የማይችል በመሆኑ ችግሩ ከታወቀ ጊዜ ጀምሮ ያለማቋረጥ በሕይወት ዘመን ሙሉ ክትትል ማድረግን ይጠይቃል።
(ምንጭ: የዓይን ጤናና ክብካቤ በፕ/ር የሺጌታ ገላዉ)
Ethiopia has announced the suspension of schools, sporting events and public meetings for at least the coming fifteen days.
The suspension starts from today, Monday March 16, 2020, according to office of the Prime Minister.
Ethiopia confirmed another coronavirus case today, raising the total number of patients to five.